የፍቅር ታሪክ 🇪🇹


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: не указана


🌹የተለያዩ ታሪካችን ያገኛሉ 🌹

➴ ለአስተያየት➴ @Rominya_1
Since 2011 E.C.

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
не указана
Статистика
Фильтр публикаций


⚠️Free ተለቋል።✅✅✅✅
ቤቲንግ ለጠመመባቹ ብቻ።

ከኛ ጋር የማይቻል ይቻላል
ድንቅ አዲስ ቻናል፣ ምን ትጠብቃላቹ፣ ተቀላቀሉ እና የድሉ ተካፋይ ሁኑ።ተቀላቀሉን 👇👇

➡️ https://t.me/+TNYsWI6KKio3Njdk


አዲስ የኢትዩጲያ ሆር ፊልም ወጣ ወጣ ወጣ ይላል ፊልሙን ለማግኘት ቶሎ በሉ
👇👇👇👇👇👇


❤️ተማሪዋ❤️



🌹…………ክፍል 50 ………..🌹

የመጨረሻ ክፍል

" ምን እያልሽ እንደሆነ እንኳን ለኔ ለራስሽም የሚገባሽ አይመስለኝም ቃልዬ ፣  ዛሬም ዛኪን እንደምታፈቅሪው  ብቻ ነው የገባኝ አሁን ያልሽኝን ልረዳውም ላምንሽም አልችልም ።

መቼም እንዳላምንሽ አርገሽ ልቤን ሰብረሽዋል አሁን የምፈልገው ከዚህ በላይ ምንም ክፍ ቃል ካፌ ሳይወጣ እንድትሄጅልኝ ብቻ ነው" አልኳት።  ቀና ብዬ ቃልዬ ስትሄድ ላለማየት እንዳቀረቀርኩ።
ረጅም ደቂቃ እያለቀሰች ቆየች። ከዝምታ ውጪ ምንም አላልኩም።
"ኤፍዬ ይቅርታ እሺ" ብላኝ እያለቀሰች ቤቱን ለቃ ወጣች።

እኔም ወጣሁ። ታምሜ ተኛሁ።

አስር ቀን ሙሉ ምን እንወሆነ በማይታወቅ በሽታ  ታመምኩ  ስራ አልሰራሁም ። የቃልዬ ምርቃት ቀን እንደምንም ተነስቼ ቀደም ብዬ የገዛሁላትን ስጦታ እና አበባ ይዤ ወደ ግቢ ሄድኩ።
ከቤተሰቦቿ መሀል ሆና ከግቢ እንደወጡ ከጀርባ ጠጋ አልኩና
"ቃልዬ" ብዬ ጠራኋት።
ዘወር ብላ እንዳየችኝ ከቆመችበት አልተንቀሳቀሰችም ። ቤተሰቦቿ ወደፉት እየሄዱ ነው። ቃልዬ እዛው ቆማ እያየችኝ በዝግታ እየተራመድኩ አጠገቧ ስደርስ እነዛ አይኖቿ ላይ ያቀረረው እንባ በጉንጯ ላይ ቀልቀል ወረደ።
ስጦታዋን ሰጠኋት። ተቀበለችኝ። አመሰግናለሁ ሳይሆን  ምናልባትም ለአስረኛ ግዜ•••
"ኤፉዬ ይቅርታ እሺ" ነበር ያለችኝ።
ፉቴን መልሼ ካጠገቧ ሄድኩ። ምናልባት ቃልዬም ከአንድ ከሁለት ቀን በሁዋላ ከቤተሰቦቿ ጋር ወደ አዲስ አበባ ትሄዳለች።
ህይወት ፣ ምኞት፣ ደስታ ፣ ስራ፣ ተስፋ ሁሉ ፣ እራሱ መኖር  ትርጉሙ አልገባህ አለኝ። ለምን እንደምኖር እራሴን ስጠይቅ ለመኖር የሚያስገድደኝ አንድ ምክንያት ብቻ ነበር ያገኘሁት።
እሷም እህቴ ነች።
የምኖረው ልኔ ብዙ ለደከመችው ለእህቴ ስል ብቻ ነበር።
የናትና ያባቴ ምትክ እህቴ እኔን ብታጣ ምን እንደምትሆን ማሰብ አልችልም። ለሷ ስል እኖራለሁ። ሂወት ቀጠለ።
ለወራት የክቡር ዶክተር አርቲስ ጥላሁን ገሰሰን  ሳላስብ ትተሽኝ የሚለውን ሙዚቃ ሳላዳምጥ ተኝቼ አላውቅም።
ከስምንት ወር በሁዋላ አይቼው የማላውቀውን የፌስቡክ አካውንቴን ከፍቼ ስመለከት መጀመሪያ ላይ የመጣው ፎቶ ቃልዬ ከሁለት ቀን በፊት የለጠፈችው ቀለበት ስታስር የተነሳችው ፎቶ ነበር። ቀለበት ያሰረችው ግን ከዛኪ ሳይሆን ከሌላ ወንድ ጋር ነው።
"ቃልዬ ከተመረቅን በሁውላ ከዛኪ ጋር አብረን እንደማንቀጥል እርግጠኛ ነኝ " ያለችው እውነት ነበር ማለት ነው አልኩ። ስልኬን ወርውሬ ግርግዳው ላይ ለጠፍኩት ፣ ብትንትኑ ወጣ።
ከተበታተነው የስልኬ ስብርባሪ መሀል ግን የቃልዬ የቀለበት ፎቶ ቅዳጅ አልነበረም።
ዳግም ህመም ዳግም ግርሻት ፣ ዳግም ስቃይ። አወይ ፍቅር ግርሻቱም አይጣል ነው ለካ።
ስልኬን ከሰበርኩት ከአንድ ወር በሁዋላ እህቴ ከወራት በፉት  በገዛችልኝ ሚኒባስ ውስጥ ቁጭ ብዬ ሰው እስኪሞላ መሪው ላይ ተደፍቼ  እየጠበኩ ነው።
መኪና ውስጥ የሚለጠፉ ጥቅሶችን እያዞረ የሚሸጥ አንድ እድሜው ከአስራ አራት የማይበልጥ  ልጅ እግር  በጋቢናው በኩል መጥቶ ምርጥ ምርጥ ጥቅሶች በቅናሽ ዋጋ እያለ የያዛቸውን ጥቅሶች ተራ በተራ እያነበበ ነው ።  አራት ጥቅሶችን አንብቦ አምስተኛው ላይ ሲደርስ እንደመባነን ብዬ ከመሪው ላይ በፍጥነት ቀና አልኩና•••
"እስቲ ቆይ ቆይ አሁን ያልከውን ድገመው !" አልኩት። ደገመው ከጠየቀኝ ሂሳብ በላይ እጥፉን ከፍዬ ጥቅሱን ገዛሁትና መኪናዬ ዳሽ ቦርድ ላይ ለጠፍኩት።

