የሐኪሞች የስራ አጥነት ቁጥር እየጨመረ ከመምጣቱ በተጨማሪ በተለያዩ በሽታዎች ተይዘው የህይወት ዋጋ እየከፈሉ ነዉ ተባለ፡፡
በህክምና የተመረቁ ስራ አጥ የህክምና ባለሙያዎች ቁጥር እየጨመረ መሆኑን የኢትዮጵያ ህክምና ማህበር አስታዉቋል፡፡
ከዚህ በተጨማሪ ሕክምና የሚያስፈልጋቸው ሐኪሞች ተገቢውን ሕክምና በፍጥነት ባለማግኘታቸው የሕይወት ዋጋ እየከፈሉ ይገኛሉ ተብሏል፡፡
ማህበሩ ሀኪሞች ብዙ ጫናዎችን ተቋቁመው ስራ እየሰሩ ቢሆንም የሰሩበትን የትርፍ ሰዓት ክፍያ ሳይከፈላቸዉ የሚቆዩባቸዉ ክልሎች መኖራቸዉን አንስቷል፡፡
ክፍያ የሚጠይቁ ሐኪሞችም ለእስር የሚዳረጉበት ሁኔታዎች የታዩበት ዓመት ነበር ሲል ማህበሩ ገልጿል፡፡
እንደሕክምና ማህበር ከሚመለከታቸው የስራ ሃላፊዎች ጋር ምክክር ለማድረግ ቢሞከርም፤ አሁንም ከችግሩ ስፋት አንጻር ለብዙዎች ችግር ምላሽ መስጠት አልተቻለም ነዉ ያለዉ፡፡
ከዚህ ቀደም ከጣቢያችን ጋር ቆይታ ያደረጉት የኢትዮጵያ ህክምና ማህበር ፕሬዝዳንት ዶ/ር ተግባር ይግዛዉ ፤ በአገራችን ያሉ የሀኪሞች ቁጥር ወደ 17ሺህ ነዉ ያሉን ሲሆን፤ ከዚህ መሃል ወደ 40 በመቶ የሚሆነዉ ወይም 1ሶስተኛዉ ብቻ የማህበሩ አባል መሆኑን አንስተዋል፡፡
የሙያ ማህበር መቅጠር አይችልም ፤ማድረግ የሚችለዉ ጉዳዩን ማሳወቅ ነዉ ያሉት ዶ/ር ተግባር፤ከጤና ሚኒስቴርም ሆነ ከክልል ጤና ቢሮዎች ጋር በጉዳዩ ላይ መነጋገራቸዉን በወቅቱ አንስተዉ ነበር፡፡
ዘንድሮ 61ኛውን ዓመታዊ የሕክምና ጉባኤና ዓለም አቀፍ የጤና አዉደ ርእይ ከየካቲት 14 – 15/2017ዓ.ም ለማካሄድ ማቀዱንም ማህበሩ አስታዉቋል፡፡
በጉባዔዉ በሃገር ውስጥ እና በውጭ ሃገር የሚኖሩ የህክምና ባለሙያዎች ያላቸውን እውቀት፣ የምርምር ግኝቶችን እና የህክምና ልምዶችን በማቅረብ የዓመቱን መሪ ቃል መነሻ በማድረግ የፓናል ውይይቶች እንደሚካሄዱም ለማወቅ ችለናል፡፡
ማህበሩ ከተመሰረተበት 1940 ዓ.ም ጀምሮ በህክምና አገልግሎት አሰጣጥ ጥራት፣ ደህንነት እና በአጠቃላይ በህክምናው ዘርፍ አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡
#EthioFM
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የትምህርት በቤቴ ቴሌግራም ገፃችንን JOIN እና ሼር ያድርጉ!
https://t.me/temhert_bebete