ያህዊ- ራ-አህ/መዝ23:1


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: не указана


እንኳን ደህ መጡ @thevoiceofGod
ያ አባቴ ብሩካን ሰላም ለናንተ ይሁን
የዚህ channel አላማ ሰዎችን ሁሉ በእግዚአብሔር ቃል በመድረስ በክርስቶስ ያሉት ለማነፅ ለማቅናት ዓላማ አግቦ የተከፈተ ነው ። ለአስተያየት @TemuforChrist
@JOAS2713

Связанные каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
не указана
Статистика
Фильтр публикаций


Day 2

ብዙ ጊዜ ድካማችንን አጉልቶ በሚያሳየን ዓለም ውስጥ፣ አለን ብለን የምናስቈጥረው ንብረት ወይም ኹነኛ ዘመድ ወይም ዝናም ቢኾን የትኛውም ዋጋ ያለው ነገር ዕለት ተዕለት ከምንጋፈጠው ዋጋ ቢስ ከሚያደርገን ኹኔታና አጋጣሚ አይሸሽገንም። ከዚህ በኀጢአት ከተበከለ የክፋት ዓለም የምንላቀቀው ለሕይወታችን ወድ ዋጋ በመክፈል ሕያው ተስፋ የሚሰጠንን እውነተኛው መሲሕ ኢየሱስን የሕይወታችን ባለቤት ስናደርገው ብቻ ነው። ሸክማችንን፣ ጥፋታችንንና ሃፍረታችንን እንዲሁም ኀጢአታችንን በፈቃዱ የተሸከመውን  የእግዚአብሔር በግ የኾነውን ኢየሱስን ፍቅሩ ልባችንን እንዲለውጥ በመፍቀድ የሚሰጠንን ነጻነትና ይቅርታ እንቀበል። በጸጋው ብርሃን ወስጥ ከዘላለም በረከቱ ባሻገር ያለውን እፎይታ እና ርካታ በእምነት ብቻ አኹኑኑ ይቀበሉ።
ልናማክሮ ዝግጁ ነን!

#ኑ_ወደ_ኢየሱስ 
#ያ_መሲሕ
#ኢየሱስ_የእግዚአሔር_ልጅ

በነገው ዮሐንስ ኢየሱስን ወደ እርሱ ሲመጣ አይቶ እንዲህ አለ፦ “እነሆ የዓለምን ኃጢአት የሚያስወግድ የእግዚአብሔር በግ። (ዮሐንስ 1:29፤)


Follow Meskerem Getu on:
Facebook  |  Instagram  | TikTok  | Threads

Follow Tesfa on:
Instagram | Facebook | Telegram | TikTok | Youtube | Threads  |  Pinterest


በሥነ መለኮት መምህር በግሩም ድፈቅ

በአገልግሎት ረጅም ለመሄድ ካሰብክ እነዚህን አትርሳ!!

አላማ ላላቸው ሰዎች አራት ምክር አለኝ!!

1ኛ ፀልይ

ፀሎት ለአንድ አማኝ መሰረታዊ ነገር ነው የክርስትና ፈር ቀዳጅ የሆነው መስራች ኢየሱስ የፀሎት ሰውም ጭምር ነበር ። ያልፀለየበት ቀን ያለ አይመስለኝም ደቀመዛሙርት ሲደክሙ እሱ ግን ከፀሎት አይለይም ሲለው አዳር ይፀልያል ። ጳውሎስ የፀሎት ሰው ነበር የመጀመሪያዋ ቤተ ክርስቲያን ምዕመናን በፀሎት የታሸ ሕይወት ነበራቸው ። በምስጋና እና በሚፈጠሩ አሁናዊ ጉዳዮች ላይ ሁሉ ይፀልያሉ ። ፀሎት የማታያቸውን የጥላት ስራዎች ያመክናል !! ስለዚህ መፀለይ መሰረታዊ ነገር መሆኑን አውቀህ ፀልይ !!

