ፒላስ 🇵 🇮 🇱 🇦 🇸


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: не указана


☜ጥቅሶች☞
☜ስነ-ስዕል☞
☜የመጽሐፍ ግብዣ☞
☜የቴክኖሎጂ መፍትሔዎች☞
☜ልብወለድ☞
☜ከታሪክ ውቅያኖስ☞
☜ቅኔና ግጥም☞
☜የመዝናኛው ዓለም ዜና☞
☜ሃገርኛ☞
☜የስራ ማስታወቂያዎች☞
☜የሕልም ፍቺዎች☞
🚪ፒላስ ኢትዮጵያ🚪

Связанные каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
не указана
Статистика
Фильтр публикаций


Today I found a very interesting project, I think many have already heard about it!
Express Smart Game (https://express.game/6mbc9m) - a subsidiary of forsage.io (350K members)
This is a very promising project where you can earn BNB on a passive just like that!
All you have to do is buy a table that suits your budget and wait! To speed up, you can invite friends! (as I do) or just wait for your profit!
You can find all the information on their website - https://express.game/6mbc9m

To everyone who registers using my link - I will transfer 0.12 BNB to purchase the first table!


⭕️መልዕክት አለኝ⭕️
ተፈላጊነት
ዶ/ር ኢዮብ
አንድ ሁለት ልጆች የነበሩት ገበሬ ነበረ፡፡ ሁለቱ ልጆቹ በእርሻ ስራው አይለዩትም ነበር፡፡ አባት ለታናሹ ልጁ የበለጠ ሃላፊነት ስለሚሰጠውና ስለሚያምነው ሁል ጊዜ ታላቅየው ጥያቄ ይፈጥርበት ነበር፡፡ አንድ ቀን አባት አምስት መቶ ብር በእጁ ላይ እንዳለውና፣ አምስት በጎችን እጁ ላይ ባለው የገንዘብ መጠን ቢያገኝ የመግዛት እቅድ እንዳለው ለታላቅ ልጁ እየነገረው ሳለ፣ ታላቅ ልጅ ይንን አጋጣሚ በመጠቀም ለምን ከእርሱ ይልቅ ለታናሹ የበለጠ ሃላፊነትን እንደሚሰጠው ጠየቀው፡፡ ይህንን ሲወያዩ ታናሽ ልጅ በዚያ አልነበረም፡፡ አባትም ቀጥተኛ መልስ ቢሰጠው ይገነዘበዋል ብሎ ስላላሰበ በብልሃት ሊያስተምረው ፈለገ፡፡

አባት ለታላቅ ልጁ፣ “እሰቲ እነዚያ ከብት የሚያረቡት ሰዎች ቤት ሂድና በግ ይሸጡ እንደሆነ አጣርተህ ተመለስ፣ ከዚያም ጥያቄህን እመልስልሃለሁ” አለው፡፡ ታላቅ ልጅ ሄዶ ተመለሰና፣ “አዎን የሚሸጡ በጎች አሏቸው” አለ፡፡ አባትም፣ “ሂድና ዋጋቸው ስንት እንደሆነ ጠይቅ” አለው፡፡ ልጅም ሄዶ መጣና፣ “ባለ 100 ብር በጎች አላቸው” አለው፡፡ አባት እንደገና፣ “ሂድና ነገውኑ በጎቹን ብንገዛቸው እኛ ድረስ ሊያመጡልን እንደሚችሉ ጠይቅ” አለው፡፡ ልጅም ሄዶ መጣና፣ “አዎን ይችላሉ” አለው፡፡ አባትም ታናሽ ወንድምህን ጥራው እስቲ አለው፡፡

