ከፋተኛ ትኩረት!!💥💥
በአማራ ፋኖ ትግል ውስጥ በየደረጃው ያሉ አመራሮች በተለይም በሕዝብ ግንኙነት ዘርፍ ሚናቸውን ይወጡ ዘንድ ኃላፊነት ያለባቸው ሁሉ ፤የድል ውሎ ዘገባ፡የሕዝብ ግንኙነትና የፕሮፓጋንዳ ሥራዎች ላይ ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ ይኖርባቸዋል።የትጥቅ ትግል ሕይወት እየተከፈለ በሚደረግ ብሎም በጎንሽ ጉዳት ሕዝባችን ከፍተኛ ችግር እየተጋፈጠ ያለበት ነው።
የሠራዊቱን ጠንካራ ጎን እስከ ትጥቅ አይነትና መጠን በፎቶ ብሎም በየአደረጃጀቱ ማሳየቱ ጥቅሙ ምንድነው? በቅርቡ እንዲህ እናደረጋለን እንዲህም ተዘጋጀተናል አይነት እቅዶችን ማሳወቁስ ይጠቅማል? ሠራዊቱ የተሠማራበት ወይም ስልጠና የሚወስድበት ቀጠና እና ቦታ ላይ ቲክቶክ መሥራት እና መሰል መረጃ ሰጪ አካሄዶች በጥብቅ ሊታዩ ይገባል።
የመረጃ እና ደህንነት መዋቅሩ አጠቃላይ የፖለቲካ እና የሕዝብ ግንኙነት ሥራው ከትግሉ ውጤታማነት አንፃር እንዴት እየተሠራ ነው? የሚለውን መገምገምና ልዩ ልዩ ፕሮቶኮሎችን አውጥቶ ማስተገብር ይኖርበታል።የአባላት ጓዳዊ ግንኙነቶች በስልክም ሆነ በሌላ መንገድ ሲደረጉ የተቋሙን ምስጢር ለሶስተኛ ወገን አሳልፎ በሚሰጥ መልኩ እንዳይደረጉ ከፍተኛ ክትትልና ጥበቃ ያስፈልጋል። ለዚህም መመሪያ ያስፈልገዋል።
በራስ ተነሳሽነትና በጀብደኝነት አልያም በደስታ የውሎ ጉዳዮችና ሌሎችንም ኩቶች በማሕበራዊ ሚዲያ ሲፅፉ፤ ከመረጃ አንፃር እና ከጥቅል ትግሉ አብርክቶ መመዘን እጅግ ጠቃሚ ይሆናል። በትግል ሂደት የሚፈጠሩ አለመግባባቶች ሲኖሩ በንዴትና በስሜት ወደ ማሕበራዊ ሚዲያ ይዞ መውጣትም መረጃ ሰጪነት ይሆናል። ከዚያ ይልቅ በመርሕ እና አሠራር ተቋማዊ በሆነ መልኩ እየፈቱ መጓዝ ለጋራ ደህንነትም ለተቋም ግንባታና ድል ያበቃል።
ድል ያለመሰዋዕትነት የማይመጣ ቢሆንም በተቻለ መጠን በአነሰ መሳዋእትነት የበዛ ድል መቀዳጀትን ታሳቢ ያደረገ ትግል ማድረግ ይጠበቃል። ይሄ የሚሆነው ደግሞ ሁሉም ለጋራ ደህንነት እየተጨነቀ ፤ጠላት ላይ ቀድሞ እያቀደ ሁለንተናዊ ብልጫ ወስዶ መታገልን ምርጫው ሲያደርግ ነው።
አንድ አማራ💪💪
አንድ ፋኖ💪💪
@Shamal Dawit
ታጋይ አምሓራ
ነፃነት በትግል እንጂ በልመና አይገኝም!