ወረቀቱ ላይ የተፃፈው  ••••
"ባልንጀራህን እንደራስህ አድርገህ ውደድ ቢልም ፣ ለባልጀራህ ሁሉን ሚስጥርህን ንገረው ግን አይልም"
የሚል ጥቅስ ነበር ። መታሰቢያነቱ ለኪያ።           .
                      .
                      .
                      .
      •••••••ተፈፀመ ••••••••
                      .
                      .
                      .
                      .
ለነበረን ቆይታ ከልብ አመሰግናለሁ ❤❤


.

.
ቤተሰቦቼ በሌላ ልብ ወለድ እንገናኛለን። በአጠቃላይ በታሪኩ ላይ ጠቅለል ያለ ሀሳብ አስተያየታችሁን ፣ ወደፊት ቢስተካከል የምትሉትን ነገር ሁሉ በኮሜንት መስጫው ስር እንደምታስቀምጡ ተስፋ እናደርጋለን 🙏🏻

https://vm.tiktok.com/ZMkkFephM/

8.5k 0 24 36 183

❤️ ተማሪዋ ❤️


❤️….. ክፍል 49 …….❤️


"ምን እሚሉት ጥያቄ ነው እስከዛሬ ምን ያህል እንደማፈቅርህ አታውቅም እና ነው ቆይ ምንድን ነው የሆንከው ፊትህ እኮ ልክ አይደለም?"
"ፉቴ ብቻ አይደለም ሁሉ ነገሬ ልክ አይደለም ቃል እባክሽ ለምጠይቅሽ ጥያቄ ብቻ መልስ ስጪኝ አንቺ ምንም ነገር አትጠይቂኝ"
"እሺ"
"ታፈቅሪኛለሽ ቃል"
"አዎ ኤፍዬ አፈቅርሀለሁ"
"ዛኪንስ ታፈቅሪዋለሽ ቃል?" ስላት ፊቷ ላይ ያየሁት ድንጋጤ እኔኑ አስደነገጠኝ።
ያ ድንጋጤዋ ነበር  የመጨረሻውን መርዶ ያረዳኝ። በቃ የቃልዬን መልስ  ድንጋጤዋ ውስጥ አየሁት።
ቃልዬ ብዬ ጠራሁዋት አይን አኗን እየተመለከትኩ።
ወዬ ማለት አልቻለችም። በቃ አቃታት። የኔም የሷም አይኖች እኩል እንባ አቀረሩ።
" ቃልዬ!" ብዬ ደግሜ ጠራኋት።
አይን አይኔን ከማየት ውጪ አቤትም ወዬም ማለት ተሳናት ቃል አፏ ተለጎመ።  የስረኛው ከንፈሯ  ይንቀጠቀጥ ጀመር።
ጣቴቻን በጣቶቿ እያፍተለተለች ተለጎመች የኔ ቃል።
ሁሉን ነገር እንደደረስኩበት ውስጧ ነግሯታል።
ይህን  ሳስብ አመመኝ ።
ቃልዬ ሁኔታዋ አንጀት ይበላል።
የሚታዘንልኝ እኔ ሆኜ ሳለሁ ቃልዬ በዛ ልክ ጭንቅ ጥብብ ሲላት ሳይ አሳዘነችኝ።
ያን ሲተናነቀኝ የነበረውን እውነት መናገር ጀመርኩ•••
ቃልዬ አውቃለሁ ሁሉን አውቃለሁ።  ከቀናት በፊት ሀረር እስከሄዳችሁባት አስቀያሚ ቀን ድረስ ይቺ ቅፅበት በኔና ባንቺ መሀል እንዳትፈጠር ስሸሻት ኖሪያለሁ።
ነገር ግን እውነትን መሸሽ ከሞት እንደማያድነኝ ተረዳሁ። አዎ ቃልዬ አንቺን ከማጣ ሞቴን እመርጣለሁ፣ መሞት አልፈልግምና አንቺን ማጣት እፈራለሁ።
እኔ ስለፈራሁት  እኔ ስለሸሸሁት የሚቀር ነገር የለም።
ሁሌም አፈቅርሻለሁ። ምንም ብትበድይኝ ምንም ብትጎጂኝ አንቺን አለማፍቀር እስክችል ድረስ አፈቅርሻለሁና  ዛሬም ቢሆን አንቺን  ክፉ የምናገርበት አንደበት የለኝም።
ክፉ ይናገረኛል አልያም ይጎዳኛል ብለሽ እንዳታስቢ እሺ? ፣ እኔ አንቺን የማፈቅርሽ የእውነት ነው ፣ የማፈቅርሽ ግን የኔ ስለሆንሽ ብቻ አይደለም።
ዛሬም የማልፈልገው አንቺን አለማፍቀር ሳይሆን እየታመምኩ፣ እየተረበሽኩ፣ እንቅልፍ እያጣሁ፣ የተበዳይነት፣ የተገፊነት ስሜት እያንገላታኝ ማፍቀርን ነው።

