💍የጋብቻ ዓላማ💍
ይህ ምስጢር ታላቅ ነው እንዳለው መጽሐፍ
መኝታውም ንጹሕ የለበትም እድፍ(፪)
እውቀትን ጥበብን ጎናጽፎት ለአዳም
ሁሉን እንዲገዛ አሰልጥኖት በዓለም
ከጎኑ አጥንት ወስዶ በረቂቅ ምስጢሩ
አስማምቶ ፈጠራት ሔዋንን ለክብሩ(፪)
አዝ= = = = =
ዘርን ለመተካት ትውልድ እንዲቀጥል
በትዕዛዘ አምላክ ከአብራክ የሚከፈል
በሕግ እና ሥርዓት በቤቱ ለኖሩት የተሰጠ ጸጋ የምሥጢር አንድነት (፪)
አዝ= = = = =
በጸሎት ለመትጋት በአንድነት ተባብሮ መንግሥቱን ለመውረስ ሕጉንም አክብሮ
ከዝሙት እርቆ ሕይወትን ለመምራት
ፈጣሪ ለሰው ልጅ ያበጀው ሥርዓት(፪)
አዝ= = = = =
በምድራዊ ኑሮ በመውጣት መግባቱ
እየተረዳዱ በአንድ እንዲበረቱ
የቤተክርስቲያንን ሥርዓት ጠብቀው
ለክብር እንዲበቁ የተሰጠ ሕግ ነው(፪)
አዝ= = = = =
ዘወትር ይታወጅ የጋብቻ ዓላማ
ሙሽሮች ልበሱ ፍቅርን እንደ ሸማ
የነፍስ ዋጋን ትተን ለሥጋ በማድላት
ከመንገድ እንዳንርቅ እንትጋ ለጸሎት(፪)
መዝሙር
በማኅበረ ቅዱሳን
"...ስለዚህ ሰው አባቱንና እናቱን ይተዋል ከሚስቱም ጋር ይተባበራል ሁለቱም አንድ ሥጋ ይሆናሉ።ይህ ምሥጢር ታላቅ ነው፥"
ኤፌ ፭፥፴፪
╭══•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ══╮
@yamazemur_getemoche
╰══•ೋ•✧๑♡๑✧• ══╯
ይህ ምስጢር ታላቅ ነው እንዳለው መጽሐፍ
መኝታውም ንጹሕ የለበትም እድፍ(፪)
እውቀትን ጥበብን ጎናጽፎት ለአዳም
ሁሉን እንዲገዛ አሰልጥኖት በዓለም
ከጎኑ አጥንት ወስዶ በረቂቅ ምስጢሩ
አስማምቶ ፈጠራት ሔዋንን ለክብሩ(፪)
አዝ= = = = =
ዘርን ለመተካት ትውልድ እንዲቀጥል
በትዕዛዘ አምላክ ከአብራክ የሚከፈል
በሕግ እና ሥርዓት በቤቱ ለኖሩት የተሰጠ ጸጋ የምሥጢር አንድነት (፪)
አዝ= = = = =
በጸሎት ለመትጋት በአንድነት ተባብሮ መንግሥቱን ለመውረስ ሕጉንም አክብሮ
ከዝሙት እርቆ ሕይወትን ለመምራት
ፈጣሪ ለሰው ልጅ ያበጀው ሥርዓት(፪)
አዝ= = = = =
በምድራዊ ኑሮ በመውጣት መግባቱ
እየተረዳዱ በአንድ እንዲበረቱ
የቤተክርስቲያንን ሥርዓት ጠብቀው
ለክብር እንዲበቁ የተሰጠ ሕግ ነው(፪)
አዝ= = = = =
ዘወትር ይታወጅ የጋብቻ ዓላማ
ሙሽሮች ልበሱ ፍቅርን እንደ ሸማ
የነፍስ ዋጋን ትተን ለሥጋ በማድላት
ከመንገድ እንዳንርቅ እንትጋ ለጸሎት(፪)
መዝሙር
በማኅበረ ቅዱሳን
"...ስለዚህ ሰው አባቱንና እናቱን ይተዋል ከሚስቱም ጋር ይተባበራል ሁለቱም አንድ ሥጋ ይሆናሉ።ይህ ምሥጢር ታላቅ ነው፥"
ኤፌ ፭፥፴፪
╭══•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ══╮
@yamazemur_getemoche
╰══•ೋ•✧๑♡๑✧• ══╯