❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ #የካቲት ፪ (2) ቀን።
❤ እንኳን #ለመላእክት_ወገን_ለሆነ_ለገዳማውያን_ባሕታውያን (መናንያን) ሁሉ አለቃ ለሆነ ለከበረ ለታላቁ አባት #ለአባ_ጳውሊ ለዕረፍት በዓል፣ ለከበረ #ለሐዋርያው_ቅዱስ_ቶማስ አንድ ከይስ ነድፎ የገደለው ሰው ተምራትን በማድረግ ከሞት ላስነሳበትና ከይሲውን በመግደል ብዙዎችን አስተምሮ ላጠመቀበት፣ ከእስክንድርያ ውጭ ለደብረ ዝጋግ ገዳም አበ ምኔት የቅዱሳን ዐፅም ቃል በቃል በማጋገር የሃይማኖት ነገር ለተረዳ ለከበረ አባት #ለአባ_ለንጊኖስ ለዕረፍት በዓል በሰላምና በጤና አደረሰን። ከእነዚህ ቅዱሳን እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
✝ ✝️ ✝️
❤#ርዕሰ_ገዳማውያን_ባሕታውያን (መናንያን) #አባ_ጳውሊ፦ ይህም ቅዱስ ከእስክንድርያ አገር ጴጥሮስ የሚባል ወንድም አለው አባታቸውም የገንዘቡ ብዛት ሊቈጠር የማይቻል እጅግ ባለጸጋ ነበር በዐረፈም ጊዜ የኀዘናቸው ቀን ሲፈጸም ርስቱንና ገንዘቡን ሊካፈሉ ጀመሩ ጴጥሮስም ታላቁን ክፍል ወደራሱ በመውሰድ የሚያንሰውን ለጳውሊ የሚሰጠው ሆነ። ስለዚህም ጳውሊ አዘነና "ከአባቴ ርስት በትክክል ለምን አትሰጠኝም?" አለው እርሱም "አንተ ወጣት ስለሆንክ ታባክነዋለህ እስከ ምታድግ እኔ እጠብቅልሃለሁ" ብሎ መለሰለት።
❤ ስለዚህም ጳውሊ ተቆጣና እርስ በርሳቸው ተጣሉ ይፈርድላቸውም ዘንድ ወደ ዳኛ ሔዱ እነርሱም ወደ ዳኛ ሲሔዱ ሰዎች ተሸክመውት ወደ ሚቀብሩበት ሲወስዱት ብዙዎችም የተከተሉትን የሞተ ሰውን አገኙ ጳውሊም ከተከተሉት አንዱን ሰው "ዛሬ የሞተው ማን?" ነው ብሎ ጠየቀው። ያም ሰው እንዲህ ብሎ መለሰለት "ልጄ ሆይ ዕወቅ አስተውል ይህ የሞተ ሰው በወርቅ በብር እጅግ ባለጸጋ የሆነ ሁል ጊዜ ደስ የሚለው ነበር አሁንም እነሆ ይህን ሁሉ ትቶ ራቁቱን ወደ መቃብር ወደማይመለስበት መንገድ ይሔዳል በኃጢአት ማዕበል ውስጥ እያለ ሙቷልና። አሁንም ልጄ ሆይ ስለ ነፍሳችን ድኅነት ልንታገል ይገባናል እኛ መቼ እንደምንሞት አናውቅምና ነገር ግን በዚህ ዓለም ውስጥ ገንዘብ ኑሮት ሥልጣንም ኑሮት ሳለ ይህን ሁሉ የተወ የተመሰገነ ነው እርሱ የቅዱሳን ሀገር በሆነች በኢየሩሳሌም ሰማያዊት ታላቅ ክብርን ይቀበላልና"።