ነገ ከነገ ወድያ ላጣሽ ልትለይኝ እንደምትችይ እያሰብኩ ማፍቀር ደከመኝ ቃልዬ።
አብሬሽ ሆኜ የተሰቃየሁት ስቃይ አጥቼሽ ከምሰቃየው ጠናብኝ ቃልዬ ።
ሀለቱም ለኔ ህመም ቢሆንም ከእውነት ጋር መታመም ይሻላል እውነትን ሸሽቼ የማላመልጥበት ደረጃ ላይ ደርሻለሁና የምደበቅበት የምሸሽበት የለኝም እውነቱን ልጋፈጠው የተገደድኩት ሁሉ ነገ ካቅሜ በላይ እስከሚሆን ታግሼ ነውና በውሳኔሽም በውሳኔዬም እንደማልፀፀት ተስፋ አደርጋለሁ።
አንድም ቀን በዚህ ልክ ትጎጂኛለሽ ብዬ አስቤ አላውቅም ነበር ቃልዬ።
ዛሬ እውነቱን ካንቺ አንደበት ሰምቼ ሀቁን ልጋፈጠው ወስኛለሁ። ስለትናንት አልወቅስሽም፣  ስለነገም አላውቅም አሁን የምፈልገው በራስሽ አንደበት እውነቱን እንድትነግሪኝ ብቻ ነው ቃልዬ።
" ዛኪን ታፈቅሪዋለሽ አደል ቃል?"
"እ ቃል እባክሽ ንገሪኝ ዛኪን ታፈቅሪዋለሽ አደል?"
ቃልዬ መልሷ ማልቀስ ብቻ ሆነ። ከጎኔ ቁጭ ብላ ስታለቅስ ሰውነቴ መንቀጥቀጥ ጀመረ። እራሴን ፈራሁት። ስሜታዊ ሆኜ ቃልዬ ላይ እጄን እንደማልሰነዝር ባውቀውም እራሴን ፈራሁት ከአጠገቧ ተነስቼ  በመራቅ  ፊት ለፉቷ ተቀመጥኩ።
አቀርቅራ ስታለቅስ ቆየችና ድንገት ቀና ብላ
"ኤፍዬ ይቅርታ!" አለችኝ። ሰማይ ተደፋብኝ። ቤቱ የሚሽከረከር መሰለኝ። ከተቀመጥከበት እንዳልወድቅ አይኔን ጨፍኜ ግርግዳውን ተደገፍኩ።
"ኤፍዬ ይቅርታ !" አለች በድጋሚ። መልስ አልሰጠኋትም።
ቃልዬ ቀጠለች ••••

"እኔና ዛኪ እዚህ ግቢ ትምህርት እንደጀመርኩ የዛሬ ሶስት አመት ነው በፍቅር አብረን የሆነው ፣ " ስትል ገና ከግር ጥፍሬ ጀምሮ ሁለመናዬን ወረረኝ። እያየኋት ልሰማት አቅም አጣሁ። ጭንቅላቴን ጉልበቶቼ መሀል ደፍቼ አቀረቀርኩ ። ቃልዬ ቀጠለች...

"ፍቅር ጀምረን ወራት ያህል እንደቆየን ስለሱ ብዙ ነገር እሰማ ጀመር ከብዙ ሴት ጋር እንደሚቀራረብ ባውቅም አምነው ነበር። ሁሉንም ነገር የምሰማው በውሬ ነው። ስጠይቀው ይክደኛል ። ያን ቀን አንተና እኔ በተገናኘንበት ምሽት አንዷ ሴት ጋደኛዬ ዛኪ ከሌላ የግቢ  ሴት ጋር  የለበትን ሆቴል ነግራኝ ነበር ሳንቲም እንኳን ሳልይዝ አለ ወደተባለበት በርሬ የሄድኩት።
ግን አጣሁት መመለሻ ሳንቲም እንኳን ልነበረኝም ። ዛኪን ከዛ በኋላ አብሬው ላልቀጥል ወስኜ ነበር። ለምን በዛ ሰአት እዛ ሆቴል በር ላይ እንደቆምኩ አንተ  ስጠይቀኝ ሌላ ግዜ እነግርሀለሁ ነበር ያልኩህ። ዛኪን አየሁት ብላ የደወለችልኝ ሴት ያንን አጋጣሚ ተጠቅማ አብረዋት  ከነበሩ ሁለት ወንዶች መሀል ከአንደኛው ጋር ልታቀራርበኝ ስትሞክር ተናግሪያት ወጣሁ። በዛ ሰአት ነበር አንተ መጥተህ ፊት ለፉቴ የቆመከው ። ይህንን ደሞ በመጠኑም ቢሆን ነግሬሀለሁ። ኤፍዬ የኔና ያንተ ነገር  ከተዋወቅንባት ምሽት ጀምሮ መቀራረባችን እና ወደ ፍቅር መግባታችን እንዴት እንዴት እንደፈጠነ ታውቃለህ።
እኔና አንተ ወደፍቅር በገባንባት ሁለት ወር ውስጥ  ከዛኪ ጋር ተኮራርፈን ነበር ።ድጋሚ የምታረቀውም አልመሰለኝም ነበር።
ነገር ግን ልጅቷ ሆን ብላ እኔን ለሌላ ወንድ ለማጣበስ ስለሱ መጥፎ እያወራች እንዳጣላችን በየቀኑ እየመጣ ይነግረኝ ነበር።  መውጫ መግቢ መቆሚያ መቀመጫ አሳጣኝ። ካንተ ጋር ሆኜ እንኳን ስንቴ እንደሚደውልና ስንቴ ተነስቼ ካጠገብህ እየሄድኩ እንደማዋራው ታስታውሳለህ።
በቃ ታረቅን።  እኔና እሱ ስንታረቅ በጣም ተጨነቅኩ።  ዛኪን የታረቅኩት ትምህርቴን ተረጋግቼ ለመጨረስ ብቻ ነበር።
አንተን ልጎዳ ብዬ ያደረኩት ምንም ነገር የለም ። ከዛኪ ጋር እዛ ግቢ ውስጥ እስካለሁ ድረስ መውጫ መግቢያ ስለሚያሳጣኝ መለያየት ከባድ ቢሆንም አብረን እንደማንዘልቅና ከተመረቅን በኋላ እንደምንለያይ እርግጠኛ ነኝ። አንተን •••ብላ ልትቀጥል ስትል መስማት አቅለሸለሸኝ።

የመጨረሻ ክፍል ረቡዕ ማታ 2:00 ላይ ❤️🙏🏻

https://www.instagram.com/reel/DD6fkUSu_mv/?igsh=MWRkNjA2dWFvMzg1eg==

6.9k 0 14 24 216

❤️❤️ተማሪዋ❤️❤️
.

