💥 ራዕያችን ወልዶ በተግባር መታየትና ለውጥን ማምጣት አለበት። አለዚያ ከንቱ ምኞት ሆኖ ይቀራል።
. የልባችን ሸክም እውነተኛ መለኮታዊ ራዕይ መሆኑን አለመሆኑን እንዴት እናውቃለን?
የልባችን ሸክም ራዕይ ልሆንም ላይሆንም ስለሚችል፣ የልባችንን ሸክም ራዕይ ነው ብለን ከመውጣታችን በፊት የልባችን ሸክም እውነተኛ ራዕይ መሆኑን አለመሆኑን ማወቅ ያስፈልጋል።
እዉነተኛ መለኮታዊ ራእይ እንደ እግዚአብሔር ቃል የሆነ፣ ልጁን ኢየሱስ ክርስቶስን የሚያሳይ፣ ለሌሎች ጥቅም መስዋዕት የሚሆን፣ ለትዉልድ የመኖር ዓላማን የሚሰጥ፣ ከንግግርና ከወረቀት ያለፈ በተግባር፣ በሥራና በፍሬ የሚታይ፣ ለትዉልድ እግዚአብሔርን መምሰልና ቅድስናን የሚሰብክ፣ በነገ ወይም በሚያመጣዉ ዉጤት እንጂ በዛሬ ሁኔታ ራሱን የማይወስን፣ ከሚታየው ከምድራዊ ሁኔታ ዉጭና በላይ የሆነ አስደናቂ ኃይል ያለው ነው።
ለእውነተኛ መለኮታዊ ራዕይ ችግርን ከነ መፍትሔው የማየት፣ ለሌሎችንም የማሳየት እና ለችግሮች መለኮታዊ መፍተሔ የመስጠት አቅም አለው። እውነተኛ ራዕይ በሁለት ገጽታዎች መካከል ማለትም በራዕዩ መነሻና የራዕዩ መድረሻ የሚኖር ነው። እውነተኛ መለኮታዊ ራዕይ አሁን እንደግለሰብ፣ እንደሀገርና እንደቤተከርስቲያን ያለ አፋጣኝ መፍትሔ የሚሻ አንገብጋቢ ጉዳይን አይተው ለዛ አንገብጋቢ አፋጣኝ መፍትሔ ለሚሻ ጉዳይ መለኮታዊ መፍትሔን ይሰጣል።
በተጨማሪ እውነተኛ መለኮታዊ ራዕይ ግልጽና የሚታወቅ ነዉ። ብዙዎች ራዕይ ሲባል ሊጨበጥ የማይችል ኃይማኖታዊ ሃሳብ ብቻ ይመስላቸዋል፡፡ ለዚህ ነው አንዳንድ ሰዎች ስለሕይወትህ፣ ስለቤተሰብህ፣ ስለአገልግሎትህና ስለስራህ ራእይ አለህ? ተብለው ሲጠየቁ ሕይወታቸውን የሚያወሳሰብ ሊደረስበት የማይችል ረቂቅ ጥያቄ የተጠየቁ ይመስላቸዋል፡፡ ነገር ግን እውነተኛ መለኮታዊ ራዕይ የማይገባ፣ የማይገለጽ፣ የማይታወቅ፣ ግራ የሚያጋባና የተወሳሰበ ሳይሆን ለማስረዳት የቀለለ፣ ለመረዳት የማይከብድ ግልጽ የሆነ ነው።
@revealjesus