የሳይበር ደህንነት ንቃተ ህሊናን ያጎለብታሉ ተብለው የተመረጡ ፊልሞች ተሸላሚ ሆነዋል።
በየአመቱ ጥቅምት ወር ኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር የሚያካሄደው ሀገር አቀፍ የሳይበር ደህንነት ወር ዘንድሮም “ የቁልፍ መሰረተ-ልማት ደህንነት ለዲጂታል ሉዓላዊነት ” በሚል መሪ ቃል ከጥቅምት 1- 30/2017 ዓ.ም በተለያዩ መርሃ ግብሮች ተከብሯል።
የአስተዳደሩ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዳንኤል ጉታ " የሳይበር ደህንነትን ለማረጋገጥ እንደ ሀገር በልዩ ትኩረት እየተሰራ ይገኛል " ብለዋል።
በጥቅምት ወር በተካሄደው የሳይበር ደህንነት ወር ከሳይበር ደህንነት ጋር የተያያዙ የአጭር ፊልም ውድድር መካሄዱ ተገልጿል።
በውድድሩ ከ1ኛ እስከ 3ኛ ደረጃን በመያዝ ላጠናቀቁ እንደየ ደረጃቸው ከ50 ሺህ እስከ 200 ሺህ ብር ሽልማት በዛሬው ዕለት ተበረክቶላቸዋል።
በሀገር አቀፍ የሳይበር ደህንነት ወሩ በ2016 ዓ.ም ሰኔ ወር ላይ ጸድቆ ተግባራዊ በሆነው “ሀገራዊ የሳይበር ደህንነት ፖሊሲ” ከተለያዩ ቁልፍ ተቋማትና ሚኒስቴር መ/ቤቶች ከተውጣጡ ተወካዮች ጋር ምክክር መደረጉን ተገልጿል።
በወሩ በተካሄዱ ኮንፈረንሶችና የአዉደ ርዕይ መርሃ ግብሮች ላይም ከሁለት መቶ ሦስት (203) ተቋማት የተዉጣጡ ከአራት ሺ አምስት መቶ በላይ (4,500) ሰዎች ተሳታፊ መሆናቸውን በተቋሙ የኮምዩኒኬሽን እና የሳይበር ደህንነት ባህል ግንባታ ኃላፊ አቶ ቴዎድሮስ ሃይሉ ገልጸዋል፡፡
@tikvahmagazine