༆ የፍቅር ክሊኒክ ༆™🥀🌹


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Книги


🔔🔔 ምን ማስተዋወቅ ይፈልጋሉ 🔔🔔❓
📌 የምንሰጣቸው የማስታወቂያ አገልግሎቶች 💸
📱➡️የ ቻናል ማስታወቂያ
📱➡️ የ ሙዚቃ ማስታወቂያ
📱➡️ የ ኮንሰርት ማስታወቂያ
📱➡️የ ድርጅት ማስታወቂያ
📱➡️ የ ሚዲያ ቻናል ማስታወቂያ
📱➡️ትሪትመንቶች እና ሌሎችም የሽያጭ ማስታወቂያዎች ✅📢 በተመጣጣኝ ዋጋ💯💯💯💯💯💯

@Yefiker_clinic98

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Книги
Статистика
Фильтр публикаций


ሁሌ ቤቴንግ መበላት ከሰለቸህ  ይሄን ቻናል ተቀላቀል ሁሌ ነው አሸናፊ እምትሆነው Ethiopia  ውስጥ  ይሄ ብቻ ነው እውነተኛ ቻናል ስለዚ ሳያመልጣህ አሁኑኑ ተቀላቀል




ልብ አንጠልጣዩ "የጠፋው ሬሳ"

              ተከታታይ ትረካ

        
#ምዕራፍ 2 #ክፍል13

.......ወዳለሁበት ሲዋከቡ መጡ ግን የነበርኩበት አልጠበኳቸውም ከመቅፅበት አልጋው ስር ተመለስኩኝ፡፡ የቤቱ ድምድምት ላይ አይጥ ሲርመሰመስ አይተው ነው መሰል "እኚ የተረገሙ ትናንሽ ፍጥረታት" ስትል ሰማሗት ትንሿ ሴትዮ በብስጭት እርር ብላ፡፡

እግዜር እንድኖር ዕድሜን ከቅፅበት እየነጠቀ ከሞት እየተሻማ እየታደገኝ ነው፡፡ "ባላመሰግነውም ምስጉን ሆነው የነፍሴ ጠበቃ ይመስገን" አልኩኝ ለራሴ በድንጋጤ አካሌን ፈልቅቆ ሊወጣ ሚወራጨውን ልቤን ደግፌ፡፡

"አንገቷን በእጅህ ይዘህ ና" ስትል ሰማሗት ትንሿ ሴትዮ ነበረች፡፡ ምን አድርጌያት እንዲህ እንደጠላችኝ እንጃ፡፡ ዳሩ እኔም አልወዳትምና መጥላቷ ግድ አልሰጠኝም፡፡ በህይወት ከተረፍኩ በህይወት እንደማይኖሮ አሳባ እንደሆነ ማወቁ ከኔ የተሰወረ እውነት አልነበረም፡፡ ተከታትለው ሲወጡ ተሰማኝ፡፡ እኔም ጊዜ ሳላጠፋ ዳናዬን ዝግ አድርጌ ዱካቸውን ተከትዬ ወጣሁ፡፡

መንገዳቸው ከመንገዴ አልመግጠሙ እፎይታን ሰቶኛል፡፡ እኔ ወደግራ ስመለስ እነሱ ደግሞ ወደ ቀኝ ነበር የታጠፉት፡፡ አሁን በመሃከላችን ያለው ድንግዝ ለይተው እንዳያዩኝ እንደሚጋርዳቸው እርግጥ ነው፡፡ የሆነ ቦታ ላይ ሶስቱም ጀርባቸውን ለኔ ሰተው ቆመዋል፡፡

በውል ግን ምን እያደረጉ እንደነበር ማወቅ አይቻለኝም፡፡ ቤቱ ከቀድሞው ይልቅ ፈፅሞ ጨልሟልና፡፡ ከእርምጃዎች በሗላ ባርሳ ያለችበት ክፍል ደረስኩ፡፡ ጊዜ ሳላጠፋ የተሳረችበትን ለመበጠስ እንዲረዳኝ ጠረጴዛውን ስቤ እሱ ላይ ወጣሁ፡፡ እጇን በእጄ ይዤ በጥንቃቄ ቆረጥኩላት፡፡ አሁን ከባዱ የአንገቷ እስራት ነው፡፡

ሰንሰለተ አንገቷን ሰርስሮታል፡፡ ቀስ አድርጌ ግንባሯን ደገፍ አደረኩን ወደ ብረቱ አስጠጋሗት፡፡ በጣም ልዝብ ባለ ሁኔታ በማስተዋል ቀስ እያደረኩ መቁረጤን ተያያዝኩት፡፡ ትንሽ ስህተት ብሰራ አንገቷን መሬት ላይ ነው ማገኘው፡፡ ይህ ደግሞ ፈፅሞ መሆን የለበትም፡፡ ሰንሰለቱ አንገቷን ሶስት ጊዜ ዞሮ ተጠምጥሞባታል፡፡ ዙሩን ከመፍታት ይልቅ ሶስቱንም መቆራረጡ እንደሚሻል አውቃለሁ፡፡

ግን ደግሞ ፅልመቱ እየተገዳደረኝ ነው፡፡ የማደርገውን እለይ ዘንድ አልተቻለኝም፡፡ ቢሆንም ጀምሬዋለሁ፡፡ እጄ ፈፅሞ በደም ተጨማልቋል፡፡ ሰንሰለቱም እንደዛው በረጋ ደም ተሸፍኗል፡፡ የሰንሰለቱን ዙር የምለየው ጣቴን ወደ አንገቷ እስራት በስደድ ነው፡፡ ስለቱ እጅግ ቢሆንም ውፍረቱ ግን እምብዛም ነበርና ለመቁረጥ አያስቸግርም ከመማረቱ በቀር፡፡

ሁለቱን ቆርጫቸዋለሁ አንደኛው ግን አንገቷን ሰርስሯት ኖሮ ሊያዘኝ አልቻለም፡፡ ምን ማድረግ እንዳለብኝ አላወኩም፡፡ ግን ደግሞ ከጣቴ የቀጠነ አንዳች መያዣ ያስፈልገኛል፡፡ ለጊዜው መቁረቱን ተውኩትና ብዙ ስለቶች የተቀመጡበትን ጠረጴዛ ወደ መስኮቱ አስጠግቼ በሚዘልቀው ወገግታ ምፈልገውን መምረጥ ተያያዝኩት፡፡ መቀስ መሳይ ረዘም ያለ በቀዶ ጥገና ጊዜ የሰውን ቆዳ ለመያዝ የሚጠቀሙበትን መሳሪያ አገኘሁ፡፡

ግን አሁንም ቢሆን ፅልመቱ እሱን ለመጠቀም አዳጋች ነበር፡፡ የማለዳውን ብርሃን ታምኜ ለይደር ባዘገያት ከንጋት በፊት ሰንሰለቱ አንገቷን ሰርስሮ ይበጥሰዋል እናም አንዳች መላ መዘየድ አለብኝ፡፡ ክፍሉ ውስጥ ወዲህ ወዲያ ተንከላወስኩ፡፡  ትንሽ እንደቆየሁም አንዱ ጥጋት ላይ የጀርባ ቦርሳ አገኘሁ፡፡

እሱን ለመሸከም ሰውነቴ በድካም እና በስቃይ ተብሰክስኮ ነበርና እየጎተትኩ ወደ መስኮቱ ወሰድኩት፡፡ እንደምንም አንስቼ ጠረጴዛው ላይ ያለውን ዘረገፍኩት፡፡ የተለያዩ ልብሶች የሚቀባቡ ነገሮች ጫማዎች እንዲሁም የሚበላ ነገር በውስጡ ይዟል፡፡

ወዲያ ወዲህ እያመሰቃቀልኩ ለኔ ሚረባኝን ማሰሴን ተያያዝኩት፡፡ በድንገት የእጅ ባትሪ አገኘሁ፡፡ ደስታዬ ወደር አልነበረውም አበራሁት ይሰራል፡፡ መሳሪያዎቼን ይዤ ወደ ባርሳ ተጠጋሁ፡፡ ባትሪውን አፌ ውስጥ ከትቼ አንገቷ ላይ እያበራሁ ነፍስ ለማዳን ታተርኩኝ፡፡

ጥንቃቄ ከተሞላው ከደቂቃዎች ፈተና በሗላ ከሰንሰለቱ አንገቷን ነፃ አወጣሁት፡፡ ወገቧ ላይ ያለውን ቀበቶም ፈትቼ ቀስ ብዬ ከብረቱ አላቅቄ እግሬ ላይ ጋደም አደረኳት፡፡ ፀጉሯን እየደባበስኩ ትንሽ ከቆየሁ በሗላ ጠምቷት እንደው ብዬ አስቤ ውሃ ላጠጣት ወለሉ ላይ አስተኝቻት ተነሳሁ፡፡ ከቦርሳው ውስጥ ካገኘሁት ምግብ ጋር ውሃ ነበርና ቀስ አድርጌ አጠጣሗት፡፡ መዋጥ ለሷ ህመሟ ነበር በስቃይ ሁለት ጊዜ ተጎነጨች፡፡ ልብስ ደራረብኩላትና እግሬ ላይ አስተኛሗት እንድታርፍ በማሰብ፡፡

ከደቂቃዎች በሗላ በውጪ በኩል በመስኮቱጋ አንድ ሰው ውልብ ሲል ታየኝ፡፡ "በእግዚአብሔር ስም" አልኩኝ ድምፅ አውጥቼ፡፡ በድጋሜ በመስኮቱጋ ወደ መጣበት ተመለሰ ይህን ትዕይንቱን እየደጋገመ ነፍሴን አስጨነቃት፡፡ ይባስ ብሎ መስኮቱጋ ድንቅር ብሎ ቆመ፡፡

"ማነው" አልኩኝ ለራሴ ሳግ በተቀላቀለበት በሚሰባበር ቃል፡፡ ጥቁር ከመልበሱ በቀር ምንም አልታየኝም፡፡ ቀስ እያለ መስኮቱን ለመክፈት...

ቶሎ ቶሎ እንድለቅላችሁ react 👍 አንበሽብሹኝ

ምዕራፍ 2 .P14...ይቀጥላል.........
            
ከተመቻቹ ÷
                
#𝐑𝐞𝐚𝐜𝐭
                
#𝐂𝐨𝐦𝐦𝐞𝐧𝐭
                
#𝐬𝐡𝐚𝐫𝐞 🙏

    ¶ 𝚈𝙴𝙵𝙸𝙺𝙴𝚁 𝙲𝙻𝙸𝙽𝙸𝙲🥀 ¶™🌐

  📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት! 📱     


ቤቲንግ ይጫወታሉ መበላትስ ሰልችቶታል እንግዲያውንሱ በነፃ ያለምንም ክፍያ በቀን ከ 50-150 odd የሚለቀቅበት ቻናል ልጠቁማቹ ይጠቀሙበታል ቻናሉን ከስር ያሉትን በመንካት ቶሎ ይቀላቀላሉ




ልብ አንጠልጣዩ "የጠፋው ሬሳ"

              ተከታታይ ትረካ

#ምዕራፍ 2 #ክፍል12

....እኔ ወዳለሁበት ክፍል እንደ ሰጋር ፈረስ የሚገሰግሱ የእግር ኮቴዎች ተሰሙኝ፡፡ እገባበት ጠፋኝ እሆነው ነገር ጨነቀኝ፡፡ በገዛ እጄ ወደሞቴ ገስግሼ እንደመጣሁ ነገሬ ሳያስፈልገኝ ለራሴው ገባኝ፡፡ ጊዜ ሳላባክን እሸሸግበት ጥጋት ፍለጋ ያዝኩ፡፡

ምንም አልታየኝም ያለሁበት ደርቄ ቀረሁ፡፡ ተስፋዬ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ እኔን ጥሎኝ ኮበለለ፡፡ አሁን በድኔ ነው ከኔጋ ያለው፡፡ በቆምኩበት ሰከንዳት ተቆጠሩ፡፡ ህይወቴ በዚህ መልኩ ይቋጫል ብዬ አስቤም ይሁን ገምቼም አላውቅም፡፡ ያልጠበቅናቸው ሊሆኑ የጠበቅናቸው ሊቀሩ የህይወት ጉዞ ነውና ቢመርም መዋጥ ነው፡፡ የሰው ልጅ ራሱን የሚጎዳው በመጠበቅ ነው፡፡ የቀጠሩት ሲቀር ያበሳጫል፡፡ ባይቀጥሩትስ ብስጭቱ ቀረ ማለት አይደል፡፡

ነገን ዛሬ የሌለንን እንዲሞላልን ሙላታችንን ስንጠብቅ ሌላ ጎዶሎ ሲታደለን የልብ ስብራት ነው፡፡ ስለጠበቅን እንጂ ሳንጠብቀው ቢቀር ይህ ለኛ ምንድነው?፡፡ "ነገ ጥሩ ይሆናል ይላሉ" ባዮቹ "ቆይ ዛሬ ለምን ጥሩ አይሆንም? ነገ ከዛሬ የተለየ ለራሱ ጥሩነትን ማን ሰጠው? የጊዜ ጥሩ አለ ወይስ ባለጊዜው ጥሩ?" እያልኩ ከራሴ እሟገታለሁ የሞት ጊዜዬ እየተቃረበ ሰመመን ደግሞ ይዞኝ እየመጠቀ፡፡

የዛሬ መጥፎ የነገ ደግሞ ጥሩ የለም፡፡ ጥሩ ነገ አይመጣም ጥሩ ሁሌም አለ፡፡ ነገ መልካም አይደለም ዛሬንም ነገንም መልካም የሚያደርግ ፈጣሪ ዓለማትን በቃሉ ያጸናው እግዜር ብቻ ነው፡፡ ቀኑም አይደለም፣ምሽቱም አይደለም፣ንጋቱም አይደለም ዛሬ ወይ ነገም አይደሉም "እግዚአብሔር ብቻ ነው መልካም" ነገ መልካም ይሆናል ብለህ የቀኑን በጎነት አትጠብቅ "ለቀኑ የራሱ ክፋት ይበቃዋልና" ይላል ታላቁ መፅሐፍ ቅዱስ፡፡

"ከዚ የትም አትርቅም ትርቅም ዘንድ አቅሙ የላትም እንዳገኘሃት አናቷን ለሁለት ክፈለው" የሚል በሚያስገመግም ድምፅ ቁጣ ተቀላቅሎበት የተሰጠ ትዕዛዝ ከሀሳብ ሽልብታ ሰርቆ አወጣኝ፡፡ ድንዛዜዬ ቅቡጭ(ድንገት እልም) አለ፡፡

በነበርኩበት ለሰከንድ ሽራፌ አልቆምኩም ወደ ውስጠኛው ክፍል ሄጄ ከአልጋው ስር ራሴን ሸሸግሁ፡፡ ሶስቱም ተከታትለው ሲገቡ ይታወቀኛል፡፡ ቤቱ ውስጥ በጭንቀት ይሁን በእልህ ከወዲያ ወዲህ ይንጠራወዛሉ፡፡

