🔸🔸🔺🔺🔹🔸
❤️ የፍቅር ጥግ ❤️
ልብ አንጠልጣይ እውነተኛ ታሪክ ❤️
ፀሀፊ ✍️ ማኔ
ክፍል 3️⃣5️⃣
ግን መቆየት አልቻልኩም ምራቄን እራሱ ለመዋጥ አቃተኝ ደሞ ጠረኗ ደስ ይላል።
አስራ ምናምን ደቂቃዎችን ታገልኩና እጆቼን ከላይዋ ላይ አንስቼ ፊቴን ላዞር ስል በማርያም ትንሽ ደቂቃ ብቻ እቀፈኝ በእቴቴ ይዤሀለሁ አለችኝ።አልተኛሽም እንዴ አልኳት።ተኝቼ ነበር ግን ስነሳ እዚህ ሁኔታ ውስጥ እራሴን ሳገኘው መተኛትን መረጥኩ አለችኝ።ስለዚህ አንቺም እኔም እያስመሰልን ነበር አልኳት። አዎ ለደቂቃዎች ከራስጋ ስትታገል እያየሁ ነበር እኔ ደሞ አቅፈኸኝ ትንሽ ደቂቃ እንድትቆይ እየፀለይኩ ነበር አለችኝ።
ይሄን ዋጋ አለው እንዴ እኔ አንቺን ማቀፌ ብዬ ጠየኳት፡፡ ምናልባትም አንተ ከምታስበው በላይ ለኔ ዋጋ አለው እኔ ደሞ በተፈጥሮዬ መታቀፍን ምወድ ሰው ነው የሆነ ሰው ሲያቅፈኝ ሰላሜን እየሰጠኝ ይመስለኛል።
በምወደው ሰው መታቀፍ ደሞ ለኔ ህልም ነው አለችኝ፡፡ ዝም ብያት ተነሳሁና ቆምኩ ትገርማለህ በእቴቴ
ይዤሀለሁ እያልኩህ ለማንኛውም እሺ ብላ ፊቷን አዙራ ተኛች።
ስታኮርፍ በራሱ ሌላ ውበት አላት ከፊት ለፊቷ ቆምኩና እሺ ነይ ተነሽ አቅፌ ሳሎን ልውሰድሽ አልኳት ዘለለች መጥታ ተጠመጠመችብኝ ደረቴ ላይ እንደህፃን ልጅ ልጥፍ ብላ አንገቴ ስር ውሽቅ አለች። በሁኔታዋ ፈገግ እያልኩ ወደሳሎን አቅፌ ወሰድኳት ሶፋ ላይ ውረጂ ብላት አሎርድም አለች በእጇ አጥብቃ ከመያዟ የተነሳ አንገቴን ህመም ተሰምቶኝ ነበር።
አረ ደከመኝ ብዬ እንድትወርድልኝ አደረኩና እኔ ቁጭ ከልኩ። እሷ ወደስልኳ ሄደች በስማም ስንቴ እንደተደወለ መጣሁ ቆይ እናቴን ላውራት ብላ ወደውጭ ወጣች።
ብዙም ሳትቆይ እዮብን ይዛው ወደውስጥ ገባች፡፡ እንዳየኝ መጣና ሰላም አለኝ።
እኔ ፊቴን እንደጣልኩት ዝም ብዬ ቁጭ አልኩ ልእልት አውሩ በሉ እኔ ምግብ ልስራ አለችና ወደውስጥ ገባች፡፡
እዮብ ሁሉንም ነገር አስረዳኝ ገና ጎዳና ላይ ብዙ አመት ስትቆይ ምትለምደው ብዙ ነገር አለ።ፊት ለፊትህ ሰው ሲታረድ እያየህ ባላየ ልታልፍ ትችላለህ ምንም የማያውቁ ህፃናት የሰቆቃ ድምፃቸውን እያሰሙ እየለመኗቸው ያለምንም ርህራሄ ሚደፍሩ ብዙ የጎዳና ልጆች አሉ አለኝ፡፡ ትንሽ ተረጋጋሁ እዮብ መረጋጋቴን ሲመለከት ዞር ዞር እያለ ቤታችንን ማደናነቅ ጀመረ፡፡
ቀጠል አድርጎ ወደ ልእልትጋ ገባና አብረው እየተሳሳቁ ምግም መስራት ጀመሩ እኔ ላጨስ ወጣሁ ውጭ ላይ ቁጭ ብዬ ሳብ ሳብ አደረኩና ሲጋራውን ጣልኩት፡፡ ትንሽ ቆይታ ልእልት መጣችና አስደነገጥከኝኮ ና ምሳ ደርሷል አለችኝ ተከትያት ገባሁ ከምሳ ቡሀላ ልእልት ልታወራኝ ምትፈልገው ጉዳይ እንዳለ ነገረችኝ።
ምን እንደሆነ ጠየኳት።
ምን እንደሆነ ጠየኳት። አሁን የእቴቴ ሙት አመት እየደረሰ ነው እና ዘመዶቻችሁ እሱ እየደገሱላት ነው።
ልክ ሙት አመት ፕሮግራሙ እንዳለፈ ግን ይዠየዚህን ቤት ጉዳይ ወደፍርድ ቤት ሊወስዱት አስበዋል። አንተ ቤት ውስጥ ስለማትኖርና አልፈልግም ብለህ ሀገር ጥለኽ ስለጠፋህ ቤቱ ተዘግቶ ከሚኖር እነሱ ቢጠቀሙበት እንደሚሻል አውርተው ጨርሰዋል።
ባለፈው አክስትህ መጥታ ነበር እና ሁሉንም የነገረችኝ እሷ ናት ከቻልክ ይሄ ቤት እቴቴ ላንተ የተወችልህ ትልቁ የህይወት አደራ ስለሆነ የሆነ መፍትሄ እንድትፈልግ ነው እንደኔ እንደኔ እንደምንም ብለህ ተመልሰህ እዚህ ቤት መኖር አለብህ አለችኝ
ይቀጥላል...
🔻ክፍል3️⃣6️⃣ከ 1️⃣5️⃣0️⃣ like በዃላ ይቀጥላል... ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like💝 ማድረግ አይርሱ።
🔺🔺🔺🔺🔺😀😀😀😀😀
ይ 🀄️ላ🀄️ሉን! 😀
💔 https://t.me/yefikirtelegramet 💔