አል - ሻባብ የጣሊያን መንግስት ለሞቃዲሾ መንግስት በቅርቡ ከለገሰቻቸው ሁለት ሄሊኮፕተሮች መካከል አንዱን መያዙ ነው በዛሬው ዕለት የተዘገበው።
የሶማሊያ ጋዜጠኞች እንደገለፁት ሄሊኮፕተሯ በሶማሊያ ጋልሙዱግ Galmudug ግዛት ውስጥ አልሸባብ በተቆጣጠረው ቦታ እንድታርፍ ተደርጋለች።
በተያዘው የፈረንጆቹ 2024 ውስጥ ለሶማሊያ ሰራዊት የጦር መሳሪያ የጫነ አይሮፕላን አልሸባብ በሚቆጣጠረው አካባቢ ሲያርፍ ይህ ለሶስተኛ ጊዜ ሲሆን ይህም አሸባሪው ቡድን የጦር መሳሪያዎቹን በእጁ እያስገባ የመቀጠሉ ማሳያ ነው።
አል ሸባብ አሁን ወደራሱ ያደረጋት ሄልኮፕተር ወደ ሶማሌ ብሄራዊ ሰራዊት የጦር መሳሪያዎች ጭና በጋልሙሉክ ግዛት አካባቢ በማጓጓዝ ላይ የነበረች ሲሆን በውስጧም ስምንት የበራሪዋ ሰራተኞች ነበሩ ተብሏል።
ጣልያን በቅርቡ ለሶማሊያ የለገሰቻቸው 4 ሄልኮፕተሮች 'Bell 412 Multipurpose' ሄልኮፕተሮች ሲሆኑ እያንዳንዳቸውም 16 ሚሊዮን ዶላር ዋጋ ያላቸው ናቸው። ይሁንና አል ሸባብ ያዛት የተባለችው ሄልኮፕተር ጣልያን ከለገሰቻቸው 2 ሄልኮፕተሮች መካከል ናት የሚሉት ከሶማሊያ የወጡ ሪፖርቶች፣ አል ሻባብ የያዛት Bell 412 ወይም ሌላ አይነት ሄልኮፕተር ስለመሆኗ የሚያስረግጡ መረጃዎች ለጊዜው አልተገኙም።
በርካታ ምንጮች እንደሚገልፁት ለሞቃዲሹ መንግስት ከተላኩት የጦር መሳሪያዎች ውውጥ 90 በመቶ የሚሆኑት በተለያዩ መንገዶች በአልሸባብ እጅ ይወድቃሉ። ይህን መሰል የጦር መሳሪያ የጫኑ አውሮፕላኖች በአልሸባብ ቁጥጥር ስር ባሉ አካባቢዎች ከማረፋቸው ባሻገር፣ የሶማሊያ ብሄራዊ ሰራዊት ወታደሮች ሳይቀር የጦር መሳሪያቸውን ብዙ ጊዜ ለአልሸባብ በመሸጥ ጫት ለመግዛት እንደሚያውሉት ይገለፃል።