የወለሉ ቅዝቃዜ ደና የጠገገ ቁስሌን ይመዘምዘው ጀምሯል፡፡ ድምፄን አውጥቼ ባማጥኩት ምነኛ ደስ ባለኝ ግና ቃሌ የሞት ጥሪን እንጂ ለስቃዬ ማስታገሻ አይሆነኝም፡፡ ያ ፀላኢ ሰይጣን አረመኔ አንደበቱ ቀንቶ የማይናገር አደዳ ቢጤ መሰለኝ ቃሎቹ በውል አይለዩም፡፡ ያቺ የከረከሰች አሮጊት የዚ ነብሰ በላ እናት ነች፡፡ ጭካኔውን እንኳ አይታ ያልረገመችው በመግደሉ ምትኮራ የሰው እርግማን ነች፡፡ አቅሙ ይኑረኝ እንጂ ሶስቱንም እገላቸዋለሁ፡፡

የውስጤ የተስፋ ማሾ ውስጤ መቀጣጠል ጀመረ፡፡ እንደምኖር አስቤ ለመግደል መመኘቴ ገረመኝ፡፡ እውነትም የእግዜር እንጂ የቀን መልካም የለውም፡፡

"እቺ ከረከንድ እራሪ ድውይ ትንሽ ሴትዮ መጥፊያዋ በመዳፌ" አልኩኝ ለበቀል ያቆበቆበ ልቤን ተማምኜ፡፡ "የኔ ነፍስ እዚ ክፍል ውስጥ የተከረቸመባት መናኛ ከየትም የበቀለች ወፍ ዘራሽ አስታዋሽ የሌላት የተረሳች መምጫዋ ማይታወቅ ፍጡር አይደለችም እንዲያውም ከስጋና ከደም ፈቃድ ውጪ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ፈቃድ ወደ ምድር የመጣች እንጂ ታዲያ በማን ፍቃድ ከኔ ትለያለች እሱ ያበጃጀውን ያፈርስ ዘንድ ማንስ ይቻለዋል?" አልኩኝ ለራሴ በለሆሳስ፡፡

በደም እና በነፍስ የተገዛች ነፍስ የዋዛ አይደለችም፡፡ እኔ የኔ አይደለሁም ባለቤቴም ዝም ይል ዘንድ ተላላ ሰነፍ ቃሉም ከንቱ አይደለምና ያድነኛል፡፡ በማዳኑ ልክ ሳይሆን ያኔ በከፈለልኝ የፍቅሩ ልክ ተገዝቼለታለሁ፡፡ የመስቀሉ ውለታ ለደካማውና ለሚፈታተነኝ ስጋዬ መዳን የደቀቀ አይደለም ለዘላለማዊቷ እስትንፋሴ እንጂ፡፡

ወደ ጓዳው ዘልቀው አልገቡም ከሳሎን ሆነው ለነፍሰ በላው ነበልባል ጋዝ እየጨመሩ ውስጡ ያቀጣጥሉታል፡፡ ይመስለኛል እሱ ግን እኔን ለመበቀል ከመውተርተር ይልቅ ቅዛዜ ውስጥ ገብቷል፡፡ "ምን ሆነሃል አንድዬ" ከሚለው የትንሿ ሴትዮ ድምፅ ውስጥ ተረዳሁት፡፡ "እቺ ሴት ከዚህ ካመለጠች ሶስታችንም መጥፊያችን ነው ሚስጥራችን ገሃድ መዘርገፉ ነው ተነስ ፈልገህ ገላግላት" ትለዋለች ግሳፄ ባገዘፈው ቃሎቿ ትንሿ ሴትዮ፡፡

እስካሁን እናትየው አንዲትም ቃል አልተነፈሰችም፡፡ "ተዪው ልጄ ተዪው እስቲ እንደው እንደ ሰው ፍጡር ለሰው ማዘን ጀምሮ ይሆን እንዴ ለሱ ብዬ ከተሸሸኩበት ከዚ ከቀረና ክርፋት ከሞላው የነፍስ ዋይታ ካየለበት የሰው አጥንት ከተከሰከሰበት ስፍራ ወጥቼ ጎረቤቶቼ ጋር ልቀላቀል ይሆን እንዴ የማለዳ ፀሃይ እንኳን እኮ ናፈቀኝ ጀምበር ስታሸልብማ አይቻትም አላውቅ ይሄ እኮ ለኔ ህመም ነው ልጄ ሰውነት እየገዛው ከሆነ ብዬ እኮ ነው ተዪው አትቆጪው" አሉ እናትዬው ንግግራቸውን ሳግ እያቆራረጠ የእናትነት አንጀታቸው አላስችል ቢላቸው፡፡

እኔም ቢሆን አሳዝነውኛል ለልጃቸው ብለው የእተጋቱት ያለው የመከራ ፅዋ መራር ነው፡፡ ከንግግራቸው ይህ ሰው ከአመታት በፊት ሰውነት የነገሰበት ሰው ነበር ማለት ነው፡፡ "ታዲያ ምን ጉድ ምንስ ቅፅበት እንደዚ ወዳለ አረመኔነት ቀየረው?" ብዬ ጠየኩኝ መልስ የሚሰጠኝ እንዳለ ሁሉ፡፡

ቀስ ብዬ ከተደበኩበት አልጋ ስር ወጣሁ የሚሆኑትን እና የሚያረጉትን በስውር እመለከት ዘንድ፡፡ በዝግታ ወደ ሳሎኑ መውጫ ጋር ደርሼ መጋለጫው ገለጥ አድርጌ መመልከት ጀመርኩ፡፡ እሱ ከአንዱ ወንበር ላይ ዘርፈጥ ብሎ ቅዝታ ውስጥ ገብቶ ተክዟል እነሱ ግራና ቀኙ ቆመዋል ትንሿ ሴትዮ በእጇ የሆነ አጀንዳ የሚመስል ነገር ይዛለች ምን እደሆነ ለማየት ስንጠራራ ባላንሴን ሳትኩና ከበስተሗላዬ የተደረደሩ ድስቶች ላይ ወደኩ ቤቱ በአንዴ ተወክቦ ፀጥ አለ በዛው ቅፅበት በሶስቱም ወደኔ......

ቶሎ ቶሎ እንድለቅላችሁ react 👍 አንበሽብሹኝ

ምዕራፍ 2 .P13...ይቀጥላል.........
            
ከተመቻቹ ÷
                
#𝐑𝐞𝐚𝐜𝐭
                
#𝐂𝐨𝐦𝐦𝐞𝐧𝐭
                
#𝐬𝐡𝐚𝐫𝐞 🙏

    ¶ 𝚈𝙴𝙵𝙸𝙺𝙴𝚁 𝙲𝙻𝙸𝙽𝙸𝙲🥀 ¶™🌐

  📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት! 📱     

6k 0 12 20 104

ልብ አንጠልጣዩ "የጠፋው ሬሳ"

              ተከታታይ ትረካ

         ምዕራፍ 2 # ክፍል11

.........ራሴን እንዴት እንዳሰብኩት ለኔም ግራ ነው፡፡ ነፍሴን ለማትረፍ ለኔው ብቁ ያልሆንኩ ሰው እሷን ለማዳን እታትራለሁ፡፡ "ሰው መሆን እንዲ ነው" ይለኛል ውስጤ ሊያጀግን እንዳሰበ ሁሉ፡፡ "አዎ ሰው ማለት ከራስ አልፎ ሌላ ሲኖር ነው የተከበሩ የዓለም ሎሬት አፈወርቅ ተክሌ "አንተ ራስህን ሲያምህ ከተሰማህ በህይወት አለህ ማለት ነው፡፡ሌሎች ሲታመሙ አንተ ከተሰማህ አንተ በትክክል ሰው ነህ ማለት ነው" ይላል እናም ልክ ነው በጣም ልክ፡፡

እናም ካለኝ አቅም ይልቅ ሰውነቴ አሸንፎኛል፡፡ ባላድናትም ላድናት ማስናለሁ አልተዋትም፡፡ ስቃዯ ውስጤ ዘልቆ ሲሰማኝ ይታወቃኛል፡፡ የቤቱ ቁር ለጉድ ነው፡፡ ወደ መውጫው ተጠጋሁና ኮሪደሩን አንገቴን አስግጌ ቃኛሁ በማን አለብኝበት ፀጥታ ፍፁም ነግሶበታል፡፡ ግድግዳውን እየታከኩኝ እንደ ድጋፍ ተመርኩዤ አዘግም ጀመር፡፡ የምሄድበትን አውቀዋለሁ ወይ እዛው ቀራለሁ ወይ እመለሳለሁ፡፡ ከዚ ሌላ ምንም ሊፈጠር አይችልም፡፡ ይሄንን አበክሬ አስቤዋለሁ፡፡ በየ አስር እርምጃዎቹ የተለያዩ ክፍሎች ይገኛሉ ክርፋታቸው የከረመ ሬሳ ብስባሽ ቢባል ማጋነን አይሆንም፡፡

የመጀመሪያውን ክፍል አልፌ ሁለተኛውጋ ስደርስ ከአንድ ጠረጴዛ ላይ ከሰውነት ላይ የተለያዩ የሰው አካል ክፍሎች ተሰድረዋል፡፡ በፍጥነት ተራምጄ አለፍኩት አሁን የማያቸውን አረመኔያዊ የሰው ልጅ ስቃዬን ሳይ ለመድኩት መሰል ወይ ደግሞ ያንን ክፉ ለመግደል ስላላመነታሁ አሰጨከነኝ እንደሁ እንጃ እንደበፊቱ አያሸብረኝም፡፡

ጥቂት ክፍሎችን እየቃኘሁ ከተጓዝኩ በሗላ የሴትየዋንና የሴቲቱን ክፍል ከሩቅ ቃኘሁት፡፡ ትኩር ብዬ ተመልክቼ አንዳች እቅስቃሴ በውስጡ አለመኖሩን ተረዳሁ፡፡ ግን ወደክፍሉ ከማምራቴ በፊት የሰዎቹን ሁናቴ ማጤን እንዳለብኝ ተረድቻለሁ፡፡ እነሱ ያሉበት ስፍራ እኔ ካለሁበት በስተጀርባ ካሉት ክፍሎች አንዱ ውስጥ ናቸው፡፡ የትኛው ክፍል እንደሆነ ግን በውል አለየውም፡፡ ሆስፒታሉ ሰፊና ትንሽ ፅልመት የወረሰው በመሆኑ ያደናግረኝ ይዟል፡፡

"እስካሁን እኔን ፍለጋ ስለምን አልመጡም?"ወይንስ እያዘናጉኝ ይሆን?"
አላውቅም ይሄ ለኔ ግድ አይሰጠኝም ከባርሳ ነፍስ ይልቅ፡፡ እኔ የነበርኩበትን ኮሪደር አልፌ በጀርባ ወዳሉት ክፍሎች የሚወስደውን መተላለፊያ ይዤ በዝጋታ እና በንቃት ሁናቴያቸውን ለማጤን ሞከርኩ፡፡ ግን ዘለግ ላለ ግዜ ለራሴ እስኪጨንቀኝ ፀጥ ብለዋል፡፡

ከደቂቃዎች በሗላ ንግግር አይሉት መልጎምጎም የሆነ የጎረምሳ ድምፅ ይሰማል፡፡ የዛኔ አረመኔ ድምፅ ነው ስቃይ ምን ማለት እንደሆነ በትንሹ ቢሆን እየተጎነጨው ነው፡፡ ጊዜ ሳላጠፋ በቀጥታ ወደ ክፍሉ አመራሁ፡፡ እግሬ ፈፅሞ ሰላም እየነሳኝ ነው፡፡ ቢሆንም ባልችም እችላለሁ፡፡ እልህ እያንጨረጨረኝ በቀል ውስጤን እያነደደ ነው፡፡

በሩን በርግጄ ገባሁ በቀጥታም መቁረጫውን አገኝ ዘንድ ከወዲያ ወዲህ ባተትኩ ግን አልነበረም፡፡ እቃዎቹን አተረማመስኳቸው የትም አልነበረም፡፡ በጣም ተበሳጨው፡፡ ወደ ሌላኛው ክፍል ገባሁ ሁለት አልጋ የያዘ ነበር፡፡ይመስለኛል የሴቶቹ ነው፡፡ በአንዱ አልጋ ትራስጌ በኩል ሁለት መንታ የሚመስሉ ህፃናት ፎቶ አለ ከጎናቸው ደግሞ መልከ መልካም ወጣት የተመረቀበት ምስል ይታያል፡፡ "እዚህ ስፍራ ላይ ይህ ፎቶ የማን አምሳያ ይሆን? የሁለቱ ጨቅላ ፎቶስ ምንድነው ትርጉሙ?" እያልኩ ራሴን ጠይቃለሁ መልስ እንደማገኝ ሁሉ፡፡

ግድግዳው ላይ ደግሞ በጥሩ ሀኔታ የተያዘ ሙሉ ሱፍ ተሰቅሏል፡፡ነገሮች የባሰ እየማረቱ ሄዱ፡፡ የማየው ሁሉ ጥያቄ እንጂ መልስ አልነበረውም፡፡ ፎቶዎቹ ወደተቀመጡበት ስፍራ ተጠጋሁ፡፡ አጠገባቸው ሌላ አልበም ተቀምጧል፡፡

ያለማንታት ብድግ አድርጌ አነሳሁት፡፡ የመጀመሪያው ገፅ ላይ አንድ ትንሽ ህፃን መለመሉን ተንጋሎ ሲስቅ ያሳያል፡፡ ትንሽ ፈገግ አስባለኝ፡፡ ቀጣዩን ገለጥኩት፡፡ አሁንም እርቃኑን በደረቱ ተኝቷል አስቀድሜ ያየሁት ድንቡሽቡሽ ቆንጅዬ ብላቴና፡፡ ግን ያየሁት ነገር አስደነገጠኝ፡፡
"ይህ እንዴት ሊሆን ይችላል?" ብዬ ራሴን ጠየኩ፡፡

ያየሁት ነገር ይበልጥ ግራ አጋባኝ፡፡ መቼም ገጠመኝም አጋጣሚም ሊሆን እንደማይችል እርግጥ ነው፡፡ ይሄን ጥያቄ ማን ሊመልስልኝ ይችላል ማንስ ያብራራልኛል?፡፡ የመጣሁበት ዓላማ እስክዘነጋ ድረስ ፈፅሞ ተቆጣጥሮኛል፡፡ የሰማሁት የቁራ ድምፅ ባያነቃኝ ኖሮ፡፡

ለዛ አረመኔ እንደ አደጋ ጥሪ መሆኑ ገብቶኛል የቁራው ጩኸት ከዚህ በሗላ ያለኝ ደቂቃ ትንሽ ነውና ተፋጥኜ መውጣት አለብኝ፡፡ አልበሙን ከነበረበት መልሼ የመኝታ ክፍሉን ለቅቄ ልወጣ ስል ጉጠት መሳዩ መቁረጫ ወለሉ ላይ ተቀምጦ አገኘሁት፡፡ "መርፌ ሚፈልግን ሞፈር ቢያነድለው...ይላል ተረቱ ልክ ነውም፡፡ እንደዛ አተራምሼ ያሰስኩትን ስተወዉ አገኘሁት፡፡

አነሳሁትና እያነከስኩኝ ክፍሉን  እያነከስኩኝ ክፍሉን ለቅቄ ልወጣ ስል.....

