ጀርመን ውድድሯን በድል ጀምራለች !
የጀርመን ብሔራዊ ቡድን የአውሮፓ ዋንጫ የመክፈቻ ጨዋታውን ከስኮትላንድ አቻው ጋር አድርጎ 5ለ1 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል።
ለጀርመን ብሔራዊ ቡድን ግቦችን ፍሎሪያን ቨርትዝ ፣ ጀማል ሙሲያላ ፣ ካይ ሀቨርትዝ ፣ ኒክላስ ፉልክሩግ እና ኤምሪ ቻን ሲያስቆጥሩ የስኮትላንድን ብቸኛ ግብ ሩዲገር በራሱ ግብ ላይ ከመረብ አሳርፏል።
የ 21ዓመቱ የፊት መስመር ተጨዋች ፍሎርያን ቨርትዝ በአውሮፓ ዋንጫው ለጀርመን ብሔራዊ ቡድን ግብ ያስቆጠረ በእድሜ ትንሹ ተጨዋች በመሆን አዲስ ታሪክ ፅፏል።
የ 36ዓመቱ የጀርመን ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ጁሊያን ኔግልስማን በውድድሩ ታሪክ ብሔራዊ ቡድን የመራ በእድሜ ትንሹ አሰልጣኝ መሆን ችሏል።
ኒክላስ ፉልክሩግ ለጀርመን ብሔራዊ ቡድን ባደረጋቸው አስራ ሰባት ጨዋታዎች አስራ ሁለት ግቦችን ማስቆጠር ችሏል።
@tikvahethsport @kidusyoftahe