ታናሽ ልጅ ሲመጣ አባት፣ “እስቲ እነዚያ ከብት የሚያረቡት ሰዎች ቤት ሂድና በግ ይሸጡ እንደሆነ አጣርተህ ተመለስ” አለው፡፡ ታናሽየው ሄዶ ተመለሰና፣ “ባለ 100 ብር፣ ጎችና እና ባለ 150 ብር በጎች አሏቸው፡፡ ነገውኑ ብንፈልግ ሊያመጡልን እንደሚችሉ ጠይቄ ተስማምተዋል” ብሎ ለአባቱ ነገረው፡፡ በመጨመርም፣ “ስለዚህ፣ የተለየ ሃሳብ ኖሮን ካልነገርኳቸው በስተቀር አምስት በጎችን በ100 ብር ሂሳብ ነገውኑ እንዲያመጡልን ተስማምቼአለሁ” አለው፡፡ አባት ወደታላቅ ልጁ ዘወር ብሎ ሲመለከት፣ ታላቅ ልጁ የራሱንና የታናሽ ወንድሙን መልስ በማሰነጻጸር ላይ እንዳለ ያስታውቅ ነበር፡፡

“አየህ ልጄ፣ አንተንና ታናሽ ወንድምህን የጠየኳችሁ አንድ አይነት ጥያቄ ነው፡፡ ያመጣችሁልኝ መረጃ ግን በጣም ይለያያል፡፡ አንተ ያችኑው የተጠየከውን ጥያቄ ነው ይዘህ የመጣኸው፡፡ ሌላ መረጃ ስፈልግ እንደገና ደጋግሜ መላክ ነበረብኝ፡፡ እርሱ ግን እኔ የፈለኩትን ፍላጎቴን በሚገባ በመረዳት የቻለውን ያህል መረጃ ይዞልኝ ነው የመጣው፣ ከተጠየቀውም በላይ ስራ ሰርቶ ነው የመጣው፡፡ ሁል ጊዜ ከአንተ ይልቅ ለእርሱ ሃላፊነትን የምሰጠው ለዚህ ነው፡፡” በማለት ቀድሞ ለጠየቀው ጥያቄ መልስን ሰጠው፡፡ ለነገሩ፣ ታላቅ ልጅ ገና መልሱ ሳይብራራ ገብቶት ነበር፡፡

የተባሉትንና የሚጠበቅባቸውን ብቻ አድርገው እጆቻቸውን የሚሰበስቡ ሰዎች ተግባርን በማከናወንና የተጠበቀባቸውን ነገር በማድረግ አንጻር ትክክለኛ ነገር አድርገዋል፡፡ በእድገት ልቆ ከመገኘት አንጻር ሲታይ ግን ባሉበት የሚረግጡ አይነት ሰዎች ናቸው፡፡ ይህ አይነቱ ምርጫ ሰዎች ሊያከናውኑ ከሚችሉት አቅማቸው በታች እንዲኖሩ ያደርጋቸዋል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ሌሎች በእድገትና በተቀባይነት አልፈዋቸው ሲሆዱ እያዩ “ለምን?” እያሉ ከመጠየቅ ያለፈ እድገት አይኖራቸውም፡፡ “ለምን ለሌሎች ያደላሉ? … ለምን ሰውን ይመርጣሉ? … ብዙም የሚፈልገኝ ሰው የሌለው ለምንድን ነው? … ” መልስ ያጣው ጥያቄያቸው ብዙ ነው፡፡

የተፈላጊነት እውነታዎች …
• ከተፈላጊነት ውጪ ምንም አይነት እድገት እንደማታገኝ እወቅ፡፡

• ተፈላጊነትህን ለመጨመር የግድ ውሸት፣ የሌላውን ሰው ስም ማጥፋት፣ ሸንጋይነትና የመሳሰሉትን መንገዶች መጠቀም የለብህም፡፡

• በትጋትህና በታማኝነትህ የሰዎችን ልብ ባሳረፍክ ቁጥር ተፈላጊነትህ እየጨመረ ይሄዳል፡፡

• ብዙ እውቀትና ችሎታ ኖሮት የልብን ከማያደርስ ሰው ይልቅ፣ ብቃቱ አናሳ ሆነ ትጉ ሰው የበለጠ ተፈላጊነት አለው፡፡

• ከሚከፈልህ በላይና ከሚጠበቅብህ በላይ በትጋት ስትሰራ ተፈላጊነትን ታተርፋለህ፡፡

• ክፍያን በገንዘብ ብቻ አትጠብቅ፡፡ ከሚጠበቅብህ በላይ ስትሰራ የግድ ለዚያ የሚመጥን ገንዘብ እጅ በእጅ ላይከፈልህ ይችላል፡፡ አንዳንድ ጊዜ ክፍያህ በመልካም ስምና ምስክርነት፣ በተሻለ የስራ እርከን እድገትና በመሳሰሉት ሁኔታዎች ሊገለጥ ይችላል፡፡

