የኬንያ ፖሊስ በኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ላይ በወሰደው እርምጃ በርካታ መደበቂያዎቹን መደምሰሱን ገለፀ፡፡
ፖሊስ ባወጣው መግለጫ ካለፈው ጃንዋሪ 3 ቀን ጀምሮ ኦፕሬሽን ኦንዳ ጃንግሊ በሚል በከፈተው ዘመቻ 14 የኦነግ ካምፖችንና መጠለያዎችን ማፍረሱንና በርካታ ጦር መሳሪያዎችን ማግኘቱን አስረድቷል፡፡
‹‹ዘመቻው የተከናወነው በኦነግ ታጣቂዎች በሚመሩ የወንጀል ኔትወርኮች ላይ ነበር›› ያለው የኬንያ ብሄራዊ ፖሊስ በዘመቻው መደበቂያቸው ከመደምሰሱም በላይ በቁጥር ያልገለፃቸው ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን አስረድቷል፡፡
ከያዛቸው እቃዎች መካከል አስር የተለያየ አይነት የጦር መሳሪያዎች፣ ሀሰተኛ ወይንም ተመመሳስለው የተሰሩ የአሜሪካ ዶላሮችና የኢትዮጵያ ብር፣ አንድ የውሀ ቦቴ፣ ሁለት መኪናዎች፣ ሁለት መቶ ኪሎ ግራም ካናቢስ፣ የሶላር ፓኔል፣ ጄኔሬተሮች፣ የተለያዩ የኦሮሞ ስነፅሁፎችና የፕሮፓጋንዳ ፅሁፎች እንደሚገኙበት ጠቅሷል፡፡
በቁጥጥር ስር የዋሉት ግለሰቦች ፍርድ ቤት እንደሚቀርቡም አስታውቋል፡፡ ፖሊስ በመግለጫው ‹‹በዘመቻችን በኢትዮጵያና ኬንያ ድንበር ላይ የነበረውን ህገ ወጥ የሰዎች ዝውወርን፣ ህገ ወጥ ማእድን ማውጣትን፣ የግለሰቦችን እገታና የማህበረሰቡን ስቃይ ለመታደግ ችለናል›› ብሏል፡፡ የኬንያ ፖሊስ የሰዎችን ህይወትና ንብረት ለማስጠበቅ ወደፊትም ማናቸውንም እርምጃዎች ለመውሰድ ዝግጁ መሆኑንም አስረድቷል፡፡
የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ይህ እርምጃ እንደተጀመረ ታጣቂዎቹ በወንጀል ተግባር ላይ እንደማይሰማሩ መግለፁ ይታወሳል፡፡ እንዲሁም በኬንያ ድንበር አቅራቢያ ቋሚ ወታደራዊ ካምፕ እንደሌለው ጠቅሶ ዘጠና አምስት ፐርሰንት እንቅስቃሴው በሌሎች የኦሮሚያ ክፍሎች ውስጥ መሆኑን ማስታወቁ አይዘነጋም፡፡
https://t.me/voa_amharic1