🌹🌹…….ክፍል 48 ……🌹🌹

.

አላወቅኩም ቆይ እስቲ ጥበቃውን ልጠይቅልሽ " ብያት ወደ ጥበቃው ስመለስ አሁንም እማርኛ እና የነጮቹን አፍ እየቀላቀለች ስላስቸገርኩህ ይቅርታ አይነት ነገር አለች ። መልስ ሳልሰጣት ሄጄ ጥበቃውን...

"አባባ የሚላላከው ልጅ አለ እንዴ ? ዲያስቦራዋ ፈልጋው ነበር?'' አልኳቸው።

"ውይ ፈለገችው እሱማ መሄጃ ሰአቱ ደርሶ ወጣኮ ምሽት ሁለት ሰአት ወደ ቤቱ ሄደ። ምን ፈልጋ ይሆን ?" እያሉ አብረውኝ ተመለሱና ልጁ እንደለለ ነገሯት።

እዛው ቆም ብዬ እኔ ከወጣሁ በኋላ የተያዙና መብራት የበራባቸውን ክፍሎች ገልመጥ ገልመጥ እያልኩ ስቃኝ። ዲያስቦራዋ ልጁን የፈለገችው ቢራ ከውጪ ገዝቶ እንዲያመጣላት እንደነበር ስትነግራቸው ጥበቃው አንዴ እሷን

አንዴ እኔን አንዴ በሩን በየተራ እየተመለከቱ።

"አይይይ ግድ ከሆነና ካስፈለገሽ እኔው ሄጄ ላምጣልሽ ይሆን የኔ ልጅ?••• ልጁማ ሰአቱ ደርሶ ወጣኮ ቀደም ብትይ ደግ ነበር?'' አሏት። አሳዘኑኝ። ለሷ ሳይሆን ለሳቸው ስል አንዳፍታ ገዝቼ ላቀብላትና ገብቼ ልተኛ አሰብኩና

"ችግር የለውም አባቴ እርሶ ከሚሄዱ እኔ አመጣላታለሁ"

ስላቸው ገና መርቀውኝ ሳይጨርሱ ለሳቸው ጉርሻ መቶ ብር ጨምራ የቢራ መግዣውን ብር ሰጠቻቸው ።

የሳቸውን ለሳቸው ሰጥቼ ቢራውን ልገዛላት ስንቀሳቀስ ከዳግም ምርቃታቸው አስከትለው ቆይ የኔ ልጅ ጠርሙስ ካልያዝክ ማስያዣ ይጠይቁሀል ጠብቀኝ ጠርሙስ ላምጣ ብለውኝ ግቢ ውስጥ ወዳለ አንድ ክፍል አምርተው አራት የቢራ ጠርሙስ ይዘውልኝ መጡ።

ተቀብያቸው ልወጣ በሩን ከከፈትኩ በኃላ እዛ አከባቢ በግራም በቀኝም ሆቴል አለማየቴን አሰብ አድርጌ••••

"እታች ወርጄ ነው የምገዛው አደል አባባ እዚህ አከባቢ በቅርብ ሆቴል የለም አደል?" ስላቸው •

"ውይ የኔ ነገር የምትገዛበትን ሳላመላክትህ ሰደድኩህ አደል የኔ ልጅ ፣ ለካ አታውቀውም እያሉ ከግቢ ወጡና ካለንበት በቀኝ በኩል ትንሽ ሄደት ብዩ ወደ ግራ ቁልቁል የምትወስድ ቀጭን

መንገድ እንዳለችና ገባ እንዳልኩ ሆቴል እንደማገኝ ነገሩኝ። ከዚህ በፊት አላውቀውም ሆቴሉን ምናልባት በቅርብ የተከፈተ ይሆናል እያልኩ ወደ ሆቴሉ አቅንቼ ግቢ ውስጥ ስገባ ግቢው ጭር ያለ ነው ። ወደ ሆቴሉ ከሩቅ ሳማትር አለፍ አለፍ ብለው ወንበር ይዘው በተከፈተው ለስላሳ ሙዚቃ የሚዝናኑ ውስን ሰዎች ይታያሉ።