• በመጨረሻ፣ ታማኝነትህንና ትጋትህን ለእኩይ አላማቸውና አንተን ለመበዝበዝ ብቻ ለመጠቀም ከሚፈልጉ ሰዎች ተጠንቀቅ፡፡

@pilasethiopia


⭕️መልዕክት አለኝ!⭕️
በቲፎዞ የሰከረ ማንነት!
ዶ/ር ኢዮብ ማሞ

ቻርልስ ብሎንዲን (Charles Blondin) በቀጭን ገመድ ላይ
በመራመድ የታወቀ ፈረንሳዊ ነው፡፡ በዘመኑ እጅግ ዝነኛ
የነበረው ይህ ሰው ከአንድ ግዙፍ ህንጻ ወደሌላኛው ህንጻ
በተዘረጋ ቀጭን ገመድ ላይ በመራመድ ተመልካቹን ትንፋሽ
በማሳጠር የታወቀ ሰው ነው፡፡ በቀጭን ገመድ ላይ
ከተራመደባቸው የከፍታ ስፍራዎች አንዱ በአሜሪካና በካናዳ
ጠረፍ ላይ በሚገኘው ናያግራ ፏፏቴ (Niagara Falls) ከፍታ ላይ
ያደረገው ይደነቅለታል፡፡

ከአሜሪካ ግዛት እስከ ካናዳ ግዛት
የፏፏቴው ጥጎች የተዘረጋውን ቀጭን ገመድ በመራመድ
ከተሻገረ በኋላ እንደገና ወደ አሜሪካው ግዛት በገመዱ ላይ
ሲመለስ የሚመለከተው ህዝብ ስለእርሱ ጭንቅ ይዞት ነበር፡፡

የሕዝቡ ጩኸት ቀልጧል፡፡ “አንተን የሚያክል የለም፣ ጀግና ነህ
… ” አሉት፡፡
ሁሉም ሰው ከተረጋጋ በኋላና ሕዝቡን ካመሰገነ በኋላ አንድ
ጥያቄ ጠየቃቸው፣
“በእርግጥም ጎበዝ እንደሆንኩ
ታምናላችሁ?” አላቸው፡፡
ሕዝቡ በአንድ ድምጽ፣ “አንተ
የምታደርገውን ሊያደርግ የሚችል ፈጽሞ አይገኝም፤ ምንም
ነገር ማድረግ ትችላለህ” በማለት አረጋገጡለት፡፡

“ይህን ያህል
ካመናችሁብኝ ከእናንተ መካከል በትከሻዬ ላይ ተሸክሜው
እንደገና በዚህ ቀጭን ገመድ ላይ እንድራመድ ፈቃደኛ የሆነ
ሰው ማን ነው?” አለ፡፡
ሕዝቡ በጸጥታ ተሞላ፡፡ አንድም ሰው
ፈቃደኛ ሊሆን አልፈለገም፡፡

ብሎንዲን ወደ አንድ የቅርብ ወዳጁ ዘወር በማለት ፈቃደኝነቱን
ጠየቀው፡፡ ይህ ወዳጁ ከፍታን እጅግ የሚፈራ ሰው ነው፡፡ ትንሽ
የወላወለው ይህ ወዳጁ በመጨረሻ ተስማማና ትከሻው ላይ
ሆኖ ያንን አስፈሪ ከፍታ አብረው ተሻገሩ፡፡

ይህ የቀጭን ገመድ
ተራማጅ #አድናቂዎቹ ብዙዎች፣ #አጋሩ ግን አንድ ሰው ብቻ እንደ
ነበር የተገለጠለትና ከደጋፊ ብዛት ከተጠናወተው ስካር ሰከን
ያለው ያን ጊዜ ነው፡፡

