TGStat
TGStat
Введите текст для поиска
Расширенный поиск каналов
  • flag Russian
    Язык сайта
    flag Russian flag English flag Uzbek
  • Вход на сайт
  • Каталог
    Каталог каналов и чатов Поиск каналов
    Добавить канал/чат
  • Рейтинги
    Рейтинг каналов Рейтинг чатов Рейтинг публикаций
    Рейтинги брендов и персон
  • Аналитика
  • Поиск по публикациям
  • Мониторинг Telegram
Wasu Mohammed - ዋሱ መሀመድ

21 Nov 2025, 07:54

Открыть в Telegram Поделиться Пожаловаться

Prev Next
"የ7ቱ ሰዎች ህይወት አልፏል" ፖሊስ

የተመረዘ ምግብ በልተዉ ከታመሙ ከ8 የአንድ ቤተሰብ አባላት ዉስጥ ነው የ7ቱ ሰዎች ህይወት ያለፈው።

ምግቡ በማንና እንዴት ተመረዘ? የፖሊስ መረጃ ከስር ተቀምጧል።

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምስራቅ ጉራጌ ዞን መስቃን ወረዳ በአብሮነት እራት ተመግበዉ በጠና ከታመሙ ስምንት የአንድ ቤተሰብ አባላት ዉስጥ አባወራዉ ከስድስት ልጆቹ ጋር ሰባት የአንድ ቤተሰብ አባላት ህይወታቸዉ ማለፉን ፖሊስ ገልጿል።

የክልሉ ፖሊስ የወንጀል መረጃ ኢንተለጀንስ ዳይሬክቶሬት ተወካይ ምክትል ኮማንደር ያለዉ ተመስገን እንደገለፁት በወረዳዉ መሰረተ ወገራም ቀበሌ ዳሾ ቆቶ ተብሎ በሚጠራዉ መንደር ህዳር 6 ቀን 2018 ዓ.ም ምሽት 1:00 ሰዓት ስምንቱ የቤተሰብ አባላት አብረዉ እራት ከተመገቡ በኋላ በድንገት መታመማቸዉ ተናግረዋል።

በአብሮነት እራት እንደተመገቡ ብዙም ሳይቆዩ ከፍተኛ ለሆነ ህመም መዳረጋቸዉን መረጃ የደረሳቸዉ የአካባቢዉ ነዋሪዎች የተጎጂዎችን ህይወት ለማትረፍ ተረባርበዉ ወደ ሆስፒታል ማድረሳቸዉ ነዉ የተነገረዉ።

ቢሆንም ከተጎዱ የቤተሰቡ አባላት የ5 ዓመቱ መንግስቱ ኃይሌ ፣የ7 ዓመቱ መክብነ ኃይሌ እና የ17 ዓመቱ ተክሉ ኃይሌ የተባሉት ሶስቱ ወንድማማቾች በዕለቱ ሆስፒታል እንደደረሱ ህይወታቸዉ ማለፉን ነዉ የተገለፀዉ።

የተቀሩ ተጎጂዎችን ህይወት በህክምና ለማትረፍ ሀኪሞች ያልተቋረጠ ጥረት ቢያደርጉም የ14 ዓመቷ መቅደስ ኃይሌ እና የ15 ዓመቱ ገብሬ ኃይሌ የሁለቱ እህትና ወንድም ህይወት ህዳር 7 ቀን 2018 ዓ.ም ምሽት 11:00 ሰዓት ሲያልፍ የሟቾች ቁጥር ወደ አምስት አሻቀበ።

ከተቀሩት ተጎጂዎች ደግሞ የ1ዓመት ከ7 ወሩ ህፃን ሲሳይ ኃይሌ ህዳር 9 ቀን 2018 ዓ.ም ጥዋት 2:00 ሰዓት ላይ ህይወቱ ሲያልፍ የስድስቱ ሟች ልጆች አባት የሆነዉ አቶ ኃይሌ አበራ ህዳር 10 ቀን 2018 ዓ.ም ለሊት በሰመመን ዉስጥ ሆኖ ከእንቅልፉ ሳይነቃ ህልፈቱ እዉን ሆኖ ልብ ሰባሪና አሳዛኝ የሆነ ዜና ተደመጠ።

