🔸🔸🔺🔺🔹🔸
❤️ ኢላሪ (እውነተኛ ታሪክ) ❤️
ልብ አንጠልጣይ እውነተኛ ታሪክ ❤️
ፀሀፊ ✍️ህሊና
ክፍል 1️⃣1️⃣
ወደ ውጪ ወጣው ምሆነው ግራ ገባኝ።ወንበር ፈልጌ ቁጭ አልኩ።ትንሽ ቆይታ ፕኑ መታ አጠገቤ ተቀመጠች።...ኢላሪ አሁን መግባት አለብሽ ሀኒ ኢላሪን ጥሩልኝ እያለች ነው እሺ ብዬ ሄድን።በሩን ከፍቼ ገባው።ሀኒም ነይ እኔጋር አለችኝ ሄጄ አጠገቡዋ ቁጭ ከአልኩ።ፕኑም ብድግ ብላ ኑ እኛ ወጣ እንበል ብላ ይዛቸው ወጣች።
ሀኒ እያለቀሰች ኢላሪ አለችኝ እጇን አጥብቄ ይዤ...ሀኒ ይቅርታ ምንም ልልሽ አልችልም ይቅር በይኝ....ኢላሪ አንቺ ምን አደረግሽ ....አላውቅም ግን ዳንም ትልቅ ስህተት ሰርቷል ብዬ ሳልጨርሰው አቋረጠችኝ።...ስሚኝ ኢላሪ ዳንም ምንም አላደረገም ፍቅር እኮ ነው ፈልጎ አይደለም ኢላሪ ስለ ፍቅር ብዙ ያልተረዳሽው ነገር አለ።
በቃ የሆነው ሆኑዋል አለችኝ።ዳን በሩን ከፍቶ ገባ።ስካሩ ትንሽ በረድ ብሎለታል።እኔም እንባዬን ጠርጌ ተነሳው ዳን ሄዶ እኔ የተነሳውበት ቦታ ተቀመጠ።የሀኒን እጅ አጥብቆ ይዞ ...ምንድ ነው ሀኒ ምን ሆነሽ ነው አላት እሷም በውስጧ ያለውን ደብቃ ዋጥ አድርጋ...ደህና ነኝ ሰሞኑን ኢላሪም እኔም ተከታተልንባችሁ አይደል አለች ፈገግ ብላ።ዳንዬ ደህና ነኝ ድካም ነው እሺ አለችው።
ሀኒ ከሆስፒታል ከወጣች አራት ቀን አለፋት።በነዛ ቀናት ከነእዮባ ጋር ተገናኝተን አናውቅም።ዛሬ ከአቤል ጋር ቁጭ ብለን ...ሰሞኑን ግን ምን ሆነሽ ነው አለኝ ...ምን ሆንኩ...እንደ በፊቱ አይደለሽም...ምንም አልሆንኩም መስሎክ ነው እሱን ተወውና ቤዛ እንዴት ናት አልኩት። ፈገግ ብሎ ....ደህና ናት ...እንዴት ነው ታዲያ ፀባዩአ ምናምን ...እረ ኢላሪ የእውነት ሴት ናት ሴት የሚለው ቃል በስርአት ይገልፃታል።
እረረ አንተ ልጅ ገባልክ እንዴ ...እረ አንደዚህ አይነት ነገር የለም...ለምን ምርጥ ልጅ ናት ደግሞ እሱዋም ተመችተሀት ይሆናል።....ዝም በይ ባክሽ ቤዛማ ትወደኛለች ከአይኑዋም ከሁኔታዋም ተረድቻለው ባንቺ ቤት ደብቀሽላታል...አንተ ደግሞ እሺ ለምኝ አብራችሁ አትሆኑም....አልችልም ኢላሪ..ለምን ...አላፈቅራትማ በጣም እጠነቀቅላታለው እቺን ልጅ ጎድቼ ከመላአክ ሴጣን ላደርጋት አልፈልግም።