የሰው ልጅ የሚሰክረው በአልኮል መጠጥ ብቻ አይደለም፡፡
የሰው ልጅ በስኬት፣ በገንዘብ ብዛትና በመሳሰሉት ጊዜያዊ
ነገሮች ሊሰክር ይችላል፡፡ ከዚህ የከፋው የስካር አይነት ግን
ከጀርባው የሚደግፈው ቲፎዞ የበዛ ሲመስለውና “ጀግና”
የሚለው ሰው ሲበራከት ራሱን የመግዛት ብቃት ከሌለው
የሚሰክረው ስካር ነው፡፡ በዚህ ጊዜ ነው ልክ አንድ በመጠጥ
ተጽእኖ ስር ወድቆ የሰከረ ሰው የሚያደርገውን እንደማያውቅ
ሁሉ በመደነቅ ተጽእኖ ስር ወድቆ የሰከረ ሰውም ማመዛዘን
የሚሳነው፡፡

አጭር ምክር …
• ያደነቀን ሁሉ አብሮን የሚዘልቅ አጋር እንዳይመስለን፡፡ ዛሬ
“ሆ” ያለን ሰው ሁሉ ነገ ሕይወት የየራሱን የቤት ስራ
(Assignment) ሲሰጠው ከእኛ ዘወር ሊል የሚችልበት አጋጣሚ
ሊፈጠር ይችላል፡፡
• ወደዚህ ዓለም የመጣነው ብቻችንን ነው፣ የምንሰናበተውም
ብቻችንን ነው … በመካከሉ ግን በዚህ ምድር ላይ ባለን ቆይታ
ለብቻችን ስንሆን የሚሞግት ኅሊና ከፈጣሪ ተሰጥቶናል
ኅሊናችንን ብናደምጠው ይበጀናል፡፡
• ከደጋፊዎችና ከአድናቂዎች ብዛት የተጠናወተን ስካር አንድ ቀን
በረድ እንደሚል አንርሳ፡፡ ያን ጊዜ የምንነጋገረው ከእውነት ጋር
ነው፡፡ እውነት በመጀመሪያ ስትመክር ለስላሳ ነች፣ ካልሰማናት
ግን በኋላ ስትፈርድ ጨካኝ ነች፡፡
• ከአእላፋት ደጋፊዎች ኃይል ይልቅ የአንዲት እውነት ጉልበት
እንደምትበረታና እንደምታሸንፍ እናስታውስና ዛሬውኑ በሰከነ
አእምሮ ከእውነት ጋር እንስማማ፡፡

@pilasethiopia



⭕ቅኔ ና ግጥም️⭕️

 * ቡቃያው ደረቀ *
ፍቅር መነነ - ዓለምን ለቀቀ
ግፍን ተፀይፎ - ቆቡን አጠለቀ፡፡

ምነው ክፋት በዛ ደግነት ቀነሰ
በንፁህ ልብ ላይ ተንኮል ተፀነሰ፡፡
ምነው
አብሮ የመኖር ጉዞ በወረት ደመቀ
ፅናት ደብዛው ጠፋ ቡቃያው ደረቀ

©ከቢኒኦኔ ገበሬ
ይግቡ⤵️⤵️⤵️
⚫ ️@pilasethiopia ⚪️
⚫ ️@pilasethiopia ⚪️
⚫ ️ @pilasethiopia ⚪️


አርቲስት ጫንያለው ወልደጊዮርጊስ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ።
ዳሰሳ አዲስ

@newsnewet


NEWS NEW 🇪 🇹
ነፃነት፦ የሌሎችን መብት በመንጠቅ ፤ የሌሎችን እምነትና አመለካከት በኃይል ለማጥፋት በመስገብገብ ፤ የወገንን ሰላም በማደፍረስና ስጋት ውስጥ በመክተት..አይገኝም!
የአንድ ሰው(ማኅበር)ነጻነት የሚረጋገጠውም ሌሎች በሚያገኙት ነፃነትና ሰላም እንጂ በሌሎች ሞት ፤ ስቃይና መፈናቀል አይደለም ፡፡

