🔸🔸🔺🔺🔹🔸
❤️ የፍቅር ጥግ ❤️
ልብ አንጠልጣይ እውነተኛ ታሪክ ❤️
ፀሀፊ ✍️ ማኔ
ክፍል 5️⃣
እንዲሁ እየተወዛገብኩ ካሁን ካሁን ደወለች ወይ መልእክት ላከች ብዬ ስልኬን እያየሁ ቤት ደረስኩ።
ቤት ስገባ የጎረቤታችን ልጅ ከእማዬጋ ቁጭ ብለው ከት ብለው ይሳሳቃሉ እኔ ስገባ ግን ልጅቷ ሳቋም ጥፍት አለ ከተቀመጠችበት ብድግ አለችና በቃ ክላስ እረፈደብኝ እቴቴ ቻው ብላት ቀና ብላ እንኳን ሳታየኝ ወጣች ከመጀመሪያውም ተናድጄ ስለነበር ለእናቴ ቆይ ይቺ ዘገምተኛ ልጅ ግን ያማታል እንዴ ምንድነው እኔ ስገባ እያሮጠ ሚያስወጣት ልጠልዛት እንዴ አልኳት።
አይ እንግዲ ስርአት በሷ ቀልድ የለም ልጄ እንደው እስከዛሬ ብዙ ሰው አውቃለሁ ግን እንደሷ ንፁህ ልብ ያለው ምስኪን ልጅ አይቼ አላቅም ልቧ ከእንቁ የከበረ ነው ውስጧ እንደወተት ነጭ ነው ክፋት አይቶት አያቅም አደራህን እንደው ካፍህ ክፉ ቃል ወጥቶ እንዳታስቀይማት አደራ አለችኝ።
እሺ በቃ ልተኛ ነው ብዬ ልገባ ስል ና ቁጭ በል በምን ተናደህ ነው አለችኝ
ነገሩን ነግሪያት የባሰ ከሷጋ መጨቃጨቅ ስላልፈለኩ አረ ደክሞኝ ነው እማ እረፍት ላድርግ በናትሽ እእ ትንሽ ብቻ ብያት ገብቼ ተኛሁ ወዲያው ስልኬ ላይ መልእክት ገባልኝ ።
ካሁን ቡሀላ አላስቸግርህም ቃሌ ነው ደህና ሁን ይላል።
አይቼው ዝም አልኩኝ።
ግን ነገሩ ከሶስት ቀን አላለፈም ነበር ደግማ መልእክት ላከች< እውነት ለመናገር ልረብሽህ ፈልጌ አልነበረም ግን ከዚህ በላይ ዝም ማለት አልቻልኩም ከፈለክ አውራኝ ከደበረህ ዝም በለኝ> ብላ ላከችልኝ።
እስከማታ ዝም ብያት ቆየሁና እኔ ዝም ብልሽ አንቺ ዝም ትይኛለሽ አልኳት።
አይ እኔ ዝም አልልህም እስከሞት ድረስ ላንተ እፋለማለሁ አለችኝ።
በቃ ያንን መልእክት ካየሁ ቡሀላ መሳቅ ማቆም አቃተኝ በትርፍ ሰአትሽ ኮሜዲ ትሰሪ ነበር እንዴ ብዬ መለስኩላት።
ከብዙ መዘጋጋት ከዛ መልሶ ማውራት ቦቻ ከብዙ ልመና ቡሀላ እኔም እየለመድኳት መጣሁ ።
ተቀጣጠርንና በድጋሜ ተገናኘን እንደተለመደው ውብ ሆና ነበር የመጣችው ቁጭ አድርጌ ሁሉንም አወራኋት ከልጅነቴ ጀምሮ ፍቅረኛ ኖሮኝ እንደማያቅ እናቴ ኮራ ጀነን ያልኩ ወንድ እንድሆን አድርጋ እንዳሳደገችኝ በህይወቼ አንድም ቀን አፍቅሬ ወይም የፍቅር ስሜት ተሰምቶኝ እንደማያቅ ነገርኳት።
በቃ የልብህን ድንግልና ለኔ ስጠኝና ዘላለሜን እንደፋኖስ እያበራሁልህ አብረን እንኑር አለችኝ።