ማታ እናቴ ደወለች እያወራሁዋት ነገ ስራ እንደማትገባ ስትነግረኝ አንድ ሀሳብ መጣልኝ።እኛም ነገ ክላስ የለንም ደግሞ አያቴም አለች የምንሄድበት የለም አልኩ እና ነገ ከጉአደኞቼ ጋር እንደምመጣ ነገርኳት ደስ አላት በቃ ነገ እንደምንመጣ ነግሪያት ቻው ብያት ዘጋውት።
ነገ የምወስዳቸው ቦታ እንዳለ ነገርኳቸው የት ሲሉ ነገ ታዩታላችሁ ብዬ ተኛው።በነጋታው ከሰዓት ወደ 6 ሰዓት ወተን ጉዞ ወደ እኔ ቤት ጀመርን።ልክ በሩጋር ስንደርስ የት ነው አንቺ ሲሉኝ በሩ ተከፈተ ኑ ብዬ አስገባዋቸው። አፋቸው አያርፍም በቃ አንቺ ያበደ ቤት ነው እያሉ ገቡ።እማዬን ሳያት እማ ስል ሁሉም እኩል ምን አሉ ዞር ብዬ...ምነው የእኔ ቤት ነው እኮ ነው ሀኒም ቀበል አድርጋ...አንቺ ምነው ታዲያ ባዶ እጃችንን አለች ...ነይ ባክሽ ብዬ ሁሉንም ከእናቴ እና ከአያቴ ጋር አስተዋወኩዋቸው።
አያቴ ፈታ ያለች ናት ስታፍታታን ውለን ሰዓት ሲደርስ ለመሄድ ተነሳን።እናቴ እና አያቴን ተሰናብተን ልንወጣ ስንል አያቴ ጠርታ ግንባሬን ሳመችኝ እኔም ደግሜ ስሚያት ቻው ቦዬ ወደ ጊቢ ሄድን።ምሽቱን ቁጭ ብለን ስናወራ አደርን።
ጠዋት ላይ የእናቴ የስልክ ጥሪ ነበር የቀሰቀሰኝ።የደወለችውም አያቴ ለሊት ታማ ሆስፒታል መግባቷን እና እኔን እንዲያመጡ እየጠቀች መሆኑን ነገረችኝ።በድንጋጤ ተነስቼ ልብስ መቀየር ጀመርኩ።ለጉአደኞቼ ነገርኳቸው አብረንሽ ካልሄድን ሲሉ ከባድ ነገር ከለ እንደምጠራቸው ነገርኳቸው ግን ሀኒ ድርቅ አለች እሄዳለው ብላ እሺ ብዬ አዲስ ነገር ካለ እንደምናሳውቃቸው ነግረናቸው ከሀኒ ጋር ወጣን።
ልክ ሆስፒታል ስደርስ በር ላይ እናቴ አባቴ አክስቴ ምናምን አሉ።ስለደነገጥኩ ሰላምታ ሳልሰጣቸው እናቴ ጋር ሄድኩ።የእናቴ ፊት ቲማቲም መስሏል...እማዬ አያቴስ እናቴ የት ናት ስላት እዚ እየጠበቀችሽ ነው ብላ ይዛኝ ገባች።
አያቴን ሳያት ደነገጥኩኝ ትናንት አብሪያት የነበርኩዋት አይደለችም ግርጥት ብላለች።እየሮጥኩ ከአልጋው አጠገብ ደረስኩ።አጠገቡዋ ቁጭ አልኩኝ።አይን አይኑዋን እያየው...እናቴ ምንድነው አያቴ እናቴ ምን ሆንሽብኝ ጠንከር በይልኝ እኔ ያላንቺ አልችልም እማ እያልኩ መንሰቅሰቅ ጀመርኩ።እንደምንም ብላ ....የኔ ልዕልት ቶሎ በይ በvideo call ሚኪ ጋር ደውይልኝ አለችኝ።ሚኪ ማለት እናቴ አንድ ወንድም እና አንድ ወንድም ነው ያላት።ሚኪ ደግሞ የእናቴ ወንድም ልጅ ነው።