ራመድ ራመድ እያልኩ ወደሆቴሉ ዘው ብዬ እንደገባሁ ፊት ለፊት ባየሁት ነገር ልቤ ስንጥቅ አለች። ወይኔ አምላኬ ምንድን

ነው የማየው ? ጭራሽ እኔ የገዛሁላትን አዲሷን ልብስ••• እያልኩ በሁለቱም እጆቼ ሁለት ሁለት ባዶ የቢራ ጠርሙዝ እንዳንጠለጠልኩ ድንጋጤዬ አብረክርኮት አልራመድ ያለኝን እግሬን በግድ እየጎተትኩ በቀስታ ወደ ተቀመጡበት ወንበር ተጠጋሁ በሆቴሉ ውስጥ  ጭልም ደሞ ብርት የሚሉ ሲበሩም ደብዛዛ ብርሀን የሚፈነጥቁ ጌጣማ አንፖሎች እዛም እዛም ተሰቅለዋል ፣
ቀረብ ስል ግራ ገባኽ አብሯት ያለው ወንድ ፊቱ በደንብ ታየኝ። ዛኪ አይደለም።ገዘፍ ያለ ነው። አስተያየቱ  ደሞ ያስፈራል። ገልመጥመጥ ሲያደርገኝ እነሱን እያየሁ በቀጥታ ወደነሱ መሄዴን ቀየር አደረኩና እንደማለፍ ብዬ አየት ሳደርግ ልጅቷም ቃልዬ አይደለችም። ቀሚሱዋም ዲዛይኗ የቃልዬ አይነት ቢሆንም ' ከለሯ 'በተወሰነ መልኩ ይለያል።
የስራሽን ይስጥሽ ቃልዬ፣ ግራ የገባኝ ደግሞ ተከትያት ሀረር ከመጣሁ በሁዋላ የተጠናወተኝ በቅርብ ርቀት ያየኋት ሴት ሁሉ ቃልዬን የምትመስለኝ በሽታ ነው ፣ ይሄ መታመም ካልሆነ ምን ይሆናል ? እያልኩ ቢራውን ገዝቼ ተመለስኩ።
የግቢው ጥበቃ የቀራቸውን ምርቃት ሁሉ አሟጠው መረቁኝ።
"የእኔን እድሜ ያድለህ ፣ ጧሪ አያሰጣህ፣ የማታ እንጀራ ይስጥህ፣ የልጅ ልጅ ያሳይህ•••••" ሌላም ሌላም ብዙ ምርቃቶች።
"አባባ " አልኳቸው እንደጨረሱ።
"ወዬ የኔ ልጅ"
"ፍቅር ይዝለቅልህ!" ብለው ይመርቁኝ አልኳቸው እንባ እየተናነቀኝ።
"ፍቅር ይዝለቅልህ ፣ የወድድካትን ያፈቀርከትን ክፉ አይይብህ ፣ ትዳርህን ይባርክልህ !
" አሜን አሜን አሜን አባቴ" አልኳቸው ዋናው እሱ ነው ። እኔ የልጅ ልጅ ማየት የምፈልገው ከቃልዬ ነው። ከቃልዬ ከነጠለኝ በሁዋላ ረጅም እድሜ ምን ሊጠቅመኝ። እያልኩ ቢራውን ሰጥቻት ወደ ክፍሌ ገባሁ።

ቃልዬ ከዛኪ ጋር ማደሯን ማሰብ አስፈሪ እንደሆነብኝ ድካምና ረሀቡ ነው መሰለኝ የወደቅኩበትን ሳላውቅ ነጋ።
ጥዋት ወደ ድሬ ዳዋ ስመለስ ቃልዬ እራሷ እስክትደውል ላልደውልላት በናቴ ማልኩ።
ሳትደዉል መሸ፣ ሳትደውል ነጋ ፣ ሁለተኛ እና ሶስተኛ ቀንም እንደዛው ልደውል ስልኬን ካወጣሁ በሁዋላ በናቴ መማሌ ትዝ ሲለኝ  ስልኬን ወደ ኪሴ እመልሰዋለሁ።
በአራተኛው ቀን ደወለች ።
"ይቅርታ ኤፍዬ በዚህ ምርቃት ሰበብ ተዋክቤ፣ ቻርጀሬ ጠፍቶ ፣ ባትሪ ዘግቶ••••"   ብዙ ብዙ  አለች ፣ ለመጥፋቷ  ብዙ ምክንያት ብዙ ሰበብ  ተናገረች ቃል። ዝም ብዬ ሰማኋት።
ስትጨርስ አንድ ነገር ብቻ ተናገርኩ ።   አንድና አንድ  ነገር ብቻ አልኳት።
"ችግር የለውም ቃልዬ በጣም ላገኝሽ እፈልጋለሁ መች ይመችሻል?" የሚል ጥያቄ ብቻ ሰነዘርኩላት። ድምፄ መሰባበሩ ለኔ ቢታወቀኝም ለሷ አላታወቃትም አልያም አላስተዋለችውም።
"ኤፍዬ አብረን ለመዋል ከሆነ ነገ ፣ ለማደር ከሆነ ግን ከነገ ወድያ"
"አይ ችግር የለውም አብረን ውለን ትሄጃለሽ"
"በቃ ነገ ከሰአት ደውልልኝ "
የቃልን ስልክ እንደዘጋሁ ጌትነት ስልክ ላይ ደወልኩ።
እቤቱን ለአንድ ቀን እንደምፈልገው ነገርኩት።
"ችግር የለውም ኤፍዬ ማደርም ትችላለህ እኔ ጀለሶቼ ጋር እሄዳለሁ" አለኝ።
ቃልዬን ላመጣት ስሄድ ለጌትነት ደውዬ  ልመጣ ነውና ቁልፉን አስቀምጠህልኝ ሂድ አልኩት።