2ኛ ቃሉን አንብብ

መፅሐፍ ቅዱስ እንድናነበው እና የእግዚአብሔር ዘላለማዊ አጀንዳ እና ፍቃድ ተረድተን ለእዚህ አጀንዳ ምላሽ ሰጥተን እንድንኖርበት የተሰጠ ሰነድ ነው ። ይህንን ካላነበብን ከእግዚአብሔር አጀንዳ ጋር ፍቃዱን ከመረዳት ጋር እንተላለፋለን ። ኢየሱስ በእዚህ ምድር እያለ እጅግ የሚያነብና በእዚህም የእውነት ተቃዋሚዎችን ፀጥ የሚያደርግ ብርቱ ነበር ጳውሎስ በሽምግልና ወራቱ እንኳ መፅሐፍ አምጣልኝ ብሎ ጢሞቲዮስን የሚጠይቅ አስገራሚ ሰው ነበር ።

"ስትመጣ በጢሮአዳ ከአክርጳ ዘንድ የተውሁትን በርኖስ፣ ጥቅልል መጻሕፍቱን በተለይም የብራና መጻሕፍቱን አምጣልኝ።"
2 ጢሞቴዎስ 4:13

3ኛ ተጠንቀቅ

በአገልግሎት በክርስትና ሕይወት ውስጥ ብዙ ሰዎች በታላቅ ክብር ጀምረዋል በትልቅ ተነሳሽነት ተስፈንጥረዋል ነገር ግን ሁሉም አልቀጠሉም የተወሰኑ ሰዎች ሩጫውን አቋርጠው ተመልሰዋል የቱ መሆን ትፈልጋለህ ? ከሚቀጥሉት ወይስ ከሚያቋርጡት ? ከሚቀጥሉት ካልከኝ ይሄንን አስብ!! ራስህን ከተንኮለኞች ጠብቅ በፀሎትህ ይሄንን አትርሳ ጌታ ከተኮለኞች እንዲጠብቅህ ፀልይ የዋህ እንጂ አጉል የዋህ አትሁን ከቻልክ ጳውሎስ ለጢሞቴዎስ የመከረውን አንብብ !!

4ኛ ልብህ አይውረድ

በክርስትና አገልግሎትህ ውስጥ ብዙ ያልጠበካቸው ነገሮች ሊገጥሙህ ይችላሉ ። የከበረ ያልከው ወርዶ ጥሩ ያልከው ተቀይሮ ልታገኝ ትችላለህ ። ለመልካም ያደረከው ለክፉ ይተረጎማል ።ያቃኑልኛል ያልካቸው የሚያጣምሙ ሊሆኑ ይችላሉ ። ይሄ አዲስ አይደለም ጴጥሮስ ስለ ጳውሎስ ሲመሰክር እንዲህ ብሏል ።

"እርሱ ስለ እነዚህ ነገሮች በመልእክቶቹ ሁሉ ጽፎአል፤ በመልእክቶቹም ውስጥ በቀላሉ ለመረዳት የሚያዳግቱ ነገሮች አሉ። ዕውቀት የጐደላቸውና ጽናት የሌላቸው ሰዎች ሌሎችን ቅዱሳት መጻሕፍት እንደሚያጣምሙ፣ እነዚህንም ደግሞ ለገዛ ጥፋታቸው ያጣምማሉ።"
2 ጴጥሮስ 3:16

ስለዚህ በሰዎች ምክንያት ለአገልግሎት ልብህ አይውረድ መቀጠል ምትፈልግ ከሆነ ወደ ጎን ማየቱን ቀንስ እያደረክ ወደ እላይ እየተመለከትክ ቀጥል ...

