"ግብር ከፍዩ እንዳይጭበረበር የሚያረግ የዲጂታል አሰራር ወደ ሥራ አስገባለሁ" ገቢዎች ቢሮ
የግብር ግዴታቸውን ሳይወጡ የሚሰወሩ ግብርከፋዮችን ለመቆጣጠር፣ ግብር ከፍዩ እንዳይጭበረበር እሚያረጉ ሁለት ሲስተሞችን ሰርቶ ወደ ስራ ሊያስገባ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።
የቢሮው የሶፍትዌር ልማት ቡድን አስተባባሪ አቶ ደረጀ በርታ ለቲክቫህ እንደገለፁት '' ግብር ከፍዩ ትክክለኛ የሆነ አገልግሎት እንዲያገኝ በማሰብ፣ቢሮው ገቢ አሰባሰቡን በማዘመን ተጨማሪ ገቢ እንዲያገኝ ለማስቻል ሁለቱ የቴክኖሎጂ ውጤቶች በራስ አቅም ሰርተናቸዋል '' ሲሉ ገልፀዋል።
የመጀመሪያው ሲስተም አይዲ አይደንትፍኬሽን ሲሆን እሚሰራው ስራም የገቢዎች ባለሙያ ሳይሆኑ መስለው በመሄድ ግብር ከፍዩ እያጭበረበረ ያሉ ሰዎች በመቆጣጠር ግብር ከፍዩ እንዳይጭበረበር ለማረግ ነው ብለዋል።
''ይህ ሲስተም ለቢሮው የቁጥጥር ባለሙያዎች የደህንነት ባር ኮድ ያለው ይህን መታወቂያ በመስጠት ግብር ከፍዩ የመታወቂያውን ባር ኮድ በስልኩ ስካን በማረግ የባለሙያውን ትክክለኛነት ማረጋገጥ እንዲችል ያደርጋል" ሲሉ ነው የገለጹት።
አክለውም "በስልካቸው ባር ኮዱን ማንበብ እማይችሉ ግብር ከፋዮች በበኩላቸው 7075 ላይ በመደወል የባለሙያውን የመታወቂያ ቁጥር ለጥሪ ማዕከል ሰራተኞች በመናገር የባለሙያውን ትክክለኛነት ማረጋገጥ ይችላሉ '' ብለዋል።
እንደ መጀመሪያ ዙር ከ200 እስከ 300 እሚሆኑ በተለይ መርካቶ አካባቢ የሚገኙ የቁጥጥር ባለሙያዎችን አሰልጥነን መታወቂያውን በመስጠት ወደስራ እናስገባቸዋለን ሲሉ አቶ ደረጀ ተናግረዋል።
በቀጣይም ይህ ሲስተም ከናሽናል አይዲ ጋር አብሮ በአንድ እንዲሆን ከኢንሳ ጋር በጋራ መስራት ተጀምሯል።
ሁለተኛው ሲስተም የእዳ ክትትል ሲስተም እንደሚባል ገልፀው '' ይህ ሲስተም ዋነኛ ስራው እዳ ኑሮባቸው እዳቸውን እሚሰውሩ ግብር ከፋዮችን ተከታትሎ ማግኘት እሚችል ሲስተም " መሆኑን አቶ ደረጀ ተናግረዋል።
ይህም "እዳ ያለባቸው ግብር ከፋዮች እዳ እንዳለባቸው በአጭር የፅሁፍ መልዕክት እሚያሳውቅ፣ በምን ያህል ጊዜ እዳቸውን መክፈል እንዳለባቸው እንደሚገልፅ አጠቃላይ ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ ያለውን የእዳ ክትትል ሂደት እሚያሳይ ሲስተም ነው '' ሲሉ አስረድተዋል።
ሁለቱም ሲስተሞች ከ15 ቀን በኋላ ወደስራ እንደሚገቡ ገልፀዋል። ለወደፊት ከኢንሳ ጋር በጋራ በመሆን የግብር አሰባሰብ ሂደቱን አንድ ደረጃ ከፍ ለማረግ እየሰሩ መሆኑን አቶ ደረጀ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልፀዋል።
#TikvahEthiopia
@tikvahethmagazine