"ኤልያስ ምግብ ሲበላ ምስሉ የለኝም" ተዋናይ ግሩም ዘነበ ነው ባለፈው ሳምንት ማክሰኞ የጥበብ መንገድ ላይ የተናገረው፤ ኤልያስ ሙሉን ዕድሜ ለሙዚቃ ነው የሰጠው ምግብ በመብላት የሙዚቃ ጊዜውን መሻማት ስላልፈለግ አብዝቶ ብስኩት እና ሚሪንዳ በመብላቱ ስኳር እንደያዘው በሸገር ኤፍ ኤም ለለዛ ሬድዮ ፕሮግራም ላይ በ 2008 ዓ/ም በሰጠው ቃለ መጠይቅ ተናግሯል።
ከአንጋፋዎቹ ድምፃውያን መሐሙድ አህመድ፣ ኩኩ ሰብስብል፣ ዓለማየሁ እሸቴና አስቴር አወቀ አንስቶ በበርካታ ሙዚቀኞችን ስራ ሰርቶ ተወዳጅነትን አትርፏል፡፡
በዘመናዊ የኢትዮጵያ ሙዚቃ ስመጥር ከሆኑ ሙዚቀኞች አንዱ የሆነው ኤልያስ ከሠራቸው አልበሞች የቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ)፣ እዮብ መኮንን፣ ዘሪቱ ከበደ፣ ሚካያ በኃይሉ፣ ሚካኤል በላይነህ፣ አብነት አጎናፍርና ኃይለሚካኤል ጌትነት (ኃይሌ ሩትስ) ጌቴ አንለይ፣ ቤሪ፣ ዳን አድማሱና ዘለቀ ገሠሠ አልበሞችም ከብዙ በጥቂቱ ይጠቀሳሉ፡፡ በቅርቡም የወጣው የልዑል ሐይሉ "እሳቱ ሰዓት" የተሰኝውን አልበም በህይወት እያለ ለህዝብ ካደረሳቸው የሙዚቃ አልበሞች መካከል የመጨረሻው ስራ ሆኖ ተመዝግቧል። በቅርቡም በተካየደው 10ኛው ኢድስ ሚውዚክ ሽልማት ፕሮግራም ላይ የክብር ተሸላሚ ነበር።
የኤልያስ ግብዓተ መሬት ነገ ሰኞ 9 ሰዓት ላይ በጴጥሮስ ወ ጳውሎስ ቤተክርስቲያ ይፈፅማል። ከቀብር ስነ-ስርዓቱ በፊት 5 ሰዓት ላይ ሙዚቃን በተማረበት ያሬድ የሙዚቃ ትምህርት ቤት የሽኝት ፕሮግራም ተዘጋጅቷል።
. @pilasethiopia .