[ . . . የባከነ ጸሎት . . . ]
.
አድርገኝ
እንደ ምንጭ ውኃ
ስጠኝ አንዳች ዕድል
የሚያረካ ፣ የማይጎድል
.
በተመስጦ የምቀመጥ
ንግግሬ የሚደመጥ
ሕዝቡ ሁሉ የሚያደንቀኝ
የዓለም ግራ ፣ የጻዲቅ ቀኝ
.
ነጭ ጢማም የበራለት
ጥበብ በውል የገራለት
ቦዲሳትቫ ፣ ጭምት ካህን
የሚያደርግ ዕውቀትህን
.
ግለጥልኝ ባክህ
ተናገር አንዲት ቃል
እያለ የኖረ
አንድ ሰው ነበረ።
.
በልጅነቱ
በወጣትነቱ
በጎልማሳነቱ
የለመነው አምላክ
ድንገት ብቅ ብሎ
እርሙን ቢናገረው
በዕድሜው ማብቂያ ቀናት
የተናገራት ቃል
“ዝምበል እባክህን” የምትል ሀረግ ናት።
[ ሄኖክ በቀለ ]
@Samuelalemuu
.
አድርገኝ
እንደ ምንጭ ውኃ
ስጠኝ አንዳች ዕድል
የሚያረካ ፣ የማይጎድል
.
በተመስጦ የምቀመጥ
ንግግሬ የሚደመጥ
ሕዝቡ ሁሉ የሚያደንቀኝ
የዓለም ግራ ፣ የጻዲቅ ቀኝ
.
ነጭ ጢማም የበራለት
ጥበብ በውል የገራለት
ቦዲሳትቫ ፣ ጭምት ካህን
የሚያደርግ ዕውቀትህን
.
ግለጥልኝ ባክህ
ተናገር አንዲት ቃል
እያለ የኖረ
አንድ ሰው ነበረ።
.
በልጅነቱ
በወጣትነቱ
በጎልማሳነቱ
የለመነው አምላክ
ድንገት ብቅ ብሎ
እርሙን ቢናገረው
በዕድሜው ማብቂያ ቀናት
የተናገራት ቃል
“ዝምበል እባክህን” የምትል ሀረግ ናት።
[ ሄኖክ በቀለ ]
@Samuelalemuu