ፀልይ አንበብ ተጠንቀቅ ልብህ አይውረድ ....
From facebook




የእግዚአብሔር ጥብበ እና ኃይል የሆነው የተሰቀለው ክርስቶስ የገለጠልን አምላክ ይባርክ


#የሚወደውን_እንወደድ
መስዋዕታችን ምህረት ከማድረግ
አምልኮአችን እግዚአብሔርን ከማወቅ ጋር ይሁንልን


#ያገኘህውን_ሁሉ_አታግበስብስ!
ጊዜው ቆየት ያለ ቢሆንም በህይወቴ አስተምረው ካለፉ ነገሮች ዛሬ አንዱ ትዝ አለኝ 😂 እንደ ጋጣሚ ሆኖ ብዙ ጊዜ ድግስ ከሄድኩ ወደ ቤት ስመለስ ሆዴ አሞኝ ነው ምመለሰው።ቤት ገብቼ አመመኝ ማለቴ የማይቀር ነገር ነው (የምርም እታመማለሁ) እህቴ በዚያን ጊዜ የምትለኝን ሁለት ነገሮች ትዝ አለኝ ዛሬ አንዱን ልንገራችሁ ።"ሁሉንም አገኘሁ ብለህ አታግበስብስ ጤናማውን(ከቤፌው)መርጠህ ብላ" ትለኝ ነበር።ከዚያ በኋላ ምክሯን በመስማት ብፌ አገኘሁ ብዬ ሁሉንም "አላገበሰብስም" በተመከሩክት መሰረት ለጤናዬ ተስማሚ የሆነውን መርጬ ማሳት ጀመርኩ። #ምን_ልላቹህ_ፈልጌ_ነው
ለሰጋ ጤንነት ተበልቶ ወደ ውጪ ለሚወጣው የተገኘው ሁሉ ማግበስበስ ልክ ካልሆነ መንፈሳዊ መብል መምረጥ እና መመገብ ይልቅ እንዴት ጥንቃቄና ትኩርትን አይጠይቅም? #ዛሬ በየሚዲያው በቴሌቪዥኑ በየሰፈሩ መንፈሳዊ መብል ሚመስሉ የኑ ብሉ ጥሪ እና ሁሉ ሙሉ ሁሉ ዝግጁ የሚሉ አሸን ናቸው።ሁሉንም እያገበሰበስን ነው ?ወይስ እየመረጥን? ወይስ ሁሉም አይቅርብኝ ከብፌው ላንሳ እያልን ይሆን? ሁሉም ማለት ባልችልም ብዙ በካይ(መርዝ)የሆኑ ባዕድ ነገር የሞላባቸው አሉና "መንፈሳዊ ብፌዎች" አገኘሁ ብለን ሁሉንም አናግበስብስ። "ተጠንቀቁ "መባሉን አንርሳ #ወዳጆቼ ዛሬ ቆም ብለን እናስብ በየሰፈሩና በየሚዲያው ያገኘናቸው ብፌዎች የእውንተኛ መበል ጤነኛነታቸው እና ተስማሚነተቸው ማረጋገጫው እና መፈተሻው በሆነው በህያውን ቃለ በመጽሐፍ ቅዱስ መመዘንና መመርመር አለብን።"መንፈሳዊ መብል"ነኝ የሚሉ ብፌዎች ከዚህ እውነተኛና ዘላለማዊ ቃል የማይስማማ ከእርሱ ያልተቀዳ ከሆነ #አሁኑኑ አውጥተን እንጣልና ወደ ባለሥልጣኑ የህይወት መገኛ፣ለመንፈሳዊ ጤንነት ፣ ለእውነተኛ አምልኮ፣ለጤናማ እድገትና በሰው ቋንቋ የተጻፈው መለኮታዊ የሆነው መብል ንፅህናው ለዘላለም የተጠበቀ በዘመናት መካከል የማይሻሻል ሁል ጊዜ አዲስ የሆነው፣ ያልተበረዘው እውነተኛ መንፈሳዊ መብሎች ወደ ሞሉበት ብፌ ወደ 66ቱ ቅዱሳት መጽሐፍት እና ወደ እውነተኛ መብል ወደ ምታቀርበው ቤተክርስቲያን እንመለሰ። ለጤናማ ህይወት ጤናማ አሰተምህሮ ያሻል። #ንቃ_ትውልዴ_ሁሉንም_ብፌ_አገኘሁ_ብለህ_አንስተህ_አትጉረስ_አታግበስብ_ቢያንስ ከመጉረስህ በፊት ቃሉን ክፈትና ይሄ ነገር እንዴት_ነው_በል ቢያንስ ጠይቅ የዳንክበትን አምላክህን ያወቀበትን አስጥለውህ_የአለም ግሳግስ ተራ የሆነ መንፈሳዊነት ሳይሆን ስጋዊነት ከተሞሉ ምግቦች ላያቸው ሲታይ ጥሩ መንፈሳዊ መብል ከሚመስሉ ነገር ግን ካልሆኑ ውስጣቸው መርዝ ምድራዊና ሰዋዊ ብቻ እና ብቻ ከተሞሉ ክርስቶሳዊ ህይወት ከሌላቸው ቅድስና አስጥለው ተራ ከሚያረጉህ የመምጣቱ ተስፋ አስጥለው ምድራዊ ከሚያረጉህ ቃሉን አስጥለው የአለም ብልጣብልጥነት(የሰው ጥበብ) ከሚያቅረቡልህ "ስፈራ" (ያው በነጩ ላለመጥራት ነው) እግርህን ከልክል።በቃ እዛ እግርህን ስትከለክል ወደ ጤነኛው ስፍራ ሂድ በየሚዲያው የሚገኘው ሁሉ አይበላም ስለዚህ ልብህንም ጆሮህንም አይንህንም (ሁለተናህን)ጠብቅ። ለጤናማ ህይወት ጤናማ አስተምህሮ ያሻናል ::

