Репост из: አል–ፈቂር ኢለሏህ( ሷድቅ አወል) አልወራቢይ
◉ሸይኻች ሸይኽ ዐብዱል ሐሚድ አል_ለተሚይ!
ሀቁን በማብራራት ባጢሉን ሲንዱ
ዲንን ለማስተማር እስከ ጫፍ ሲሄዱ።
የሙብተዲዕን ሴራ ለኡማው ሲያስረዱ
የጥመት አንጃዎች ምቀኞች ነደዱ።
ምን ቢጣጣሩ የቢድዓ አካላት
ለመንሐጀ ሰለፍ ጠባቂ እኮ አላት።
አንዱ ቢከረበት ሊሆን አበሳ
ዲንና መንሐጁን ሊሸጥ ቢነሳሳ
ተገልብጦ ቢሆን የሱና ነቀርሳ
የሰለፎችን ስም በመጥፎ ሚያነሳ
ዑለሞች አሉን የዲን አንበሳ
በጭራሽ ማይፈሩ የወቃሽ ወቀሳ!!
ጥቅም ፈላጊው ቢያጠለሻቸው
ሼኻችን ሀቅን በመርዳት ላይ ናቸው።
ስማቸውን ለማርከስ አትድከም ይብቃህ
አንድም ከኛ የለም ባጢልህን ሚሰማህ!
ምን ቢፍጨረጨር ቢያነጋ ሳይተኛ
ዑለሞች ናቸው የሰለፍያ ዘበኛ!
ሀቅን ስለያዙ ምን ቢያጣጥሏቸው
አንድ መሆናችን ቢያንጨረጭራቸው
በደዕወተ ሰለፍ ቢቀላም ፊታቸው
ሙቱ ቢغይዚኩም ነው የምንላቸው‼️2×
እኔ ስገረም በእውቀታቸው
ለካ የሼኽ ዑሰይሚን ደረሳ ናቸው።
ያላታለላቸው ዱንያ ብልጭልጭ
ረድ ነቅድ አይተዉም ማንም ቢበሳጭ!
ግዜያዊ ጥቅም ገንዘብ ያልበገራቸው
ለገጠር ከተማው ለተውሂድ ብርሃን ሰበብ ናቸው።
ደዕወተ ሰለፍን በማሰራጨት
ኡማውን አነቁት ከተኛበት።
ስራችን እንዲሆን ለሸሪዓ ተስማሚ
ለቢድዓ አካላት ሆነዋል ኮርኳሚ።
በጣም ደስ የሚለኝ ከንግግራቸው
"ጉድ እኮ ነው!" ይላሉ ነገር ሲገርማቸው።
እኔን ለማስከፋት ከሀቅ ለማስወጣት
ቢሉኝ "ለተሚይ"
ታዲያ ለምን ይክፋኝ ለተሞ እኮ ናቸው
ሱንይ ሰለፍይ።
አይደሉም ሙብተዲዕ ኢኽዋን ሱፍይ
ደግሞም ሀዳድይ።
እስኪ ነቃ እንበል እስኪ እናስተንትን
እንጣል ተዐሱብን እንተው ቅጥፈትን።
ሀቅን እንፈልጋት ከውስጥ ከልባችን
አንሰማም እንበል አላዋቂዎችን።
አንተ ሙብተዲዕ ሆይ አትበል እርር
በሀቅ መፅናታቸው ምንኛ ሲያምር
ስማቸውን ማጥፋት ምንም አይጠቅምህም
ሀቅን ተቀበል ቢያጥወለውልህም!
ምንም ብትለፈልፍ እኛ አንሰማህም
እሳቸውን ሚያስተች ማስረጃ የለህም!
አንተ አላዋቂ ሆይ አቸኩል ለወሬ
ከጎናቸው ነበርክ ምን ተገኘ ዛሬ
አሁን ተከረበትክ ምነው ሳዳትዬ?
ትላንት በአቋምህ ነበር ያፀደከው
ዛሬ ተገልብጠህ ለምን ውሸት አልከው?
እራስህን ከራስህ ለምን አጋጨኸው?
የሀቁንስ መንገድ እንደምን ጠላኸው?
ከነርሱ አልደመርም እንዳላልክ እዬዬ
አሁን ተከረበትክ ምነው ሳዳትዬ?
