ልብ አንጠልጣዩ ተከታታይ ትረካ
ምዕራፍ 2 #ክፍል 5
...እጆቼን በሃይል ጎትቶ ከተቀመጥኩበት
ምንጭቅ አርጎ አነሳኝ በዚ ጊዜ ከብረት
ወንበሩ ጋር ተገናኝቶ የነበረው የአካሌ
ክፍል እየተቦጫጨቀ ወንበሩ ላይ ቀረ ወለሉ ላይም ወረወረኝ...ጀርባዬ እና ታፋዬ በደንብ የተጎዱ የሰውነት አካሎቼ
ናቸው ወንበሩ ዳማ መሰይ ክፍተት
ባይኖረውማ ኖሮ ቆዳዬ እንደ ሚገፈፍ
አንዳች ጥርጥር የለኝም...
...ስቃዬን ቃላት ችለው አይገልፁትም እዛው ወለሉ ላይ ሆኜ ክፉኛ መንቀጥቀጥ
ጀመርኩኝ ጉልበትና ጭንቅላቴን አጋጥሜ
ኩርምት ብዬ እየተንከጠቀጥኩኝ ሳለ
ይባስ ብሎ አረመኔው ሰውዬ አጥንት ድረስ ዘልቆ ሚሰረስር ቀዝቃዛ ውሃ
እላዬ ላይ ደፋብኝ ስቃዬን በእጥፍ አበዛው፡፡
ገና ያልደረቀ ቁስሌ ነፍሴ ድረስ ዘልቆ
የሚሰማ ክፉ ህመም ሆነብኝ ምንም ቃል
ማውጣት ተስኖኛል ዝም ብቻ ሌላ ምንም
ውሃውን እየደጋገመ ይደፋብኝ ጀመር
...አንዳዴ ሞት እየናፈቁ አለማግኘት በፈጣሪ
እንደመረሳት ይመስለኛል የሞት መልዓክ
ለኔ ሲሆን ዘገየ እንዲ ስሰቃይ እያየ ዝም
ብሎኛል አልጠራው ነገር አቤት አይለኝ
መፈጠሬን እስክጠላ የደስታም ቀን
አሳልፌ የማውቅ እስከማይመስለኝ ድረስ
በወለደኝ ማህፀን ተማረርኩ...
አይኔ ከመከደን በማይተናነስ ሁናቴ በትንሹ ገርበብ ብሎ ተከፍቶ አንባዬን ዝም ብሎ ይሸኛል ከናፍሮቼ
ከጥርሴ ጋር ተስማምተው ይብረከረካሉ
በኤሌክትሪክ የተጠበሰው ገላዬ
አሁን ብርድ እያቆረፈደው ቁስሉም እየመዘመዘኝ ደቂቃዎች በፀጥታ ተጓዙ...
መላ ሰውነቴ ዝሏል ደክሟል ባዘውመም
አይለሰማኝም ለመነሳሳት ስሞክር
አሀሸየደጋገምኩ መውደቅ ጀመርኩ ቢያቅተኝ እዛው ተንንጋለልኩ....አይኖኖቼን ገጥሜ
ቀጣይ ስቃዬን መጠባበቅ ጀመርኩ
ሰውዬው ካለሁበት ክፍል ይውጣ አይውጣ ምንም አላውቅም ብቻ ሁሉም
ፀጥ ብሏል...አዛው የተኛሁበት መቅረት
አልፈለኩም እንደምንም በመሬቱ ላይ
ለመንፏቀቅ ሙከራዬን ጀመርኩ ያን ያህል ባልፈጥንም ችዬው መሳቤን ቀጠልኩ ደሜ ከውሃው ጋር ተቀላቅሎ
ወለሉን ጋርዶታል...ክንዴ አካሌን መሸከም ተስኖታል እንደዛም ሆኖ
አልቆምኩም እየተንፏቀኩ ነው በመሃል
እጄን አሟልጮኝ በግንባሬ ወለሉ ላይ አረፍኩኝ ክፉኛ መታኝ...ግን አሁንም
አለሁ አየተነፈስኩ...
በድጋሜ መንፏቀቄን ቀጠልኩ የክፍሉ
ጥግ(ኮርነር) ጋ ሽጉጥ አልኩኝ...
ጉልበቴን ከአገጬ አጋጥሜ በእጆቼ እግሮቼን ይዤ ተቀመጥኩኝ የጀርባዬ
ቁስል ከግድግዳው ሲነካካ ያለው ህመም በዛ ላይ ቅዝቃዜው...አሁን በጥቂቱም ቢሆን እየተረጋጋሁ ነው ግድግዳው ብርዱን እየተከላከለልኝ ነው
አካሌ መንቀጥቀጡን ባያቆምም እንኳ...
ትንፋሼን ወደራሴ አካል እየተነፈስኩ ሰውነቴን ለማሞቅ መኮርኩ ግን አልቻልኩም በጡት ማስያዣና በፓንት ብቻ ሆኜ ቁሩ ከበደኝ...እዛው በተቀመጥኩበት ደቂቃዎች ተቆጠሩ ሰውዬው ግን የለም ቀና ብዬ ክፍሉን
ተመለከትኩት ልብሴ ተበጫጭቆ ወለሉ ላይ ታየኝ ትንሽ ቀና ስል ደግሞ የብረቱ
ወንበር ላይ ከኔ ተቦጭቆ የቀሩው
የሰውነቴ ስጋ ታየኝ አይኔን ወዲያውኑ ከሱ ላይ አነሳሁ መመልከት አልቻልኩም
ሌሎች የሚታዩኝ ነገሮች ቢኖሩ የማሰቃያ
ስለቶች እና አንድ ጠረጴዛ ብቻ ነው...
በድንገት "ግደላት ለምን አትገላትም አንገቷን በጥሰው አካሏን ቆራርጠው ቆዳዋንም ግፈፈው አይኗን መንቅረው
ምላሷን ጎልጉለው ጥፍሮቿን ንቀል
ጡቷንም ቁረጥ" የሚል ሰቅጣጭ እና ተስፋ የሚያስቆርጥ ንግግር በሴት
አንደበት ሲነገር ሰማሁ ትንሿ ሴትዮ መሰለችኝ ልክ ንግግሯን እንዳበቃች
እርምጃው ፈጠን ያለ ኮቴ ወዳለሁበት ክፍል ሲመጣ ተሰማኝ.......
ምዕራፍ 2 .P6...ይቀጥላል.........
ከተመቻቹ ÷
#𝐑𝐞𝐚𝐜𝐭
#𝐂𝐨𝐦𝐦𝐞𝐧𝐭
#𝐬𝐡𝐚𝐫𝐞 🙏
¶ 𝚈𝙴𝙵𝙸𝙺𝙴𝚁 𝙲𝙻𝙸𝙽𝙸𝙲🥀 ¶™🌐
📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት! 📱