Addis Ababa Education Bureau

Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: не указана

ይህ ቻናል የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የቴሌግራም ቻናል ሲሆን በከተማ አስተዳደሩ እስከ ትምህርት ቤት ድረስ የተከናወኑ እንዲሁም ሀገራዊ ፣ አህጉራዊ እና አለማቀፋዊ የትምህርት መረጃዎች ተደራሽ የሚደረጉበት ነው፡፡

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
не указана
Статистика
Фильтр публикаций

በከተማችን አዲስ አበባ የምትኖሩ የአውሮፓውያኑን 2025 አዲስ ዓመት የምታከበሩ ሁሉ እንኳን ለአዲሱ አመት አደረሳችሁ ፤ዓመቱ የሰላም፣ የደስታ እና የስኬት እንዲሆንላችሁ እመኛለሁ።

መልካም አዲስ ዓመት !

Happy New Year 2025 to everyone around the world. May the New Year bring peace, health, prosperity, and success to you and your loved ones.

ከንቲባ አዳነች አቤቤ

(ታህሳስ 22/2017 ዓ.ም)

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

Imo: - https://s.channelcom.tech/vlWdNr?from=TG
What Sapp: - https://whatsapp.com/channel/0029VaHFiBpA2pLF0lLslK2D
flickr :- https://www.flickr.com/photos/197652854@N04/
You Tube: https://www.youtube.com/@addisababaeducationbureau9728
TikTok፡- https://www.tiktok.com/@aaeducationbureau
Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau
Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc
Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication
Blog: - http://www.aacaebc.wordpress.com/
Instagram: - https://www.instagram.com/aacaeb/
Website: - aaceb.gov.et
Email;- aacaebc@gmail.com

ትምህርት ቤቱ ለሒሳብና እንግሊዘኛ ትምህርት በሰጠው ትኩረት ለተለያዩ ትምህርት ተቋማት ሞዴል መሆን የቻሉ ማዕከላት ማቋቋሙን የማዕከላቱ ተጠሪ መምህራን ጠቁመው ተማሪዎቹ ከማዕከላቱ ባሻገር ትምህርት ቤቱ ባቋቋመው የኦዲዮ ቪዥዋል ክፍል በድምጽና ምስል የተደገፈ ትምህርት በማግኘት ላይ በመሆናቸው ውጤታቸው በመሻሻል ላይ መሆኑን ገልጸዋል።

ትምህርት ቤቱ ስርአተ ትምህርቱን በአግባቡ ተግባራዊ በማድረጉ የተማሪዎቹን የሒሳብና እንግሊዘኛ ትምህርት በማሻሻል ላይ እንደሚገኝ በተለያየ ጊዜ በተደረገ ድጋፍና ክትትል መረጋገጡን የትምህርት ቢሮ የስነዜጋ መሻሻልና የተማሪዎች ጉዳይ ባለሙያ አቶ ባይሳ ፀጋዬ ገልጸው ከመደበኛው የመማር ማስተማር ስራው ባሻገር ተቋሙ በከተማ ግብርና ስራም ውጤታማ ተግባራትን በማከናወን ላይ መሆኑን አመላክተዋል።

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

Imo: - https://s.channelcom.tech/vlWdNr?from=TG
What Sapp: - https://whatsapp.com/channel/0029VaHFiBpA2pLF0lLslK2D
flickr :- https://www.flickr.com/photos/197652854@N04/
You Tube: https://www.youtube.com/@addisababaeducationbureau9728
TikTok፡- https://www.tiktok.com/@aaeducationbureau
Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau
Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc
Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication
Blog: - http://www.aacaebc.wordpress.com/
Instagram: - https://www.instagram.com/aacaeb/
Website: - aaceb.gov.et
Email;- aacaebc@gmail.com

ትምህርት ቢሮ ያወረደውን የሒሳብና እንግሊዘኛ ትምህርት ስትራቴጂ ተግባራዊ በማድረጉ የተማሪዎች ውጤት መሻሻል ማሳየቱን የአቃቂ ብሩህ ተስፋ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አስታወቀ።

