የቅዱስ ጴጥሮስ ስፔሻላይዝድ ሆሰፒታልን አስመልከቶ በማኅበራዊ ሚዲያ እየተሠራጩ የሚገኙ የሐሰት መረጃዎችን በተመለከተ የተሠጠ መግለጫ
••••••••
መጋቢት 19/2012 ዓ.ም
ሐሙስ መጋቢት 17 ቀን 2012 ዓ.ም ከአራት ሰዓት በኋላ ወደ ቅዱስ ጴጥሮስ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ድንገተኛ ክፍል የመጡ አንድ ታካሚ እንደማንኛውም ታካሚ ቅድመ-ምርመራ አልፈው በድንገተኛ ክፍል ትሪያጅ ተደርገው የኮቪድ19 ሥጋት ምልክቶች የለባቸውም ተብሎ የነበረባቸውን ተጓዳኝ ሕመም ሕክምና እየተከታተሉ ነበር፡፡
ታካሚዋ የነበረባቸውን ተጓዳኝ ሕመም ሕክምና በድንገተኛ ጽኑ ሕሙማን ሕክምና ክፍል ውስጥ ሕክምና እየተከታተሉ ባሉበት ወቅት የጤና ሚኒስቴር የኮቪድ19 ምርመራ ለማስፋት በጀመረው Severe Acute Respiratory Infection ( SARI) በሚባለው ኢኒሼቲቭ ላይ በኮቪድ 19 የሥጋት ምልክቶች አሁን ያለውን Case Definition የማያሟሉ ግን በጤና ተቋማት ውስጥ ያሉ የሳንባ ምች በሽታ (Pneumonia) ያለባቸው ታካሚዎች ለመድረስ በወጣው ኢኒሼቲቭ መሠረት ታካሚዋ የምርመራ ናሙና ተወስዶላቸው ነበር፡፡
አርብ መጋቢት 18 ቀን 2012 ዓ.ም በተላከው የምርመራ ውጤት መሰረት ታካሚዋ ወደ ለይቶ ማቆያ እንዲዘዋወሩ ተደርጓል፡፡ ታካሚዋን ሲያክሙ የነበሩ ሙያተኞች ቅድመ-ጥንቃቄ ለመውሰድ ወደ ሆቴል እንዲገቡ ተደርጎ ሙያቶቹ በአሁኑ ሰዓት ምንም ዓይነት የጤና ዕክል እንዳላጋጠማቸውና ከምርመራ በኋላም ወደ ሥራ ገበታቸው እንደሚመለሱ ሆስፒታሉ ይገልጻል፡፡ የተካሚዋ የመጀመሪያ ዙር ምርመራ ነጻ ነው።
ከታካሚዋ ጋር በተያያዘ ከእርሳቸው ጋር የቅርብ ግንኙነት የነበራቸው ሰዎች (አስታማሚዎች) ምርመራ ተደርጎላቸው ውጤታቸው ኔጌቲቭ ስለኾነ ታካሚዋ አጋላጭ ምክንያቶች ስለሌላቸው ናሙናቸው በድጋሚ ተወስዶ ውጤቱ እየተጠበቅ መኾኑን እየገለጸ ታካሚዋም በአሁኑ ሰዓት በሕክምና ላይ እንደሚገኙ ያስታውቃል፡፡
ሆስፒታሉ የኮቪድ 19 ወረርሽኝ በዓለም ላይ ከተከሰተ ጊዜ ጀምሮ በሆስፒታሉ ለሚገኙ ሠራተኞች የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠናዎችን በመሥጠት ላይ ይገኛል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም የዓለም ጤና ድርጅት ባስቀመጠው መመሪያ መሠረት የኢንፌክሽን መከላከያ ማስክ፣ የሃንድ ሳኒታይዘር እንዲሁም አስፈላጊ የሚባሉ መሣሪያዎችን እያቀረበ ይገኛል፡፡
የታካሚዋን ሕክምና ሲከታተሉ የነበሩ ባለሙያዎች ለኮቪድ 19 ቫይረስ ብቻ ሳይኾን ታካሚዋ የነበራቸው ተጓዳኝ በሽታ መከላከያ እንዲጠቀሙ ስለሚያስገድድ መከላከያ ማስክና ግላብ መጠቀማቸውን ያስገነዝባል፡፡ በሆስፒታሉ ግቢ ውስጥም በአሁኑ ሰዓት የመከላከያ ቁሳቁስ ዕጥረት የሌለ መኾኑን እየገለጸ ኅብረተሰቡም ኾነ የጤና ባለሙያዎች በድንጋጤ ያለአግባብ መከላከያ ማሰኮችንና ግላቦችን መጠቀም ወደፊት ዕጥረት ሊያስከትል የሚችል መኾኑን በመገንዘብ በአግባቡና በፕሮቶኮሉ መሠረት እንዲጠቀሙ ያሳስባል፡፡
አሁን የተፈጠረውን ጉዳይ በሚመለከት ወቅታዊ መረጃዎችን የሚያሳውቅ መኾኑን ይገልጻል፡፡
ቅዱስ ጴጥሮስ ሆስፒታል
@shegye @tenamereja