💐የእግዜር ልጓም💐
ክፍል 22
ተከታታይ ልብ-ወለድ
✍Aksan Adane
...... አንተ ዚያድ ድጋሚ ተጣራሁ መልስ የለም ዚያድ ተጠጋሁት አረፋ ደፍቆ ነበር ጩኸቴን አቀለጥኩት ግርርርርርር ብለው ተሰበሰቡ ምን አድርገሽው ነው ?
አንደኛዋ ጮከችብኝ እኔ አሁን መምጣቴ ነው ማን ምን እንዳደረገው በምን አውቃለሁ? ወንዶቹ በፍጥነት ተሸክመው አስወጡት ልከተላቸው ቃጣኝ አንደኛው እጄን ይዞ አስቆመኝ የቀሩት ክፍሉን ሲቃኙ ዚያድ ራሱን ለማጥፋት አደገኛ መርዝ መውሰዱን አንደኛው አረጋገጠ ::
ለምን ዚያድ በኢየሱስ ሳታምን ለምን በውስጤ እርርርር ያለ በጩኸት የማይወጣ ቁጭት ተሰማኝ ::
ክፍሉ እንዲፀዳ ተደረገ ከዚህ የተሰቀለ አልጋ ላይ ቁጭ ብዬ አለቅስ ጀመር ::
የሞተ ያህል ነው የተሰማኝ :: ከሰዓታት በኋላ አቶ ዴቪድ አንዱን አስከትሎ መጣ ::
:-ዜማ እንደምን ነሽ ? ጓደኛሽ ደህና ይሆናል የሀኪም እርዳታ አግኝቷል :: አለኝ
:-ጥሩ ነው ::
በቃ ራስሽን አረጋግተሽ ለመተኛት ሞክሪ መልካም አዳር ብለውኝ ወጡ ::
ስለ ዚያድ ፀለይኩ ጌታ ሆይ ይህቺን ነብስ አሳልፈህ ትሰጠኛለህ ዚያድ ወደ መንግስትህ ሳይመጣ ለሲዖል ማገዶ አይሁን ግን አንተን የሚከራከርህ የሚያዝህ የለምና ሁሉ በፈቃድህ ይሁን አሜን:: ለመተኛት ሽፍንፍን ካልኩ በኋላ እናቴ ትውስ አለችኝ እንደገና ሲሜን ከፍቼው ደወልኩላት ::
ሁለቴም ሳይጠራ አነሳችው ኸረ ልጄ በሰቀቀን አለቅሁኝ ምነው ምነው ምን አደረግንሽ? አይበቃም ወይ ስሞት ተጠርተሽ ነው መምጣት የፈለግሽው?
አንድም ቃል ሳልተነፍስ ብዙ አወራች ::
:-እናቴ በቅርቡ እመጣለሁ በቅርቡ አታስቢ ራስሽን ጠብቂ እኔ እጅግ በጣም ደህና ነኝ ደግሞም ናፍቃችሁኛል እወድሻለሁ እናቴ::
ስልኩን ናታን ቀማት ዜማ የት ነሽ? ለምንድነው ያለሽበትን የማትነግሪን
:-እኔም አላውቀውም ነቲ
:-እሺ ስልኩን አትዝጊው ዜማ እያዳመጥሽኝ ነው?.
:-እሱን ማድረግ አልችልም ::
:-እኮ ለምን? አሁን ምን እያደረግሽ ነው በምን ሁኔታ ውስጥ ነው ያለሽው ?
:-ደህና ነኝ አታስቡ ጌታ መልካም አድርጎልኛል ::
:-ይኸውልሽ ዜማ አንተ ደህና ነሽ አይደል? ያለሽበትን ላታውቂው ትችያለሽ ነገሮችን በደንብ ታስታውሺያለሽ? እባክሽ ዜማ እኛ እኮ ቤተሰቦችሽ ነን ጉዳትሽን ማየት ስለማንፈልግ ነው ምንም ገጥሞሽ ከሆነ እውነቱን ንገሪኝ ህመም :እርግዝና ምንም ይሁን በህይወት መኖርሽ ይቀድማል ዜማ አድምጪኝ የት ነሽ?
ኸረ በስማም በል ናቲ ፍፁም ጤነኛ ነኝ አሁንም አእምሮዬን እንደታመምኩ እያሰብክ ነው? እንደሱ አይደለም እንደምትለው ያለ ነውር ውስጥም አልገባሁም እመነኝ ናቲ የምትለው እና ያለሁበት ሁኔታ ፍፁም የተራራቀ ነው ::
በቅርቡ እመጣለሁ ደህና ቆዩልኝ ::
ስልኩን ዘጋሁት ::
💐💐 @wengelbeArt 💐💐
"የሠላሙ ንጉስ በቤቴ ሲገባ ሰላምና ፍቅር ተከትሎት ገባ " የተሰኘውን የምህረት መዝሙር ከፍቼ እየተባረኩበት በሰላም ተኛሁ ::
ዚያድ ከሶስት ቀን በኋላ ነበር የነቃው ሲነቃ ዜማን ካላመጣችሁ ብሎ ሁካታ ሲፈጥር እንደነበር አቶ ዴቪድ ነገረኝ :: የሆነ ሊነግርሽ ያሰበው ነገር ያለ ይመስለኛል እኔ ቀርቤ ላወጣጣው ብሞክር አላመነኝም አለኝ ::
እናም ትወናው በተሳለጠ መንገድ ይሄድ ጀመር ከአለባበስ ጀምሮ እስከ ንግግር ለመመሳሰል ሳምንት አልፈጀብኝ ደግሞ አለምን ለመምሰል:: ኸረ ግማሽ ቀንም አይፈጅ ክርስቶስን ለመምሰል ሲሆን ነው እኛ ክርስቲያኖች ተራራ የሚሆንብን :: ከሴቶቹ ጋር ተቀራረብን ፕሮቶኮል በፕሮቶኮል እየሆንን አጀንዳዊ ስብሰባ ሁሉ ይደረግ ጀመር ::
እውነቱን ነው አቶ ዴቪድ እንደ አስመሳይ የሚታመን ሰዉ የለም ::
ሰዎቹ ክህደቴን እውነት አድርገው ተቀብለውታል:: እውነትም ሰይጣን የልብን አያውቅም የኔ እግዚአብሔር እንደ
አንተ ማነው? ሲጀመር እንዴት አወዳድራለሁ አንተ እኮ ብቸኛ ነህ::
በየመሀሉ ሀሳቤ ይወሰድብኛል በአምላኬ ማንነት እደነቃለሁ::
ቀንደኛ አባል መስዬ ቁጭ አልኩላችሁ :: ሰዎችን እንዴት አባል እናድርግ እንዴት እናጥምድ እንዴት የደም መስዋዕት ይቅረብ በሚሉ ጉዳዮች መሠባሠባችን ቀጥሏል ::
ያው አሁን ታምኜም የለ ዚያድን ማግኘት እንድችል ሆንኩ ይንቃ እንጂ ከፍተኛ የጨጓራ ቁስለት ስላጋጠመው በህክምና እየተረዳ ነው :: ላገኘው ወደ ተኛበት ቦታ ሄድኩ .......
........ይቀጥላል.......
✍written by Aksan Adane
💐💐
@wengelbeArt 💐💐
💐💐
@wengelbeArt 💐💐