እንደዚህ ስተለኝ በድጋሜ ከት ብዬ ሳኩና ልብም ድንግልና አለው እንዴ አልኳት።
ቀላል አሁን ምላሽህን ንገረኝ አለች።
ባሁን ሰአት ምንም ልላት እንደማልችልና ግን እንደስከዛሬው እንደማልዘጋት እንደጓደኛ እንደምቀርባት ምናልባት ለሷ የፍቅር ስሜት እንዲሰማኝ ካደረገች አብሪያት እንደምሆንና ያንን ማድረግ ካልቻለች ግን እንደምንለያይ ነገርኳት።
በራሷ በጣም እርግጠኛ ነበረች አታስብ ማመን እስኪያቅትህ ድረስ በቅርብ ጊዜ ውስጥ ነው ፍቅር የሚይዝህ አለችኝ።
ኮንፊደንሷ ደስ እንደሚል ነግሪያት አብረን ጊዜ አሳለፍን።
ከዛ ቀን ቡሃላ ጠዋት በእናቴ ፈንታ ከእንቅልፌ ምትቀሰቅሰኝ እሷ ሆነች ምሳ ሰአት እንኳን ምሳ መብላት እንዳለብኝ ምታስታውሰኝ እሷ ሆነች።
በተገናኘን ቁጥር የሆነ ስጦታ ይዛልኝ ትመጣለች ።
በፍፁም ያልተገባ ነገር አታደርግም ረጋ ያለች ናት ከኔጋ አብራኝ እየሄደች በተአምር አይኗ ሌላ ወንድ ላይ አያርፍም።
አክብሮቷ ላቅ ያለ ነው እኔ አጥፍቼ ቀድማ ይቅርታ ምትጠይቀኝ እሷ ናት አትወደኝም እንዴ ብዬ እስክጠራጠር ድረስ ትልቅም ትንሽም ጥፋት ባጠፋ ቀድማ ይቅርታ ትጠይቀኝና ሼም ታሲዘኛለች።
ስራ ቦታ ካሉት ጓደኞቼጋ ካስተዋወኳት ጊዜ ጀምሮ ሁሉም ጓደኞቼ በጣም ነው ሚወዷት ስትመጣ በፍቅር ነው ሚቀበሏት እኔም እንዳለችው እሷን ለማፍቀር ብዙ ጊዜ አልፈጀብኝም ነበሮ ግን የፍቅር ስሜት በራሱ ምን እንደሆነ ስለማላቅ ከራሴ ስሜትጋ እየታገልኩ ነበር የቆየሁት።
በመጨረሻም እኔ እራሴ አብረን እንድንሆን ጠየኳት።
(እናቴ ከልጅነቴ ጀምሮ የሰው ልጅ አጥብቆ የፈለገው ነገር መጥፊያው ነው ትለኝ ነበር)
.
.
.
ይቀጥላል
10 ሰው ከታች ያለውን ሊንክ start ካደረጋችሁ ክፍል 6 አሁን ይለቀቃል ፍጠኑ
(ሊንኩ ምንድን ነው ለምትሉ አዲስ game ነው መስራት እምትፈልጉ ይጠቅማችዃል ስሩ መስራት እማትፈልጉ ደግሞ start በማድረግ አብሮነታችሁን አሳዩን)
http://t.me/zoo_story_bot/game?startapp=ref930303744
🔻ክፍል 6️⃣ከ 1️⃣5️⃣0️⃣ like በዃላ ይቀጥላል... ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like💝 ማድረግ አይርሱ።
🔺🔺🔺🔺🔺😀😀😀😀😀
ይ 🀄️ላ🀄️ሉን! 😀
💔 https://t.me/yefikirtelegramet 💔