ቶሎ ቶሎ እንድለቅላችሁ react 👍 አንበሽብሹኝ

ምዕራፍ 2 .P12...ይቀጥላል.........
            
ከተመቻቹ ÷

                
#𝐑𝐞𝐚𝐜𝐭
                
#𝐂𝐨𝐦𝐦𝐞𝐧𝐭
                
#𝐬𝐡𝐚𝐫𝐞 🙏

    ¶ 𝚈𝙴𝙵𝙸𝙺𝙴𝚁 𝙲𝙻𝙸𝙽𝙸𝙲🥀 ¶™🌐

  📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት! 📱     

6.9k 0 13 7 106

ልብ አንጠልጣዩ "የጠፋው ሬሳ"

              ተከታታይ ትረካ


         ምዕራፍ 2 # ክፍል10

....አናቱን ብዬ ሁለት ቦታ ልከፍለው ለራሴ ወሰንኩ፡፡ ያነሳሁትን መጥረቢያ ለነዛ ሁሉ ስቃይ መልስ መሆኑ ለኔ ነው ሚገባኝ፡፡ ከአብሯደጓቼ ጋር መጥቼ ብቻዬን ሊሰደኝ ያቆበቆበው ወይንም ደግሞ ሊቀላኝ የዳዳው ይህ ደም የጠማው መጥረቢያ ነው፡፡ የስቃዬን በትር ሚሰነዝረው ደግሞ ከፊት ለፊቴ ጀርባውን ሰቶኝ የተገተረው ጣእረ ሞት የህይወቴ ጨለማ ነው፡፡ በእጄ ፍትህ የጨበጥኩና ለፍርድ በቅንነት እንደቆመ ታማኝ የህግ ሰው የምዳኛቸውን የነፍሳት ዋይታ በደስታ የምቀይር ያህል ውስጤ ሊሰይፈው ማለ፡፡ ብምረው አይማረኝ ብዬ መጥረቢያውን ስሰነዝረው ከበስተሗላዬ "ወይኔ ልጄን" ብላ ትልቋ ሴትዮ ገፈተረችኝ፡፡

ወትሮም የሰውዬው ቁመት ረዥም ነበርና መጥረቢያውም ካሰብኩበት ማረፉ ቀርቶ ጀርባው ላይ በግራ በኩል ከትከሻው ዝቅ ብሎ አጥንቱ ላይ ተሰንቅሮ ተጣብቆ እዛው ቀረ፡፡ ክፍሉ ነግሶበት ከነበረው ፀጥታ ሰገሮ አምጦ የዋይታ ድባብ ሰፈነበት፡፡ ከትንሿ ሴትዮ ጋር እየተወረጫጩ ያውሩ እንጂ በመሃላቸው የቃል ልውውጥ አልነበረም፡፡ አልፎ አልፎ በንዴት ስትናገር ቃል ታወጣለች እንጂ ፀጥ ብሎ ነበር፡፡ሴትየዋ ስትገፋኝ በክፍሉ ካለው አንዱ ጠረጴዛ ጋር ተላተምኩኝ፡፡ በዛች ቅፅበት ተረባርበው በድኔን ለቀብር እንዳይመች አርገው ይሰነታትሩታል ብዬ ባስብም ግን ማንም የኔ ነገር ግድ አልሰጠውም፡፡ ይልቁኑ ያንን ጥልማሞት ሰይጣን ነፍሰ በላ ከስቃዩ ሊታደጉት መጥረቢያውን ለመንቀል ይውተረተራሉ፡፡ ከሱ ሚወጣውን የሲቃ ድምፅ ስሰማ በደስታ ነፍሴ ስትዘል ተሰማኝ፡፡

ቀልባቸው ከኔ አለመሆኑ ሲገባኝ በድንጋጤ እየተብሰከሰከ የነበረ ሰውነቴን አጀግኜ የሞት ሞቴን ተነስቼ ከክፍሉ ወጣሁ፡፡ አልፎ አልፎ ከሚገባው ፀዳል በቀር ከክፍሉ ውጪ ያለው ስፍራ ፅልመት ወርሶቷል፡፡ ይሄ ለኔ ግድ አልነበረውም ከዚ ሞት ካጠላበት የአረመኔዎች ታዛ በህይወት መውጣቴን ተስፋ አድርጌ ወደ ፊት መንጓዴን ተያያዝኩት፡፡

እግሬ ግን ብዙ ሊያራምደኝ አልቻለም፡፡ ክፉኛ የተመታው ከጉልበቴ በታች ያለው አካሌ እርምጃዬ በጀመረ ቁጥር በእጥፍ ስቃዬን ይበረታል፡፡ ተማርኮ ከመሞት እየሸሹ መሞት ለኔ ክብር አለው፡፡ "ቆሜማ አልሞትም አዎ አልሞትም" አልኩኝ ለራሴ፡፡ ትንሽ እንደተራመድኩ ከአንዱ ክፍል ውስጥ በሰመመን የሚያቃስት የሲቃ ድምፅ ደረሰኝ፡፡ እንደኛው እድል ዞራበት ወደ ሞቱ የገሰገሰ የገዳይ ግዳይ ሊሆን የተዘጋጀ የመስዋዕት በግ ይሆን እንደሁ ብዬ ወደ ክፍሉ ገባሁ፡፡

ነገር ግን ያየሁትን ማመን አልቻልኩም፡፡ "ባርሳ" ነበረች፡፡ ከቆመ ብረት ጋር ስለት ባለው የአንገት ሰንሰለት ታስራለች፡፡ ሁለት እጆቿ ወደየ አቅጣጫቸው በገመድ ታስረዋል፡፡ የለበሰችው ልብስ በደም ወይቧል፡፡ ለሰከንድ ተሳስታ ዝቅ ብትል አንገቷ ከላዯ ላይ ተቀንጥሶ ከወለሉ ላይ መንከባለሉ አይቀርም፡፡

ባርሳ ፍፁም ከባድ የህይወት ትግል ውስጥ ነች፡፡ ከጀርባዋ በኩል ያለው ክፍት መስኮት የሚያስገባው ወገግታ ክፍሉን አፍክቶታል፡፡ እንዴት ልረዳት እንደምችል እያንሰላሰልኩኝ ወደሷ ተጠጋሁ፡፡ ህመሟ በቀል የማይገለፅ ነው፡፡ በገመድ የታሰረ የመሰለኝ እጇ በካቦ ሽቦ የታሰረ ነበር፡፡ እጇን ሰርስሮ ወደ ውስጦ ሊዘልቅ ምንም አልቀረውም፡፡

ከእስራቱ አለፍ ብሎ ያለው አካሏ የደም ሽል ይዞ ውጥር ብሏል፡፡ ደምስሯ ሊበጠስ የሰከንድ ዕድሜ ቢቀረው ነው፡፡ ሞት አልፈለጋትም እንጂ ደጁን እየቆረቆረች ነው፡፡ የሞት መልአክ አይቶ እንዳላየ ለቁም ስቃይ ሸለማት፡፡ እንባዬ ከአይኔ መዝረብረብ ጀመረ፡፡ እንዴት አድርጌ ልርዳት እንዴትስ ላግዛት፡፡

እግሯ አካሏን መሸከም አቅቶት ይብረከረካል፡፡ እህል አይቶ ማያውቀው አንጀቷ ይንዘፈዘፋል፡፡ ዝቅ ባለች ቁጥር ወደ አንገቷ የሚሰርገው እሾህ መሳይ ስለት ያለው ሰንሰለት ነፍሷን ያስጨንቃታል፡፡ መኖር የጓጓች እስትንፋሷ እጅ አልሰጥ ብላ የዛለ አካሏን ለመኖር በሚደረግ ጦር ሜዳ ላይ አዝምታዋለች፡፡ አንድ ነገር አሰብኩኝ የታሰረችበት ቆሞ ያለው ብረት ከመሬቱ ጋር የተቸነከረ አይደለምና ከነ አካሏ ቀስ አድርጌ መሬት ላይ ለማንጋለል፡፡

ግን የእጇን እስራትስ እንዴት ልፈታው እችላለሁ፡፡ እሷ አላወቀችኝም የማወቅ ልኩ ላይ አይደለችምና፡፡ እኔ ከማልቀስ ውጪ ላረግላት የቻልኩት ቅንጣት አልነበረም፡፡ ከፊት ለፊቷ ቆሜ ለዚ ስቃይ እንደተውኳት ብታውቅ ምነኛ አምርራ እንደምጠላኝ ሳስበው ራሴን ረገምኩኝ፡፡ ብኩን ነኝ የማልረባ፡፡ የእግሬ ህመም ትንሽም ቢሆን ጋብ ብሎልኛል፡፡

ባርሳን ሳያት ሄጄ እሷ ላይ አለመጠምጥሜ ገረመኝ፡፡ ይሄን እርጋታ ከየት አመጣሁት ወይንስ ደነዘዝኩ፡፡ አሁን ከራሴጋ ሳወራ በቅጡ ማሰብ እየጀመርኩ ነው፡፡ ከድንዛዜዬ ነቅቼ ገባውን መቃኘት ጀመርኩኝ፡፡ እጇን ከፈታሗት መላ አካሏ ወደ መሬት ቁልቁል መምዘግዘጉ ነው እንደዛ ከሆነ ደግሞ አንገቷ እዛው ይቀላል፡፡ ስለዚህ ሰውነቷ ከብረቱ ጋር ተጣብቆ የሚቀርበትን ሁኔታ መፍጠር አለብኝ ስል አሰብኩ፡፡

ክፍሉ ውስጥ ካለው ከአንዱ አልጋ ላይ ቀበቶ መሳይ ማሰሪያ አገኘሁ፡፡ ወደርሷም ተጠጋሁና ከዳሌዋ ከፍ አድርጌ ከብረቱ ጋር የፊጢኝ አሰርኳት፡፡ አካሏ ከመድከሙና ከመቁሰሉ የተነሳ እያንዳንዱ ንኪኪዬ ለሷ ህመሟ ነው፡፡ አሁን ደግሞ ሌላ ስንክሳር እጇ የታሰረበት ካቦ ፈፅሞ በኔ አቅም የሚፈታም የሚበጠስም አልነበረም፡፡ የአንገቷም ሰንሰለት እንደዛው፡፡

ባርሳን ፈፅሞ እዚ ጥያት አልወጣም፡፡ ከሞትንም አብረን ነው እንጂ፡፡ የታሰረችበትን ለመበጠስ የሚረዳኝን መሳሪያ ሁለቱ ሴቶች ከጣረ ሞቱ ጋር አንድ ላይ በሚሆኑበት ክፍል ውስጥ ተመልክቼዋለሁ፡፡ እናም አመጣዋለሁ፡፡

ይቀጥላል ...........


ቶሎ ቶሎ እንድለቅላችሁ react 👍 አንበሽብሹኝ

ምዕራፍ 2 .P11...ይቀጥላል.........

            
ከተመቻቹ ÷

                 #𝐑𝐞𝐚𝐜𝐭
                 #𝐂𝐨𝐦𝐦𝐞𝐧𝐭
                 #𝐬𝐡𝐚𝐫𝐞 🙏

    ¶ 𝚈𝙴𝙵𝙸𝙺𝙴𝚁 𝙲𝙻𝙸𝙽𝙸𝙲🥀 ¶™🌐


  📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት! 📱 
    


ልብ አንጠልጣዩ "የጠፋው ሬሳ"

              ተከታታይ ትረካ

          ምዕራፍ 2
#ክፍል 9

...ከፊት ለፊቴ ድንቅር ብላ ቆማለች ፊቷ ላይ እልህና  ይነበብባታል ኮስተር ብላ ከእግር እስከራሴ ተመለከተችኝ
ምንም ሳትናገር ዙሪያዬን ትዞረኝ ጀመር እኔም በልበ ሙሉነት እና
ያለ አንዳች ፍራቻ ፀጥ ብዬ ቆምኩኝ
ድጋሜ ፊለተፊቴ መጥታ ቆመች
ተጠጋችኝ አንዳች ነገር እንደሚያሸት ሰው አየር በአፍንጫዋ መሳብ ጀመረች
የለበስኩትን ቀሚስ በእጇ እየነካካች
ፈገግ ቁጣ እያለች ትመለከተኛለች
ድንገት "የሞትሽ መስሎኝ ነበር አለሽ እንዴ" ብላ ጠየቀችኝ
"አዎ አለሁኝ መኖር ስለቻልኩ ሳይሆን
ማኖር የሚችል አምላክ ስላለኝ አለሁ"
ብዬ መለስኩላት ማሽሟጠጥ በሚመስል መልኩ ከንፈሯን አንቀሳቅሳ
አንገቷን ነቀነቀች ውሰጤ የነበረው
ቁጣና ንዴት ወዴት እንደሸሸ አላውቅም ብቻ እርግት ብዬ ቆሜያለሁ
ከዛም የሆነ የረሳችውን ነገር ያስታወሰች ይመስላል ግንባሯን
ጭምድድ አርጋ ፊቴን አትኩራ ተመለከተችኝ "ማነው ስምሽ" የሚል
ጥያቄን ሰነዘረች "ሜርሲ" አልኳት ፈጠን ብዬ "ከዚ ቀደም እዚ ክፍል
ሆስፒታል ውስጥ ተመልክቼሻለሁ
ግን እንደዛሬው አልተዋብሽም ነበር
የማንን ቀሚስ እንደለበሽ ታውቂያለሽ"
ብላ ጥያቄዋን አስከተለች እኔም ዝቅ ብዬ እያየሁት "አይ አላውቅም ማን
እንዳለበሰኝም እንጃ" ብዬ ለጥያቄዋ ምላሽ ሰጠሁ  ግራ የተጋባች ይመስላል
"ማን እንዳለበሰኝ አላውቅም?" ብላ ጥያቄዬን በጥያቄዋ መለሰች እኔም
የአንደበቴን ቃል ትቼ በአንገቴ ንቅናቄ
አውንታዬን አሳየሗት ከቅድሙ ይበልጥ አተኩራ ተመለከተችኝ...እኔም
ወዲያውኑ እግሯ ስር ብርክክ ብዬ
"እባክሽን ከዚ አውሬ አትርፊኝ ለውለታሽ የፈለግሽውን አደርግልሻለሁ"
አልኳት ድንገት ተቀየረችና ከፍ ባለ ድምፅ "ማንን ነው አውሬ አንድዬን ነው
አውሬ" ብላ ስትጮህ ከሌላኛው ክፍል
ሁካታ ድምፅ ተሰማኝ ከአይኔ የእንባ
ዘለላ እየወረደ ተማፀንኳት እሷ ግን
ፍንክች አልል አለች የሆነ ኮቴ እኛ ወዳለንበት ክፍል ሲያመራ ተሰማኝ
"አንድዬን ሰው ነው አውሬ ያረገው
እንጂ ሰፈር መንደሩ ያወቀው ትሁት
የተመሰገነ ልጅ ነበር ግን ሰው ብላ" ስቅስቅ እያለች ማልቀስ ጀመረች
ወዲያውኑ አረመኔው ሰው ደም የለመደ መጥረቢያውን ይዞ ድንገት
አጠገባችን ተገኘ ባለሁበት አጎነበሼ
የመጨረሻ እንባዬን አነባሁ ተንሰቅስቄ
አለቀስኩኝ ድንገት ከመሬት ሊያነሳኝ
ፈርጠም ያለ እጅ ክንዴ ላይ አረፈ
ቀና ብዬ አየሁት አረመኔው ሰው ነበር
መጥረቢያውን ጥሎ እጁን ዘረጋልኝ
እኔም በሱ ታግዤ ከመሬት ተነስቼ ቆምኩኝ ፊቱን ለተመለከተው ለመግለጽም ቃልን ነው ሚያሳጣው
እኔን ካነሳኝ በሗላ ትንሿን ሴትዮ ለማባበል ተጠጋት እሷ በአግራሞት
ሆነ ተደንቃ ትመለከተዋለች
ይመስለኛል ለምን እንዳልገደለኝ
ለኔ ጥያቄ እንደሆነብኝ ሁሉ እሷም
ጥያቄ ሆኖባታል አሁን እሱ ሴትየዋ
ወደኔ እንዳታይ ሙሉ ለሙሉ ከልሏታል
እኔም ድምፅ በሌለው አረማመድ ወዳስቀመጠው መጥረቢያ ተጠጋሁ
አባብለውኝ ከምሞት በጭካኔ ቢገለኝ
እመርጣለሁ ከዚ በላይ ለመሰቃየት
ዝግጁ አይደለሁም
መጥረቢያውን አንስቼ በሁለት እጄ ጨበጥኩት በለዘበ እርምጃም እሱን
መጠጋት ጀመርኩ ከሴትየዋ ጋ የተስማሙ አይመስሉም
እየተወረጫጩ ነው ሚነጋገሩት በኔና
በሰውዬው መሃል አንንድ እርምጃ ሲቀረን አቋቋሜን አስተካክዬ መጥረቢያውን ከፍ አድርጌ.....


