ዲያቆን ያረጋል አበጋዝ


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: не указана


This channel is not operated by Deacon Yaregal Abegaz- ይህ ገጽ የሚንቀሳቀሰው በዲ/ን ያረጋል አበጋዝ አይደለም
https://youtube.com/@yaregalabegaz?si=1f5NHTaQ2l2LbxWQ
“ዕለት ዕለት የሚከብድብኝ የአብያተ ክርስቲያናት ሁሉ አሳብ ነው።”
— 2ኛ ቆሮ 11፥28

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
не указана
Статистика
Фильтр публикаций


Репост из: ማኅበረ-መድኃኔዓለም
👉 ©የነነዌን ጾም ማሳለጫችን ይኹን!!

#የምህረት በር
  በ ቃኘው ወልዴ


ንስሐን [በአንጻረ-ሕዝበ-ነነዌ] አጥብቆ ሰባኪ ፣ መንፈሳዊነት ለሚጎረብጠው መንቻካ ልብ አለዛቢ ዘይት ፣ መንፈሳዊ ቁመናን ከራስ ጠጉር እስከ እግር ጥፍር በዓይነ ሕሊና የሚከስት መስታወት ፣ የእግዚአብሔርን ምሕረት እና የእኛን ምንነት መሳ ለመሳ እያሳየ ነፍስን ኧረ ንቂ እያለ ወትዋች......
መጽሐፍ #የምሕረት_በር!
የነነዌን ጾም ማሳለጫችን ይኹን!!

ከተጣልኹበት ሰማኝ!!
‹‹... ተጣልኹ ፣ እርሱም ከተጣልኹበት ከጥልቁ ሰማኝ ፣ ሞት በሲኦል መካከል አሳለፈኝ ፣ አንተ ግን ጠበቅኸኝ፡፡ ባሕር ከበበኝ አንተም ያለ መቅዘፊያ ጠበቅኸኝ፡፡ አንተ በጥልቁ ቆለፍኽብኝ ፣ ወደ ባሕሩም ጣልኸኝ፡፡ ወደ ባሕሩ ጥልቅ ወረድኹ ፤ እሞት ዘንድ ግን አልተውኸኝም፡፡ ሞት ሰለቀጠኝ ፣ አንተ ግን በአፉ ውስጥ ሕያው አድርገኽ አኖርኸኝ፡፡ ምንም እንኳን ውኃው ቢሸፍነኝም ፥ እታፈን ዘንድ ግን አልተውኸኝም፡፡ ዳሩ ግን መደነቅ ያዘኝ! ህየንተ ሞት ሕይወት ከፍ ከፍ አደረገኝ! ተስፋዬ ሙሉ ለሙሉ ሲሟጠጥ አንተ መለስኸኝ፡፡ ስለዚኽ ከጥልቁ ባሕር አንደበቴ በብዙ አመሰገነኽ ፤ ከባሕሩ ጠለልም በደስታ ለገናናው ስምኽ ዘመርኩልኽ!🙏 ጌታ ኾይ፥ በኢየሩሳሌም ባለው ታላቅ ቤተ መቅደስ በታቦቱ ተውኩኽ [ከአንተ ተለይቼ ወጣኹ] ፣ ነገር ግን በመሬት ሥር በጥልቁ ለእኔ መንገድን ስታዘጋጅልኝ አገኘኹኽ! አንተ ከውኆች በላይና በታች ፣ በእርሱ ውስጥና ከርሱ ወዲያም በምልዓት አለኽ፡፡ አድባራት ፣ ቀላያት ፣ አቅጣጫዎች ኹሉም ያለማቋረጥ ያለመታከት ያመሰግኑኻል!! ...»
[የምሕረት በር፣ ገጽ 261]
መጽሐፉን በ፦ግዮን መጻሕፍት ያገኙታልhttps://t.me/GhionBookStore1623








The River Of Fire - Doctor Alexandre Kalomiros.pdf
4.7Мб
'The River Of Fire - Doctor Alexandre Kalomiros.pdf'


ስጋ እና ደሙ የምንወስደው ለመታሰቢያ ይሁንላችሁ ነው ያለው እንጂ አማናዊ አይደለም የሚሉ አሉ እንዴት ይታያል?

ቃል ኪዳን በነገረ ድህነት እንዴት ይታያል?