አሁን አሜሪካ ነው አጎቴም ባለቤቱሞ እዛ ከአያቴ ጋር ነበር የሚኖሩት።ሚኪ አሜሪካ ከመሄዱ በፊት አብረን ነው ያደግነው በጣም ነው ምንዋደደው ከሄደ በሁዋላም በቀን አንዴ ሳናወራ አንቀርም ነበር።ጊቢ ስገባ ግን እኔም ቢዚ ሆንኩ እና ተጠፋፋን ወደዛ ሲሄድ 17 አመቱ ነበር። እሱ አሁን 24 አመት ይሆነዋል እኔ ደግሞ 20።
አያቴ በጣም ነው ምትወደው በእኔና በእሱ ቀልድ አታውቅም።እንዳለችውም ለሚኪ ተደወለላት እሱ ደንግጦ ሁኔታዋን እየጠየቃት ነው እሷ እንደምንም እያቃሰተች ...አንድ ትልቅ ቤት አለኝ እሱ ቤት ያንተ እና የኢላሪ ነው።ድሮም በእናንተ ስም ነው።ልላው ሀብቴን እንደፈለጉት ይሄን ግን በወረቀት አስፍሬዋለው እሺ ልጄ አለችው።
አያቴ ተይ እንዲ አትበይ እያልኩኝ ድንገት ዝም አለች።እየጮኩኝ ዶክተሩን ጠራውት እኔን ጎትተው አስወጡኝ።ዶክተሩ ወጣ አሉ ነፍሳቸው አለ ግን ለሚሆነው ነገር እራሳችሁን ነገር አዘጋጁ ጠንከር በሉ ብሎ ሄደ። ትንሽ ተረጋጋው እዚው ሆስፒታል ሀኒ ከጎኔ ሆና አሳለፈች።ሚኪ እና ቤተሰቦቹ ወደ ኢትዮጵዪ ሊመጡ ነው።እንደምንምንም ነጋ ቁርስ ከበላን በኃላ ሀኒን ሂጂ ብላትም ልትሰማኝ አልቻለችም።
ለሊት 10 ሰዓት ላይ አያቴ ያለችበት room መግባት ስለማይቻል በመስታወት አይቻት እንቅልፍ እንቢ ስላለን ለመናፈስ ከሀኒ ጋር ወጣን።ትንሽ ተናፍሰን ወደ ውስጥ ተመለስን። ልክ ስንገባ ግን እናቴ መሬት ላይ እናቴ እያለች ታብዳለች ሁሉም እያለቀሱ ነው።እየሮጥኩኝ አያቴ የነበረችበት ክፍል ስገባ አያቴን በጨርቅ ሸፍነዋታል ነርሷም ዞር ብላ ..ይቅርታ የእኔ እመቤት መግባት አይቻልም እያለች ትገፋኝ ጀመር።እሷን ገፍትሬ አያቴን የሸፈኑበትን ጨርቅ ገለጥኩት።
አይኑዋ ተሸፍኑዋል አበድኩ ጎትተው አስወጡኝ።የሆነ ሰዓት ሰማይ ምድሩ ዞረብኝ ብዠ አለብኝ።አይኔን ስገልጥ ግሉኮስ ተደርጎልኝ ተኝቻለው።እሱን ነቅዬ እየሮጥኩ አያቴ ጋር ሄድኩ ግን አያቴ አልነበረችም።የቀብር ቀኑዋም ደረሰ እነ ሚኪም ሳይመጡ አትቀበርም ተብሎ አንድ ቀን አድራ ተቀበረች።ሚኪ እንደመጣ ጥምጥም ብዬበት እንደጉድ ተላቀስን።ብሩኬ አቤላ ዳን ልዑሌ እናም ጉአደኞቼ የአቤላ ጉአደኞችም ለቅሶ ደርሰው መተው ተሰናብተውኝ ሄዱ።
አያቴ ከሞተች በኃላ ሰው መሆን አቃተኝ ታመምኩ ሆስፒታል ገባው።ዊዝድሮው ልሞላ ነበሮ ግን አባቴ አይሆንም ብሎ ጊቢ የሚያውቃቸው ሰዎች ስለነበሩ እነሱን አናግሮልኝ ፍቃድ ተቀብሎ ስመለስ ያመለጠኝን እንደምሸፍን ነግሮ አስፈቅዶልኝ መጣ።