የተገኘ ሁሉ አይበላም!
ተገኘ ተብሎም ሁሉንም ማግበስበስ ልክ አይደለም!
✍ወንድማችሁ ተሙ ነኝ






What a great God, glory and praise be to Him alone


What a great God, glory and praise be to Him alone


Amanuel Assegid የተወሰደ ግሩም መልዕክት
ከናዝሬት የሆነው የእስራኤል መሲሕ የዓለም ንጉሥ ሞተ። በሞቱ የመጨረሻ እስትንፋስ ይቅርታን፣ እምነትንና ድነትን ተናገረ። ይህን ድምጽ ግን አሁን ዝም አለ፤ ዕርቅን ያበሰረው ያ የመኸሪ ጌታ ሳንባ መስራት አቆመ። ይሄ ኢየሱስ ክርስቶስ ሞተ።

የሚቅበዘበዘውን መንጋ በብዙ ርህራሄ ተመልክተው ያነቡ አይኖችን ተከደኑ። ምኅረትን ለማይገባቸው ዘርግተው ያቀፉ እጆች ተዝለፈለፉ። ለምጻሞችን የዳሰሱ መዳፉች ኅልው አልባ ሆኑ። የብዙዎችን ለቅሶ የሰሙ ጆሮዎች ተደፈኑ። ኢየሱስ ክርስቶስ ሞተ።

የእግዚአብሔርን መንግሥት ያወጁት አንደበቶቹ ረጭ አሉ። የሚናወጥ ማዕበልና ወጀብ ዝም ያሰኘው ድምጽ ፀጥ አለ። በውሃ ላይ የተራመዱ እግሮቹ መስራት አቆሙ። ኢየሱስ ክርስቶስ ሞተ።

ለኅጥአን የሚደማው ልቡ ስራውን አቆመ። የዓለም ብርሃን በሞት ጥላ ውስጥ ገባ። ወደ እግዚአብሔር መግቢያ በር የሆነው በታተመ መቃብር ገባ። የበጎች እረኛ በበጎቹ ተገደለ። ትንሣኤና ሕይወት የሆነው ጌታ ተገደለ። ኢየሱስ ክርስቶስ ሞተ።