በዲያቆን ያረጋል አበጋዝ


Репост из: ቤተ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
“ላገቡት” የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ምክር

ባልና ሚስት አንድ መኾናቸውን ብዙ ጊዜ ስለ ተማራችሁት እርሱን አልደግምላችሁም፡፡ ከዚህ ተነሥቼ ግን ጥያቄ ልጠይቃችሁ፦ ከሰውነታችሁ ውስጥ አንዱ ሕዋስ ቢታመም ቆርጣችሁ ትጥሉታላችሁን? ከሕመሙ ይፈወስ ዘንድ የምትጥሩ አይደላችሁምን? ለትዳር አጋራችሁም እንደዚህ መኾን አለባችሁ፡፡ እንደዉም'ኮ፥ ከሰውነታችሁ ሕዋስ ውስጥ ያለው በሽታ አንዳንዴ ላይድን ይችላል፡፡ የትዳር አጋራችሁ ግን፥ ምንም ክፉ ቢኾንም ሊለወጥ ይችላል፡፡ በሰውነታችን ላይ የሚኖረው አንዳንዱ ችግር ለምሳሌ ልምሾ እጅ ወይም እግር ሥራ መሥራትን ሊከለክለን፣ በሌላዉ የሰውነታችን ክፍል ላይ ጫና ሊያሳድርብን ይችላል፤ ነገር ግን ይበልጥ እንክብካቤ እናደርግለታለን እንጂ ቆርጠን አንጥለዉም፡፡ ታዲያ መዳን ለማይችለው ሰውነታችን ይህን ያህል እንብካቤ እያደረግንለት ሳለ፥ የመዳን (የመለወጥ) ዕድል ያለው አካላችንን (ባለ ትዳራችንን) መቁረጥ (መፍታት) እንደ አማራጭ ማስቀመጣችን እንዴት ብናብድ ነው?








Репост из: ቤተ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
አንተ ሰው እስኪ ንገረኝ!

አንድን የሥጋ ቁስል ለመፈወስ ለእያንዳንዱ ሰው ከባድ ነው፤ የነፍስን ቁስል መፈወስ ግን ለኹሉም ቀላል ነው፡፡ የሥጋ ቁስል ለመፈወስ መድኃኒት ብሎም ገንዘብ ያስፈልጋል፤ ነፍስን ለመፈወስ ግን ቀላል ብሎም ወጪን የማይጠይቅ ነው፡፡ ሥጋን ከዚያ ከሚያሰቃይ ቁስሉ ለመፈወስ አድካሚ ነው፡፡ ምክንያቱም በቀዶ ጥገና ምላጭ መቀደድ አለበት፤ መራራ መድኃኒቶችም ሊጨመሩበት ይገባል፡፡ ነፍስን ለመፈወስ ግን እንዲህ ዓይነት ነገር አያስፈልግም፡፡ ፈቃደኛ መኾን ብቻ በቂ ነው፤ ፍላጎቱ ካለ ኹሉንም ነገር ለማድረግ ቀላል ነው፡፡ የእግዚአብሔር መግቦቱም እስከ አሁን ድረስ ይህ ነው፡፡ ሥጋ ቢቆስል ያን ያህል ከባድ ጉዳትን አያመጣብንም፤ ምክንያቱም ምንም ባንታመምም እንኳን ሞት መጥቶ ይህን ሥጋችን ያፈርሰዋል፤ ያበሰብሰዋልምና፡፡ ነፍሳችን ብትታመም ግን ጉዳቱ ብዙ ነው፡፡ እግዚአብሔር የነፍስን ሕመም ለመፈወስ መድኃኒቱ ቀላል፣ ምንም ወጪና ስቃይ የሌለበት ያደረገውም ስለዚሁ ነው፡፡ ታዲያ ምንም እንኳን በሕመሙ ምክንያት የሚያገኘን ጉዳት ያን ያህል ብዙ ባይኾንም የገንዘብ ወጪን የሚጠይቀው፣ ሐኪም የሚያስፈልገው፣ ብዙ ስቃይ ያለበት ሥጋችን ሲታመም እርሱን ለማከም እጅግ የምንደክም ኾነን ሳለ፥ እጅግ ብዙ ጉዳት የሚያመጣውን፣ እርሱን ለመፈወስ ወጪ የማይጠይቀውን፣ ለማስታመም ሌሎች ሰዎች የማያስቸግረውን፣ እንደ ምላጩና እንደ መራራ መድኃኒቱ ስቃይ የሌለበትን ይልቁንም ከእነዚህ አንዱስ እንኳን ሳይፈልግ በእኛ ኃይል ባሉ ምርጫና ፈቃድ ብቻ መዳን የሚችለውን፣ ይህን ማድረግ ሳንችል ስንቀርም ከባድ ፍርድና ቅጣት ስቃይም እንደሚያገኘን በእርግጥ እያወቅን የነፍሳችንን ቁስል ችላ የምንል ከኾነ ሊደረግልን የሚችል ምሕረት እንደ ምን ያለ ምሕረት ነው? እኮ የምናገኘው ይቅርታ እንደ ምን ያለ ይቅርታ ነው?

(ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ - ትምህርት በእንተ ሐውልታት መጽሐፍ #በገብረ_እግዚአብሔር_ኪደ የተተረጎመ)


Репост из: ቤተ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
አበው ስለ #እመቤታችን_ዕረፍት እንዲህ አሉ፦

"ሌሎች በድንግልና የኖሩ ሴቶች "ለሞት የሚሆኑ ልጆችን አንሰጥህም" በማለት ሞትን ተቃወሙት፡፡ ድንግል ማርያም ግን አንድ ልጅ በመውለድ በልጅዋ ሞት ራሱ እንዲሞት አደረገችው፡፡ ከዐለት ጋር እንደተጋጨ የተፈረካከሰው በማሕፀንዋ ፍሬ ነውና ሞት ወደ እርስዋ ሲቀርብ ተብረከረከ።"
#ቅዱስ_ጎርጎርዮስ_ዘኑሲስ

"ልጃቸው ተሰብስበው ወዳሉበት መጥታለችና አዳምና ሔዋን ዛሬ ደስ አላቸው። በዚህች ቀን ታላቁ ዳዊት በራሱ ላይ የተዋበ አክሊል የደፋችለትን ሴት ልጁን አይቶ ደስ አለው። በዚህች ቀን ነቢዩ ኢሳይያስ ትንቢት የተናገረላት ድንግል ወደ ሙታን ሥፍራ ልትጎበኘው መጥታለችና ደስ አለው። በዚህች ቀን ብርሃን ሲበራባቸው አይተዋልና ነቢያት ሁሉ ከመቃብራቸው ራሳቸውን ቀና አደረጉ። አርያም በጣፋጭ የመላእክት ዝማሬ ተሞላ፣ ምድር ደግሞ ኀዘንን በተሞሉ በሐዋርያት ለቅሶ ተሞላች፡፡ ሙታንም ሕያዋንም ትርጉሙን ሊገልጹት በማይችሉት [የተለያየ] ዜማ ሰውና መላእክት በዚያች ዕለት አብረው ጮኹ።"
#ቅዱስ_ያዕቆብ_ዘሥሩግ

"የቃሉ አገልጋዮችና ምስክሮች የነበሩት ሐዋርያት በሥጋ የወለደችውን የእናቱን ዕረፍትና እርስዋን የሚመለከቱ የመጨረሻዎቹን ምሥጢራትም ማየት ነበረባቸው፡፡ ይህም የሆነው የክርስቶስ የዕርገቱ የዓይን ምስክሮች እንደሆኑ ሁሉ የወለደችውም እናቱ ወደዚያኛው ዓለም ለሸጋገርዋ ምስክሮች መሆን ስላለባቸው ነው።"
#ቅዱስ_ዮሐንስ_ዘደማስቆ

(በ Deacon Henok Haile የተሰበሰበ)


አስተርዮ ማርያም

በዘመነ አስተርዮ የጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መገለጥ የሆነበትና የአምላካችን አንድነትና ሦስትነት የተገለጠበት ብቻም ሳይሆን በጥር ፳፩ የከበረች እናቱ ቅድስት ድንግል ማርያም የዕረፍት ቀን በመሆኑ “አስተርዮ ማርያም” በማለት በዓልን አናደርጋለን፡፡

