የግብአት አቅርቦትና ስርጭት ፣ የትምህርት መረጃ ዝግጅትና የትምህርት ቴክኖሎጂ ልማትና አስተዳደር ዘርፍ የአንድ ወር እቅድ አፈጻጸም ግምገማ አካሄደ።
(ጥር 5/2017 ዓ.ም) የግብአት አቅርቦትና ስርጭት ፣ የትምህርት መረጃ ዝግጅትና የትምህርት ቴክኖሎጂ ልማትና አስተዳደር ዳይሬክቶሬቶች በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ለማከናወን በእቅድ ያስቀመጧቸው ተግባራት የአፈፃፀም ሪፖርት የቢሮው ምክትል ቢሮ ኃላፊና የዘርፉ ኃላፊ አቶ ሳምሶን መለሰ በተገኙበት አቅርበው አስገምግመዋል::
ወርሃዊ የስራ አፈጻጸሞችን መገምገም ለችግሮች አፋጣኝ መፍትሄ ለመስጠት ጠቃሚ መሆኑን የተናገሩት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ እና የዘርፉ አስተባባሪ አቶ ሳምሶን መለሰ በሪፖርት የቀረቡ ወርሃዊ የሥራ አፈጻጸሞች በበለጠ ትኩረት ስራችንን እንድናከናውን ያግዛሉ ሲሉ ተናግረዋል፡፡ አቶ ሳምሶን አያይዘውም ዳይሬክቶሬቶቹ ስራን በትስስር ለመስራት ያሳዩትን ቁርጠኝነት አድንቀው ፤ የስራ ክፍሎቹ በጋራ መስራት አንዱ ለአንዱ አቅም የሚፈጥርበትና ለስራችን ስኬታማነት መልካም አጋጣሚ መሆኑን በመረዳት የስራ ትስስርን በባህል አድርገው መቀጠል እንዳለባቸው ተናግረዋል፡፡ አክለውም ዳይሬክቶሬቶቹ የሪፎርም ስራ መደበኛ ስራችን ግብ እንዲመታ በማድረግ በኩል ከፍተኛ ሚና እንዳላቸው በመውሰድ በቀጣይ በትኩረት ሊሰራበት ይገባል በማለት አሳስበዋል፡፡
በውይይቱ ላይ በሶስቱ ዳይሬክቶሬቶች የሚገኙ ዳይሬክተሮች ፤ ቡድን መሪዎችና ባለሙያዎች የተሳተፉ ሆነዋል፡፡
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ!
https://linktr.ee/aacaebc