ብርሽን አበዛልሻለው በማለት ባጭበረበረው ገንዘብ ባጃጅ የገዛው ተጠርጣሪ በቁጥጥር ሥር ዋለ።
"ባህላዊ መድኃኒት ቀማሚ ነኝ ፀሎት አደርግልሻለው ብርሽንም አበዛልሻለው" በማለት ከአንዲት ግለሰብ ከ736ሺ ብር በላይ በማታለል የተቀበለው ግለሰብ በቁጥጥር ስር መዋሉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል።
የወንጀል ድርጊቱ የተፈፀመው በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 6 ጎፋ ቅዱስ ገብርኤል አደባባይ አካባቢ ነው። ግለሰቡ ከግል ተበዳይ አጭበርብሮ በተቀበለው ገንዘብም ባጃጅ ገዝቶ በተቀመጠበት ቴፒ ከተማ በቁጥጥር ስር መዋሉን የፖሊስ መረጃ ያሳያል።
ተጠርጣሪው የባህላዊ መድኃኒት ቀማሚ እና ፈዋሽ ነኝ በሚል "አባ መንግስቱ" የሚል ማህበራዊ ሚዲያ በመክፈት አንዲት ታዋቂ የኢትዮጵያ አርቲስት የሰጠችውን ኃይማኖታዊ የፈውስ ምስክርነት ከሌላ ሰው ላይ አውርዶ በራሱ አካውንት የፈወስኳት እኔ ነኝ በማለት ይለቃል።
ይህን ቪዲዮ የተመለከተች የግል ተበዳይ ባህላዊ መድኃኒት እፈልጋለሁ በማለት ወደ ግለሰቡ በመደወል ስትጠይቅ እንደሚሰራላት ይነገራታል።
ከጊዜ በኋላ ግለሰቡ አካውንትሽ ላይ ስንት ብር አለ ብሎ ግለሰቧን በመጠየቅ ብርሽን አበዛልሻለው ብሎ በማሳመን በተለያ ስም በከፈተው የባንክ አካውንት በተለያዩ ጊዜያት እና ቀናት በድምሩ 652ሺ ብር ወደ ራሱ አካውንት እንድታስገባለት ያደርጋል።
ይህም አልበቃው ብሎ ከሌሎች ተበድራ 84,800 ብር ተጨማሪ እንድታስገባለት ማድረጉን በጎፋ አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ የተጣራው የወንጀል ምርመራ መዝገብ ያስረዳል።
ተከሳሽ በአጠቃላይ 736,800ብር እንዲላክለት ያደረገ ሲሆን ብርሽ በዝቶልሽ ይመለስልሻል እያለ ቀጠሮ እየሰጠ ሲጠፋ እና መታለሏ የገባት የግል ተበዳይ ወደ ፖሊስ በመምጣት የተፈፀመባትን ወንጀል ትናገራለች።
ፖሊስም የግለሰቧን አቤቱታ መነሻ በማድረግ እና የምርመራ መዝገብ በማደራጀት ለግለሰቡ የተላከበትን አካውንት ሲያጣራ ግለሰቧ በተለያዩ ቀናት በተለያየ አካውንት ገንዘቡን መላኳን አረጋግጧል።
ግለሰቡ በተለያዩ ስሞችና በተለያዩ ባንኮች አካውንት መኖሩን ያጣራው ፖሊስ ግለሰቡን የፍርድ ቤት መያዣ ትዕዛዝ በማውጣት ከአዲስ አበባ ከተማ ውጭ ደቡብ ምዕራብ ክልል በምትገኘው ቴፒ ከተማ ድረስ በመሄድ በቁጥጥር ስር ማዋል ችሏል።
ግለሰቡ በቁጥጥር ከዋለ በኋላ በተላከለት ገንዘብ ኮድ (1) 05224 ደቡብ ምዕራብ ጊዜያዊ ሠሌዳ ያለው አንድ ባጃጅም የገዛ ሲሆን ተጠርጣሪው ከነ ኤግዚቢቱ በቁጥጥር ስር መዋሉን ፖሊስ ገልጿል።
አሁን አሁን በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች እፈውሳለሁ ባህላዊ መድኃኒት ቀማሚ ነኝ የሚሉ ምንም አይነት እውቅናና ፍቃድ የሌላቸው ግለሰቦችን እያስተዋሉ መሆኑንና ህብረተሰቡ ጥንቃቄ እንዲያደርግ ፖሊስ አሳስቧል።
🔗 ከላይ በ Screenshots የተያያዙት ፎቶ 1 እና ፎቶ 2 "አባ መንግስቱ" በሚል ስም የተከፈተ የቴሌግራም ግሩፕ ለማሳያነት የተወሰደ ሲሆን ተጠርጣሪው የዚህ ግሩፕ አስተዳዳሪ ይሁን አይሁን በፖሊስ መረጃ ላይ የተገለጸ ነገር የለም።
@tikvahethmagazine