ከ Amanuel Assegid የተወሰደ ግሩም መልዕክት
ከናዝሬት የሆነው የእስራኤል መሲሕ የዓለም ንጉሥ ሞተ። በሞቱ የመጨረሻ እስትንፋስ ይቅርታን፣ እምነትንና ድነትን ተናገረ። ይህን ድምጽ ግን አሁን ዝም አለ፤ ዕርቅን ያበሰረው ያ የመኸሪ ጌታ ሳንባ መስራት አቆመ። ይሄ ኢየሱስ ክርስቶስ ሞተ።
የሚቅበዘበዘውን መንጋ በብዙ ርህራሄ ተመልክተው ያነቡ አይኖችን ተከደኑ። ምኅረትን ለማይገባቸው ዘርግተው ያቀፉ እጆች ተዝለፈለፉ። ለምጻሞችን የዳሰሱ መዳፉች ኅልው አልባ ሆኑ። የብዙዎችን ለቅሶ የሰሙ ጆሮዎች ተደፈኑ። ኢየሱስ ክርስቶስ ሞተ።
የእግዚአብሔርን መንግሥት ያወጁት አንደበቶቹ ረጭ አሉ። የሚናወጥ ማዕበልና ወጀብ ዝም ያሰኘው ድምጽ ፀጥ አለ። በውሃ ላይ የተራመዱ እግሮቹ መስራት አቆሙ። ኢየሱስ ክርስቶስ ሞተ።
ለኅጥአን የሚደማው ልቡ ስራውን አቆመ። የዓለም ብርሃን በሞት ጥላ ውስጥ ገባ። ወደ እግዚአብሔር መግቢያ በር የሆነው በታተመ መቃብር ገባ። የበጎች እረኛ በበጎቹ ተገደለ። ትንሣኤና ሕይወት የሆነው ጌታ ተገደለ። ኢየሱስ ክርስቶስ ሞተ።
ወዶኛል፤ ራሱንም ለእኔ አሳልፎ ሰጥቷል። (ገላ. 2፥20