አሁንም መዘንጋት የሌለበት በቀል ሌላ በቀል ያተርፍ ይሆን እንጂ አያክምም፡፡
JOIN US @newsnewet
https://telegram.me/newsnewet


#ወገግታ
የግጥም ወ ስዕል ምሽት
ሰኞ ጥቅምት 17
በሀገር ፍቅር

@pilasethiopia


Репост из: ምስክር ጌታነው ሚዲያና ፕሮሞሽን(You tube-Misiker media ምስክር ሚዲያ)
Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
ገራሚ ግጥም
#በላይ_በቀለ_ወያ
❤️❤️ኦሮሞ አቃፊ ነው
አማራ....❤️❤️
#share n #join
@Misikrmedia
@Misikrmedia


Репост из: ምስክር ጌታነው ሚዲያና ፕሮሞሽን(You tube-Misiker media ምስክር ሚዲያ)
ዜ ማ ቃ ል LYRICS
@muzicalword

የሰው ልጅ ክቡር፣
ሰው መሆን ክቡር፣
ሰው ሞቷል ሰው ሊያድን፣
ሰውን ሲያከብር፣
በደግነት፣ በፍቅር፣ በክብር ተጠርቶ፣
በክብር ይሄዳል፣ ሰው ሊኖር ሰው ሞቶ።

የተሰጠኝ ህይወት ዛሬ በነፃነት፣
ሰው ተከፍሎበታል ከደምና ከአጥንት፣

ስንት ወገን ወደቀ በነፃነት ምድር፣
ትናገር አድዋ፣ ትናገር ትመስክር፣
ትናገር አድዋ፣ ትናገር አገሬ፤
እንዴት እንደቆምኩኝ ከፊታችሁ ዛሬ።

በኩራት፣ በክብር፣ በደስታ፣ በፍቅር፣
በድል እኖራለሁ ይኸው በቀን በቀን፣
ደሞ መከራውን ያን ሁሉ ሰቀቀን።

አድዋ ዛሬ ናት አድዋ ትናንት፣
መቼ ተነሱና የወዳደቁት፣
ምስጋና ለእነሱ ለአድዋ ጀግኖች፣
ለዛሬ ነፃነት ላበቁኝ ወገኖች፣

የጥቁር ድል አምባ፣ አድዋ፣
አፍሪካ፣ እምዬ ኢትዮጵያ፣
ተናገሪ የድል ታሪክሽን አውሪ።

#እንዴት_ይህን_የመሰለ_ታሪካዊ_ሙዚቃ_ተጻፈ

(የጂጂ የቀድሞ ማኔጀርና ጓደኛዋ እንዲሁም ቤዝ ጊታሪስት
ቶማሥ ጎበና Thomas Gobena (Tommy T) ጋር
ካደረግኩት ቆይታ የቆነጠርኩት ነው።)

