በትራፊክ አደጋ 7 ሰዎች ህይወት ወድያውኑ ተቀጠፈ።
ከሟቾች በተጨማሪ ስድስት ተጓዦች በከባድ ተጎድተዋል።
አደጋው ዛሬ ጥዋት ትግራይ ከመቐለ 50 ኪ/ሜ ርቀት ላይ ወቕሮ ክልተ አውላዕሎ ዓደቀሳንድድ ተብሎ በሚጠራው ቦታ ነው የደረሰው።
አደጋው የደረሰው ሚኒባስ መኪና ከቅጥቅጥ የህዝብ ማመላለሻ አውቶቡስ ጋር ተጋጭተው እንደሆነ የክልተ ኣውላዕሎ ወረዳ ፖሊስ ገልጿል።
አሰቃቂ ግጭቱ የህዝብ ማመላለሻ ቅጥቅጥ አውቶቡሱ ከመቐለ ወደ ሓውዜን ሲጓዝ ሚኒባሱ ደግሞ ከሓውዜን ወደ መቐለ ሲጓዝ በጠመዝማዛ ቦታ ላይ ነው የተከሰተው።
በዚህም ሹፌሩ ጨምሮ 7 ሰዎች ወዲያው ህይወታቸው ሲያልፍ 6 ሰዎች በከባድ ሁኔታ ተጎድተዋል።
የአደጋው መነሻ እየተጣራ መሆኑን ፖሊስ ገልጿል።
መረጃው የድምጺ ወያነ ነው።
#TikvahEthiopiaFamilyMekelle
@tikvahethiopia