(ታህሳስ 22/2017 ዓ.ም) ትምህርት ቤቱ በስትራቴጂው መሰረት የተማሪዎችን የመጻፍ፣የማንበብ እና የማስላት ብቃትን መሰረት በማድረግ ለይቶ በተከታታይ ባደረጋቸው ድጋፎች ተማሪዎቹ በሁለቱ የትምህርት አይነቶች ውጤታቸው በመሻሻል ላይ መሆኑን በምዘና ማረጋገጡን የትምህርት ቤቱ ርዕሰ መምህር አቶ ታደሰ አለሙ ገልጸው ተቋሙ ውጤታማ መሆን የቻለው ከወላጆች፣መምህራን እና ተማሪዎች ጋር የአራትዮሽ ፊርማ ተፈራርሞ ተግባራዊ እንቅስቃሴ ማድረግ በመቻሉ እንደሆነ አስረድተዋል።

ርዕሰ መምህሩ አያይዘውም ትምህርት ቤቱ በ2016 በ6ኛ እና 8ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና ያስፈተናቸው ተማሪዎች በሙሉ ወደ 9ኛ ክፍል መዘዋወራቸውን ጠቁመው ቀደም ሲል በነበሩበት ፉሪ አንደኛ ትምህርት ቤት የነበራቸው ውጤታማነት በዚህኛው ትምህርት ቤት መደገሙን በመግለጽ በዚህ አመትም የተማሪዎችን ውጤትና ስነምግባር ስራው ተጠናክሮ መቀጠሉንም አስገንዝበዋል።

የአባከስ ትምህርት ስልጠናው የትምህርት ቤቱ ተማሪዎች አራቱን የሒሳብ ስሌቶች ቀላል በሆነ መንገድ እንዲገነዘቡ ታስቦ ለአንድ ወር ያህል መሰጠቱን የስልጠናው አስተባባሪ መምህር ቴውድሮስ ገደቤ ገልጸው ስልጠናው በዋናነት በተለምዶ የሒሳብ ትምህርት ከባድ እንደሆነ የሚታሰበውን የተዛባ እሳቤ በማስቀረት ተማሪዎች በትምህርቱ ውጤታማ እንዲሆኑ ለማድረግ ታስቦ መዘጋጀቱን አስረድተዋል።

ተመራቂ ተማሪዎቹ ወላጆችን ጨምሮ የትምህርት ቤቱ አጠቃላይ ማህበረሰብ በተገኙበት የሰልፍ ስነ ስርአት በስልጠናው ከወሰዱት ትምህርት ጋር የተገናኙ ጥያቄዎች ቀርቦላቸው በፍጥነት በመመለስ አድናቆት የተቸራቸው ሲሆን ተመራቂ ተማሪዎችና ወላጆች ለመምህር ቴውድሮስ ገደቤ የምስጋና ስጦታ አበርክተዋል።

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

Imo: - https://s.channelcom.tech/vlWdNr?from=TG
What Sapp: - https://whatsapp.com/channel/0029VaHFiBpA2pLF0lLslK2D
flickr :- https://www.flickr.com/photos/197652854@N04/
You Tube: https://www.youtube.com/@addisababaeducationbureau9728
TikTok፡- https://www.tiktok.com/@aaeducationbureau
Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau
Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc
Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication
Blog: - http://www.aacaebc.wordpress.com/
Instagram: - https://www.instagram.com/aacaeb/
Website: - aaceb.gov.et
Email;- aacaebc@gmail.com

አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12 የሚገኘው ብስራት አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎችን በሒሳብ ትምህርት ውጤታማ ለማድረግ በትኩረት እየሰራ እንደሚገኝ አስታወቀ።

(ታህሳስ 22/2017 ዓ.ም) ትምህርት ቤቱ ተማሪዎችን በሒሳብ ትምህርት ውጤታማ ለማድረግ በአባከስ ትምህርት ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች በዛሬው እለት ያስመረቀ ሲሆን ተመራቂ ተማሪዎችም በቀጣይ ሌሎች ተማሪዎችን እንደሚያሰለጥኑ ተገልጿል።