❤ የከበረ ጳውሊም ይህን ነገር በሰማ ጊዜ ከልቡ አዘነ እንዲህም አለ "የዚህ የኃላፊው ዓለም ገንዘብ ምኔ ነው ምን ይጠቅመኛል ከጥቂት ቀኖች በኋላ ትቼው ራቁቴን የምሔድ አይደለሁምን" አለ። ከዚህም በኋላ ወደ ወንድሙ ተመልሶ "ወንድሜ ሆይ ወደ ቤታችን እንመለስ ከእንግዲህ ስለ ገንዘብ ምንም ምን ከአንተ ጋር አልነጋገርም" አለው።
❤ ከዚህም በኋላ ከወንድሙ ሸሽቶ ከሀገሩ ወጣ ከመቃብር ቤት ውስጥም ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት መንገዱን ይመራው ዘንድ ወደ እግዚአብሔር እየጸለየና እየማለደ ኖረ። ወንድሙ ጴጥሮስም በሀገር ውስጥ እየዞረ ሲፈልገው ሰነበተ ግን አላገኘውም ታላቅ ኃዘንንም አዘነ። የተመሰገነ ጳውሊ ግን ሦስት ቀኖች ያህል በዚያች መቃብር ቤት ሲኖር መብልና መጠጥን አላሰበም ፍርሀትና ድንጋፄም አልደረሰበትም አምላካዊ ኃይል ትጠብቀው ነበርና።
❤ በአራተኛዪቱም ዕለት እግዚአብሔር ወደርሱ መልአኩን ላከ ከዚያም ነጥቆ ወሰደው በምሥራቅ በኵል በምትገኝ በረሀ ውስጥ አኖረው በዚያም የውኃ ምንጭ አለ መልአኩም ሰላምታ ሰጥቶት ወደ ሰማይ ዐረገ የከበረ ጳውሊም አራዊት የሚኖሩበትን ጒድጓዶች አግኝቶ ወደ አንዲቱ ፍርኩታ ገባ ልብሱንም ሰኔል ሠርቶ ለበሰ። እንዲህም ብሎ ጸለየ "የሕያው የእግዚአብሔር ልጅ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ርኀራኄ ከሌለው ጠላት እጅ ጠብቀኝ አድነኝም ተጋድሎዬን እስከምፈጽም ተጸናኝ ዘንድ ቸርነትህ ወደእኔ ትምጣ የትውልድ ሁሉ ንጉሥ ሆይ ኃይል ጌትነት ክብር ገንዘብህ ነውና ለዘላለሙ"።
❤ በዚያችም ዋሻ ውስጥ ሰማንያ ዓመት ኖረ ከሰውም ከቶ ማንንም አላየም ልብሱም ከሰኔል ቅጠል የተሠራ ነው እግዚአብሔር ወደ ማታ ሁል ጊዜ ወደርሱ ቁራን ይልክለታል ከርሱም ጋራ ግማሽ እንጀራ አለ ያንን ለከበረው ጳውሊ ይሰጠዋል።
❤ የክብር ባለቤት እግዚአብሔርም ቅድስናውንና ጽድቁን ይገልጥ ዘንድ በወደደ ጊዜ መልአኩን ወደ ታለቅ አባት ወደ እንጦንዮስ ላከ ይህም እንጦንዮስ በበረሀ ውስጥ መኖርን የጀመረ እርሱ እንደሆነ በልቡ ያስብ ነበር መልአኩም እንዲህ አለው "እንጦንዮስ ሆይ ከአንተ የሁለት ቀን ጎዳና ርቆ በበረሀ ውስጥ ሰው አለ የዓለም ሰዎች ከሚረግጥባቸው የእግሩ ጫማዎች እንደ አንዲቱ ሊሆኑ የማይገባቸው ስለ ርሱም ጸሎት ዓለም ተጠብቆ የሚኖር ምድርም ፍሬዋን የምትሰጥ ጠል በምድር ላይ የሚወርድ በምድር በሚኖሩ ኃጢአተኞች ሁሉ ላይ ፀሐይ የሚወጣ የሰውም ፍጥረት በእግዚአብሔር እጅ ውስጥ ተጠብቆ የሚኖር"።