ደረስኩ ተገናኘን ። ስማኝ ከጀርባ ገባች። ደንዝዣለሁ። ምንም አላወራም ቃልዬ ግን ምን ያህል እንደናፈቅኳት ፣ ስለሰሞኑ የምርቃታቸው ወከባ ምን ያህል ግዜ እንዳሳጣት እያወራችልኝ የማውራት እድል ሳትሰጠኝ  እነ ጌትነት ቤት ደረስን።የማውራት እድል ብትሰጠኝ ምን እንደማውራ አላውቅም።
ገብተን ትንሽ እንደቆየን ከምን እንደምጀምር ምን እንደምላት ጨነቀኝ።
ካንድም ሁለት ሶስቴ ልጀምር እልና የሆነ የሚረብሽ ስሜት እየተናነቀኝ አቋርጠዋለሁ። ተነስቼ ወደ መታጠቢያ ቤት እሄድና በቀዝቃዛ ውሃ ፊቴን ታጥቤ እመለሳለሁ።
ቃልዬ ቡና ለማፍላት እየተንጎዳጎደች ሁኔታዬን ማስተዋል አልቻለችም።
አቦሉን እንደጠጣን •••
"በቃ ሁለተኛውን አታፍይ ይቅር " አልኳት።
"ለምን ኤፍዬ?" አለችኝ ፊት ፊቴን እያየች።ፊቴ ልክ እንዳልሆነ ያስተዋለችው ያኔ ነበር። መጥታ አጠገቤ ተቀመጠች።
"ምን ሆነሃል ኤፍዬ ችግር አለ?" አለችኝ አገጬን ይዛ ወደግራም ወደቀኝም ገልበጥ ገልበጥ እያደረችኝ።
"አዎ ችግር አለ ቃል"አልኳት አገጬ ላይ ያለውን እጇን ይዤ ከአገጬ ላይ እያወረድኩት።
"ምንድን ነው እሱ?" አለችኝ ልቧን በግራ እጇ ደገፍ አድርጋ እየተመለከተችኝ። ልቧ ነገራት ብዬ በውስጤ እያሰብኩ  ዝም አልኩ።
"ኤፊዬ!" ብላ ተጣራች።
"ወዬ ቃል"
"ምን ሆነሀል ?" ምን ሆንኩ እንደምላት ቸገረኝ።
"ቃልዬ" አልኳት።
"ውዬ"
"ታፈቅሪኛለሽ?"
.
.
ክፍል 49 ከ150 ላይክ ቡሀላ ይቀጥላል



https://t.me/saloda_trading

6.2k 0 15 14 232

❤️ ተማሪዋ ❤️

🌹………ክፍል 47 …………🌹
.
.
.
.
ሊጠናቅ 3 ክፍሎች ብቻ ቀሩት 🫶ሼር ይደረግ


ጅቦቹ ቢኖሩም እነቃልዬ እዛም የሉም። የት ይሆኑ? እኔና እሷ ያደርንበት ሆቴል ይዛው ትሄድ ይሆን? እሱም ለሀረር አዲስ ከሆነ ሁለቱም ሀረርን በደንብ ስለማያውቋት ወደምታውቀው ወደዛው እኔና እሷ ወደነበርንበት ነው ይዛው የምትሄደው በርግጠኝነት ሌላ ቦታማ አያድሩም።

ደሞ ፀጥታውን ወድጄዋለሁ ስትል አልነበር እዛ ነው የሚሄዱት።

እኔና ቃልዬ ያደርንበት ፔንስዬን በር ላይ ስደርስ ከምሽቱ ሶስት ሆኖ ነበር።

ገባሁ... ጥበቃውን ሰላም ስላቸው አላስታወሱኝም። ቀጥታ ወደሚከፈልበት ክፍል ገብቼ ከፈልኩና ቁልፍ ወስጄ ቁልፉ ላይ ባለው ቁጥር መሰረት ወደ ክፍሌ አመራሁ። ቃልዬ እዛው ግቢ ውስጥ ብትሆን እና ብታየኝ ደንታ አልነበረኝም። እሷ አየኝ አላየኝ ብላ ትፍራ እንጁ እኔ ምን አስፈራኝ እያልኩ ከክፍሌ ወጥቼ የግቢው ጥበቃ ወደሆኑት ሰው ሄድኩና ሰላም ብያቸው እዛው እሳቸው ካሉበት በስተግራ የግንብ አጥሩ ስር ባለች አንዲት ጠፍጣፋ ድንጋይ ላይ እየተቀመጥኩ...

"ስገባ አላወቁኝም አደል አባባ? እኔም እገሌ ነኝ ሳልሎት ገባሁ እንጂ እንዳላወቁኝ አውቁያለሁ?" አልኳቸው።

"ኧረ አለየሁህም የኔ ልጅ ይቅር በለኝ የኔ ልጅ"

"ችግር የለውም የዛሬ ሶስት ወር አከባቢ ከሴት ጓደኛዬ ጋር መጥተን ነበር"

"አይ የኔ ልጅ እዚህ ስንቱ በየእለቱ እየመጣ ይሄዳል ማንን ከማን ለይቼ አውቃለሁ ብለህ ነው?"

"በርግጥ ልክ ኖት ከባድ ነው፣ ያኔ ግን ልንሄድ ተሰናብተናት ከወጣን በሁዋላ ተመልሰን መጥተን ነበር ፣ እንደውም ደግ አደረጋችሁ እንኳን ተመለሳችሁ የማታ ጉዞ ጥሩ አይደለም ብለውን ነበር አያስታውሱም?"

ውይ ውይ ውይ አስታወስኩ ጥዋት ስትሄዱ ቁርስ ይብሉበት አባቴ ብላ ብር የሰጠችኝ ልጅ ከሷ ጋር የነበርከው አንተ ነህ አደል ይቅር በለኝ የኔ ልጅ ታድያ እሷን የት ጥለሀት መጣህ ደና ነች??

እሷ ጣለችኝ እንጂ እኔማ ቃልዬን ጥዬ የት እሄዳለሁ አልኩና ለራሴ ለሳቸው...

"አይ እኔ አልተመቸኝም ነበርና እሷ ከወንድሟ ጋር ቀድማኝ ነው የመጣችው፣ ደሞ ክፋቱ ስልኬን እቤት ረስቼው መምጣቴ ነው፣ እዚሁ አልጋ እንደሚይዙ ነበር ከመምጣታቸው በፊት ያወራነው

ምናልባት በአንዱ ክፍል ከሆኑ ብዬኮነው ወደዚህ አልመጡም አደል አባቴ ?"

