.ምክር_ዘቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ
እስኪ ንገሩኝ! ከእናንተ መካከል ከመዝሙረ ዳዊት ውስጥ አንዲት ምዕራፍ ወይም ከሌላው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ጥቂት [በቃልህ] ድገም ቢባል ይህን ማድረግ የሚችል ማን ነው? አንድ ሰውስ እንኳ አይገኝም፡፡
እጅግ የሚያሳዝነው ነገር ግን ይኼ ብቻ አይደለም፡፡ ከመንፈሳዊ ነገሮች አንጻር እንደዚህ አእምሮ የጎደላችሁ ኾናችሁ ሳለ ዲያብሎሳዊ በኾኑ ነገሮች ላይ ግን እሳት የላሳችሁ ናችሁ፡፡ እንዲህም በመኾናችሁ አንድ ሰው መጥቶ ዲያብሎሳዊ ዘፈኖችንና የዝሙት ሙዚቃዎችን ንገሩኝ ቢላችሁ፥ ከእናንተ መካከል እነዚህን በትክክል የሚያውቁና ደስ ተሰኝተው የሚደግሙአቸው ብዙ ሰዎችን ያገኛል፡፡
ለምንድን ነው እንደዚህ የምትኾኑት? ከእናንተ መካከል “እኔ መነኰሴ አይደለሁም፡፡ ሚስት አለችኝ፡፡ ልጆች አሉኝ፡፡ የቤተሰብ መሪ ነኝ” የሚል ምክንያት የሚያቀርብ ሰው ሊኖር ይችላል፡፡ ለምን እንደዚህ ትላላችሁ? ብዙዎችን ያጠፋው “ቅዱሳት መጻሕፍትን ማንበብ ለመነኰሳት ብቻ ነው” የሚለው አመለካከታችሁ ነው፡፡ ከመነኰሳቱ ይልቅ ይበልጥ ማንበብ ያለባችሁ ግን እናንተ ናችሁ፡፡ ይበልጥ መድኃኒት የሚያስፈልጋቸው ሰዎች በዓለም የሚኖሩና ዕለት ዕለትም ቁስል የሚያገኛቸው ሰዎች ናቸውና፡፡ ስለዚህ ካለማንበባችሁም በላይ “የእኛ ማንበብ ትርፍ ነገር ነው” ብላችሁ ማሰባችሁ በራሱ የዲያብሎስ አሳብ ነው፡፡ ወይስ ንዑድ ክቡር የሚኾን ጳውሎስ፡- “ይህም ኹሉ እኛን ሊገሥጸን ተጻፈ” ያለውን አላደመጣችሁምን? (1ኛ ቆሮ.10፡11)፡፡
አንተ ሰው እስኪ ንገረኝ! ወንጌልን በእጅህ ለመያዝ ብትፈልግ አስቀድመህ እጅህን ትታጠባለህ፡፡ ታዲያ በወንጌሉ ውስጥ ያለውን ቃለ እግዚአብሔር ከዚህ በላይ እጅግ አስፈላጊ እንደ ኾነ አታስብምን? ብዙ ነገሮች ምስቅልቅላቸው የወጣው በዚህ ምክንያት ነው፡፡
ቅዱሳት መጻሕፍትን ማንበብ ጥቅሙ እንደ ምን የበዛ እንደ ኾነ ማወቅ የምትሻ ከኾነ መዝሙረ ዳዊትን ስትሰማና የአጋንንትን ዘፈን ስታደምጥ ምን እንደምትኾን፣ ቤተ ክርስቲያን ስትኾንና ቤተ ተውኔት ስትቀመጥ እንዴት እንደምታስብ ራስህን መርምር፡፡ ያን ጊዜ በነፍስህ ላይ የሚስተዋለው ልዩነት እንደ ምን ታላቅ እንደ ኾነ ትገነዘባለህ፡፡ ነፍስህ አንዲት ብትኾንም ቅሉ እዚያ ስትኾንና እዚህ ስትኾን በአኳኋንዋ እንዴት እንደምትለያይ ታስተውላለህ፡፡ ይኸውም የተወደደ ጳውሎስ፡- “ክፉ ባልንጀርነት መልካሙን አመል ያጠፋል” እንዳለው ማለት ነው (1ኛ ቆሮ.15፡33)፡፡ ስለዚህ ዘወትር ከመንፈስ ቅዱስ የኾኑ መዝሙራትን ልንሻ ይገባናል፡፡ ግዕዛን ከሌላቸው ፍጥረታት ያለን ብልጫ ይህ ነውና፡፡
ለሌሎች ይደርስ ዘንድ ሼር አድርጉት
የቴሌግራምና ዩቱብ ቻናሌ መቀላቀል ለምትሹ
ዩቱብ
https://www.youtube.com/@12Samual
ቴሌግራም
https://t.me/tsidq