የባለቤቷንና የስድስት ልጆችዋን ህልፈት ለማወቅ ያልታደለችዉ ወይዘሮ ዳመነች ደንበል በሚኒሊክ ሆስፒታል በከፍተኛ የጥንቃቄ ክፍል ዉስጥ ሆና በህክምና እየተረዳች በህወት መኖሯን ነዉ ፖሊስ የተገለፀዉ።

ተጎጂዋ ቤተሰቡን በጅምላ ወደ ሞት ያወረደዉን ጉዳይ ልትተርክ በህይወት ትተርፍ ይሆን?ወይስ እሷም የባለቤቷና የልጆችዋ እጣ ገጥሟት ከቤተሰቡ መሀል አንድም ለወሬ ነጋሪ ሳይተርፍ በጅምላ እቺን አለም የመሰናበታቸዉ አሳዛኝ ዜና ይደመጣል? የሚለዉን ለመገመት ይከብዳል።

ፖሊስ ተጎጂዎች የተመገቡት ምግብ የተመረዘዉ በማንና እንዴት?የሚለዉን እዉነታ ለማረጋገጥና የተፈፀመዉን ድርጊት አጣርቶ እዉነታዉ ለማረጋገጥ ከምስራቅ ጉራጌ ዞን እና ከመስቃን ወረዳ የተወጣጣ የምርመራ አጣሪ ግብረ ኃይል አዋቅሮ ምርመራ የማጣራቱን ስራ መጀመሩን የተናገሩት ኮማንደር ያለዉ ተመስገን የምርመራ ግብረ ኃይሉ በድርጊቱ የሌሎች እጅ ሊኖር ይችላል በሚል ጥርጣሬ አስር ሰዎችን በቁጥጥር ስር አዉሎ ምርመራ እያጣራ መሆኑን ገልፀዋል።

ተጎጂዎች በዳግማዊ ምንሊክ ሆስፒታል ህክምና ተከታትለዋል ያለዉ ፖሊስ የሟቾች የአስክሬን ምርመራ ዉጤት እየተጠበቀ መሆኑንና ስለጉዳዩ የተሻለ ፍንጭ ሊሰጥ እንደሚችል መረጃ ሊገኝ እንደሚችል ይገመታል።

የክልሉ ፖሊስ ሚድያ ክፍል ይህ ዜና በሚድያ ይፋ እስካደረገበት ሰዓት ድረስ ከስምንቱ ተጎጂዎች ዉስጥ አንዷ የሆነችዉ የቤቱ እማወራ በአዲስ አበባ ምንሊክ ሆስፒታል በህክምና እየተረዳች መሆኑን አረጋግጧል።

በተለያየ ጊዜ እቺን አለም የተቀላቀሉት ከ46 ዓመቱ አባት እስከ 1 ዓመት አ7 ወር እድሜ ያለዉ ህፃን እቺን አለም በተመሳሳይ ሰአት ለመሰናበት የተገደዱበት ተግባር የተለየ ግኝት ካለ መረጃዉን ለህዝብ ይፋ የምናደርግ ይሆናል ሲል የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን መረጃውን አጋርቷል።
#ዋሱመሐመድ
አሁናዊ ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናሉን join በማድረግ በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ
https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4
https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4
https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4

27.2k 0 36 433
Каталог
Каталог каналов и чатов Подборки каналов Поиск каналов Добавить канал/чат
Рейтинги
Рейтинг каналов Telegram Рейтинг чатов Telegram Рейтинг публикаций Рейтинги брендов и персон
API
API статистики API поиска публикаций API Callback
Наши каналы
@TGStat @TGStat_Chat @telepulse @TGStatAPI
Почитать
Академия TGStat Исследование Telegram 2019 Исследование Telegram 2021 Исследование Telegram 2023
Контакты
Справочный центр Поддержка Почта Вакансии
Всякая всячина
Пользовательское соглашение Политика конфиденциальности Публичная оферта
Наши боты
@TGStat_Bot @SearcheeBot @TGAlertsBot @tg_analytics_bot @TGStatChatBot