ቶሎ ቶሎ እንድለቅላችሁ react 👍 አንበሽብሹኝ

ምዕራፍ 2 .P10...ይቀጥላል.........

            
ከተመቻቹ ÷

                 #𝐑𝐞𝐚𝐜𝐭
                 #𝐂𝐨𝐦𝐦𝐞𝐧𝐭
                 #𝐬𝐡𝐚𝐫𝐞 🙏

    ¶ 𝚈𝙴𝙵𝙸𝙺𝙴𝚁 𝙲𝙻𝙸𝙽𝙸𝙲🥀 ¶™🌐


  📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት! 📱     

9.7k 0 19 52 108

ልብ አንጠልጣዩ ተከታታይ ትረካ


ምዕራፍ 2
#ክፍል8

...ልክ እንደ ህፃን ልጅ አቅፎኝ ሲራመድ
ይታወቀኛል ወዴት እንደሚወስደኝ
ባላውቅም ልቤ ግን ለሰከንድ አልጠረጠረውም ነፍሴም በብዙ ታምናበታለች....እርግት ያለው የእርምጃው  ድምፅ ደስታን ይሰጠኛል
ትንሽ እንደተጓዘም ከአንድ ስፍራ በጥንቃቄ አስቀመጠኝ ቀስ እያለም የለበስኩትን ልብስ አንድ በአንድ ማውለቅ ጀመረ ከቁስሌ ጋር ተጣብቆ የነበረው ሲነሳ ልቤ ክፍል እስክትል ያስጨንቀኛል፡፡
እርቃኔን ማንም አይቶኝ ስለማያውቅ በጣም ደነገጥኩኝ ጡቶቼን በእጆቼ ሸሸኳቸው ግን እሱ ቃል ሳያወጣ
በእጆቹ መዳበስ አረጋጋኝ ዝም ብዬም
ቁጭ አልኩኝ የተመሰቃቀለውን ፀጉሬን
ማስተካከል ጀመረ ወዲያውኑ ለብ ያለ ውሃ ውስጥ በተነከረ ፎጣ ገላዬን
ማፅዳት ጀመረ ህመም እንዳይሰማኝ
እጅግ ተጠንቅቆ...ከላዬ ላይ ያፀዳውን
ደም አንዳች ነገር ውስጥ ሲጨምቀው
ይታወቀኛል...
እርጋታ በተሞላበት ሁኔታ መላ አካላቴን
አፀዳው...ነገር ግን አሁንም ድረስ
ፊቴን አለማጠቡ እና አይኔን እንድገልፅ አለማረጉ
ጥያቄም ግርምትም ሆኖብኛል...እንዳላየው ለምን ፈለገ?
ድምፁንስ ለምን አውጥቶ አያወራኝም?
ብቻ ብዙ ብዙ ጥያቄ ውስጤ ይመላለሳል ለዚ ሁሉ ጥያቄም መልሴ
ዝም ብቻ ነው...አሁንም በድጋሜ ከተቀመጥኩበት አቅፎ አነሳኝ ከዛም
አልጋ ላይ ይመስለኛል አስቀመጠኝ...
ወዲያውኑ ቀዝቀዝ ያለ ዘይት መሳይ ነገር ቁስሌን ሲቀባኝ ታወቀኝ...ይህ ሰው
ሊያይድነኝ የተላከ መሆን አለበት
አልኩኝ...ዘይቱ ቁስሌን ሲያገኘው አነስተኛ ህመም ነበረው ግን ስቃዩን
ችዬ ዝም አልኩኝ ከጨራረሰ በሗላ
መዓዛው የሚያውድ ሙሉ ቀሚስ አለበሰኝ ከዛም የነበርኩበት አልጋ ላይ
በጀርባዬ አስተኛኝ ጭንቅላቴ ከአልጋው ወጣ እንዲል አደረገው
ቅድም ያሰረውን ፀጉሬን መፍታት ጀመረ...
በውሃ በራሳ ፎጣ ፊቴን ሸፈነው...
ለብ ባለ ውሃ ፀጉሬን ማጠብ ጀመረ ቀስ እያለ እያበጠረ በእርጋታ ማጠቡን ቀጠለ...እርጥቡ ፎጣ ፊቴ ላይ ያለው
የደም ቅርፊት ማራስ ጀመረ ይህን ሰው
እስካየው ነፍሴ አብዝታ ጓጉታለች
ፀጉሬን ከጨረሰ በሗላ አደራርቆልኝ
ቅባት እየቀባ ያበጥረው ጀመር ከዛም
በውል አሰረልኝ ሲወጣም የእግሩ ኮቴ
ተሰምቶኛል ግን ለደቂቃዎች ስጠብቀው አልተመለሰም ደቂቃዎችም ሰዓትን መተካት ጀመሩ ግን የለም
በጣም ጨነቀኝ ፎጣው ፊቴ ላይ እንዳለ ነው እኔም በጀርባዬ እንደተንጋለልኩ
ቀስ ብዬ ፊቴን በጋረደው ፎጣ የራሰውን ደም መጠራረግ ጀመርኩ
ከዛም አይኔ ተገለጠ ቀስ ብዬም ተነስቼ ቁጭ አልኩኝ ዙሪያዬን ስቃኝ
አንዳች ነገር የለም አካባቢው ከላዬ ላይ
በወረደው የደም እድፍ ተጨማልቋል
ለመውረድ ፈልጌ ቁልቁል ስመለከት
የሚያምር ነጭ ጫማ አለ ቀስ ብዬ በእርጋታ አደረኩት...
የለበስኩትንም ስመለከት እጅግ ውብ የሆነ የሀገር ባህል ልብስ ነው ያለሁበትን እስክረሳ ድረስ ደስ አለኝ
እየተሽከረከርኩም እራሴን አየሁ...
ክፍሉ ውስጥ መንጎራደድ ጀመርኩ
ጠረጴዛ ላይ አንዳች የሚበላ ነገር
ተቀምጧል ጠጋ ብዬም አየሁት የታሸገ የዓሳ ስጋ ነው እጅግ እርቦኛል
ጥርግ አርጌም በላሁት አሁን በርትቻለሁ አካሌም ታድሷል
ያንን አረመኔ አሁን ማጥፋት እችላለሁ
ውስጤ በድጋሜ በእልህ ተሞላ
አይኔንም ወደ መውጫው ሰደድኩት
እልህ በለ፡ተሞላው እርምጃ ከክፍሉ ወጣሁ ኮሪደሩ ላይ አንዳች አይታይም
ፀጥ ረጭ ብሏል ጥንቃቄ በተሞላው
መልኩ ዙሪያዬን እየቃኘሁ
መራመድ ጀመርኩ...ፀጥታው እጅግ ያስፈራል ቀጥ ብዬ ከሴቶቹ ጋር ወደ ሚገናኝበት ክፍል አመራሁ ነገር ግን
አይኔ ከ ባርሰናይት ጋ አብረን ወደተኛንበት ክፍል ላይ አረፈ ጠጋ
ብዬም በመስታወት ተመለከትኩ
ከመኝታው ላይ ባርሳ የለችም
ያ አረመኔ አንዳች አርጓት ይሆን እንደው ብዬ ሰጋሁ...ክፍሉን ቅኝቼ
ፊቴን ወደሗላ ስመልስ ትንሿ ሴትዮ.........


ምዕራፍ 2 .P9...ይቀጥላል.........
            
ከተመቻቹ ÷

                
#𝐑𝐞𝐚𝐜𝐭
                
#𝐂𝐨𝐦𝐦𝐞𝐧𝐭
                
#𝐬𝐡𝐚𝐫𝐞 🙏

    ¶ 𝚈𝙴𝙵𝙸𝙺𝙴𝚁 𝙲𝙻𝙸𝙽𝙸𝙲🥀 ¶™🌐

  📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት! 📱     

10.7k 0 22 14 103

ልብ አንጠልጣዩ ተከታታይ ትረካ


          ምዕራፍ 2
#ክፍል7


.....ወደ ቀልቤ ሳልመለስ ደቂቃዎች ተቆጠሩ የሚሆነውን በማላስተውልበት ሁኔታ ሰከንዳት
ብዙ ተጓዙ ነገር ግን በዛሁ አልቀረሁም
ያለሁበትን ካስረሳኝ ሰመመን ነቃሁ
በደም የተጨማለቀ አይኔን ለመግለጥ
ሞከርኩኝ ግን አልቻልኩም
ምንም እንኳ ብነቃ አካሌን መዘዝ
ተስኖኛል የቅድሙ ቅዝቃዜ ፈፅሞ
የለም ግን ሳይኖር ቀርቶ ሳይሆን
የኔ መደንዘዝ ነው...ሰውነቴ ስለሚፈጠርበት ነገር ምላሽ ለመስጠት አቅም የለውም ነቅቼም
በድን ሆኛለሁ...በዚ ሁኔታ ውስጥ እያለሁ ደቂቃዎች አብዝተው ተጓዙ
እናም ሰውነቴን ለማገላበጥ ነቅነቅ
ስል ከጭንቅላቴ ጋር እንደ ትራስ የሚመስል ነገር ተሰማኝ በጣም
ደነገጥኩኝ ባዶ ወለል ላይ ነበር የተዘረርኩት እና ከየት መጣ ማንስ
አመጣው ይሄን ጥያቄ እስክመልስ
ድረስ እንቅስቃሴዬን ገታሁ...
ደም
የተጋገረበትን አይኔን በመዳፌ ለማፅዳት  ሞከርኩ ነገር ግን ደርቆ
ነበርና ቀላል አልሆነልኝም...ያለውንም
ሁናቴ በእጆቼ መዳፍ ለማጣራት እጄን
ወደ ትራሱ ሰደድኩት ነገር ግን አስቤ
እንደነበረው ትራስ አይደለም...በጣም
ደነገጥኩኝ የሰው እግር ነበር እጄን
ወደነበረበት መለስኩኝ ልቤ ክፉኛ
ተወራጨ አንድም በደስታ አንድም
በጭንቀት...ደስታው የሚረዳኝ ሰው
የመጣ መሰለኝ ጭንቀቱ ደሞ ያ ሰው
ማነው የሚለው ነበር...ከአንደበቴ ቃል
አውጥቼ አወራ ዘንድ አልቻልኩም
ቃሎቼ ከአንደበቴ ሳይወጡ ከንፈሬ
ላይ ይመክናሉ ምላሴ እንደቀድሞው
አይታዘዝም ወይ አጠገቤ ያለው ሰው
ራሱ ቢያወጋኝ ምን አለ ወይ ደግሞ
የአይኔ ሽፋሽፍቶች ከብሌኔ ቢሸሹ ምን ነበር ይህን የኔ ደራሽ ባየሁት አልኩኝ
መዳፌ አላረፈም ደጋግሜ ዳሰስኩት
ነካካሁት ከናፍሬ ባይሸሽም ነፍሴ ግን
ከልቧ እየሳቀች ነው የሆነ ሰው ብቻ
መድህኔ ነው ልበለው ያንን አረመኔ
ነፍሰ በላ የሰው ስጋ ጥማተኛውን
አፈር እንዳስበላው ይሰማኛል ነፍሱንም ስለ ጠፉት ነፍሶች ብሎ
እንደቀጣት ውስጤ ይነግረኛል የጓደኞቼን በቀል የስጋቸውን ደም
የነፍሳቸውን ሲቃ አንዱ አዳኝ(ላልቶ)
የስቃዩን እና የሰቆቃውን ምንጭ
እንዳደረቀ ይሰማኛል...አካሌ ከነበረበት ድንዛዜ እየወጣ ነው መሰል ቅዝቃዜው ይሰማኝ ጀምሯል ከቅዝቃዜው ይልቅ ግን
ውስጤ ድረስ የተሰማኝ ፀጉሬ መሃል
የሚርመሰመሱት ጣቶች ነበሩ
ፍፁም ሰላም ሰጡኝ ብዙ ተስፋን ሞሉኝ ፀጉሬ ከዚ በፊት ተዳብሶ
እስከማያውቅ እንግዳ ሆነብኝ ጣቶቹ
የጭንቅላቴን ቆዳ ሲነኩት ይጎረብጣሉ
አይመቹም ግን እስከዛሬ ሲነኩኝ ከነበሩት ከለሰለሱ መዳፎች ይልቅ ልዩ
ደስታን ሰጥተውኛል የተለየ ስሜትም
አላቸው፡፡
ለማንም አሳልፎ የማይሰጠኝ ብርቱ
ክንድ አጠገቤ እንዳለ ነፍሴ አመነች
እኔም ተስማማሁ...ጣቶቹ ፀጉሬ መሃል
ሲዋኙ እኔ በምናብ ክንፍ እላለሁ በፀደይ ወራት ውስጥ በለመለመ መስክ ላይ ለዘብ ባለች ፀሃይ ታጅቤ
ከልካይ በሌለው ሜዳ ላይ ስቦርቅ
ይታየኛል ግን ብቻዬን አልነበርኩም
አንድ የማላውቀው ግን ደግሞ
ደስታዬን እጥፍ ያደረገ ወጣት አብሮኝ
አለ አላወራውም እሱም አያወራኝም
ግን አንዳችን ላንዳችን ደስታ ነበርን
ፀሃይ አዘቅዝቃ ወደ ጎጆዋ ስትገባ እሱ
ግን ከኔጋ ነበር ከፀሃይ ብርሃን ይልቅ
ለኔ ያስፈልገኛል ግን አላውቀውም
አላወራውምም...ከሄድኩበት የሰመመን ደስታ መለስ አልኩኝ
በጣቱ ንክኬ በመዳፉ መዳሰስ ሰላም
የሚሰጠኝ ይህ ማነው እግሮቹ ላይ
ተኝቼ ምንስ ያኩራራኛል እንደ መከታዬ ያሰብኩት ይህ ሰው ማነው?