የአምላክ እናት እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በዚህ ምድር ላይ ፷፬ ዓመታትን ከኖረች በኋላ መንፈስ ቅዱስ ባስገነዘባት መሠረት በክብር ዐርፋለች፡፡ የዚህን ዓለም መከራና ሥቃይ ለሰዎች ድኅነት የተቀበለችው ክብርት እናታችን በሥጋ ብትሞትም እንደ ልጇ ደግሞ በትንሣኤዋ ተነሥታለች፤ ይህም የሆነው በተቀደሰች ዕለት ነሐሴ ፲፮ ነው፡፡

እመ ብርሃን ከእናትና ከአባቷ ጋር ሦስት ዓመት፣ በቤተ መቅደስ ፲፪ ዓመት፣ ከተወዳጁ ልጅዋ ጋር ፴፫ ዓመት ከሦስት ወር፣ ከጌታችን ዕርገት በኋላ ከወንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስ ጋር ፲፭ ዓመት፣ በድምሩ ፷፬ ዓመት በዚህ በኃላፊው ዓለም ኖራ ጥር ፳፩ ቀን በ፵፱ ዓመተ ምሕረት በክብር ዐርፋለች፡፡

ክርስቲያኖች በሙሉ ይህንን በዓል ልናከብር ይገባልና ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ሥርዓትን ሠርታልናለች፡፡ “አስተርዮ ማርያም” በሕዝበ ክርስቲያን ዘንድ የሚከበር በዓል በመሆኑ በሀገራችን ኢትዮጵያ እና በመላው የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት ማኅበረሰብ ዘንድ በድምቀት ይከበራል፡፡ በዓሉን የምናከብረውም የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን ከዚህ ዓለም ድካም ማረፍ በማዘከር ብቻ ሳይሆን አማላጅነቷና ተረዳኢነቷን በማሰብና ተስፋ በማድረግ ነው፡፡

ስለዚህም እመ ብዙኃን እናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ዐሥራት ሀገሯን ኢትዮጵያን እንድታስባት፣ ለእኛም ለሕዝቦቿ ሰላምን፣ ፍቅርንና አንድነትን ታሰጠን እንዲሁም ለነፍሳችን ድኅነትን ትለምልን ዘንድ ዕረፍቷን መዘከር ይገባል፡፡

የአምላካችን እግዚአብሔር ቸርነት፣ የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነትና ተረዳኢነት አይለየን፤ አሜን!!!

#ማህበረ_ቅዱሳን


Репост из: ማኅበረ ቅዱሳን ዋናው ማእከል
''ቦሩ ሜዳ'' የፊት ለፊት የጥያቄና መልስ መድረክ

''ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ለምን የአዋልድ መጻሕፍትን ትጠቀማለች ?''

“ቦሩ ሜዳ” በማኅበረ ቅዱሳን ወርኃዊ የስብከተ ወንጌል ጉባኤ ላይ

ቀን፡- ጥር 25/2017 ዓ/ም
ከቀኑ 7፡30 ጀምሮ

በጠቅላይ ቤተ ክህነት አዳራሽ

እርስዎም ከወዳጅ ዘመድዎ ጋር በመገኘት ከአዋልድ ማጻሕፍት ጋር ተያይዞ ያለዎትን ጥያቄ በማንሳት ምላሽ ያገኙ ዘንድ ተጋብዘዋል፡፡


Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
ፕሮቴስታንትች የገድል መጽሀፍ ይጽፋሉ፣ ይጠቀማሉ

#ዲያቆን_ያረጋል_አበጋዝ




Репост из: ንሥር መጻሕፍትና የጽሕፈት መሣሪያ (Eagle Books and Stationery)
ዜና ድጋሚ ኅትመት !