ማንም የትም ቢሄድ ማን ቢሆንም ምንም
ሀቅ ግን ሀቅ ናት አትቀያየርም‼2×
ማንም ቢነቅፋቸው ማን ቢኻልፋቸው
አቡ ዐብዱል ሐሊም ለሀቅ ታጋይ ናቸው።
ዛሬ ተገልብጠህ ብትላቸው ጃሂል
አዋቂ ሼኽ ናቸው ያላሉ ውልውል!
ለዚህም ምስክር ከደረሶቻቸው
ሙሐመድ ኪርማኒይ ሻኪር ሱልጧን ናቸው
ሁሰይን ሙሳን ብትል...በጣም ብዙ ናቸው።
በጊዜ መሄድ ያልተቀያየሩ
በሄዱበት ሁሉ ሀቅን ሚያስተምሩ
ባለ ብዙ እውቀት ብርቅዬዎች ናቸው።
ተወዳጅ የሆኑ ከነ ሼኻቸው።
መንሀጀ ሰለፍ ያስከበራቸው!
እውነተኛ መሆን ሀቅ ያላቃቸው።
ኡማው ዘንድማ ያስወደዳቸው
በሀቋ ላይ ፍንክች አለማለታቸው
ቀጣፊ ውሸታም አለመሆናቸው‼
ይሄ ኬት መጣ ብለህ ብጠይቅ
አንተ ጃሂል ያልከው እንዳስተማራቸው ጠንቅቀህ እወቅ‼
እውቀትን ለማካፈል ስስታም ያልሆኑ
እኔን ብቻ ስሙኝ በጭራሽ ያላሉ።
በስተመጨረሻም ዱዐ ላርግላቸው
ከሙብተዲዕ ሴራ እንዲጠብቃቸው
ያላዋቂን ወሬ ሊያርቅላቸው።
የኛን ውድ ሼኽ እንዲያልቃቸው።
የሀቋንም መንገድ ላያስለቅቃቸው።
በመንሐጀ ሰለፍ እንዲያፀናቸው
እድሜያቸውን ረጅም እንዲያደርግላቸው።
እንዲያስተምሩ ለደረሶቻቸው
ድርብርብ እውቀትን ይጨማምርላቸው።
በሀቋም መንገድ ላይ ሁነው ይውሰዳቸው!!
📝የ'አብዱል ሐኪም ልጅ!
@Abdul_halim_ibnu_shayk
ሀቁን በማብራራት ባጢሉን ሲንዱ
ዲንን ለማስተማር እስከ ጫፍ ሲሄዱ።
የሙብተዲዕን ሴራ ለኡማው ሲያስረዱ
የጥመት አንጃዎች ምቀኞች ነደዱ።
ምን ቢጣጣሩ የቢድዓ አካላት
ለመንሐጀ ሰለፍ ጠባቂ እኮ አላት።
አንዱ ቢከረበት ሊሆን አበሳ
ዲንና መንሐጁን ሊሸጥ ቢነሳሳ
ተገልብጦ ቢሆን የሱና ነቀርሳ
የሰለፎችን ስም በመጥፎ ሚያነሳ
ዑለሞች አሉን የዲን አንበሳ
በጭራሽ ማይፈሩ የወቃሽ ወቀሳ!!
ጥቅም ፈላጊው ቢያጠለሻቸው
ሼኻችን ሀቅን በመርዳት ላይ ናቸው።
ስማቸውን ለማርከስ አትድከም ይብቃህ
አንድም ከኛ የለም ባጢልህን ሚሰማህ!
ምን ቢፍጨረጨር ቢያነጋ ሳይተኛ
ዑለሞች ናቸው የሰለፍያ ዘበኛ!
ሀቅን ስለያዙ ምን ቢያጣጥሏቸው
አንድ መሆናችን ቢያንጨረጭራቸው
በደዕወተ ሰለፍ ቢቀላም ፊታቸው
ሙቱ ቢغይዚኩም ነው የምንላቸው‼️2×
እኔ ስገረም በእውቀታቸው
ለካ የሼኽ ዑሰይሚን ደረሳ ናቸው።
ያላታለላቸው ዱንያ ብልጭልጭ
ረድ ነቅድ አይተዉም ማንም ቢበሳጭ!