ረዘም ላሉ ደቂቃዎች ከደባበሰኝ በሗላ
እግሩ ከጭንቅላቴ ስር ሲነሳ ተሰማኝ
አትሂድ ልለው ብዬ አልቻልኩም...
አንደበቴ ታስሯል የክንዱ መፈርጠም ፆታውን ነግሮኛል አይቼ እንዳለየው
አይኖቼ ተጋርደዋል ባለሁበት
ሆኜ እጄን እየዘረጋሁ ዙሪያዬን ዳሰስኩ አንዳች አልነበረም ግን ከተኛሁበት ለመናሳት ስጥር ድግፍግፍ
አድርጎ አነሳኝ አሁንም አጠገቤ እንዳለ
ታወቀኝ ጥሎኝም እንዳይሄድ ባለችኝ
ኢምንት አቅም ያዝኩት እሱም ከኔ አልሸሸም...ግን ማነው?....

ቶሎ ቶሎ እንድለቅላችሁ react 👍 አንበሽብሹኝ

ምዕራፍ 2 .P8...ይቀጥላል.........
            
ከተመቻቹ ÷

                 #𝐑𝐞𝐚𝐜𝐭
                 #𝐂𝐨𝐦𝐦𝐞𝐧𝐭
                 #𝐬𝐡𝐚𝐫𝐞 🙏

    ¶ 𝚈𝙴𝙵𝙸𝙺𝙴𝚁 𝙲𝙻𝙸𝙽𝙸𝙲🥀 ¶™🌐


  📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት! 📱     

12.2k 0 24 11 137

ልብ አንጠልጣዩ ተከታታይ ትረካ


ምዕራፍ 2
#ክፍል6


......እሳት ጎርሶ እሳት ለብሶ ሲራመድ የእግሩ ዳና ይናገራል...ከዚ ስቃይ ለመገላገል እና የስጋዊ ጉዞዬን እንደጨረስኩ ይሰማኛል እዛው ተቀምጬ እንዳለሁ ፀጉሬን ይዞ እየጎተተ ወደ
መሃል አስጠጋኝ...የቆሰለው አካሌ ከወለሉ ጋር በተፈጠረው ፍትጊያ
እየተላላጠ ስቃዬን አበዛው በድጋሜ
እጅግ ቀዝቃዛ ውሃ ደፋብኝ አቤት ስቃይ
...ወለሉ ላይ ኩርምት ብዬ ተኝቼ አካሌ
ይንዘፈዘፋል ትንፋሼ እየተቆራረጠ ልብ
ምቴ ሊቆም እንደሆነ ይሰማኛል ግን ዘገየ
እኔ ስቃዩን አልቻልኩትም ከበደኝ...ፀጉሬን
ከአይኔ ላይ ገለል አድርጌ ስመለከት ጀርባውን ለኔ ሰቶኝ ከአንድ ጠረጴዛ ፊት ለፊት ቆሟል
ነገር ግን ምን ያደርግ እንደነበር መለየት አልተቻለኝም ጭንቅላቴ ለአንገቴ እንደ አንዳች ከባድ ሸክም ሆኖበታል...
እየደጋገምኩ ለመነሳት ብሞክርም አልቻልኩም...ጤናማ ሆነህ ያደረካቸው
ተራ ነገሮች አቅምህ ተሟጦ ስታስባቸው
ምነኛ እንደሚናፍቁ አሁን ተረዳሁኝ...
አንዳች ክስተት ተፈጥሮ ከዚ ሞት ካጠላበት የተረገመ ቤት ሞቼም ቢሆን
በወጣው አልኩኝ...ወለሉ ላይ ተንጋልዬ
ሽቅብ ሰውዬውን ስመለከት ያንን ደም የለመደ መጥረቢያ ይዞ ወደኔ እየተራመደ
መጣ አጠገቤም ደርሶ መጥረቢያውን
መሬት አስደግፎ ይዞረኝ ጀመር ለምን እንደሆነ ምክንያቱን ባላውቅም...ልክ በአይኔ ትይዩ ሲደርስ ጫማውን ስመለከተው ትናንሽ ስጋዎች እና የረጋ የደም ጠብታ ይታይበታል...አሟሟቴን ማሰብ ጀመርኩ "ድንገት ሳላስበው
ጭንቅላቴን ሁለት ያረገው ይሆን ወይስ
አንገቴን በጥሶ ይጥላዋል?" እያልኩ
መልስ አልባ ጥያቄዎችን ራሴን ጠየኩት
በተኛሁበት እየዞረኝ ደቂቃዎች ተቆጠሩ...
ነገር ግን ሰውዬው እስካሁን አንዳች ነገር
አላደረገኝም ይህ ሁኔታ ግራ ሆነብኝ...
በድንገት ሌላው ክፍል ባርሳ እንዳለች ትዝ አለኝ ትኑር ትሙት ግን አንዳች አላውቅም...አረመኔው ሰውዬ እንደጨቀነቀው እየተሰማኝ ነው ያለማቋረጥ ዝም ብሎ ይዞረኛል ስሜቱን በደንብ ለመረዳት እንደምንም ክንዴን ተመርኩዤ ቀና ስል ደም ባቆረፈደው ጫማ ከስር ወደላይ በግራ ጉንጬ በኩል ጥርሶቼ የተራገፉ እስኪመስለኝ ድረስ
ህመሙ ዘልቆ ተሰማኝ...ከሰውዬው ምት
የባሰው ደግሞ ጭንቅላቴን የተቀበለው
ወለል ነበር ደም ደም ሸተተኝ አፍንጫዬን
ነሰረኝ ጭንቅላቴም መድማት ጀመረ...
በዚ ሁኔታ ውስጥ እያለሁ በድጋሜ ፀጉሬን ይዞ ጎተተኝና ግድግዳ አስደግፎ
አስቀመጠኝ ከዛም የመጥረቢያውን ስለት አዞረና የግራ እግሬን ከጉልበቴ በታች ያለውን አጥንቴን ክፉኛ መታኝ ድምፄንም ከፍ አድርጌ ጮውኩኝ እየደጋገምኩ ጮውኩኝ አምርሬም አነባሁ
አጥንቴን ስለመታኝ ህመሙን አልቻልኩትም እግሬን ታቅፌ ወለሉ ላይ
ተኛሁኝ እግዜር ምን እስከሆን እየጠበቀኝ
እንዳለ ጥያቄ ሆኖብኛል መላ አካሌ ዝሏል ሞት ብቻ ነው የቀረኝ ግን ደሞ
ሞቴ በጣም ዘገየ...ሰውዬው አሁንም ፀጉሬን ይዞ ጎትቶ ግድግዳው ላይ
አስደገፈኝ ደሜ ከአናቴ ሲንቆረቆር ገላዬ
ላይ ይታወቀኛል የእግሬ አጥንት የተሰነጠቀ እስኪመስለኝ ድረስ ይቆረጥመኛል በዚ ስቃይ ውስጥ እያለሁ
ቀዝቃዛውን ውሃ በድጋሜ ደፋብኝ ከዛም ፊት ለፊቴ ተንበርክኮ አንገቴን ሲጥ አርጎ
አንቆ እየደጋገመ ከግድግዳው ጋር በሃይል ያጋጨኝ ጀመር ከዛም የፊጢኝ ያነቀውን አንገቴን ለቀቀው ወዲያውኑ ተዝለፍልፌ ወለሉ ላይ ተንጋለልኩ ደሜ ያለማቋረጥ እየፈሰሰ
በጆሮዬ ስር ይወርዳል የማየው ነገር ሁሉ መሽከርከር ጀመረ...
እያዞረኝ እንደሆነም ተሰማኝ ቀስ በቀስ የማየው ነገር እየደበዘዘ መጣ
ወዲያውኑም ጭልም አለብኝ ምንም ማየት አልቻልኩም ኩርምትምት እንዳልኩኝ
በደም ተጨማልቄና ረጥቤ ራሴን ሳትኩኝ.........

ምዕራፍ 2 .P7...ይቀጥላል.........
            
ከተመቻቹ ÷

                
#𝐑𝐞𝐚𝐜𝐭
                
#𝐂𝐨𝐦𝐦𝐞𝐧𝐭
                
#𝐬𝐡𝐚𝐫𝐞 🙏

    ¶ 𝚈𝙴𝙵𝙸𝙺𝙴𝚁 𝙲𝙻𝙸𝙽𝙸𝙲🥀 ¶™🌐

  📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት! 📱     


ልብ አንጠልጣዩ ተከታታይ ትረካ


             ምዕራፍ  2  
#ክፍል 5


...እጆቼን በሃይል ጎትቶ ከተቀመጥኩበት
ምንጭቅ አርጎ አነሳኝ በዚ ጊዜ ከብረት
ወንበሩ ጋር ተገናኝቶ የነበረው የአካሌ
ክፍል እየተቦጫጨቀ ወንበሩ ላይ ቀረ ወለሉ ላይም ወረወረኝ...ጀርባዬ እና ታፋዬ በደንብ የተጎዱ የሰውነት አካሎቼ
ናቸው ወንበሩ ዳማ መሰይ ክፍተት
ባይኖረውማ ኖሮ ቆዳዬ እንደ ሚገፈፍ
አንዳች ጥርጥር የለኝም...
...ስቃዬን ቃላት ችለው አይገልፁትም እዛው ወለሉ ላይ ሆኜ ክፉኛ መንቀጥቀጥ
ጀመርኩኝ ጉልበትና ጭንቅላቴን አጋጥሜ
ኩርምት ብዬ እየተንከጠቀጥኩኝ ሳለ
ይባስ ብሎ አረመኔው ሰውዬ አጥንት ድረስ ዘልቆ ሚሰረስር ቀዝቃዛ ውሃ
እላዬ ላይ ደፋብኝ ስቃዬን በእጥፍ አበዛው፡፡
ገና ያልደረቀ ቁስሌ ነፍሴ ድረስ ዘልቆ
የሚሰማ ክፉ ህመም ሆነብኝ ምንም ቃል
ማውጣት ተስኖኛል ዝም ብቻ ሌላ ምንም
ውሃውን እየደጋገመ ይደፋብኝ ጀመር
...አንዳዴ ሞት እየናፈቁ አለማግኘት በፈጣሪ
እንደመረሳት ይመስለኛል የሞት መልዓክ
ለኔ ሲሆን ዘገየ እንዲ ስሰቃይ እያየ ዝም
ብሎኛል አልጠራው ነገር አቤት አይለኝ
መፈጠሬን እስክጠላ የደስታም ቀን
አሳልፌ የማውቅ እስከማይመስለኝ ድረስ
በወለደኝ ማህፀን ተማረርኩ...
አይኔ ከመከደን በማይተናነስ ሁናቴ በትንሹ ገርበብ ብሎ ተከፍቶ አንባዬን ዝም ብሎ ይሸኛል ከናፍሮቼ
ከጥርሴ ጋር ተስማምተው ይብረከረካሉ
በኤሌክትሪክ የተጠበሰው ገላዬ
አሁን ብርድ እያቆረፈደው ቁስሉም እየመዘመዘኝ ደቂቃዎች በፀጥታ ተጓዙ...
መላ ሰውነቴ ዝሏል ደክሟል ባዘውመም
አይለሰማኝም ለመነሳሳት ስሞክር
አሀሸየደጋገምኩ መውደቅ ጀመርኩ ቢያቅተኝ እዛው ተንንጋለልኩ....አይኖኖቼን ገጥሜ
ቀጣይ ስቃዬን መጠባበቅ ጀመርኩ
ሰውዬው ካለሁበት ክፍል ይውጣ አይውጣ ምንም አላውቅም ብቻ ሁሉም
ፀጥ ብሏል...አዛው የተኛሁበት መቅረት
አልፈለኩም እንደምንም በመሬቱ ላይ
ለመንፏቀቅ ሙከራዬን ጀመርኩ ያን ያህል ባልፈጥንም ችዬው መሳቤን ቀጠልኩ ደሜ ከውሃው ጋር ተቀላቅሎ
ወለሉን ጋርዶታል...ክንዴ አካሌን መሸከም ተስኖታል እንደዛም ሆኖ
አልቆምኩም እየተንፏቀኩ ነው በመሃል
እጄን አሟልጮኝ በግንባሬ ወለሉ ላይ አረፍኩኝ ክፉኛ መታኝ...ግን አሁንም
አለሁ አየተነፈስኩ...
በድጋሜ መንፏቀቄን ቀጠልኩ የክፍሉ
ጥግ(ኮርነር) ጋ ሽጉጥ አልኩኝ...
ጉልበቴን ከአገጬ አጋጥሜ በእጆቼ እግሮቼን ይዤ ተቀመጥኩኝ የጀርባዬ
ቁስል ከግድግዳው ሲነካካ ያለው ህመም በዛ ላይ ቅዝቃዜው...አሁን በጥቂቱም ቢሆን እየተረጋጋሁ ነው ግድግዳው ብርዱን እየተከላከለልኝ ነው
አካሌ መንቀጥቀጡን ባያቆምም እንኳ...
ትንፋሼን ወደራሴ አካል እየተነፈስኩ ሰውነቴን ለማሞቅ መኮርኩ ግን አልቻልኩም በጡት ማስያዣና በፓንት ብቻ ሆኜ ቁሩ ከበደኝ...እዛው በተቀመጥኩበት ደቂቃዎች ተቆጠሩ ሰውዬው ግን የለም ቀና ብዬ ክፍሉን
ተመለከትኩት ልብሴ ተበጫጭቆ ወለሉ ላይ ታየኝ ትንሽ ቀና ስል ደግሞ የብረቱ
ወንበር ላይ ከኔ ተቦጭቆ የቀሩው
የሰውነቴ ስጋ ታየኝ አይኔን ወዲያውኑ ከሱ ላይ አነሳሁ መመልከት አልቻልኩም
ሌሎች የሚታዩኝ ነገሮች ቢኖሩ የማሰቃያ
ስለቶች እና አንድ ጠረጴዛ ብቻ ነው...
በድንገት "ግደላት ለምን አትገላትም አንገቷን በጥሰው አካሏን ቆራርጠው ቆዳዋንም ግፈፈው አይኗን መንቅረው
ምላሷን ጎልጉለው ጥፍሮቿን ንቀል
ጡቷንም ቁረጥ" የሚል ሰቅጣጭ እና ተስፋ የሚያስቆርጥ ንግግር በሴት
አንደበት ሲነገር ሰማሁ ትንሿ ሴትዮ መሰለችኝ ልክ ንግግሯን እንዳበቃች
እርምጃው ፈጠን ያለ ኮቴ ወዳለሁበት ክፍል ሲመጣ ተሰማኝ.......


ምዕራፍ 2 .P6...ይቀጥላል.........
            