እኔ፦ "ቶሚ፤ አድዋ ይገርመኛል። ሲሰራ ታስታውሳለህ??"
ቶማሥ፦ "ታስታውሳለህ?? እንዲያውም ይገርመኛል፤
ልንገርህ። ፕሮፌሠር ሀይሌ ገሪማ አድዋ የተሠኘውን
ፊልማቸውን በአሜሪካ እንደነገ ሊያስመርቁ እንደዛሬ የኔን ባንድ
ተከራዩ። Instrument ብቻ ነበር ልንጫወት የታሰበው።
ከዚያ ፕሮፌሠር ሀይሌ መጡና "እስቲ፤ የፊልሙን ምርቃት
የሚከፍት ዘፋኝም ፈልግ። ብቻ ሴት ኢትዮጵያዊት ትሁን" አሉኝ።
እሺ ብዬ ማንን እንደምጋብዝ እያሰብኩ ቤቴ ሄድኩና ከጓደኞቼ
ጋር ልምምድ ጀመርን።
ማታ 2 ሰዓት ተኩል ገደማ ጂጂ ሁለት ሺፍት ሥራዋን ጨርሳ
ወደ ቤቷ ልትሄድ ስትል ጎራ አለች።
"አንቺ፤ ፕሮፌሠር ሀይሌ ዘፋኝ ይፈልጋሉ። ለምን አንቺ
አትሠሪም?!" አልኳት።
"መጣሁ!" ብላ እየሮጠች ወጣች። 4 ሠዓት ሲል መጣች።
"አዲስ ሙዚቃ ሠርቻለሁ። እናጥናው።" አለች።
"አንቺ ልጅ አብደሻል እንዴ?! አይሆንም!" አልኳት።
እኔ፦ ለምን???!
ቶማሥ፦ እንዴ ፕሮፌሠር ሀይሌ እኮ ናቸው። በጣም ነው
የምንፈራቸው። የማይሆን ሥራ ይዘን ገብተን አበላሽተን
ቢገሉንስ??
ከዚያ "ዝምብለሽ "እማማ ኢትዮጵያ" የሚለውን ዝፈኝ እንጂ
አይሆንም" አልኳት። ተስማማች። በማግስቱ ጠዋት መድረክ
ላይ ወጥተን ልትዘፍን ስትል በምልክት "ፀጥ በሉ!" አለችን።
በጣም ብዙ ህዝብ ነበር። ትላልቅ እንግዶች ከፊት ነበሩ። እኛ
መጫወት አቆምን።
"አድዋ"ን ያለ ሙዚቃ በድምጿ ብቻ መዝፈን ጀመረች።
"የሠው ልጅ ክቡር..........." ስትል ክው አልኩ።
ሰምተነው አናውቅም። በ 1 ሰዓት ተኩል የተደረሠ ዘፈን ነው።
ከዚያ ከሀይሌ ጋር የተቀመጡ ነጭ ምሁራን እንባቸውን
ያወርዱታል። ቋንቋው አይገባቸውም። ጂጂ ራሷ ደንግጣ
እየዘፈነች ወደኔ ዞራ "ምንድነው?!" የሚል አስተያየት አየችኝ።
በምልክት "ቀጥይ!" አልኳት። ስትጨርስ ቤቱ በእግሩ ቆመ።
ፕሮፌሠር መጡና "እቺን ጉደኛ መተዋወቅ እፈልጋለሁ" ብለው
ተዋወቋት። ያልመጣ ሠው አልነበረም። ከነሱ መሀል የ 7
ግራሚ አሸናፊዋና የ Bob Marley ልጅ ሚስት Lauren Hill
ነበረች። እሷም ከትላልቅ የሙዚቃ ፕሮዲዩሰሮች ጋር አገናኘቻት።
ከአመታት በኋላ አልበም ሆኖ ወጣ። ይሄ ነው ታሪኩ።"


ለሌሎች ማስነበቦን ያስታውሱ
👇more n more👇

🦁 @muzicalword 🦁
🦁 @muzicalword 🦁
🦁 @muzicalword 🦁


Репост из: NEWS NEW 🇪 🇹
ጃኖ ባንድ በመላው አፍሪካ ሙዚቃ ሽልማት (አፍሪማ) ላይ በሁለት ዘርፍ እጩ መሆን ችለዋል።

ለ6ተኛ ጊዜ በሚደረገው አፍሪማ ሽልማት ላይ ጃኖ ባንዶች
በምርጥ ባንድ በአፍሪካ እና በምርጥ ባንድ በአፍሪካ ሮክ ላይ ስለታጩ ለእነዚህ የሐገራችን ሙዚቃ ባንድ አቀንቃኞች afrima.org ላይ በመግባት ድምፅ ስጡ!