"ኧረ አልመጡም የኔ ልጅ ይሄው እንግዲህ አዳሬም ውሎዬም እዚሁ ነው ። ዛሬ በግቢው ሶስት ክፍል ብቻ ነው የተያዘው ሁለቱ ጠና ጠና ያሉ ሰዎች ናቸው።

አንደኛዋ እንኳን እዚሁ ነው የከረመችው እዛ አንተ አሁን ገብተህ ከወጣህበት ጎን በስተግራ ነው ያለችው ። ዲያቦራ ነው ምን አላችሁት ስማቸውን ብቻ ከውጪ ነው የመጣችው "

"ዲያስቦራ”አልኳቸው

" አዋ እንደዛ ነች ቀን ቀን ዘመዶቿ ዘንድ እየዋለች አዳሯ እዚህ መሆኑን ነው የሰማሁት " ከነሱ ውጪ ማንም የለም እንግዲህ ምናልባት ከተማ አምሽተው ሊመጡ ይሆን የኔ ልጅ ? " አሉኝ። "ይሆናላ አባቴ" እስቲ መጣሁ ከሌላ ሰውም ቢሆን ስልክ ለምኜ ልደውልላት። ብያቸው ልወጣ ስል

"እህ ና ከዚሁ መደወል ትችላለህ የኔ ልጅ ና ግባና ሂሳብ ክፍሏን አስደውይኝ በላት" አሉኝ ፡፡

"ችግር የለውም አባቴ ስልክ አላጣም" ብያቸው ወጣሁ። ስልክ መች አጣሁ የጠፋችብኝው ቃልዬ ነች እንጂ እያልኩ ። ስልኬን ከኪሴ አወጣሁና ቃልዬ ስልክ ላይ ደወልኩ።

"የደወሉላቸው ደንበኛ ከአገልግሎት መስጫ ክልል ውጪ ናቸው ትላለች ፣ ቃልዬ እኔን ከገልግሎት መስጫ ክልል ውጪ አደረገችኝ እንጂ እሷማ እዚሁ ነች።" እያልኩ ሁለተኛ ዙር ፍለጋዬን ጀመርኩ እኔና ቃልዬ የሄድንበትንም ያልሄድንበትንም ቦታ ሁሉ እየገባሁ ፈለኳት የለችም። የሚወስድ ይውሰደውና የት እንደወሰዳት ግራ ረባኝ።

ምናልባትም ቃልዬ ያን ግዜ መጨፈር እየፈለገች በግድ ይዣት ስለወጣሁ እስኪወጣላት ልትጨፍር ወደዛ ጭፈራ ቤት ቆይተውም ቢሆን መምጣታቸው አይቀርም በሚል ተስፋ ወደዛው ሄድኩና ጥጌን ይዤ መጠጣት ጀመርኩ። በባዶ ሆዴ ስለነበር የምጠጣው ወድያው ነበር አናቴ ላይ የወጣው። እነ ቃልዬ ሳይመጡ የቃልዬ ዘፈን መጣ፣ ያ ከወጣን በሁዋላ ገብተን ካልደነስንበት ያለችኝ ዘፈን••• የብሶት ስሜት ከደረቴ ስር

ሲፈነቀል የተሰማኝ ገና ክላሲካሉ ላይ ነበር ።

ዘፈነ ፀሀዬ...

ጥንድ ጥንድ ሆነው ሲሄዱ ባይ ሳጣሽ የኔን ሲሳይ ፣ ቀናሁ በሰዎች ላይ ዛሬም ሳላይሽ ላድር ነው ወይ እባክሽ ነይ ዝርያዬን ባስስ ባስስ አንቺ እንደሁ የለሽም

ባንጋጥጥ ወደሰማይ••••

ቃልዬን በአይነ ህሊናዬ ፊት ለፊት እያየኃት አብሬው ዘፈንኩ። ቃልዬ ሳትመጣ ዘፈኑ አለቀ።

በር በሩን እያየሁ እኩለ ለሊት አለፈ። ከብዙ ግራ የገባቸው ዘፈኖች በኋላ የመጣው አንድ ዘፈን የብሶት ሰንኮፌን ሁሉ አጥቦ አወጣው።

በቃልዬ ፍቅር የመጨረሻውን ብሶት እና ምሬት ፣ የመጨረሻውን ሀዘን እና መከፋት የማስተናግድበት የመጨረሻው ሰአት እስኪመስለኝ ዘፈኑንን እየሰማሁ አብሬው ስዘፍን እስከዛሬ ለማንም አልቅሼ የማላውቀው እኔ ኤፍሬም ለቃልዬ አነባሁላት። ዘፈኑ ሲያልቅ ወደ ዲጄው ሄድኩና በፍቅር አምላክ ይሁንብህ ይሄን ዘፈን ድገመው አልኩት።

"ኧረ ጣጣ የለውም ከፈለክ በመሀል በመሀል ሌላ ዘፈን እያስገባሀ አምስቴ እደግምልሀለሁ አያሳስብህ!"

"አይ በመሀል ሌላ ዘፈን ሳታስገባ አሁኑኑ ድገመው እባክህ" አልኩት ደገመው...

ሳላስብ ትተሽኝ ቢጠፋኝ ሚስጥሩ በንባ ተጥለቅልቀው አይኖቼም ታወሩ አንቺ አለሽኝ ብዬ ለሁሉም ሳወራ ብቸኛ አረግሽኝ ለንባዬ ቦይ ልስራ ትዝ አይልሽም ወይ አቅፌሽ አቅፈሽኝ...