ሳይንስ እና ሃይማኖት

..✍ሳይንስ የሰው ልጅ ከእግዚአብሔር የተሰጠውን አዕምሮ ተጠቅሞ ያስገኘውና በዚህ ዓለም ያለውን የኑሮ ድካም ማቅለያው የዕውቀት ዘርፍ ሲሆን ሃይማኖት ደግሞ ከአምላኩ ከእግዚአብሔር ጋር የሚያገናኘው መንገድ ነው። ነገር ግን የሳይንስን ውሱንነት ያልተረዱ ሰዎች ሃይማኖትን በሳይንሳዊ ዕውቀት ለመተንተን ሲሞክሩና ወደ ተሳሳተ ግንዛቤ ሲያመሩ ይስተዋላል። በሌላ መልኩ ደግሞ ሳይንስ ለመንፈሳዊ ሰዎች እርባና የሌለው ነው ብለው የሚያምኑም አሉ።
ይህንን በተመለከተ ለሚነሱ ጥያቄዎችና ፍልስፍናዊ አስተያየቶች፣ ጸሐፊው መምህር ያረጋል አበጋዝ፣ በዚህ መጽሐፉ ከሳይንስና ከሃይማኖት ጋር በተገናኙ ፍልስፍናዊ አስተሳሰቦች ዙሪያ ሰፊ ጥናት በማድረግ ከጥልቅ ትንታኔ ጋር አቅርቦልናል። ስለሆነም መጽሐፉን አንብበን የተሻለ ግንዛቤ እንድናገኝና እንድንጠቀምበት እየጠየቅኩ፣ ለመምህር ያረጋል ዕድሜና ጤናን ለእናንተ ለአንባብያን ደግሞ መልካም ንባብ እንዲሆንላችሁ እመኛለሁ።

ቀሲስ ሰሙ ምትኩ (ፕሮፌሰር)
ቦትስዋና የሳይንስና ቴክኖሎጂ ኢንተርናሽናል ዩኒቨርሲቲ




  ይህ መንፈሳዊ እና ሳይንሳዊ እሳቤዎችን የተነተነ በግሩማን ሐሳቦች የታጨቀው [የተሞላው]  በመምህረ ቤተክርስትያን ዲያቆን ያረጋል አበጋዝ የቀረበ ጥዑም ማዕድ[መጽሐፍ ]  ለ ሁለተኛ ጊዜ የታተመ ሲሆን በግዮን መጻሕፍት  ያገኙታል።# ግዮን መጽሐፍት ለመላው ከሀገር ውጪ እና ሀገር ውስጥ ለምትገኙ አንባብያን  በDHL እና በEMS እንዲሁም የ Delivery አገልግሎት በመስጠት መጻሕፍትን ተደራሽ እናደርጋለን ።

ይደውሉልን !📞፦0913083816
                      ፦0912198891
   https://t.me/GhionBookStore1623


Репост из: ማኅበረ ቅዱሳን ዋናው ማእከል
ስለሆነም በተደጋጋሚ እየተፈጸሙባት የሚገኙትን እነዚህን እኩይ ተግባራት ከዚህ በላይ በዝምታና በትዕግስት ማለፍ መንፈሳዊ ተልዕኮዋን በአግባቡ እንዳትወጣ የሚያደርጋት ከመሆኑም በላይ መብቷን በእጅጉ የሚጋፋ፣ጥንታዊያን አባቶች ለሥርዓተ አምልኮ መፈጸሚያ ሲጠቀሙባቸው የነበሩና በትውልድ ቅብብሎሽ አሁን ያለው ትውልድ የተረከባቸው ንዋያተ ቅድሳቶቿን አደጋ ላይ የሚጥል ሁኔታ ከመፈጠሩም በላይ በሥርዓተ አምልኮዋ ላይ በማላገጥ በምዕመናን ዘንድ ቁጣ እንዲቀሰቀስ የሚያደርጉ በርካታ ተግባራት እየተፈጸሙ በመምጣታቸው ምክንያት እነዚህ እኩይና ጸብ አጫሪ ተግባራት ሕጋዊ እልባት እንዲያገኙ ማድረግ የግድ የሚልበት ደረጃ ላይ ደርሳለች።

ስለሆነም ቅድስት ቤተክርስቲያናችን ጉዳዩን በልዩ ሁኔታ ማጥናት፣መከታተልና ሕግን መሰረት ያደረገ መፍትሔ እንዲያገኙ ማድግ አስፈላጊ ሆኖ ስላገኘችው ወቅታዊ ሁኔታውን በዝርዝር በማጥናት ተቋማዊ እልባት የሚያገኝበትን መንገድ የሚያጠና ኮሚቴ ተቋቁሞ ወደ ሥራ እንዲገባ ያደረገች ሲሆን የቤተ ክርስቲያናችን የሕግ አገልግሎት መምሪያም በሕግ አግባብ ተጠያቂነትን በማረጋገጥ ፍትሕ ማግኘት የሚቻልበትን ሁኔታ ለመፍጠር አስፈላጊውን መረጃ በማሰባሰብና በማደራጀት ክስ መመስረት የሚያስችለውን ሁኔታ በማመቻቸት ወደ ተግባር ለመለወጥ በዝግጅት ላይ ይገኛል።