ቢሮው በ2017 ዓ.ም ተማሪዎችን በሒሳብና እንግሊዘኛ ትምህርት ውጤታማ ለማድረግ ያወረደውን ስትራቴጂ ተግባራዊ ለማድረግ ትምህርት ቤቱ የተለያዩ ተግባራትን በማከናወን ላይ እንደሚገኝ የትምህርት ቤቱ ርዕሰ መምህር አቶ ቶፊቅ ሙሰማ ጠቁመው ለተማሪዎች የተሰጠው የአባከስ ስልጠናም የዚሁ ስትራቴጂ አካል መሆኑን አስታውቀዋል።

ርዕ ሰ መምህሩ አያይዘውም ትምህርት ቤቱ ምክሰኞን የሒሳብ ቀን በሚል ሰይሞ የተለያዩ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎችን በመስራት ላይ እንደሚገኝ ጠቁመው ተማሪዎቹ በትምህርቱ ያመጡትን መሻሻል በምዘና የማረጋገጥ ስራ እየተሰራ እንደሚገኝ አመላክተዋል።

የሪፎርም አገልግሎት አሰጣጥ ድጋፍ ክትትልና ምዘና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ተስፋገኘሁ ለገሰ በስድስት ወራት የተከናወኑ የመልካም አስተዳደርና አገልግሎት አሰጣጥ ፤ የቅንጅታዊ አሰራር እና አጠቃላይ የሪፎርም ስራዎች ተግባራትን ሪፖርት በዝርዝር አቅርበዋል::

በተጨማሪም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የእቅድና በጀት ዝግጅት ክትትልና ግምገማ ዳይሬክተር አቶ ጌታሁን ለማ የስድስት ወር ስትራቴጂክ እቅዱን መሰረት በማድረግ የተከናወኑ ዋናዋና ተግባራትን ሪፖርት አቅርበው በቀረቡት ሁለት ሪፖርቶች መሰረት በተሳታፊዎች ውይይት ተካሂዷል።

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

Imo: - https://s.channelcom.tech/vlWdNr?from=TG
What Sapp: - https://whatsapp.com/channel/0029VaHFiBpA2pLF0lLslK2D
flickr :- https://www.flickr.com/photos/197652854@N04/
You Tube: https://www.youtube.com/@addisababaeducationbureau9728
TikTok፡- https://www.tiktok.com/@aaeducationbureau
Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau
Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc
Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication
Blog: - http://www.aacaebc.wordpress.com/
Instagram: - https://www.instagram.com/aacaeb/
Website: - aaceb.gov.et
Email;- aacaebc@gmail.com

የቢሮ የ2017 ዓ.ም የስድስት ወራት እቅድ አፈጻጸም አጠቃላይ የቢሮው ሰራተኞች በተገኙበት ተገመገመ።

(ታህሳስ 22/2017 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የ2017 ዓ.ም የስድስት ወራት ስትራቴጂክ እና የሪፎርም ስራዎች እቅድ አፈጻጸም የቢሮ ሰራተኞች በተገኙበት ተገመገመ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የቢሮ ኃላፊ አማካሪና የዘርፍ ሃላፊ ወይዘሮ አበበች ነጋሽ ቢሮው የ2017 ዓ.ም እቅዱን በሩብ ዓመቱ መጀመሪያ የሚመለከታቸውን አካላት በማሳተፍ ውይይት አድርጎ ወደስራ መገባቱን ገልፀው ፤ ከአጠቃላይ እቅዱ በስትራቴጂክ እቅድ የተቀመጡ ግቦች እና በሪፎርም ስራዎች የተከናወኑ ተግባራት በሥራ ክፍሎችና በየዘርፎቹ ተገምግመው የተግባራት አፈጻጸሙ በከፍተኛ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ሪፖርቱ እንደሚያሳይ አብራርተዋል::