ባሳለፍነው አመት በተደረገው በዚህ የሽልማት ውድድር ላይ ድምፃዊ ቤቲ ጂ በ3 ዘርፍ በመጫት 3ቱንም ማሸነፏ ይታወሳል።
🦁 @newsnewet 🦁
🦁 @newsnewet 🦁
🦁 @newsnewet 🦁


Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
ናፍቆት

join👉 @pilasethiopia


🎵 -
የድምፃዊት ዘሪቱ ከበደ ስንብት ለኤልያስ መልካ።



😭 @muzicalword 😭


🚷
ሰዎችን ቆመው እንዲሄዱ የሚያደርጋቸው እግር አይደለም።
ቆሞ ለመሄድ ከእግር በፊት ዋስትና የሚሆነው የሚኬድበት መንገድ...የሚቆምበት መሬት
(ሃገር) ነው።
የምትሄድበት መንገድ የተዘጋ 'ለት.... የቆምክበት መሬት(ሃገር) የከዳህ 'ለት........ እግር
እያለህ መሄድ አትችልም.......ወኔ እያለህ ጉልበት የለህም....ወደ ህልምህ የማትደርስበት
እግር ይዘህ ሽባ ትሆናለህ !!!

#join
👇👇👇
👉💡 @pilasethiopia💡👈
ለአስተያየቶ 👇👇👇
🖱 @nafbook🖱


ሊያዩት የሚገባ ጊዜውን የጠበቀ ምርጥ መርሀግብር ቢመጡ አብዝተው ያተርፋሉ #share it

. @pilasethiopia .


"ኤልያስ ምግብ ሲበላ ምስሉ የለኝም" ተዋናይ ግሩም ዘነበ ነው ባለፈው ሳምንት ማክሰኞ የጥበብ መንገድ ላይ የተናገረው፤ ኤልያስ ሙሉን ዕድሜ ለሙዚቃ ነው የሰጠው ምግብ በመብላት የሙዚቃ ጊዜውን መሻማት ስላልፈለግ አብዝቶ ብስኩት እና ሚሪንዳ በመብላቱ ስኳር እንደያዘው በሸገር ኤፍ ኤም ለለዛ ሬድዮ ፕሮግራም ላይ በ 2008 ዓ/ም በሰጠው ቃለ መጠይቅ ተናግሯል።

ከአንጋፋዎቹ ድምፃውያን መሐሙድ አህመድ፣ ኩኩ ሰብስብል፣ ዓለማየሁ እሸቴና አስቴር አወቀ አንስቶ በበርካታ ሙዚቀኞችን ስራ ሰርቶ ተወዳጅነትን አትርፏል፡፡

በዘመናዊ የኢትዮጵያ ሙዚቃ ስመጥር ከሆኑ ሙዚቀኞች አንዱ የሆነው ኤልያስ ከሠራቸው አልበሞች የቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ)፣ እዮብ መኮንን፣ ዘሪቱ ከበደ፣ ሚካያ በኃይሉ፣ ሚካኤል በላይነህ፣ አብነት አጎናፍርና ኃይለሚካኤል ጌትነት (ኃይሌ ሩትስ) ጌቴ አንለይ፣ ቤሪ፣ ዳን አድማሱና ዘለቀ ገሠሠ አልበሞችም ከብዙ በጥቂቱ ይጠቀሳሉ፡፡ በቅርቡም የወጣው የልዑል ሐይሉ "እሳቱ ሰዓት" የተሰኝውን አልበም በህይወት እያለ ለህዝብ ካደረሳቸው የሙዚቃ አልበሞች መካከል የመጨረሻው ስራ ሆኖ ተመዝግቧል። በቅርቡም በተካየደው 10ኛው ኢድስ ሚውዚክ ሽልማት ፕሮግራም ላይ የክብር ተሸላሚ ነበር።

የኤልያስ ግብዓተ መሬት ነገ ሰኞ 9 ሰዓት ላይ በጴጥሮስ ወ ጳውሎስ ቤተክርስቲያ ይፈፅማል። ከቀብር ስነ-ስርዓቱ በፊት 5 ሰዓት ላይ ሙዚቃን በተማረበት ያሬድ የሙዚቃ ትምህርት ቤት የሽኝት ፕሮግራም ተዘጋጅቷል።

. @pilasethiopia .



