Репост из: ሱፊይ አሕለሱና ወልጀመዐህ
🔴 ማዘን ሲገባ መደሰት
🔷 ‹ነብዩሰለሏሁ አለይሂ ወሰልም የሞቱት በተወለዱበት ቀን ስለሆነ በዚያ ቀን ማዘን ሲገባችሁ መደሰት አግባብ አይደለም፡፡ በነብዩ መሞት የመደሰት ያህል ነዉ› የሚል ተቃዉሞ ይደመጣል፡፡ ከምዕተ ዓመታት በፊትም ተነስቶ ነበር፡፡ ኢማም ጀላሉዲን
አልሱዩጢ በቂ ምላሽ በመስጠትገላግለዉናል፡፡ እርሱኑ እንደወረደ
ባቀርበዉ የተሸለ ነዉ፤‹‹ወከፈላሁል ሙእሚኒነል ቂታል›፡
🟢‹‹የነብዩ ሰለሏሁ አለይሂ ወሰለም መወለድ ለኛ ታላቁ ጸጋችን ሲሆን፣ህልፈታቸዉ ደግሞ ታላቁ
መከራችን ነዉ፡፡ ሆኖም ሸሪዐዉ ለጸጋ የሚደረግ ምስጋናን ይፋ በማድረግ፣ መከራን ደግሞ በመታገስና በመደበቅ አዟል፡፡ ልጅ ሲወለድ ዐቂቃ ይደረግ ዘንድ ያዘዘ ሲሆን፣ዓላማዉም ደስታንና ምስጋናን ይፋ
ለማድረግ ነዉ፡፡ በአንጻሩ ሰዉ ሲሞት እርድ እንዲታረድ ወይም ሌላ ነገር ይደረግ ዘንድ አላዘዘም፡፡ እንዲያዉም ሙሾንና የበረታ ሀዘን
ማሳየትን ከልክሏል፡፡ ስለዚህም የሸሪዐዉ መሠረታዊ መርህ ያመላከተዉ
በዚህ ወር (በረቢዕ) ሀዘንን መግለጽን ሳይሆን በነብዩ መወለድ የተሰማ
ደስታን ይፋ ማድረግን ነዉ፡፡›
ምንጭ: ሁስነል መቅሰድ ፊዐመሊል መዉሊድ
https://t.me/sufiyahlesuna