💐እግዚአብሔር በልጁ ልደት ሳመን፨፨፨🎄
#ከዘላለም ዘመን በፊት በቅድመ ዓለም #ባለመለወጥና ባለ መለየት በባሕርይ መስሎ በአካል አህሎ #ያለ _ እናት የተወለደው የእግዚአብሔር አብ ልጅ #ከዘላለም ዘመን በኃላ በድኅረ ዓለም በሰው አምሳል ሰውን አህሎ #ያለ_አባት ከድንግል ማሪያም ተወለደ (ገላ.4፥4)።
#ተቀዳሚም ተከታይም የሌለው #የእግዚአብሔር አንድያ ልጅ #በቃል ወደ ፈጠረው ዓለም #በእግሩ መጣ #በሰራው ኃጢአት ምክንያት ከገነት ወደ ምድር ያስወጣውን ሰው #ፍቅር ግድ ቢለው ተከትሎት ወጣ #በዓፀደ ገነት በድምፁ ፍለጋ የጀመረውን ዓዳም #በገፀ ምድር ወርዶ በስጋው አገኘው።
#የኢየሱስ ክርስቶስ መወለድ የአንድ ሰው ወደዚህ ዓለም መቀላቀል አይደለም፤ #የማይታየው አምላክ በሥጋ የተገለጠበት #ዲያብሎስ ዱካ አጥፍቶ ገነት ዘልቆ #ዓዳምን አታልሎ ወደ ዓለም ባስገባው ኃጢአትና ሞት #የፈቃዱ ባሪያ ያደረገውን #የሰው ዘር በሞላ በገዛ ደሙ ሊቤዥ #እግዚአብሔር የሄደበት የፍቅር ጥግ #ረቂቅ ምስጢር ነው።
#በዚህ ዓለም አሰከ-አሁን 1.8 ትሪሊዮን ገደማ ህጻናት ተወልደዋል #ነገር ግን ሁሉም የተወለዱት ለእራሳቸው ነው፡፡#ኢየሱስ ክርስቶስ ግን የተወለደው ለእኛ ነው #በጨለማ ለሚኖሩት ብርሃን #በሞት አገርና ጥላ ላሉት ሕይወት ሊሆን ነው፡፡(ኢሳ.9፥6)።
#የዘላለም አባት ሳለህ #ህጻን የተባልህ #ዓለማትን በመዳፍህ ይዘህ #በድንግል አቅፋ ያደርህ #ሰማየ ሰማያት የማይችሉህ #በመጠቅለያ የታጠፍህ #እኛን በእጅ ባልተሰራ ቤት ልታሳድር #አንተ በግርግም ያደርህ #ፅድቅ የሞላበትን ሰማይ መኖሪያህን ለእኛ ሰጥተህ #ኃጢአት የበዛበትን ምድር የከተብህ #የቆሙ መላዕክት ክብርና ውዳሴ ሳይማርክህ #የወደቁ ሰዎች ኃጢአትና ሞት ያስጨነቀህ #ለዘላለም የፀናው ዓለምህን ትተህ #በቅፅበት የወደቀውን ዓለም #ልታነሳ መጣህ።...
#እወድሃለሁ።
#ከዘላለም ሞት ሊያድነን በተወለደው #የቤዛነት ሥራ አምኖ ዳግም በመወለድ እንጂ #ልደቱን በማክበር የሚመጣ ብፅዕና የለም፡፡#በቤተልሔም የተወለደው #በልባችን ሲወለድ የዘላለም ሕይወት ይሰጠናል።
💐💐 @wengelbeArt 💐💐