❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን" ❤
❤ #ኅዳር ፳፬ (24) ቀን።
❤ እንኳን #በእግዚአብሔ_ዙፋን_ዙርያ ለሚቆሙ #የቅድስት_ሥላሴ_ዙፍን ለሚያጥኑ #ለሃያ_አራቱ_ካህናተ_ሰማይ_ቅዱሳን_ለሱራፊል ለበዓላቸው መታሰቢያ፣ #ለናግራ_አገር_ቄስ ለከበረ #ለቅዱስ_አዝቂር፤ እርሱ ጋር አብረው ሰማዕትነት ለተቀበሉ #አርባ_ስምንት_ሰዎች ለዕረፍታቸው በዓል፣ #ለፃን_አገር_ለሆነ_ለአባ_ዮሴፍ_ለዕረፍታቸው እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን በስንክሳሩ ከሚታሰቡ፦ #ከቅዱሳን_ጋይዮስ_ከቃርዮስ ከጽኑዕ መስተጋድልም ከሆነና መልካም ስም አጠራር ዜና ካለው #ከአባ_ዲዮስቆሮስም ከመታሰቢያቸው ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
✝ ✝ ✝
❤ #ሃያ_አራቱ_ካህናተ_ሰማይ_ቅዱሳን_ለሱራፊል፦ እሊህም ሥጋ የሌላቸው ረቂቃን የእውነት ካህናት የሆኑ ከቅዱሳን ሁሉ በላይ የሆኑና ከሰማይ ሠራዊት ሁሉ ከፍ ከፍ ያሉ ናቸው እነርሱም ለእግዚአብሔር ቀራቢዎች በመሆን ለሰው ወገን የሚማልዱ ከእጃቸው ውስጥ ካለ ማዕጠንት ጋር እንደ ዕጣን የቅዱሳንን ጸሎት የሚያቀርቡ ናቸው ያለእነርሱም አቅራቢነት ጽድቅና ምጽዋት ወደ እግዚአብሔር አይቀርብም።
❤ ወንጌላዊ ቅዱስ ዮሐንስ በራእዩ እንዲህ ብሎ እንደ ተናገረ። "በዙፋኑ ዙርያ ሃያ አራት መንበሮች አሉ በእነዚያ መንበሮችም ሃያ አራት አለቆች ተቀምጠዋል ነጭ ልብስ ለብሰዋል በራሳቸውም ላይ የወርቅ አክሊል አለ። ሁለተኛም እንዲህ አለ "ሌላም መልአክ መጥቶ በመሠዊያው ፊት ቁሞ የወርቅ ጽንሐሕ ይዟል በመንበሩ ፊት ባለ በወርቁ መሠዊያ ላይሞ የቅዱሳንን ሁሉ ጸሎት ያሳርግ ዘንድ ብዙ ዕጣንን ሰጡት። የዕጣኑም ጢስ ከቅዱሳኑ ጸሎት ጋር በዚያ መልአክ እጅ ወደ እግዚአብሔር ፊት ዐረገ"።
❤ "የነበረ የሚኖር የአማልክት አምላክ እግዚአብሔር ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ ነው" እያሉ በመዓልትና በሌሊት ዕረፍት የላቸውም። እሊህም እንስሶቹ ለዘላለሙ ሕያው ለሚሆን በዙፋን ላይ ለተቀመጠ ለሱ እንዲህ እያሉ ክብር ምስጋና አቀረቡ።
❤ እሊህ ሃያ አራቱ አለቆች አክሊላቸውን በዙፋኑ ፊት አውርደው ለዘላለሙ ሕያው ለሚሆን በዙፋን ላይ ለተቀመጠ ለእርሱ ሰገዱለት። አክሊላቸውንም ወደ ዙፋኑ ፊት ወስደው "አቤቱ ፈጣሪያችን ኃይልና ምስጋና ክብር ላንተ ይገባል ይሉታል አንተ ሁሉን ፈጥረሃል የተፈጠረውም ሁሉ በአንተ ፈቃድ ይኖራልና"።
❤ እነርሱ በእግዚአብሔር ዘንድ በባለሟልነት እጅግ የቀረቡ መሆናቸውንና ስለሁላችን የአዳም ልጆች ስለሚለምኑና ስለሚማልዱ ከብሉይና ከሐዲስ የከበሩ መጻሕፍት ምስክር ኑነዋል ስለዚህም የበዓላቸውን መታሰቢያ እናደርግ ዘንድ የቤተ ክርስቲያን መምህራን አዘዙ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በሃያ አራቱ ካህናተ ሰማይ በአማላጅነታቸው ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
✝ ✝ ✝
❤ #ቄስ_ቅዱስ_አዝቂር፦ ይህም ንጉሥ አዝቂርን ወደ ወህኒ አስገብተው እንዲዘጉበት ጠባቂዎቹንም ከሰው ወገን ማንም እንዳይገባ ብሎ አዘዘ። ቅዱስ አዝቂርም በጸለየ ጊዜ የወህኒ ቤቱ ደጃፍ ተከፈተና ሃምሳ ሰዎች ወደርሱ ገቡ እርሱም በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አጠመቃቸው።