ወዶኛል፤ ራሱንም ለእኔ አሳልፎ ሰጥቷል። (ገላ. 2፥20


የሥላሴ አስተምህሮ መሠረት ያደረገባቸው አምስት መሠረታውያን ነጥቦች
1:- መጽሐፍ ቅዱስ ፣ እግዚአብሔር አንድ ብቻ እንደ ሆነ ያስተምራል።
2:- መጽሐፍ ቅዱስ ፣ አብ ፍጹም አምላክ እንደ ሆነ ያስተምራል።
3:- መጽሐፍ ቅዱስ ፣ ወልድ ፍጹም አምላክ እንደሆነ ያስተምራል።
4:- መጽሐፍ ቅዱስ ፣ መንፈስ ቅዱስ ፍጹም አምላክ እንደሆነ ያስተምራል።
5:- መጽሐፍ ቅዱስ አብ ፣ ወልድና መንፈስ ቅዱስ የተለያየ አካል እንዳላቸው ያስተምራል። ይህ ማለት
#ኢየሱስ ክርስቶስ እግዚአብሔር አብ አይደለም ወይም እግዚአብሔር አብ ኢየሱስ ክርስቶስ አይደለም።
#ኢየሱስ ክርስቶስ መንፈስ ቅዱስ አይደለም ወይም መንፈስ ቅዱስ ኢየሱስ ክርስቶስ አይደለም።
#እግዚአብሔር አብ መንፈስ ቅዱስ አይደለም ወይም መንፈስ ቅዱስ እግዚአብሔር አብ አይደለም።
*
የትምህርተ ሥላሴ መሠረታውያን
ከተስፋዬ ሮበሌ
@thevoiceofGod ይቀላቀሉን
@thevoiceofGod


ያህዊ- ራ-አህ/መዝ23:1:
እንኳን አደረሳችሁ
🌻🌻🌻🌻🌻
የዚህ ቻናል ቤተሰቦች
የ2014 ዓመት
መዝ 91 ነው


ያህዊ- ራ-አህ/መዝ23:1:
እንኳን አደረሳችሁ
🌻🌻🌻🌻🌻
የዚህ ቻናል ቤተሰቦች
የ2014 ዓመት
መዝ 91 ነው


ያህዊ- ራ-አህ/መዝ23:1:
እንኳን አደረሳችሁ
🌻🌻🌻🌻🌻
የዚህ ቻናል ቤተሰቦች
የ2014 ዓመት
መዝ 91 ነው


Репост из: Kolfe Kale Hiwot Church Youth Ministry
🔥🔥#ከዛሬ_ሰኞ_ጀምሮ 🔥
🔥🔥 #ከ11ሰዓት_ጀምሮ 🔥
ልዩ የትምህርትና የአምልኮ ጉባኤ 🔥መንፈስ ቅዱስ🔥🔥🔥
በእየለቱ ስለመንፈስ ቅዱስ ሙላት ይጸልያል
በኮልፌ ቃለ ህይወት ቤተክርስቲያን ወጣቶች የተዘጋጀ


Репост из: Solomon kebede Tessema


“እኔስ፦ አቤቱ፥ ማረኝ፤ አንተን በድያለሁና ነፍሴን ፈውሳት አልሁ።”
— መዝሙር 41፥4


Репост из: Kolfe Kale Hiwot Church Youth Ministry
👋👋ሰላም ለእናንተ ይሁን👋👋
ዘውትር ረዕቡ
ከ11:30 ጀምሮ
የጸሎት
የዝማሬ
የትምህርት ጊዜ
ኑ ከእኛ ጋር አምልኩ ተማሩ
በኮልፌ ቃለ ህይወት ቤተክርስቲያን
#በወጣት_አገልግሎት_የተዘጋጀ


ዘዳግም 32
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁰ በምድረ በዳ በጥማት፥ የነፋስ ጩኸትም በሞላበት ውድማ አገኘው፤ ከበበው ተጠነቀቀለትም፤ እንደ ዓይን ብሌን ጠበቀው።
¹¹ ንስር ጫጩቶቹን እንደሚያወጣ፥ በእነርሱም ላይ እንደሚሰፍፍ፥ ክንፎቹን ዘርግቶ ወሰዳቸው፥ በክንፎቹም አዘላቸው።
¹² እግዚአብሔር ብቻውን መራው፤ከእርሱም ጋር ሌላ አምላክ አልነበረም

Показано 20 последних публикаций.