🦋……………
ሚጨንቀኝ ትላንት ፣ ምፈራው ነገ የለኝም ………እስከነ ስህተቴ ትላንትን ወደዋለው ፣ ጥፋቴ ላይ የመቆየት ትግስት የለኝም አንድ አንዴ ጥፋት መሆኑን አውቄው ሳይሆን እንዲው ይሰለቸኝና ተወዋለው ከዛን ካለፈ በኃላ ፈገግ እልና ለካ ስሳሳት ነበር የምልባቸው ጊዜያቶች ብዙ አሉ።
ለራሴ ስነግረው ያደኩት ነገር "ለተፈጠረ ነገር ባርያ አደለሽም " ለዚህም ምንም ነገር አይጨንቀኝም ፣ ህይወቴ ውስጥ ለሚመጡም ለሚሄዱም ነገሮች ግድ ኖሮኝ አያውቅም ፣ እስካሉ የእውነት ወዳቸዋለው ሲሄዱ እንደነበሩኝ እንኳን ለማስታወስ ዘነጋቸዋለው …… ዝናቡ ቢያበሰብሰኝም ማንም ጥላ ይዞ እንዲመጣልኝ ጠብቄም ፈልጌም አላውቅም ።
አሁን ግን ፍርሃት ሲወረኝ ይሰማኛል ፣ መቶ እንደ ልጅ አቅፎ ውስጡ እንዲሸሽገኝ እመኛለው ……" በቃ አልሄድኩም ፣ ትቼሽ አልሄድም " ሚለውን ቃል ናፍቃለው ………
አብረን ሆነን የምጠጣው ቡና ሚጣፍጠኝ እኔ ጎበዝ ቡና አፊይ ስለሆንኩ እንጂ ከሱ ጋር ስለምጠጣው አይመስለኝም ነበር ፣ ቀልዶ ስስቅ ቀልድ አዋቂ ስለሆነ እንጂ እሱ ስላወራው እንደሆነ አልገባኝም ፣ሰላም ሚተነፍሰው ማንነቱን የማደንቀው ሚደነቅ ሆኖብኝ እንጂ ልቤን በተለየ እንደሚያንጫጫት አልተረዳውም
ትሁት ነፍሱ ውብ ልቡን ያዞርብኛል ብዬ ስለማላስብ ግድ የለሽንነቴን አላስተዋልኩትም ፣ ምን አልባትም ለሱ ሚሰማኝ ስሜት የፍቅር አይመስለኝም ነበር ፣ የህይወቴን ስም ባጣው ሰዓት አብሮኝ ስለነበር በየእርምጃዎቼ ስለተከተለኝ ውለታው የያዘኝ መስሎኝ ነበር………
ግን ከዛች ጠዋት በኃላ ፈርቼ ማላውቀው ፍርሃት አለት ነፍሴን ሲርዳት ተሰማኝ ………
"ልሄድ ነው ካናዳ "
"ለስንት ጊዜ "
" አመት ወይም አመታት "
"እህ ፣ እዚህ ያለው ስራስ "
" አንቺ ስላለሽ እንጂ ፣ ቤተሰቤም ስራዬም እኮ እዛ ነው "
"ወደ ጁሩ አርሴማ ልታሰራ ስላሰብከው ጤናጣብያስ ?"
ዝም አለኝ
"እውነት ልትሄድ ነው " አልኩት ቃላቶቼን እያንቀጠቀትኩ……
" ስለምታፈቅሪው አይደል ሲመለስም የተቀበልሽው ፣ እርግጠኛ አልነበርሽ ስለሱ ስትነግሪኝ ፣ ታድያ ምን እሰራለው እዚህ ደስታሽ እሱ ከሆነ ደስታሽ ነው ደስታዬ ፣ " ምንም አልመለስኩለትም አይኖቼ በጭንቀት ካዘጋጀው ሻንጣ ላይ ተክዘዋል ………
"አፈቅርሻለው ፣ ግን ከልብሽ ጋር ታግዬ አይደለም በንፅፅር የኔ እድትሆኚ አልፈልግም ፣ ወደምትፈልጊው አቅጣጫ ብረሪልኝ "
" ባረኩት ነገር አልፀፀትም ፣ እሱን በማፍቀሬ ፣ ሲመጣም በማውራቴ ……… የትኛውም ነገር አይፀፅተኝም ፣ " አልኩት
አዎ አልፀፀትም "ባላወራው እንዴት አውቅ ነበር አንተን እንደምወድህ "ለራሴ ነው ያልኩት
"ሰላም ግባ " ቦርሳዬን ከአልጋው ላይ አንስቼ ወደመውጫው ተሳብኩ ፣
"አሚን "
እንደቆረጠ ገባኝ ………
ይሂድ ግን ተመልሶ ይመጣ ይሁን ?… ለመጀመርያ ጊዜ ፍርሃት 'ነገዬን ' ሲኮረኩመው ተሰማኝ ………
ትዝታ /@tiztawe