✝ ንጉሥ ሰራብሄልም በሰማ ጊዜ በወህኒ ቤት አውጥተው ወደሌላ አገር እንዲወስዱት አዘዘ በጉዞም ላይ ስሙ ኪርያቅ ከሚባል ሰው ጋር ተገናኘ ቀስሲስ አዝቂርም ኪርያቅን "ኪርያቅ ሆይ ላንተ የምሥራች ይገባል ለሰማዕትነት ይወስድሃልና" አለው። የንጉሥ ሎሌዎችም ሰምተው አሥረው ከእርሱ ጋር ወሰደቱ። ዳግመኛም ሁለት ሰዎች ተገናኙትና "ስለ ክርስቶስ አጥምቀን" አሉት ያን ጊዜም ቅዱስ አዝቂር ጸለየና ከበረሃ ቦታ ውኃ አፍልቆ ከኪርያቅ ጋር አጠመቃቸው።
❤ ከዚህም በኋላ ወደበረሀ ውስጥ በደረሱ ጊዜ ለእርሳቸውም ለእንስሶቻቸውም የሚጠጡት ውኃ አጥተው ወደ እግዚአብሔር እንዲለምንላቸው ቅዱስ አዝቂርን ለመኑት በጸለየም ጊዜ ደመና መጣ በመሐል እጅ በመመታፈን መጠን በገብታ ላይ ዘነበ ሰባት መቶ ያህል ሰዎች ከእንስሶቻቸው ጋር ጠጥተው ረኩ።
❤ ወደ ንጉሡም በአቀረቡት ጊዜ "ወደ አገራችን ያመጣኸው ይህ አዲስ ትምህርት ምንድነው?" አለው ቅዱስ አዝቂርም "ነቢያት በኦሪት ከሰበኩት በቀር ሌላ አዲስ ትምህርት አላመጣሁም" አለ ንጉሡም ይህን ሰምቶ በክርስቲያን ሃይማኖት ላይ ተዘባበተ። ከአይሁድ መምህራንም አንዱ ተነሥቶ እንዲህ አለ "ጌታዬ ሆይ ወደ አገሩ እንዲወስዱትና በዕንጨት ላይ ሰቅለው በሕይወት ሳለ በእሳት እንዲአቃጥሉት እዘዝ" አለው ንጉሡም እንደ አይሁዳዊው ቃል አዘዘ።
❤ ወደ ናግራን አገርም በአደረሱት ጊዜ በዕንጨት ላይ ሰቅለው ከበታቹ እሳትን አነደዱ ቅዱስ አዝቂርም ወደጌታችን ጸለየ በዚያንም ጊዜ ከማሠሪያው ተፈትቶ ከእሳት ውስጥ በደኅና ወጣ አይሁድም በደንጊያ እንውገረው ተባብለው በወገሩት ጊዜ ደንጊያዎች ተመልሰው ከአይሁድ የሚበዙትን ገደሉ። ከተረፉትም ሰይፍን አንሥተው የቅዱስ አዝቂርን ራስ ቆረጡ ምስክርነቱንም ፈጽሞ የሰማዕትነት አክሊል ተቀዳጀ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በዚህ በቅዱስ አባት አዝቂር ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
✝ ✝ ✝
❤ #አባ_ዮሴፍ፦ ለዚህም ቅዱስ ወላጆቹ በሃይማኖት የበለጸጉ ናቸው ነገር ግን ያለርሱ ልጅ አልነበራቸውም የቤተ ክርስቲያንንም ትምህርት መጽሐፍት ማንበብን እያስተማሩ መልካም አስተዳደግን አሳደጉት መልኩም እንደ ያዕቆብ ልጅ ዮሴፍ ያማረ ነበር በአደገም ጊዜ ሞትን የዚህ ዓለም ኀላፊት ማሰብ በልቡ አሰበ ወደ አንድ ገዳም ሆዶ መነኰሰ በጾም በጸሎት በመስገድ ተጋድሎ የተተከለ ሆኖ ጸና በአቱንም ዘግቶ በዕለ እሁድ ከቊርባን ጊዜ በቀ አይወጣም ነበር።
❤ ዜናውም በተሰማ ጊዜ ከእርሱ በረከቱን ይቀበሉ ዘንድ በአገር ዙርያ ያሉ ሰዎች የሚመጡ ሆኑ አባትና እናቱም የልጃቸውን ወሬ በሰሙ ጊዜ እርሱን ያገናኛቸው ዘንድ ወደ እግዚአብሔር እየለመኑ ነበር ወሬው በሰሙ ጊዜ ስልጃቸው መገኘት እንዲጸልይላቸው ወደ እርሱ ሄዱ እርሱ ልጃቸው እንደሆነ አላወቁምና ሰው ገላል ባለ ጊዜ ልጃቸው መሆኑን እራሱ ገለጸላቸውና ለማንም እንዳይናገሩ አዘዛቸው።
❤ እግዚአብሔር ድንቆች ተአምራትን የማድረግ ሀብት ሰጠው ሰይጣን እስከ ቀናበት ድረስ ወደ አገረ ገዢውም ሆዶ ይህ መነኵሴ ዮሴፍ ብዙ ገንዘብ እንዳለው አስመስሎ ነገር ሰራበት መኰንኑም በሰንሰለት ማሰርያዎች አሰረው በማግስቱም ማሰርያዎቹ ከላዩ ወደ ምድር ወድቀው ተገኙ መኰንኑም አይቶ ደነገጠ ለቅድስናውም ተገዥ ሆነ።
❤ ብዙ ከተጋጋደረ በኋላ እግዚአብሔር ከአገለገለ በኋላ በዚች ዕለት በሰላም አረፈ። በክብርም ቀበሩት ከመቃብሩም ቁጥር የሌላቸው ብዙ ተአምራት ተገለጡ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በአባ ዮሴፍ ጸሎት ይማረን በከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የኅዳር 24 ስንክሳር።