አማካሪዋ አክለውም በ6 ወራት አፈፃፀም የታዩ እጥረቶች ላይ ከአጠቃላይ ሰራተኞች ጋር መወያየት መልካም ተግባራት የበለጠ ተጠናክረው እንዲቀጥሉ የሚያግዙ ጠቃሚ ሀሳቦች ለመውሰድ እንደሚረዳ አብራርተው እቅዱን ለማዳበር የሚጠቅሙ ገንቢ ሃሳቦች ማንሳት ከተሳታፊዎች ይጠበቃል ብለዋል::

የቢሮ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ሲሳይ እንዳለ በበኩላቸው ቢሮው በሪፎርም ድጋፍና ክትትል እንዲሁም ቅንጅታዊ አሰራርን አጠናክሮ እየሰራው ያለው ሥራ ሰፊ መሆኑን ጠቅሰው ይህም ለተሻለ ውጤት ያበረከተውን አስተዋፅኦ በማጤን በልዩ ትኩረት ተጠናክሮ መቀጠል ይገባዋል ብለዋል :: በተጨማሪም ለስራው ውጤታማነት ሁሉም ኃላፊነቱን እንዲወጣ አሳስበዋል ::

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ የትምህርት ስራዉን ዲጂታላዝ ለማድረግ ለትምህርት ማህበረሰቡ በተለይም ለግል ትምህርት ተቋማት በቀጣይ የሚቀርበዉን የኢ-ስኩል ትግበራን ለማሳካት የዲጂታል መታወቂያ ምዝገባ ማከናወን ትልቅ አቅም የሚፈጥር መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ሀላፊዉ አክለዉም ቀደም ሲል በመንግስት ትምህርት ቤቶች ላይ ምዝገባዉ መከናወኑን ጠቅሰው ፤ በግል ትምህርት ቤቶች የሚከናወነውን የዲጂታል መታወቂያ ምዝገባ ለማካሄድና አፈፃፀሙን ውጤታማ ለማድግ ሁሉም የግል ትምህርት ተቋማት ተገቢዉን ዝግጅት እንዲያደረጉ አሳስበዋል፡፡ በተጨማሪም በዲጂታል መታወቂያ የምዝገባ ስርዓት ዘመቻ ውስጥ በግል ትምህርት ተቋማት የሚገኙ ተማሪዎችና በትምህርት መዋቅሩ ውስጥ ያሉ አካላት ሁሉም የዲጂታል መታወቂያ እንዲኖራቸው ለማድረግ እንደሚሰራ ተናግረዋል::

በመድረኩ የዲጂታል መታወቂያን አስመልክቶ ግንዛቤ ማስጨበጫ ሰነድ ቀርቦ በተሳታፊዎች ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽ የተሰጠ ሲሆን በንቅናቄ መድረኩ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮናስ አለማየሁ ፣ የብሄራዊ መታወቂያ ፕሮግራም ጽ/ቤት አስተባባሪ አቶ ዮዳሄ አርአያስላሴ ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ሀላፊ አቶ ዲናኦል ጫላ ፣ የክፍለ ከተሞች ትምህርት ፅ/ቤት ሃላፊዎች ፣ የግል ትምህርት ቤት ርዕሳነ መምህራንና ጉዳዮ የሚመለከታቸዉ አካላት ተገኝተዋል::

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

Imo: - https://s.channelcom.tech/vlWdNr?from=TG
What Sapp: - https://whatsapp.com/channel/0029VaHFiBpA2pLF0lLslK2D
flickr :- https://www.flickr.com/photos/197652854@N04/
You Tube: https://www.youtube.com/@addisababaeducationbureau9728
TikTok፡- https://www.tiktok.com/@aaeducationbureau
Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau
Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc
Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication
Blog: - http://www.aacaebc.wordpress.com/
Instagram: - https://www.instagram.com/aacaeb/
Website: - aaceb.gov.et
Email;- aacaebc@gmail.com

Показано 10 последних публикаций.