⭕️ጥቅሶች⭕️
ሳና
ይግቡ ⤵️⤵️⤵️
🦅 @pilasethiopia 🦅
🦅 @pilasethiopia 🦅
🦅 @pilasethiopia 🦅


Репост из: ምስክር ጌታነው ሚዲያና ፕሮሞሽን(You tube-Misiker media ምስክር ሚዲያ)
አዝነናል!
ዜማ ቃል
ነፍስ ይማር!
@muzicalword
"...ሙዚቃ ከእነ ሙሉ ክብሯ ነው በእርሱ ( በኤልያስ መልካ )
በኩል የምታልፈው ..."
ዘሪቱ ከበደ ፤ (ልዕልቷ) የሙዚቃ ባለሙያውን ኤሊያስ መልካ
የገለፀችበት ድንቅ አባባል፡፡

አዲስ አበባ
(አብነት፤ አዲስ ከተማ) የተወለደው ኤልያስ መልካ
በልጅነቱ በእግር ኳስ ጎበዝ ነበር - ‹‹ትንሹ ማራዶና -›የሚል
ቅፅል ሥም ነበረው፡፡

ኤልያስ መልካ - ብዙ ሰው ነው
1 ጊታሪስት (ሊድ)
2 ቤዚስት
3 ፒያኒስት
4 ድራመር
5 ሳክስፎኒስት
6 ኮንዳክተር
7 ገጣሚ (የረቀቀ)
8 ዜማ ደራሲ
9 አቀናባሪ
10 ፕሮዱዩሰር ይሄን ሁሉ መሆን ለአንድ ሰው በጣም ከባድ ነው ።

ስለኤልያስ መልካ ደግነት ደግሞ ጥቂት እናውጋ …
የሙዚቃ አቃናባሪው ፤ ሊድ ጊታር የሚጫወተው ሳይሆን ጊታር
የሚያናግረው ሚካኤል ሀይሉ እንዲህ ይላል …
‹‹የመጀመሪያ ጊዜ ያየሁት ጊዜ ፈርቼ ነበር ና ስትጫወት
ማየት እፈልጋለሁ "ግባ" አለኝ፡፡ ስቱዲዮ ውስጥ ገባሁ፡፡ …
በጣም ደስ አለኝ፡፡
"ጊታር አለህ?" አለኝ‹
ለጊዜው የለኝም›አልኩት፡፡ .. ‹"የምታጠናበት የለህም? ዘኪ ያንን ቦርሳ
አምጣልኝ" ብሎ "ይሄ ጊታር ከአሁን በኋላ ያንተ ናት ብሎ
ሰጠኝ፡፡"
... ኤልያስ መልካ መዚቃን እንደሥራ አይቆጥረውም፡፡
የሚጠፋበት የራሱ የሙዚቃ ዓለም አለው፡፡ አራት እና አምስት ቀናት ሳይተኛ የሚሰራ ታላቅ ሙዚቀኛ ነበር፡፡

😭😭 @muzicalword 😭😭
😭😭 @muzicalword 😭😭
😭😭 @muzicalword 😭😭



⭕ከታሪክ ውቅያኖስ️⭕️
​​ኢሬቻ ሎሬት ፀጋዬ ገ/መህን እንደፃፈው
.
ጸገመ

ይግቡ ⤵️⤵️⤵️
📃 @pilasethiopia 📃
📃 @pilasethiopia 📃
📃 @pilasethiopia 📃



⭕️ጥቅሶች⭕️

ደራሲ በዓሉ ግርማ
========
ሕይወት፣ በሁለት ዘለዓለማዊ ጨለማዎች መካከል ብልጭ ብላ፣ መልሳ ድርግም የምትል ብልጭታ ናት፡፡ ሀሴትና ሥቃይ አለ፡፡
መኖር ደስታ ነው፡፡ሞት ስቃይ ነው፡፡
መውደድ ደስታ ነው፡፡መለየት ሥቃይ ነው፡፡
ይግቡ ⤵️⤵️⤵️
🦅 @pilasethiopia 🦅
🦅 @pilasethiopia 🦅
🦅 @pilasethiopia 🦅


Репост из: Robomiz
Opening exhibition: graduates 2019 from Ale school of fine arts.
📆 Monday Oct7, 6:30pm-2pm
📍Alliance ethio-francies
Free entrance

Показано 20 последних публикаций.

208

подписчиков
Статистика канала