ከተመቻቹ ÷

                
#𝐑𝐞𝐚𝐜𝐭
                
#𝐂𝐨𝐦𝐦𝐞𝐧𝐭
                
#𝐬𝐡𝐚𝐫𝐞 🙏

 
   ¶ 𝚈𝙴𝙵𝙸𝙺𝙴𝚁 𝙲𝙻𝙸𝙽𝙸𝙲🥀 ¶™🌐

  📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት! 📱     


ልብ አንጠልጣዩ ተከታታይ ትረካ

             ምዕራፍ  2  
#ክፍል 4


...ከኮቴው ጋር ከብዙ ስለቶች መሀል ስለት ሲፈለግ የሚሰማው ድምፅ ጆሮዬ ላይ አቃጨለ ከዛም አብዝቶ ወደኔ
ተጠጋ አንዳች ድቡልቡል ነገር አፌ
ውሴጥ አሰገባ በዚህ ጊዜ በድንጋጤ
አይኔን እስከመጨረሻው ግልጥ አድርጌ
ከፈትኩት ነገር ግን ከመብራቱ በቀር
አንዳች አልታየኝም አፌ ውስጥ የከተተው ነገር ማሰሪያ ነበረውና
ከጭንቅላቴ ጋር የፍጢኝ አሰረው መጮህ እየፈለኩ ግን አልቻልኩም ፍፁም ለስቃይ የታሰበ ነገር ነው አይኖቼን ዘግቼ "የልጅህ የክርስቶስ ደም
ከበረዶም ይልቅ ከበደል ያነፃልና በደል
መተላለፌን በአሪያም ዛሬም ድረስ
ህያው ሆኖ ስለኔ በሚቃትተው ደምህ
አንፃኝ በመንግስትህም አስበኝ" ብዬ
የመጨረሻ ቃሌን ለአምላኬ በልቤ አንደበት ነገርኩት...አይኔን ከድኜ ሞቴን
በመጠባበቅ ነኝ...ድንገት ሰውዬው ቀረብ ብሎ ከላይ የለበስኩትን
በመቀስ እየቆራረጠ ከላዬ ላይ ገፈፈው
በጡት ማስያዣ ብቻ ቀረሁ በድጋሜ ሱሪዬንም መቅደድ ጀመረ ጫማዬንም
አወለቀው ልክ ካልሲዬን ሲያወልቀው
እግሬ ላይ ከነበረው ቁስል ጋር ተጣብቆ
ነበርና ክፉኛ አመመኝ አሁን እርቃኔን ነኝ
ከአይኖቼ የሚፈሰው እንባ ቁልቁል ወደ
ጆሮዬ ይምዘገዘጋል...እላዬ ላይ የበራው
መብራት ለኔ ቅርብ ከመሆኑ የተነሳ ሰውነቴን አግሎታል መላ አካሌን ላብ
ሲጠምቀኝ ይታወቀኛል...ግን ከዚ ሙቀት ውስጥ እላዬ ላይ የደፋው እጅግ
ቀዝቃዛ ውሃ አወጣኝ...የእግሮቼ አውራ ጣቶች ላይ ምን እንደሆን እንጃ ቁንጥጥ
አድርጎ እንዲይዘኝ አደረገ...ሰውዬው ከኔ
ርቆ ሲሄድ ይሰማኛል ግን ከክፍሉ እንዳልወጣ ተረድቻለሁ በመቀጠልም እንደ ማብሪያና ማጥፊያ አይነት ድምፅ
ያለው ነገር ተሰማኝ ቀመቅፅበት
መላ አካላቴን ለሰከንዶች ያህል አርገፈገፈኝ ወዲያውኑ አቆመው መተንፈስ አቃተኝ በአፍንጫዬ ብቻ የሚገባው አየር አልበቃሽ አለኝ አሁንም
በድጋሜ የማብሪያ ማጥፊያውን ድምፅ
ሰማሁት እንደገና አርገፈገፈኝ አሁን ትንሽ
ቆየት አድርጎብኛል ከዛም አጠፋው ደም ስሮቼ በአየር እጦት ክፍኛ ተወጥረዋል
አይኔ አብዝቶ ፈጠጠ ነፍስ ግቢ ነፍስ ውጪ ከባድ ስቃይ የምይዘው የምጨብጠው ጠፋኝ እንደፈለኩ የምምገው አየር አብዝቶ ናፈቀኝ ከየትም
ላላመጠው ነገር...በዚ ሁሉ ጭንቅ ውስጥ ሳለሁ ሰውዬው ሲራመድ በድጋሜ ተሰማኝ ለቅፅበትም ቢሆን ትንሽ መረጋጋት ተሰማኝ...ነገር ግን
ብዙ አልቆየም ነበር ያንን ቀዝቃዛ አካልን
የሚቆርጥ ውሃ በላዬ ላይ ከለበሰብኝ
ከተቀመጥኩበት ብረት ወንበር ጋር የተነካካው የአካሌ ክፍል ውሃ ሲነካው
ህመሙን መቻል አቃተኝ...ወዲያውኑ ያንን ማብሪያ ማጥፊያ በድጋሜ ተጫነ
ውሃው ስቃዬን አባሰው...ያበራውን ሳያጠፋ እየተርገፈገፍኩኝ ውሃውን
ይጨምርብኝ ጀመር ረዘም ላሉ ሰከንዶች
ከቀጠለ በሗላ አጠፋልኝ...አሁን ምንም
የማረግ አቅም አልነበረኝም አየር የተባለ
ጉሮሮዬ ጋር አይደርስም አይኔ ሲገለበጥ
ይታወቀኛል ግን ያልጠበኩት ነገር ሆነ
ሰውዬው አፌ ውስጥ ያስገባውን ነገር
አወጣልኝ ወዲያውኑ አስመለሰኝ እጅግ
ፍጥነት ባለው አተነፋፈስ አለከለኩኝ እየደጋገመ ያስመልሰኛል...አልቻልኩም
አቅሜ ፈፅሞ ተሟጧል...የክፍሉን ዋናውን መብራት አበራውና አይኔ ላይ ተደንቅሮ የነበረውን አጠፋው ከአንዱ ጥግ ቆሞ አተኩሮ ይመለከተኛል ግራ
የተጋባ ይመስላል አይኖቹ አይረገበገቡም የተሰፋፋው ፊቱ ፈፅሞ
አይፈታም ደም የለመዱ እጆቹ ርህራሄ የላቸውም የሰው የማይመስለው ልቡ ምህረትን አያውቅም ብቻ ዝም
ብሎ ይመለከተኛል ለምን እንደሆነ ለኔ ፍፁም ግራ ነው...እንደዚ እንደተፋጠጥን ደቂቃዎች ተቆጠሩ ወደራሴ እየተመለስኩ ስመጣ የራሴ ስጋ ሽታ
ሸተተኝ በኤሌክትሪክ ሾክ ገላዬ ተጠብሶ
ነበር ትንሽ እንደቆየ ገላዬ ላይ ያለው እርጥበት ሲደርቅ ወደኔ መራመድ ጀመረ
የተዘቀዘቀውን ወንበር እንደመጀመሪያው
አስተካክሎ አስቀጠው ከውንበሩ
ጋ የታሰረውን የእጅና የእግር ማሰሪያ ፈታልኝ ከዛም ከፊት ለፊቴ ሁለት እጄን
ይዞ እግሩን ከፍቶ ቆመ ጭንቅላቴን
መሸከም አቅቶኝ አጎንብሻላሁ እጄን በእጁ እንደያዘ ለሰከንዶች ፀጥ ብሎ ከቆየ በሗላ ሳላስበው.....


ምዕራፍ 2 .P5...ይቀጥላል.........
            

ከተመቻቹ ÷

                
#𝐑𝐞𝐚𝐜𝐭
                
#𝐂𝐨𝐦𝐦𝐞𝐧𝐭
                
#𝐬𝐡𝐚𝐫𝐞 🙏

    ¶ 𝚈𝙴𝙵𝙸𝙺𝙴𝚁 𝙲𝙻𝙸𝙽𝙸𝙲🥀 ¶™🌐

  📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት! 📱     


ልብ አንጠልጣዩ ተከታታይ ትረካ


             ምዕራፍ  2  
#ክፍል 3

.. ..አይኔ ያየውን ማመን አቃተኝ "ባርሳ" ነበረች ድንጋጤና ደስታ በአንድ ላይ ተቀላቀሉብኝ ግን አንዲትም ቃል አልተነፈስኩም እሷም እንደኔ የፊጥኝ ታስራለች ፊቷ ላይ የደም ነጠብጣብ ይታየኛል አይን አይኔን እያየች አንባዋ ቁልቁል ወደ ጆሮዋ ይወርዳል አሁን ያለሁበት ሁኔታ ጥሩ ባይሆንም ግን የተስፋ ጭላንጭል ይታየኛል "በአንበሶች ጉድጓድ የተጣለውን ዳንኤልን ያየ አምላክ አይኑም ክንዱም ለኔ እንደማይዝሉ አምናለሁ" ብዬ ለራሴ አውርቼ ባርሳን እያየሁ ጭንቅላቴን ነቀነኩኝ ፊቴን ከሷ ላይ መልሼ በአቧራ ካደፈው መስታወት አሻግሬ ተመለከትኩ አነስ ምትለዋ ሴት የተለያዩ የህክምና መስጫ መድሃኒቶችን ይዛ አረመኔውን ሰውዬ ካላከምኩህ ብላ ትሟገተዋለች እሱ ደግሞ አለመፈለጉን በምልክት ያሳያታል ምን እንደምትለው ለማወቅ ቢቸግርም ብቻ ብዙ ነገር እያወራችው ነው ከወዲያ ወዲህ እየተንጎራደደ የሆነ ነገር ማብሰልሰል ውስጥ የገባ ይምስላል ግራ እጁን ወገቡ ላይ አድርጎ የቀኝ እጁን ደግሞ አፉ ላይ አድርጎ ሌባና መሃል ጣቱን ከፍና ዝቅ እያደረገ ይንጎራደዳል ትልቋ ሴትዮ ቁጭ ብላ ትመለከተዋለች ብቻ አንዳች ነገር እያሰበ ነው ትኩረታቸው ወደኛ ሊሆን እንደማይችል በተረዳሁ ጊዜ ወደ ባርሳ ተመለስኩኝ እሷ አሁንም ወደኔ እየተመለከተች ነበር "ባርሳ" ብዬ ጠራሗት እጅግ ዝግ ባለ ድምፅ "ሜርሲ ደና ነሽ ደግሜ አይሻለሁ ብዬ አላሰብኩም ነበር ከመሞቴ በፊት ስላየሁሽ ፈጣሪዬን አመሰግናለሁ" አለች በእንባ ሳግ በሚቆራረጥና በለዘበ ድምፀት "ሽሽሽሽ እንደዚ አትበይ ባርሳ አይዞሽ ተስፋ አትቁረጪ እስካሁን የቆየሽው ለምክንያት ነው እሱ እኛን ከመግደሉ በፊት ራሳችንን ገለን ልንጠብቀው አይገባም አይዞሽ ባርሳዬ" ስላት ከንፈሯን እየነከሰች እንባዋን ለማቆም መጣር ጀመረች የሷ መበርታት ለኔም አቅም ነው...በድጋሜ አይኔን ወደ ሰዎቹ መለስኩኝ ነገር ግን ማንም አልነበረም ወዲያው አይኔን ወደ ክፍሉ መልሼ የክፍሉን በር ተመለከትኩ ማንም አልመጣም ባርሳን ዝም እንድትል ነግሪያት ለደቂቃዎች ፀጥ አልን ግን አንዳች ነገር አልተከሰተም ለምን እንደው እንጃ ከአይኔ መሰወራቸው ጨንቆኛል "ባርሳ ይሄስ ማነው" ብዬ ጠየኳት አጠገቧ የተኛውን ለማየት ያልተመቸኝን ክፍሉ ውስጥ ያለውን ሌላኛውን ሰው "ባባ ነው" አለችኝ በጣም እንዳዘነች ፊቷ አብዝቶ ይናገራል "ምን ሆኖል በጣም ተጎድቷል እንዴ..." እያልኩኝ ጥያቄዬን ሳልጨርስ ከፍ ባለ ድምፅ "ግደላት" የሚል ድምፅ ሰማሁ አይኔን ወደ መስታወቱ መለስኩኝ ትንሿ ሴትዮ ነበረች ለአረመኔው ሰውዬ ስታወራ የነበረችው ትልቋ ሴት ቁጭ ብላ ትመለከታቸዋለች ወዲያውኑ ሰውዬው እርምጃውን አፍጥኖ በእልህ እኛ ወደነበርንበት ክፍል ሲምዘገዘግ መጣ በሩንም ብርግድ አርጎ ገብቶ ቀጥ ብሎ ወደኔ መጣ ከዛም በራስጌ በኩል ሆኖ የተኛሁበትን አልጋ እየገፋ ወደ ውጪ ይዞኝ ወጣ ባርሳ አይን ላይ ያየሁትን ፍቅርና ፍራቻ ቃል አይገልፅልኝም በትንሿ ሴት መሪነት ወደ ሌላ ክፍል ተወሰድኩኝ ምንም አላልኩኝም ነበር...ክፍሉ ውስጥ ገባሁ እስከዛሬ ያልተመለከትኩት በስለት የተሞላ አስፈሪ እና አሰቃቂ ቦታ ነው ሰውዬው የታሰርኩበትን ቀበቶ መፍታት ጀመረ ልክ እንደጨረሰም አንጠልጥሎ ከአንድ የማይንቀሳቀስ ተለቅ ያለ የብረት ወንበር ላይ አስቀመጠኝ...ወዲያውኑ እጄን ለክንድ ማስቀመጫ ተብሎ ከተሰራበት የወንበሩ ክፍል ጋር አጥብቆ አሰረው ወረድ ብሎም ከመዳፌ ትንሽ ከፍ ብሎ በድጋሜ አሰረኝ እግሬንም እንዲሁ ከወንበሩ ጋር አሰረው አስሮ እንደጨረሰ ከኔ ራቅ ሲል ክፍሉን መመልከት ጀመርኩኝ የተለያዩ የእጅ እና የእግር ጣቶች በየቦታው ተንጠባጥበዋል ጥፍሮችም ጭምር ከተቀመጥኩበት በስተ ቀኝ በኩል ያየሁት ነገር ከምንም በላይ ሰቅጥጦኛል ከአንድ ሰርቢስ ላይ በአንድ ላይ የተቀመጡ የአይን ኳሶች ይታዩኛል በሌላኛው ሰርቢስ ላይ ደግሞ ጆሮና ምላስ ተቀምጧል አጥወለወለኝ አንገሸገሸኝም የማረገውና የምሆነው ጠፋኝ ሆዴ ተላወሰ አስመለሰኝም እዛው በተቀመጥኩበት ራሴ ላይ ለቀኩት ቀና ብዬ ስመለከት ከበላዬ የተለያየ አይነት ቅርፅ ያላቸው መርፌዎች ይታዩኛል ዶክተሮች ለህክምና የሚጠቀሙት መብራትም አለ ሰውዬው ጋውን ለብሶ ወደኔ መጣ የተቀመጥኩበትንም ወንበር ትንሽ ከፍ አድርጎ ወደሗላ አንጋለለው አሁን ካሁን ወደኩኝ ስል ወንበሩ ግን አልወደቀም ነበር አሁን ለመወራጨትም ሆነ ለምንም የማያመች አቀማመጥ ነው ያስቀመጠኝ ዶክተሮች ለቀዶ ጥገና የሚጠቀሙበትን መብራት አበራው አይኔ እሱን መመልከት አልቻለም ነበር ጨፈንኩት ይህ ሰው ሊያሰቃየኝ እንደፈለገ ግልፅ ነው በቀሉን ለመመለስ ይመስላል ከዛም ክፍሉ ውስጥ ይበራ የነበረውን መብራት አጠፋው አይኔን ከፍቼ ግራ ቀኜን ስመለከት አንዳች አልታየኝም የመብራቱ ጉልበት ከፍተኛ ነበር እዛው ባለሁበት አንደበቴን ዘግቼ ፀጥ ብዬ መጠበቅ ጀመርኩ ከሰከንዳት በሗላ ሰውዬው ወደኔ ሲመጣ የእግር ኮቴው ተሰማኝ...

