በደሴ ከተማ ዛሬ ምሽት በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ2 ሰዎች ህይወት አለፈ።
በከተማዋ በተለምዶ ዳንዲ ቦሩ ተቋም መገንጠያ በሚባለው አካባቢ ቲዮታ ስቴሽን ተሽከርካሪ ባደረሰው አደጋ 2 ሰዎች ሲሞቱ አንድ ሰው ደግሞ ከባድ ጉዳት እንደደረሰበት ተገልፅዋል።
በደሴ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የትራፊክ ክፍል አደጋ መከላከል ቁጥጥር ክፍል ሀላፊ ኢንስፔክተር አደፍርስ ታፈሰ እንደተናገሩት አደጋውን ያደረሱ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውለዋል።
አደጋው በዛሬው እለት ምሽት 12:00 አካባቢ የደረሰ ሲሆን በአደጋው በጉልት የሚተዳደሩ የ2 ሰዎች ህይወት ማለፉ ተገልጿል።
ፖሊስ የአደጋውን ዝርዝር ሁኔታ አጣርቶ መረጃ እንደሚሰጥ ጠቁሟል።
(ከድር መሀመድ)
https://youtu.be/T_s7lK_5I3g