አሸናፊ ግርማ የዋናው ብራንድ አምባሳደር ሆኖ ተሾመ !
የቀድሞ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ውጤታማ ተጨዋች አሸናፊ ግርማ የዋናው ስፖርት አልባሳት ብራንድ አምባሳደር በመሆን ተሹሟል።
በኢትዮጵያ የስፖርት ኢንደስትሪ ውስጥ በተቀላቀለ ጥቂት አመታት ውስጥ ተቀባይነት እያገኘ የመጣው ዋናው ስፖርት አሸናፊ ግርማን የሰሜን አሜሪካ ብራንድ አምባሳደር አድርጎ ሾሟል።
በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ በተደጋጋሚ የአመቱ ኮከብ ተጨዋች በመሆን አኩሪ ታሪክ የፃፈው አሸናፊ ግርማ በአሁን ሰዓት ኢትዮጵያን የሚያኮሩ የነገ ኮከቦችን ለማፍራት በታዳጊዎች ላይ እየሰራ ይገኛል።
በአሁኑ ሰዓት በካናዳ በአሰልጣኝንት ሙያ ላይ የሚገኘዉ አሸናፊ ግርማ በስምምነቱ ደስተኛ መሆኑን ገልፆ “ ይህ ስምምነት በኢትዮጵያ እና በካናዳ በእግር ኳስ ልማት ዙሪያ የምሰራቸዉን ስራዎች እንደሚያጠናክርልኝ እምነቴ ነዉ" ብሏል።
የዋናው ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ሀ/ስላሴ ገ/ክርስቶስ በበኩላቸው “ በኢትዮጵያ እግርኳስ ጉልህ አሻራቸዉን ካስቀመጡ ተጨዋቾች አንዱ አሸናፊ ግርማ ጋር በጋራ ለመስራት መስማማታችን አስደስቶኛል። ስምምነቱ ነገ ሀገራቸዉን የሚያኮሩ እግር ኳስ ተጨዋቾችን ለማፍራት የሚደረጉ ተግባራትን በጉልህ ያግዛል።" ብለዋል።
ዋናው ስፖርት በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ለተለያዩ ከለቦች እንዲሁም ለኢትዮጵያ ከ17ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን የስፖርት ትጥቅ አቅራቢ መሆን ችሏል።
ዋናው ከሀገር ውጪ በመውጣትም የላይቤሪያ ዋናው ብሄራዊ ቡድን ይፋዊ የስፖርት ትጥቆች አቅራቢ ነዉ።
ይህም ኢትዮጵያዊውን የስፖርት አልባሳት ብራንድ "ዋናው ስፖርት'ን በአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታዎች ላይ የታየ የመጀመሪያዉ ብራንድ ያደርገዋል።
@Tikvahethsport @kidusyoftahe