❤ አባ እንጦንዮስም ይህን ቃል በሰማ ጊዜ ተነሥቶ ወደ በረሀው መካከል ተጓዘ እግዚአብሔርም ከእርሱ ጋር ሁኖ ጎዳናውንም እንደሚጠርግለት አምኖ ሲጓዝ የሰውና የአራዊትን ፍለጋ አገኘ ያንንም ፍለጋ ተከትሎ ከቅዱስ ጳውሊ በዓት ደረሰ በሩንም አንኳኳ የከበረ አባ ጳውሊ ግን ከሰይጣን ሥራ እንደሆነ አስቦ ታላቅ ደንጊያ ወስዶ ከመዝጊያው ጀርባ አኖረ አባ እንጦንዮስም "ይሰጠኝ ዘንድ ፈለግሁ አገኝ ዘንድ ለመንኩ ይከፈትልኝም ዘንድ ቡሩን አንኳኳሁ" ብሎ አሰምቶ ተናገረ። በዚያንም ጊዜ ከፈተለትና ገባ እርስ በርሳቸውም በመንፈሳዊ ሰላምታ አጅ ተነሣሥተው በአንድነትም ጸልየው ተቀመጡ።
❤ አባ እንጦንዮስም "አባቴ ሆይ ስምህ ማነው?" አለው አባ ጳውሊም "አንተ ስሜን ካላወቅህ እስከዚች ቦታ ለምን ተጓዝክ" ብሎ መለሰለት በዚያችም ሰዓት እግዚአብሔር የእንጦንዮስን ልቡን ገለጠለትና "ገዳማዊ ጳውሎስን አየው ዘንድ ስለተገባኝ እኔ ብፁዕ ነኝ" አለ ከዚህም በኋላ እርስ በእርሳቸው የእግዚአብሔርን ልዕልናውን ቸርነቱን ይነጋገሩ ጀመር በመሸም ጊዜ ቍራ መጥቶ አንዲት ሙሉ እንጀራ ጣለለት አባ ጳውሊም አባ እንጦኒን "አንተ የእግዚአብሔር አገልጋይ እንደሆንክ አሁን አወቅሁ እስከ ዛሬ ሰማንያ ዓመት በዚህ በረሀ ስኖር እግዚአብሔር ሁልጊዜ የሚልክልኝ ግማሽ እንጀራ ነበር እነሆ አሁን ምግብህን ላከልህ" አለው።
❤ ከዚህም በኋላ ተነሥተው የማዕድ ጸሎት ጸለዩ በልተውም እግዚአብሔርን አመሰገኑት መላ ሌሊቱንም ሲጸልዩ አደሩ። ነግቶ ፀሐይ በወጣ ጊዜም እርስ በርሳቸው ሰላምታ ተሰጣጡ አባ እንጦኒም "አባቴ ሆይ በዚህ ሁሉ ዘመን ሥጋውንና ደሙን ከወዴት ትቀበላለህ?" አለው የከበረ ጳውሊም "እግዚአብሔር መልአኩን ይልክልኛል በቀዳሚት ሰንበትና በእሑድ ሰንበት በየሳምንቱ ከሥጋውና ከደሙ ያቀብለኛል በዘመኑም ሁሉ እንዲህ ያደርግልኛል" ብሎ መለሰለት።
❤ ከዚህም በኋላ አባ እንጦኒ አባ ጳውሊን "አባቴ ሆይ ይህ አስኬማ በምድር ላይ ይበዛ እንደሆነ ወይም አለመብዛቱን ትነግረኝ ዘንድ እሻለሁ" አለው። የከበረ ጳውሊም ወደ ሰማይ ተመለከተና ፈገግ አለ። ከዚህም በኋላ አዘነ ጩኾም አለቀሰ አባ እንጦንዮስም "ፈገግ ስትል በአየውህ ጊዜ ደስ አለኝ በአዘንክም ጊዜ አዘንኩ" አለው። የከበረ ጳውሊም እንዲህ ብሎ መለሰለት "እሊህ ተራሮችና በረሐዎች እግዚአብሔር ከሁሉ አገሮች መርጦ ለሚሰበስባቸው ንጹሐን ርግቦች ማደሪያዎች ይሆናሉ"።