✞ሳር ቅጠሉ ሰርዶው✞
ሳር ቅጠሉ ሰርዶው ሰንበሌጥ ቄጤማው
በዚያች ቀን በዚያች ወር ለምልሞ የነበረው
በእልልታ ዘመሩ በደስታ ተሞልተው
ጌታ መወለዱን የምስራች ሰምተው
እረኝነት ትንሽ የወራዳ ግብር
ብሎ ሰው በልማድ ደንግጎ ነበር
የብዙ ሰው ራስ መሆኑን እረኛ
ክርስቶስ ሲወለድ ተረዳነው እኛ
አዝ= = = = =
የተነበዩለት ነቢያት በሙሉ
ጌታ ተወለደ የምሥራች በሉ
ሰውን በመውደዱ ሰማያዊው ንጉሥ
ይኸው ተወለደ እኛን ለመቀደስ
አዝ= = = = =
የሩቅ ምስራቅ ሰዎች ሰብአ ሰገል ሰምተው
ሊሰግዱለት መጡ በኮከብ ተመርተው
ዕጣንና ከርቤ ወርቁንም አመጡ
እንደየ ስርአቱ እጅ መንሻ ሰጡ
አዝ= = = = =
ስለተወለደ መድኅን የእኛ ተስፋ
በደል ተወገደ ኃጢአትም ጠፋ
መዝሙር
ዲያቆን መገርሳ በቀለ
"አንቺም ቤተ ልሔም ኤፍራታ ሆይ፥ አንቺ በይሁዳ አእላፋት መካከል ትሆኚ ዘንድ ታናሽ ነሽ፤ ከአንቺ ግን አወጣጡ ከቀድሞ ጀምሮ ከዘላለም የሆነ፥ በእስራኤልም ላይ ገዥ የሚሆን ይወጣልኛል።"
ሚክ ፭፥፪
╭══•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ══╮
@yamazemur_getemoche
╰══•ೋ•✧๑♡๑✧• ══╯
ሳር ቅጠሉ ሰርዶው ሰንበሌጥ ቄጤማው
በዚያች ቀን በዚያች ወር ለምልሞ የነበረው
በእልልታ ዘመሩ በደስታ ተሞልተው
ጌታ መወለዱን የምስራች ሰምተው
እልል በይ ቤተልሔም ሃሌ ሃሌሉያ
የፍቅር የሰላም ነሽና ገበያ(፪)
እረኝነት ትንሽ የወራዳ ግብር
ብሎ ሰው በልማድ ደንግጎ ነበር
የብዙ ሰው ራስ መሆኑን እረኛ
ክርስቶስ ሲወለድ ተረዳነው እኛ
አዝ= = = = =
የተነበዩለት ነቢያት በሙሉ
ጌታ ተወለደ የምሥራች በሉ
ሰውን በመውደዱ ሰማያዊው ንጉሥ
ይኸው ተወለደ እኛን ለመቀደስ
አዝ= = = = =
የሩቅ ምስራቅ ሰዎች ሰብአ ሰገል ሰምተው
ሊሰግዱለት መጡ በኮከብ ተመርተው
ዕጣንና ከርቤ ወርቁንም አመጡ
እንደየ ስርአቱ እጅ መንሻ ሰጡ
አዝ= = = = =
ስለተወለደ መድኅን የእኛ ተስፋ
በደል ተወገደ ኃጢአትም ጠፋ
መዝሙር
ዲያቆን መገርሳ በቀለ
"አንቺም ቤተ ልሔም ኤፍራታ ሆይ፥ አንቺ በይሁዳ አእላፋት መካከል ትሆኚ ዘንድ ታናሽ ነሽ፤ ከአንቺ ግን አወጣጡ ከቀድሞ ጀምሮ ከዘላለም የሆነ፥ በእስራኤልም ላይ ገዥ የሚሆን ይወጣልኛል።"
ሚክ ፭፥፪
╭══•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ══╮
@yamazemur_getemoche
╰══•ೋ•✧๑♡๑✧• ══╯