ምዕራፍ 2 .P4...ይቀጥላል.........
            

ከተመቻቹ ÷
                
#𝐑𝐞𝐚𝐜𝐭
                
#𝐂𝐨𝐦𝐦𝐞𝐧𝐭
                
#𝐬𝐡𝐚𝐫𝐞 🙏

    ¶ 𝚈𝙴𝙵𝙸𝙺𝙴𝚁 𝙲𝙻𝙸𝙽𝙸𝙲🥀 ¶™🌐

  📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት! 📱      


ልብ አንጠልጣዩ ተከታታይ ትረካ


             ምዕራፍ  2  
#ክፍል 2

   

...........አይኑ ደም መስሎ በእጁ በደም የተጨማለቀ ቢላ ይዞ ፊት ለፊቴ ቆሟል ከጀርባው የሚንጠባጠበው ደም ወለሉን አጨቅይቶታል በሱሪው ላይ ሳይቀር ይፈስ ነበር ይህ ሰው በሰው ሀይል የሚሞት አይደለም ብዬ ደመደምኩ ከንፈሬ መንቀጥቀጥ ጀመረ ቀስ እያልኩ ወደሗላ ለመሸሽ መሞከር ጀመርኩኝ እዛው የቆመበት ቦታ ሆኖ አይኑን እኔ ላይ ተክሎ አንገቱን ወደ ግራ ወደቀኝ እያደረገ ይመለከተኝ ጀመር እንዴት ፈጥኖ እርምጃ እንዳልወሰደብኝ አንገቴንም እንዳልቀላው ግርምት ሆኖብኛል አራቴ እንደተራመድኩ እሱን የጣልኩበት ጠረጴዛ ጋ ደረስኩ ከዚ በሗላ ለመሸሽም አመቺ አይደለምና ዝም ብዬ በፍርሃት ተውጬ ቆምኩኝ ፀጉሬ ተፈቶ በከፊል ፊቴን ሸፍኖታል የድነሸጋጤ ላብ ያረጠበው ጉንጭና ግንባሬ ላይ ተለጥፏል...ቆሞ ሲመለከተኝ የነበረው አረመኔው ሰው አሁን ወደኔ መምጣት ጀምሯል ይዞት የነበረውን ቢላ ወለሉ ላይ ጥሎ የስንት ሰው አንገት የቀላበትን የደም ጥማተኛውን መጥረቢያ አንስቶ ወደኔ መጠጋቱ ቀጠለ አይኔን ጨፍኜ የአምላኬን ስም ጠራሁ "ዛሬም በአርያም ህያው ሆኖ ስለኔ በሚማልደው ስለ ምድር ሀጢያት በጨካኞች በፈሰሰው ደምህ ነፍሴን ከበደልና ከሀጢያት አንፅተህ በመንግስትህ አስበኝ በልጅህ ልጅነትን አግኝቻለሁና የምህረት አባቴን አንተንም ብቻ በድያለሁና ይቅር በለኝ" ብዬ ፀሎቴን አድርሼ አይኔን ገለጥኩኝ መጥረቢያውን በእልህ አጥብቆ ይዞታል አሁን ነፍሴ መጨነቋን ትታ መች ከስጋዬ እንደምትለይ በጉጉት እየጠበቀች ነው ሞት ፊትለፊቴ ቆሞ ውስጤ ግን ሰላም ይሰማኛል...በቀኝ እጁ የያዘውን መጥረቢያ ወደ ግራ እጁ ቀየረው ከዛም ወደኔ ተጠግቶ በከፍተኛ ሀይል በጥፊ መታኝ አወዳደቄን ስላልተቆጣጠርኩት በጭንቅላቴ ከወለሉ ጋር ተላተምኩኝ እዛው ወለሉ ላይ እንዳለው አይኔን ስገልጥ የማየው ምስል ድብዝዝ ያለ ነበር አይኔ እየተስለመለመ ተከደነ የሚሆነው እስከማይታወቀኝ ድረስ ራሴን ሳትኩኝ...ብቻ እግሬን ይዞ ሲጎትተኝ የሆስፒታሉ መብራት እንደለመደው ሲበራና ሲጠፋ በጭላንጭል ይታየኛል ከደቂቃዎች በሗላ ግን ምንም ማየት አልቻልኩም...ረዘም ላለ ደቂቃ ራሴን መሳቴ የታወቀኝ አምልጬ የየወጣሁበት ሁለቱ ሴቶች ያሉበት ክፍል ራሴን ሳገኝ ነው ይመገቡበት ከነበረው ክፍል ግን የተለየ ነበር እንደነቃሁ ዙሪያ ገባዬን ተመለከትኩ ግን ከሰመመን መንቃቴ መሰለኝ ያስተዋልኩት ነገር የለም አሁንም ራሴን እያዞረኝ ነው በእጆቼ ጭንቅላቴን ልደገፍ እጄን ላነሳ ስል አልንቀሳቀስ አለኝ ከጭንቅላቴ ትንሽ ቀና ብዬ ስመለከት እጄ ከወገቤ ጋር ከተኛሁበት የብረት አልጋ ላይ የፊጢኝ ታስሯል...ሰፋ ያለ ጥቁር ቀበቶ ነበር...ሶስቦታ ላይ ታስሬያለሁ ደረቴ ወገቤጋና እግሬ ጋር ነበር አለለመሞቴ የታወቀኝ አሁን ነው በህይወት መኖሬ እጅግ ደንቆኛል አሁን ዙሪያ ገባዬን ተመለከትኩ እንደኔ የታሰሩ ሁለት ሰዎች ይታዩኛል ነገር ግን ማንነታቸውን መለየት አልተቻለኝም አጠገቤ ካለው ወዲያኛው ክፍል ውስጥ በአቧራ ከነተበው መስታወት አሻግሬ ለመመልከት ሞከርኩ ሁለቱ ሴቶች ከዛ አረመኔ ጋር እየተጨቃጨቁ ይመስለኛል ጠፍሮ የያዘኝን ቀበቶ ለመፍታት ክፉኛ ታገልኩኝ እራሴንም እስክጎዳ ድረስ ተፍጨረጨርኩ ተወራጨሁ ግን ከኔ አቅም በላይ የጠነከረ ነበርና ምንም ማረግ አልቻልኩም አቅሜን ሳውቅ ፍርዴን መጠበቅ ጀመርኩ አረመኔውና ሴቶቹ አሁንም ይጨቃጨቃሉ በኔ ነገር እንደሚሆን ውስጤ እየጠረጠረ ነው ልብሱን አውልቆ የጀርባ ቁስሉን አሳያቸው ትንሿ ሴትም ሁለቱን እዛው ያሉበት ቦታ ትታቸው ክፍሉን ለቃ ወጣች ወዴት እንደሆነ ባላውቅም  በድንገት እኔ ከታሰርኩበት ክፍል ውስጥ "ሜርሲ" የሚል ድምፅ ተሰማኝ በአቧራ ከነተበው መስታወት ባሻገር የላኩትን አይኔን እና ቀልቤን መለስ አድርጌ አብረውኝ ከታሰሩት ሁለት ሰዎች መሃል ስመለከት...


ምዕራፍ 2 .P3...ይቀጥላል.........
            

ከተመቻቹ ÷
                
#𝐑𝐞𝐚𝐜𝐭
                
#𝐂𝐨𝐦𝐦𝐞𝐧𝐭
                
#𝐬𝐡𝐚𝐫𝐞 🙏

    ¶ 𝚈𝙴𝙵𝙸𝙺𝙴𝚁 𝙲𝙻𝙸𝙽𝙸𝙲🥀 ¶™🌐

  📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት! 📱       


ልብ አንጠልጣዩ ተከታታይ ትረካ


       ምዕራፍ  2  
#ክፍል 1   

...........እየቀረበኝ እንደሆነ ኮቴው ይነግረኛል ውስጤ ግን ቅንጣት ፍራቻ አልነበረበትምዝግጁ ነበር እኔ ያለሁበት ጠረጴዛ እጅግ ተቃርቧል ልቤ ባይፈራም የልብ ምቴ ግን አብዝቶ ጨምሯል በእልህ ከንፈሬን ነክሼ ሁኔታውን መጠባበቅ ጀምሬያለሁ ለሚመጣው ነገር ምላሽ ለመስጠት ሙሉ በሙሉ  ነኝ መዳፌ ጠንከር ብሎ ቢላውን ጨብጧል በቀል ውስጤ እንደ ዘይት ይፈላል ቁጭት አንጀቴን ይበላኛል ምሬት ውስጤ ይርመሰመሳል ነገር ግን ሳላስበው እያላበኝ ነበር ከጥቂት እርምጃዎች በሗላ ካለሁበት እና ከተደበኩበት ሰፍራ ደርሷል እኔ ጋር ሲደርስም ቀጥ ብሎ ቆመ ጊዜ ሳያባክን ወዲያውኑ አጎንብሶ ላሲቲኩን ሲገልጠው...................


...በዛው ቅፅበት ወደሌላኛው ጠረጴዛ ስር ቦታ በመቀየሬ አላገኘኝም ነበር...አቋቋሙ ጀርባውን ለኔ ሰቶኝ መቆሙን በተረከዙ ተረዳሁ ከተደበኩበትም ጠረጴዛ ስር ቀስ ብዬ ወደሗላ ለመውጣት ሞከርኩ ከሗላዬ ያለው ነገር ቢኖር ግድግዳ እና ወደ ውጪ የሚያስወጣው መንገድ ብቻ ነው እዚ ቦታ ላይ ቆሜ ሰውዬው በሰከንድ ሽርፍራፊ ቢዞር እና ቢያየኝ የምሸሸግበት አንዳች ነገር የለም...እንቅስቃሴየሰን ለማድመጥ በሚመስል መልኩ በፀጥታ ቆሟል እኔም ካለሁበት ቦታ ፀጥ ብዬ ማሰብ ጀመርኩኝ ከዛም ቀስ አልኩና ገልጦ አይቷቻው ወዳለፈቻው ጠረጴዛዎች ጥንቃቄ በተሞላው መልኩ ቦታ ቀየርኩ ተደብቄ የነበረበት ጠረጴዛ የመጨረሻው ነበርና የመያዝ እድሌ ሰፊ ነበር ቦታ ከመቀየሬ ቅፅበት የመጨረሻውን ጠረጴዛ በእግሩ መትቶ ገለበጠው ወዲያውኑ የያዘውን መጥረቢያ ባለ አቅሙ ወለሉ ላይ አላተመው ይመስለኛል እኔን እንዳገኘኝ እርግጠኛ ሆና ለኔ የሰነዘረው ነው...ነገር የያዘኝ አምላክ ሊተወኝ አይደለምና ተርፌያለሁ...በጣም የተበሳጨ ይመስላል የያዘውን መጥረቢያ በድጋሜ ወርውሮ ከግድዳው ጋር አላተመው...ሰውዬው ከሚፈጥረው ሁካታ በቀር ክፍሉ ጸጥ እንዳለ ነው በጣም በፈጠነ እርምጃ ወደነበረበት ከክፍሉ ሌላኛው ቦታ ሄደ በዚህ ጊዜ ከተሸሸኩበት ስፍራ ወጥቼ ራሴን ሸሽጌ ዙሪያ ገባዬን እየቃኘሁ የያዝኩትን ስለት አሰናድቼ እሱን መከተል ጀመርኩ...አሁንም ቢሆን በላስቲክ የተንጠለጠሉትን መለየት ለኔ ከባድ ነው ድንገት የሰማሁት ድምፅ እርምጃዬን ትቼ እንድቆም አደረገኝ ያ አረመኔ ሰውዬ ያንን የዋይታና የሰቆቃ ጩኸት ድምፅ ከፍቷል ይህን ድምፅ ስሰማ አብዝቼ እረበሻለሁ ጣቶቼ እርስ በእርስ መጨባበጥ አቅቷቸው ይብረከረካሉ ይሄ ድምፅ ድምፅ ብቻ አይደለም አንዳች የድግምት ሃይል አለበት ዋይታው በድንገት ፀጥ አለ ወዲያውኑ የተብረከረኩ ጣቶቼ ፀኑ አብዝተውም ጨበጡ ይህ ዋይታ ተሰምቶ ፀጥ ሲል ድምፅ ሲሰማ የሰውዬውን ፍጥነት አውቀዋለሁ ስለዚም ያለ አንዳች እንቅስቃሴ ባለሁበት ቆምኩኝ ዋይታው ጀመረ ወዲያውኑ አፍንጫዬን በሸፈንኩበት ከፊሉ ጨርቅ ወደ ጆሮዬ የሚመጣውን የዋይታ ድምፅ ላለመስማት ጆሮዬ ውስጥ ጠቀጠኩኝ ከዛም ቀጥ ብዬ ወደሰውዬው አመራሁ ምን እንደሆኑ ያላስተዋልኳቸው የላስቲክ እስሮች ብዛታቸው ወደ ሰላሳ ይጠጋል ወለሉ በእግሬ በርከክ ብዬ አንዱን የፊቴን ክፍል ከወለሉ ጋር አዋድጄ ሰውዬው የቆመበትን ቦታ አየሁት ጀርባውን ሰቶኝ ነው የቆመው በመሃላችን ያለው ልዩነት በጣም ጠቧል ልቤ ከመፍራት ይልቅ የያዝኩትን ቢላ እንድሰነቅርበት ይገፋኛል አንድ ነፍሴ በጥፋም አይገደኝ እያለች ታበረታኛለች ክንዴ ከጎልያድ ክንድ ይልቅ ጉልበታም ነኝ ይለኛል ብቻ አንዳች ሀይል ወደሰውዬው ገፋኝ ያንን አረመኔ ለማጥፋት እግሬ ተንደረደረ ጥርስ እና ጥርሴ በእልህ ተጋጩ የማላውቀው የማልቆጣጠረው ድፍረት ወደፊት ነዳኝ ብዙ ሰው ነፃ እንደሚያወጣ ለሀገሩ ሟች ንጉስ እንደሆንኩም ተሰማኝ አሁን ተጠንቅቄ ተጉዤ ከጀርባው ቆሚያለሁ ቢላውን ጎኔ ላይ ሻጥ አድርጌ አጠገቤ የነበረውን የብረት መዶሻ አንስቼ መሰንዘር ነበር የቀረኝ አደረኩት ጭንቅላቱ ላይ ባለ በሌለ ሃይሌ አሳረፍኩበት ነገር ግን አልወደቀም ነበር ይልቁኑ ዞሮ ሊያየኝ ዳዳው በዚህ ጊዜ ከጎኔ የሻጥኩትን ቢላ አውጥቼ ከማጅራቱ ትንሽ ዝቅ ብሎ ሰነቀርኩበት ከፊቱ የነበረው ጠረጴዛ ላይ በደረቱ ወደቀ ቢላውን ነቅዬ ደጋግሜ ወጋሁት ወጋጋሁት ጨከጨኩት የማቃሰት ድምፅ ያወጣል እንጂ አይጮህም ነበር ነገር ግን ቢላው አላረካኝም የስንቱን ህይወት የቀጠፈበት ያ ነፍሰ በላ መጥረቢያ ብልጭ አለብኝ ቀጥ ብዬም ተወርውሮ ወደ ወደቀበት ስፍራ አመራሁ አነሳሁት እሱ ያረገው እንደነበር መሬት ለመሬት እየጎተትኩ ያንን ሰቅጣጭ ድምፅ እያሰማሁ አንገቱን ቆርጬ ስጋውን ለአሞራ ልመግብ ተዘጋጅቻለሁ መጥረቢያውን ከፍ አድርጌ ትከሻዬ ላይ አስቀምጬ ነፍሱን ከስጋው ልለያት ጠረጴዛው ጋ ስደርስ የማየውን ማመን አቃተኝ ጠረጴዛና ወለሉ በደም ከመጨማለቅ ውጪ ሌላ አንዳች ነገር የለም ሰውዬው በቦታው ላይ አልነበረም በጣም ደነገጥኩኝ አንገቴን ሳላንቀሳቅስ አይኔ እስከቻለው አካባቢዬን ተመለከትኩ እሱ ተኝቶ ከነበረበት ጠረጴዛ አካባቢ የደም ነጥብጣብ አለ የነጠብጣቡ አቅጣጫ ርቆ እንዳልሄዴ ያሳያል ጠረጴዛው ላይ ቢላውም የለም "በቀሉ ይቅርብኝ ራሴን ላድን' ብዬ ከዛ ክፉና አረመኔያዊ ተግባር ከሚፈፀምበት መንደር ተስፋ ቆርጬ ነፍሴን ለማትረፍ እና ለመሸሽ ወስኜ መጥረቢያውን ጥዬ ስዞር...