ግዜያዊ ጥቅም ገንዘብ ያልበገራቸው
ለገጠር ከተማው ለተውሂድ ብርሃን ሰበብ ናቸው።
ደዕወተ ሰለፍን በማሰራጨት
ኡማውን አነቁት ከተኛበት።
ስራችን እንዲሆን ለሸሪዓ ተስማሚ
ለቢድዓ አካላት ሆነዋል ኮርኳሚ።
በጣም ደስ የሚለኝ ከንግግራቸው
"ጉድ እኮ ነው!" ይላሉ ነገር ሲገርማቸው።
እኔን ለማስከፋት ከሀቅ ለማስወጣት
ቢሉኝ "ለተሚይ"
ታዲያ ለምን ይክፋኝ ለተሞ እኮ ናቸው
ሱንይ ሰለፍይ።
አይደሉም ሙብተዲዕ ኢኽዋን ሱፍይ
ደግሞም ሀዳድይ።
እስኪ ነቃ እንበል እስኪ እናስተንትን
እንጣል ተዐሱብን እንተው ቅጥፈትን።
ሀቅን እንፈልጋት ከውስጥ ከልባችን
አንሰማም እንበል አላዋቂዎችን።
አንተ ሙብተዲዕ ሆይ አትበል እርር
በሀቅ መፅናታቸው ምንኛ ሲያምር
ስማቸውን ማጥፋት ምንም አይጠቅምህም
ሀቅን ተቀበል ቢያጥወለውልህም!
ምንም ብትለፈልፍ እኛ አንሰማህም
እሳቸውን ሚያስተች ማስረጃ የለህም!
አንተ አላዋቂ ሆይ አቸኩል ለወሬ
ከጎናቸው ነበርክ ምን ተገኘ ዛሬ
አሁን ተከረበትክ ምነው ሳዳትዬ?
ትላንት በአቋምህ ነበር ያፀደከው
ዛሬ ተገልብጠህ ለምን ውሸት አልከው?
እራስህን ከራስህ ለምን አጋጨኸው?
የሀቁንስ መንገድ እንደምን ጠላኸው?
ከነርሱ አልደመርም እንዳላልክ እዬዬ
አሁን ተከረበትክ ምነው ሳዳትዬ?
ማንም የትም ቢሄድ ማን ቢሆንም ምንም
ሀቅ ግን ሀቅ ናት አትቀያየርም‼2×
ማንም ቢነቅፋቸው ማን ቢኻልፋቸው
አቡ ዐብዱል ሐሊም ለሀቅ ታጋይ ናቸው።
ዛሬ ተገልብጠህ ብትላቸው ጃሂል
አዋቂ ሼኽ ናቸው ያላሉ ውልውል!
ለዚህም ምስክር ከደረሶቻቸው
ሙሐመድ ኪርማኒይ ሻኪር ሱልጧን ናቸው
ሁሰይን ሙሳን ብትል...በጣም ብዙ ናቸው።
በጊዜ መሄድ ያልተቀያየሩ
በሄዱበት ሁሉ ሀቅን ሚያስተምሩ
ባለ ብዙ እውቀት ብርቅዬዎች ናቸው።
ተወዳጅ የሆኑ ከነ ሼኻቸው።
መንሀጀ ሰለፍ ያስከበራቸው!
እውነተኛ መሆን ሀቅ ያላቃቸው።
ኡማው ዘንድማ ያስወደዳቸው
በሀቋ ላይ ፍንክች አለማለታቸው
ቀጣፊ ውሸታም አለመሆናቸው‼
ይሄ ኬት መጣ ብለህ ብጠይቅ
አንተ ጃሂል ያልከው እንዳስተማራቸው ጠንቅቀህ እወቅ‼
እውቀትን ለማካፈል ስስታም ያልሆኑ
እኔን ብቻ ስሙኝ በጭራሽ ያላሉ።
በስተመጨረሻም ዱዐ ላርግላቸው
ከሙብተዲዕ ሴራ እንዲጠብቃቸው
ያላዋቂን ወሬ ሊያርቅላቸው።
የኛን ውድ ሼኽ እንዲያልቃቸው።
የሀቋንም መንገድ ላያስለቅቃቸው።
በመንሐጀ ሰለፍ እንዲያፀናቸው
እድሜያቸውን ረጅም እንዲያደርግላቸው።
እንዲያስተምሩ ለደረሶቻቸው
ድርብርብ እውቀትን ይጨማምርላቸው።
በሀቋም መንገድ ላይ ሁነው ይውሰዳቸው!!
📝የ'አብዱል ሐኪም ልጅ!
@Abdul_halim_ibnu_shayk