"ወደ ተራራ ጫፍ"
ዘማሪት አስቴር አበበ
#1 ) ከህልውናህ ሰፈር ከምትገኝበት
ንግግር ጸሎቴ አንተው ከሆንክበት
ጠንቀቅ ካላልኩኝ ካልጠበቅኩ እግሮቼን
እልፍ የሚለይ ጉዳይ ከቦኛል ዙሪያዬን
በገለባ ናፍቆት በጠፊ ፍለጋ
አይለቅብኝ ቀኔ አርቆኝ ከአንተጋ
ወደ ተራራው ጫፍ ሳበኝ ወደራስህ
ነፍሴም ድና እንድትቀር አቅልጣት በክብርህ
መባዘን አይደለም መዋል ከአንተ ጋራ
ስለ ላዩ ምክርህ ነፍሴን ስታዋራ
ሰብሰብ ብሎዋል ቀኔ አልተዝረከረከም
የማይወሰድ እድል ከዚህ በላይ የለም
#2 ) አንተን ብቻ ይሁን የማይበት አይኔ
ልቤ ሄዶ ይቅር ከላዩ ሰፈሬ
ጆሮዬም ይቀሰር ከላይኛው ሃገር
አጥፋኝ ከምድሩ ፍለጋዬ ይሰወር
አንገቴን አስግጌ በመናፈቅ ህይወት
ለአፍታ ጎንበስ ሳልል አንዳች ከሌለበት
እጅ ሰጥቶ ለአንተ ውስጥና ውጪዬ
ስንቄ ሆኖ ፍቅርህ ይጠቅለል እድሜዬ
ጥሜ ረሃቤ ናፍቆቴ መሻቴ
ጉጉቴ ፍላጎቴ ሩጫዬ መገስገሴ
አንተን ለማግኘት ነው
በቃ እፈልግሃለሁ በቃ ተርቤሃለሁ
በቃ በጣም ጠምተኸኛል በቃ አይኖቼ ናፍቀውሃል
በቃ ናፍቄሃለሁ በቃ ደጅ ደጅ አያለሁ
በቃ የውስጤ ጥም ነህ በምንም የማልለውጥህ
አንተን የተራበ የሚጠግበው አንተን ነው
አንተን የተጠማ የሚረካው አንተን ነው
ፊትህን የፈለገ ሲያገኝህ ያርፋል
ፈልጎ ክብርህን በእጅህ መች ይረካል
አይደለሁም ሰነፍ ተመከርኩ በቃልህ
የውስጤን ረሃብ አይደፍነውም የእጅህ
ነፍሴን የምታረካ ሙላት ነህ የልቤ
የኑሮዬ ፍሰሃ የዕድሜ ልክ ሃሳቤ
share♻️share♻️share♻️
🎼🎼 𝙟𝙤𝙞𝙣 & 𝙨𝙝𝙖𝙧𝙚 🎼🎼
@Protestantmezemur
@Protestantmezemur
─── ❖ ── ✦ ── ❖ ───
ዘማሪት አስቴር አበበ
#1 ) ከህልውናህ ሰፈር ከምትገኝበት
ንግግር ጸሎቴ አንተው ከሆንክበት
ጠንቀቅ ካላልኩኝ ካልጠበቅኩ እግሮቼን
እልፍ የሚለይ ጉዳይ ከቦኛል ዙሪያዬን
በገለባ ናፍቆት በጠፊ ፍለጋ
አይለቅብኝ ቀኔ አርቆኝ ከአንተጋ
ወደ ተራራው ጫፍ ሳበኝ ወደራስህ
ነፍሴም ድና እንድትቀር አቅልጣት በክብርህ
መባዘን አይደለም መዋል ከአንተ ጋራ
ስለ ላዩ ምክርህ ነፍሴን ስታዋራ
ሰብሰብ ብሎዋል ቀኔ አልተዝረከረከም
የማይወሰድ እድል ከዚህ በላይ የለም
#2 ) አንተን ብቻ ይሁን የማይበት አይኔ
ልቤ ሄዶ ይቅር ከላዩ ሰፈሬ
ጆሮዬም ይቀሰር ከላይኛው ሃገር
አጥፋኝ ከምድሩ ፍለጋዬ ይሰወር
አንገቴን አስግጌ በመናፈቅ ህይወት
ለአፍታ ጎንበስ ሳልል አንዳች ከሌለበት
እጅ ሰጥቶ ለአንተ ውስጥና ውጪዬ
ስንቄ ሆኖ ፍቅርህ ይጠቅለል እድሜዬ
ጥሜ ረሃቤ ናፍቆቴ መሻቴ
ጉጉቴ ፍላጎቴ ሩጫዬ መገስገሴ
አንተን ለማግኘት ነው
በቃ እፈልግሃለሁ በቃ ተርቤሃለሁ
በቃ በጣም ጠምተኸኛል በቃ አይኖቼ ናፍቀውሃል
በቃ ናፍቄሃለሁ በቃ ደጅ ደጅ አያለሁ
በቃ የውስጤ ጥም ነህ በምንም የማልለውጥህ
አንተን የተራበ የሚጠግበው አንተን ነው
አንተን የተጠማ የሚረካው አንተን ነው
ፊትህን የፈለገ ሲያገኝህ ያርፋል
ፈልጎ ክብርህን በእጅህ መች ይረካል
አይደለሁም ሰነፍ ተመከርኩ በቃልህ
የውስጤን ረሃብ አይደፍነውም የእጅህ
ነፍሴን የምታረካ ሙላት ነህ የልቤ
የኑሮዬ ፍሰሃ የዕድሜ ልክ ሃሳቤ
share♻️share♻️share♻️
ድንቅ ዝማሬዎችን ከፈለጉ
ይህን link⬇️ተጭነው ይቀላቀሉ
🎼🎼 𝙟𝙤𝙞𝙣 & 𝙨𝙝𝙖𝙧𝙚 🎼🎼
@Protestantmezemur
@Protestantmezemur
─── ❖ ── ✦ ── ❖ ───