ምዕራፍ 2 .P2...ይቀጥላል........

ከተመቻቹ ÷
                
#𝐑𝐞𝐚𝐜𝐭
                
#𝐂𝐨𝐦𝐦𝐞𝐧𝐭
                
#𝐬𝐡𝐚𝐫𝐞 🙏

    ¶ 𝚈𝙴𝙵𝙸𝙺𝙴𝚁 𝙲𝙻𝙸𝙽𝙸𝙲🥀 ¶™🌐

  📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት! 📱       

14.8k 0 38 25 170

የጠፉው ሬሳ ምዕራፍ ሁለት ይጀመር የምትሉ እስኪ እጃቹን አሳዩኝ 🖐️🖐️

👍 1k like ሲገባ ይለቀቅላቹሀል።


እንዲያ_ነኝ 🥹

:
:
« ሳቄ መለያዬ ነው። ለመሳቅ መስፈርት የለኝም። ሰዎች በሳቄ ነው የሚያስታውሱኝ። ለመደሰት ትንሽ ነገር የሚበቃኝ ሰው ነኝ። ተው ዝም ብለክ አትገልፍጥ ሲሉኝ ግራ ይገባኛል። አሁን መሳቅ ፈገግ ማለት ምን ችግር አለው እላለሁ። አይገርምም ግን እያደግኩ ስመጣ ግን ነገሮች እየተቀያየሩ መጡ። ሰዎች ቁም ነገር አልባ እና ሁሌም ህፃን አድርገው ይመለከቱኝ ጀመር።
አንተ አይገባህም! አንተ ምን አለብህ? እንተስ የደላው የለም ይሉኛል። ከፍቶኝ እንኳ ከፍቶኛል ስላቸው ከቀልድ ይቆጥሩታል!
ለካ አንዳንዴ ፈገግታና ሳቀ ሰው ያሳጣል! ለካ ከቁም ነገረኛ ለመቆጠር ትንሽ መጨፈገግ፣ ሳቅና ፈገግታን ማፈን ይጠይቃል። አሁን አሁን እንደ ድሮው ባይሆንም እስቃለሁ፣ ግን እንደ ድሮው ሳቄ ቶሎ አይመጣም።
እኔኮ ስንት ነገር በውስጤ አፍኜም እስቃለሁ። የሚያባብለኝ ስለሌለም እንዲሁ እስቃለሁ። የሚጠይቀኝ ባይኖር ሳቅና ፈገግታ ለሚያበዛ ሰው ስለ ልቡ ደህና መሆንና ደስተኛ ስለመሆኑ መጠየቅ ነውር ተደረገ እንዴ እላለሁ። ደስተኛ ነው ተብሎ ተፈርዶበት አድማጭ አጥቶ፣ የልቡን ለማውራት ሲሞክር አትቀልድ እየተባለ እንዲሁ እንደሚስቅ ሰው ግን የሚያሳዝን ሰው ግን አለ? ሃሃሃ… ነገሩ ግን ያስቃል። እኔ ግን አሁንም መሳቅ አላቆምኩ ምኑ ጋር ነው ጥፋቴ እስኪ ንገሩኝ እእእእእ.............

{ ብቻ እኔ እንዲያ_ነኝ! » }


ከተመቻቹ ÷

                 #𝐑𝐞𝐚𝐜𝐭
                 #𝐂𝐨𝐦𝐦𝐞𝐧𝐭
                 #𝐬𝐡𝐚𝐫𝐞 🙏

    ¶ 𝚈𝙴𝙵𝙸𝙺𝙴𝚁 𝙲𝙻𝙸𝙽𝙸𝙲🥀 ¶™🌐


  📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት! 📱


.     ም.1 #የመጨረሻው ክፍል

ልብ አንጠልጣዩ "የጠፋው ሬሳ"

            
  ተከታታይ ትረካ

                
#ክፍል_24

...ላይ ሊያሳርፈው ሲል ራሴን ከሆስፒታሉ ጥግ ላይ ተኮራምቼ ሳላስበው ይዞኝ ከተመመው የሰመመን እንቅልፍ ጉዞ ተመልሼ ከእንቅልፌ ነቃሁ ደህና መሆኔን አላመንኩም ራሴንም ጠርጥሬ ከተቀመጥኩበት ተነስቼ ደጋግሜ ሰውነቴን እየደባበስኩ ደህንነቴን አረጋገጥኩ...እኔ ብዙ ጊዜ ነፍሴን ያስጨነቃትን ነገር ነው በህልሜ ማየው...እየደባበስኩ ደህንነቴን እየተመለከትኩ ሳለ አይኔ የቅድስቴ በድን ላይ አረፈ እዛው እንደተንጋለለ ነበር ማንም አልነካውም ቀስ ብዬ ተጠጋሁ በእጄም እጇን ነካሁት ገላዋ ከቀረዶ በልጦ ቀዝቅዟል የሷን በድን ምን ማድረግ እንዳለብኝ እያሰብኩኝ ሳለ በድንገት የእግር ኮቴ ሰማሁ ወዲያውኑ አጠገቤ ካለው ክፍል ገብቼ ራሴን ከሚመጣው ሰው ሸሸኩኝ እየመጣ የነበረውም ሰው ያ አረመኔ ጨካኝ ገዳይ ነበር በድኑን ሊወስድ እንደመጣ ገመትኩኝ ልክም ነበርኩ ልክ በድኑ ጋ ሲደርስ በርከክ አለና እላዯ ላይ የደረቀውን ደም በጣቱ ፈቅፍቆ ወደ አፉ ሰደደው ቀምሶትም በደም የበለዘ ጥርሱን ፈገግ አደረገ...ከዛም ፀጉሯን ይዞ እያንፋቀቀ መሬት ላይ እየጎተተ ይዟት መሄድ ጀመረ እኔ ካለሁበት ክፍል ትንሽ ራቅ ሲል ርቀቴን ጠብቄ መከተል ጀመርኩኝ በድን ሳይና በደም ስጨማለቅ የመጀመሪያዬ ነው ነገር ግን ከዚህ በፊት ይህን ሁሉ ክስተት እንደተመለከተ ሰው ልቤ ደንዳና ሆኗል...ብቻ አንድ ነገር መሆን አለበት ከዚህ አካባቢ እነዛን ሶስት አረመኔዎች ገድዬ እወጣለሁ ወይ ደግሞ እንደጓደኞቼ እዚሁ እቀበራለሁ ስጋዬንም ይቀራመቱታል እንጂ መቼም ቢሆን አልሸሽም...ትንሽ እንደተጓዘም በህልሜ ወዳየሁት መበለቻ ክፍል ይዟት ገባ ይሄን ሰው ማጥቃት ካለብኝ እንደዚህ ክፍል ሊያመቸኝ የሚችል የለምና እራሴን በጥንቃቄ አዘጋጀሁ ልክ ክፍሉ በር ጋር ስደርስ አንገቴን ወደ ውስጥ አስግጌ ተመለከትኩ ክፍሉ ፀጥ ረጭ ብሏል አንድም ሰው አልነበረም የቅድስቴም በድን የለም ወደ ክፍሉም ዘለቅ ብዬ ገባሁ እስካሁን ያላየሁት የተለየ በር ተከፍቷል ወደሗላም ተመልሼ የሚከተለኝ ሰው አለመኖሩን አረጋገጥኩ በተከፈተው በርም ቀስ ብዬ ወደ ውስጥ ገባሁ ነገር እጅግ የሚሰነፍጥ ከባድ የስጋ ሽታ ክፍሉ ላይ ሰፎበታል ሽታውን መቋቋም ስላልቻልኩ ወዲያውኑ ተመለስኩኝ ከዛም አንድ ሀሳብ አሰብኩኝ ከውስጥ የለበስኩን ቲሸርት ቀድጄ አፍንጫዬንና አፌን ሸፈንኩበት ወደ ውስጥም አመራሁ አልፎ አልፎ ቢሆን ሽታው ወደ ውስጤ ይገባል ነገር ግን ከመጀመሪያው የተሻለ ነበር ይህ ክፍል የተለየ ክፍል ነው እንደሌሎቹ ያን ያህል ብርሃን የለውም ጨለም ያለ ነው...አሁን ሙሉ ለሙሉ ወደ ውስጥ ገብቻለሁ ነገር ግን ከፊት ለፊቴ ከሚታየኝ የላስቲክ መጋረጃ በቀር አንዳች ነገር አይታይም ወደ ላስቲኩም እርምጃዬን ጀመርኩ ቀስ ብዬ ጥንቃቄ በተሞላበት መልኩ ነው እንቅስቃሴዬን የማረገው ከቅድሙ ይልቅ ነበር እየበረታ መጣ ቢሆንም ግን ገዳይን ለመግደል ጉዞ ላይ ነኝ ላስቲኩን ገለጥ አድርጌ ወደ ውስጥ ገባሁ አይኔም ቀድሞ ያረፈው ወደላይ ከተንጠለጠሉት በላስቲክ የታሰሩ ነገሮች ላይ ነበር ምን እንደሆኑ ግን መለየት አልቻልኩም በእያንዳንዱ በተሰቀሉት ነገሮች በታች ለሁላቸውም ጠረጴዛ አለ መስመራቸውን ጠብቀው ነበር በረድፍ የተደረደሩት እየተጓዝኩም ወደ መሃላቸው ተጠጋሁ ወደ አንዱም የታሰረ ላስቲክ ቀረብ ብዬ ስመለከት ውስጡ ነጫጭ የስጋ ትሎች ይርመሰመሳሉ ይሄን ባየው ጊዜ በድንጋጤ ወደሗላ ስመለስ ከአንዱ የላስቲክ እስር ጋር ተጋጨሁ ሲንቀሳቀስም ድምፅ አወጣ በሁለት እጆቼም ይዤ ለማቆም ሞከርኩኝ ነገር ግን ያ ክፉ ሰው ድምፁ ወደተሰማበት ቦታ ሲመጣ ኮቴው ተሰማኝ ይሄንንም ባረጋገጥኩ ጊዜ ከአንዱ ጠረጴዛ ስር ተደበኩኝ የሆነ ስለት መሬት ላይ እየጎተተ እንዳለ ከሚሰማው የሚሰቀጥጥ ድምፅ ተረዳሁ እኔም የያዝኩን ስል ቢላ አሰናድቼ መጠበቄን ጀመርኩ ጠረጴዛዎቹ ረዘም ባለ ላስቲክ ስለተሸፈኑ  ከስር ያለውን ነገር ካልተገለጠ በቀር በቀላሉ አያሳዩም ይሄ ነገር ትንሽም ቢሆን ሰላም ሰቶኛል መሬት ላይ ሲጎተት የነበረው የስለት ድምፅ አሁን ላይ ወደ ጠረጴዛዎቹ ላይ የተቀየረ ይመስላል...ይህንንም ከምሰማው ድምፀሸ ለይቻለሁ...እየቀረበኝ እንደሆነ ኮቴው ይነግረኛል ውስጤ ግን ቅንጣት ፍራቻ አልነበረበትምዝግጁ ነበር እኔ ያለሁበት ጠረጴዛ እጅግ ተቃርቧል ልቤ ባይፈራም የልብ ምቴ ግን አብዝቶ ጨምሯል በእልህ ከንፈሬን ነክሼ ሁኔታውን መጠባበቅ ጀምሬያለሁ ለሚመጣው ነገር ምላሽ ለመስጠት ሙሉ በሙሉ  ነኝ መዳፌ ጠንከር ብሎ ቢላውን ጨብጧል በቀል ውስጤ እንደ ዘይት ይፈላል ቁጭት አንጀቴን ይበላኛል ምሬት ውስጤ ይርመሰመሳል ነገር ግን ሳላስበው እያላበኝ ነበር ከጥቂት እርምጃዎች በሗላ ካለሁበት እና ከተደበኩበት ሰፍራ ደርሷል እኔ ጋር ሲደርስም ቀጥ ብሎ ቆመ ጊዜ ሳያባክን ወዲያውኑ አጎንብሶ ላሲቲኩን ሲገልጠው...................


                 "
#የጠፋው_ሬሳ"
                "
#የጠፋው_ሬሳ"
               "
#የጠፋው_ሬሳ"
              "
#የጠፋው_ሬሳ"

  ምዕራፍ
#አንድ በዚህ መልኩ ተጠናቋል
  ምዕራፍ ሁለትንም ለመቀጠል የእናንተ ፍላጎት ይወስናል በcomment box ውስጥ ተነጋገሩ
         በቅርብ ቀን እንጀምራለን


አስተያየት ወይም ጥያቄ ካላችሁ በውስጥ መስመር አድርሱኝ

👉
@Chanaz_72
👉
@Firaan90

ምዕራፍ 2  ___በቅርቡ....

ከተመቻቹ ÷

                
#𝐑𝐞𝐚𝐜𝐭
                
#𝐂𝐨𝐦𝐦𝐞𝐧𝐭
                
#𝐬𝐡𝐚𝐫𝐞 🙏

    
¶ 𝚈𝙴𝙵𝙸𝙺𝙴𝚁 𝙲𝙻𝙸𝙽𝙸𝙲🥀 ¶™🌐

  📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት! 📱

Показано 20 последних публикаций.