ከዚህ ጎን ለጎንም ከፍ ሲል እንደተገለጸው በጠቅላይ ቤተክህነት ከሚገኙ መምሪያዎች መካከል ጉዳዩ በቀጥታ የሚመለከታቸውን መምሪያዎች በማካተት የተቋቋመው ኮሚቴም ዝርዝር ጥናቶችን በሚገባ በማጥናትና ችግሮቹን ለይቶ ከመፍትሔ ሀሳብ ጋር በአጭር ጊዜ ውስጥ በማቅረብ በቤተክርስቲያኒቱ ማዕከላዊ አስተዳደር አማካኝነት ተቋማዊ አቋም የሚወሰድበትና በቅዱስ ሲኖዶስ ደረጃ የማያዳግም መፍትሔ የሚሰጥበትን ሁኔታ ለማመቻቸት የሚያስችል ሥራ በመሥራት ላይ መሆኑን እየገለጸች በሁለቱም ዘርፎች የተገኙ ውጤቶችን በተመለከተ በተከታታይ ለሕዝበ ክርስቲያኑ እንዲገለጽ የምታደርግ መሆኑን ከወዲሁ እያስታወቀች በጉዳዩ ዙሪያ ሙያዊ ድጋፍ ለመስጠት ፈቃደኛ የሆኑ ምዕመናንና ምዕመናት በተቋቋመው ኮሚቴ አማካኝነት የሚደረግላቸውን ጥሪ ተቀብለው ለቤተክርስቲያናችን መብት መከበር የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ እናት ቤተክርስቲያን ጥሪዋን ታቀርባለች።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን
መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት
አዲስአበባ -ኢትዮጵያ
ጥር ፲፯ቀን ፳፻ ፲ወ፯ ዓ.ም


Репост из: ማኅበረ ቅዱሳን ዋናው ማእከል
የቤተክርስቲያንን መብትና ጥቅም ለማስከበር እና የሕግ ተጠያቂነትን ለማረጋገጥ በጥብቅ እየተሰራ ነው።

ጥንታዊት፣ታሪካዊትና ዓለም አቀፋዊት የሆነችው የኢትዮጵያ ኦርቶዶከስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን መንፈሳዊ አገልግሎቷን ለማስፋፋት በምታደርጋቸው እንቅስቃሴዎች ሁሉ የሌሎችን መብትና ጥቅም ባለመንካት በትዕግሥትና በማስተዋል የምትጓዝ አገራዊ ኃላፊነት የሚሰማት ሰላምን አብዝታ የምትሰብክ መንፈሳዊት ተቋም መሆኗ ይታወቃል።

ቤተክርስቲያናችን ሥርዓተ አምልኮቷን ለማስፋፋት በተጓዘችባቸው አያሌ ዓመታት አገራችን ኢትዮጵያ የራሷ ፊደላትና የራሷ የቀን አቆጣጠር ባለቤት እንድትሆን ያስቻለች፣በሊቃውንቶቿ የመጠቀ እውቀት አማካኝነት የሥነ ጥበብ፣የሥነ ስዕል፣የዕጽዋትና የጠፈር ምርምርና ጥናቶችን በማከናወን ተጨባጭ ውጤቶችን ለዓለም ያበረከተች ጥንታዊት ተቋም ስለመሆኗም አያሌ ማስረጃዎችን ማቅረብ ይቻላል።

ይሁን እንጂ ይህች ለአገረ መንግስት መመስረትና መጽናት፣ለእውቀት መስፋፋት፣ ለአብሮነት መጎልበት፣ ትውልድን በሥነ ምግባር ቀርጻ ፍቅርና አንድነትን በተግባር የሰበከች እናት ቤተክርስቲያን ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በተለያዩ አካላት መብትና ጥቅሟን የሚነኩ፣በአስተምህሮቿ፣በዕምነቷ፣በንዋያተ ቅድሳቶቿ ላይ መሰረታቸውን ያደረጉና ትዕግስቷን የሚፈታተኑ ክብርና ሉአላዊነቷን የሚዳፈሩ እኩይ የትንኮሳ ተግባራት እየተፈጸመባት ይገኛል።



Показано 20 последних публикаций.