👉
ዘመቻ ወደ ቲክቶክ ‼️‼️‼️‼️‼️
♨️በቂ ጊዜ ያላችሁ መሻይኾችና ኡስታዞች ሆይ‼️
ከየመስጂዱ እየተገለለና እየተፈናቀለ ያለዉ የአህባሽ መንጋ ቲክቶክ ላይ ተንቀሳቃሽ ምስሎችን እየቆራረጠ፣ መረጃዎችን እየቀላቀለና ያለ አግባብ እየተረጎመ የአህሉሱናዎችን ስም እያጠፋ ወጣቱንም እያሳሳተ የተበከለ አቂዳዉን በሰፊዉ በመርጨት ላይ ስለሆነ በቲክቶኩ አለም መዝመት የግድ ያስፈልጋል።
👉እኛ ቲክቶክን አንጠቀምም ብለን ብንተወዉም ይህ ሀረር ላይ የበቀለዉ የጥፋት ጭፍራ ግን ያለ የሌለ አቅሙን ተጠቅሞ ህዝባችንን በማደናገር ላይ ተሰማርቷል።
♨️አዎ ጉዳዩ ከአሳሳቢነትም በላይ ነዉ‼️
ስለዚህ ጊዜና ብቃቱ ያላችሁ ኡስታዞችና መሻይኾች ይህንን ጥፋት እያየን ዝም ማለታችን
👉1 ኛ ሙንከር ሲስፋፋ እያየን ዝም በማለታችን አላህ ፊት ያስጠይቀናል።
👉2 ኛ አህባሾች ባጢላቸዉን ሲዘሩ እያየን ዝም ስንላቸዉ የዋሁ ህዝባችን እነርሱ የተናገሩት ሀቅ ላይ ስለሆኑ ነዉ። እነዚህ ዝም ያሉት ደግሞ ሀቅን ስላልያዙ ነዉ። የሚል አደገኛ ድምዳሜ ላይ ይደርሳል። እንጂ ሆደሰፊነት ነዉ፣ ወይም ሙስሊሙ ለካፊር መሳለቂያ እንዳይሆን አስበዉ ነዉ ብሎ አይረዳህም።
እናም አማራዉን በአማረኛ፣ ኦሮሞዉን በኦሮሞኛ፣ ስልጤዉን በስልጤኛ፣ ዐረቡን በዐረበኛ አጠቃላይ አጥፊዉ በሚናገረዉና በሚገባዉ ቋንቋ መናገር፣ መርዙን መንቀል፣ ህዝቡን ከጥፋቱ መታደግ፣ ጅህልናዉንና ማምታቻዉን ለህዝብ ማጋለጥ፣ የጥፋት ምላሱን እንድሰበስብና ገዳይ መርዙን እንድዉጥ ማድረግ ኢስላማዊ ግዴታችን ነዉ።
ማሳሰቢያ ‼️
አህባሾችም ላይ ሆነ ሌሎች የተሳሳቱ ወገኖች ላይ መልስ ስንሰጥ መዘንጋት የሌለብን ነገራቶች ይኖራሉ።
ጥቂቶችን ልጥቀስ
① እናስተካክላለን ብለን ሌላ ጥፋት እንዳናስከትል በቂ እዉቀትና መረጃ ላይ ተመርኩዝን መሆን አለበት‼️
② ከቁርአንም ሆነ ከሀዲስ በምናቀርበዉ መረጃ ላይ እርግጠኛ መሆን ግድ ነዉ‼️
③ ለፍዞል ቁርአንንም ሆነ ሌላ ዐረበኛ ቃልን ስናነብ መኻሪጀል ሁሩፍ ላይ እና ዒዕራቡ ላይ ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ ይኖርብናል‼️
③ ቪድዮዉ አሰልቺ እንዳይሆን በተቻለ መጠን አጠር ያለ ቢሆን ይመረጣል‼️
④ እነርሱ ቢያደርጉትም ትምህርቱ ፍፁም ከዉሸት፣ ከስድብና ከዘለፋ የራቀ መሆን አለበት‼️
⑤ መልስ ከተሰጠባቸዉ ወገኖች በኩል ለሚመጣብን አፀፋዊ መልስና ዘለፋ አለመደናገጥና አስገዳጅ ነገር ካልተፈጠረ በስተቀር ጀምሮ አለማቋረጥ‼️
⑥ ግድ ሁኖብን እንጂ ቲክቶክ አስደሳች አለም ስላልሆነ ከሚጋረጡብን የጎንዮሽ ሙንከራቶች እራሳችንን ማራቅና ነፍስያችንን ማሸነፍ‼️
⑦ በየአቅጣጫዉ ለህዝቡ ተደራሽ ይሆን ዘንድ በቲክቶክ የተለቀቁ ትምህርቶችን እንደ ቴሌግራም፣ ፌስቡክ፣ ዋትስአፕ የመሳሳሉ ሌሎች ማህበራዊ ትስስር ገፆች ላይ በሰፊዉ ማሰራጨት‼️
✍ ሙርሰል ሰይድ ጨፌ 30/5/2017
👉ጆይን
https://t.me/murselseid