ነፍሴ በእጁ በሆነችው ጌታዬ እምላለሁ ረመዷንን ማግኘት አሏህ በእኛ ላይ ከዋላቸው ትልልቅ ኒዕማዎች ነው።
ይህን እድል (የዘንድሮን ረመዷን) ያላገኙ ስንት ወንድም እህቶቻችን አልፈዋል? እስኪ በዙሪያችን እናስተውል።
አምና ከኛ ጋር ፆመው የነበሩ ወንድሞች የዚህችን ረመዷን መገናኘት እየናፈቁ የተለዩ የሉምን? አሁንስ አልገባንም? አሏህ አሁንም ሌላ እድል ሰጥቶናል እንዴት እንጠቀመው ይሆን?
ምናልባት ይህ ረመዷን የመጨረሻ ረመዷናችን አለመሆኑን ምን አሳወቀን? ዘንድሮም ሚዲያ ላይ ባልረባው ተጥደን፣ እንቅልፍና ምግብ አግበስብሰን፣ ዛዛታና ወሬ አብዝተን እንደዋዛ የምናሳልፈው ረመዷን ነው? በውስጣችን የተለየ ኒያ ከሌለ አሁን እንወስን! ይህ የመጨረሻ ረመዷናችን ሊሆን ይችላል እንደሰለፎቻችን ሰፊውን ጊዜ ለቁርአን እንስጥ።
ሰለፎቻችን ሐታ የዒልም ሐለቃቸውን ትተው ፊታቸውን ወደ ቁርአን ያዞሩ ነበር፡ በየቀኑ በቀን ሁለቴም ያኸትሙ ነበር።
ስለ ኢማን፣ ኢስቲቋማ፣ ስለ ኻቲማችን፣ ስለ ቀብር፣ ስለ ሲሯጥ፣ ስለ መሕሸር፣ ስለ ጀሀነም አብዝተን ለራሳችንም ሆነ ለቤተሰቦቻችን ዱዐእ የምናደርግበት፡ ራሳችንን የምንተሳሰብበት፣ በግልጽም በድብቅ ለሰራናቸው ጥፋቶች ምህረት የምንጠይቅበት፣ ጌታችንን አብዝተን የምናመሰግንበት ታላቁ ወር ከፊታችን ነው። አሁንስ ኒያችንን ጠንከር አናደርግምን?
በዚህች ወርኮነው ቁርአን የወረደልን፣ በዚህች ወርኮነው #ለይለቱል_ቀድር (የመወሰኛይቱ ሌሊት) የምትገኘው።
ይህች ሌሊት (ከብጤዋ ሌሊት ውጭ) ከአንድ ሺ ወር በላይ እንጂ አንድ ሺ ወርን የምትመጥን አይደለም የተባለችው፡ ደረጃዋን በውል የሚያውቃት እርሱ ብቻ ነው።
ليلة القدر #خير من ألف شهر
ሱብሀነሏህ! ይህ አሏህ ለዝች ኡማ ካጎናጸፋት ጸጋዎች ነው ። እኛንስ ለዚህ አህል ካደረገን እንዴት ልናሳልፈው አሰብን?
በአዘቦት ሞባይል ላይ የማዘውተር ልምድ ያለን ወንድም እህቶች በረመዷን ሶሻል ሚዲያ nearly ባንጠቀም የግድ የሚመለከተንን ጉዳይ አክሰስ ለማድረግ ቢሆን እንጂ። እናም በቋሚነት ትምህርት የምትከታተሉ ካልሆነ እና አስገዳጅ ሁኔታ ከሌለ ውድዱን ጊዜ እዚህ ሰፈር ኢንቨስት ባናደርገው።
አሏህ ረመዷንን አግኝተው አምነውና ተሳስበው ከሚፆሙት ያድርገን።
Nb;
ጽሁፉ የቪዲዮው ትርጉም አይደለም፡ ተያያዥ ማንቂያ ስለሆነ አብሮ የተለጠፈ ነው።
ሸይኽ ዐብዱረሕማን ሱደይስ