ያ. ጫወታና ሳቅ እየደባበሽኝ በዛ ደስታ ምትክ እንባ ፈረድሽበት ኧረ ምን ተሰማሽ ምን ይላል ያንቺ አንጀት....ዘፈኑ ሲያልቅ ውስጤ የነበረው መጥፎ ስሜት ሁሉ በንባ ተጠርጎ የወጣ ያህል ቅልል አለኝ። ከዛ በሁዋላ እዛ ቤት መቆየትም ሌላ ዘፈን መስማትም ቃልዬን መፈለግም አልፈለኩም። አልጋ ወደ ያዝኩበት ክፍል አመራሁ። የግቢው ጥበቃ በሩን እንደከፈቱልኝ

"አላገኘሀቸውም የኔ ልጅ?" አሉኝ።

"አዋ አባባ " ብያቸው ብቻ ገባሁ።

ወደክፍሌ ሳመራ ዲያስቦራ የተባለችው ከኔ ክፍል ጎን ያለችው ሴት የክፍሏን መስኮት ከፍታ በለሊት ልብስ እንደቆመች ፀጉሯን እየነካካች ወደ ግቢው ታማትራለች። እድሜዋ ከሰላሰ ብዙ አይርቅም። ስታየኝ አየኋት። ምን ታፈጣለች እሷም እንደኔ የጠፋባትን ፍቅረኛዋን ፍለጋ ነው እንዴ የመጣችው እያልኩ ወደ ክፍሌ እየሄድኩ ደግሜ አየት ሳደርጋት አሁንም እያየችኝ ነው። አስተያየቷ የሆነ ነገር ልትጠይቀኝ የፈለገች ትመስላለች ። ፊቴን መልሼ ወደ ክፍሌ ራመድ ስል••..

"ይቅርታ ወንድም ኢዝ ዜር ኖ ሆስት?" አለችኝ። ወይ ጣጣ ለራሴ ሂወት ተደበላልቆብኛል የምን ድብልቅልቁ የወጣ ነገር ነው የምትናገረው ይቺ ደሞ አልኩና ለራሴ ። ግቢው ውስጥ አልጋ ለያዙ ሰዎች የሚያስፈልጋቸውን ከውጪ ገዝቶ የሚያቀርበውን አስተናጋጁን ፈልጋ እንደጠየቀችኝ ቢገባኝም

"ምን አልሽኝ?" አልኳት እሷን።

"ሰው የለም ግቢ ውስጥ መልክት መላክ ፈልጌ ነበር" አለችኝ ያው እንግሊዘኛውን እንግሊዘኛውን በሚል አነጋገር። እና ከውጪ ቆልፈውብሽ ነው እንዴ የሄዱት ወጥተሽ አጠይቂም እያልኩ በሆዴ...
.
.

https://vm.tiktok.com/ZMk8WD6kN/

8.7k 0 18 56 273

ቀጣይ ክፍል 46 ማታ 2 ሰአት ይለቀቃል


❤️ተማሪዋ❤️
.

.

🌹…….. ክፍል 45…….🌹
.
.
ልክ እሩብ ጉዳይ ለሰባት ላይ ዛኪ በርሳ ጀርባው ላይ ጣል አድርጎ ከግቢ ብቅ ሲል አየሁት።ቃልዬ ተከተለችው ፣ ዘንጣለች። ቀድመው ደወለው ነው መሰል ባጃጅ በር ላይ ነበር የጠበቃቸው።

ተከታትለው ገቡ፣ ከሀለቱ ውጪ ሌላ ሰው ወደባጃጇ አልገባም።

ባጃጇ ተነስታ መሄድ እንደጀመረች ብዙም ሳትርቅ ተከተልኳት።

ቀጥታ ወደ መነሀሪያ ነው እየሄዱ ያሉት። የምይዝ

የምጨብጠው ግራ ገባኝ።

ልክ ሼል ደርሰው ወደ መናሀሪያ ከመዞራቸው በፉት አንዲት ሚኒባስ ስትክለፈለፍ መጣች። ሀረር ሁለት ሰው አለ ረዳቱ

አንገቱን ብቅ አድርጎ።

እነቃልዬን የጫነው ባለባጃጅ ለሚኑባስ ረዳት በእጁ ምልክት አሳየው ሚኒባሷ ቆመች ። እነቃልዬ ከባጃጇ ላይ ወርደው ሚኒባሷ ውስጥ ገቡ። ወደ ሀረር ነጎዱ።

የሰው ባጃጅ መሪ በቡጢ እየመታሁ እዛው በቅርቤ ወዳለው ማደያ አስጠጋሁና አቆምኳት፣ ቀልፉን እኔም ጋደኛዬም ለምናውቀው ነዳጅ ቀጂ ሰጥቼው ለጋደኛዬ ደውዬ ነገርኩትና ወደ ሀረር ለመሳፈር ወደመናሀሪያ ሮጥኩ።የገባሁበት ሚኒባስ አልሞላም። ተቁነጠነጥኩ።

እንደምንም ሞላ እነቀልዬ ወደሀረር ጉዞ ከጀመሩ ከሀያ አምስት ደቂቃ በኃላ የተሳፈርኩባት ሚኒባስ ወደ ሀረር ጉዞ ጀመረች ከፊት ለፊት ሚኒባስ ባየሁ ቁጥር ይሄ እነቃልዬ ያሉበት ይሆን?

እያልኩ። እነሱን ተከትዬ ወደሀረር እየተጓዝኩ ነው ። ከቃልዬ ጋር ስንሄድ አምስት ደቂቃ የተጓዝኩት ያልመሰለኝ መንገድ አምስት ቀን የተጓዝኩ ያህል ቢረዝምብኝም ሀረር ደረስኩ....

ሀረር እንደደረስኩ ለምን እንደመጣሁ፣ ምን እንደማደርግ፣ ወዴት እንደምሄድ ግራ ግብት አለኝ። ምግብ ትናንት ምሳ ሰአት ላይ እንደበላሁ ነኝ። የት እንደማገኛቸውም ፣ ባገኛቸው ምን እንደምላቸውም የማውቀው ነገር አልነበረም።

የሆነ ቦታ ተቀምጠው አልያም ከተማ ውስጥ እኔ ያስጎበኘኋትን የጀጎል በሮች ልታስጎበኘው ዘወር ዘወር እያሉ ፊት ለፊት ብንገጣጠም ፣ ምን እንደሚሰማኝ፣ ምን እንደማደርግ፣ ምን እንወምትል፣ እና ምን እንደምላት አላውቅም ። ይህን ሳላውቅ ነው እንግዲህ ቅናት የሚባል ዛር እያንዘረዘረኝ ተከትያቸው የመጣሁት። ግን ይሄ ቅናት ነው እንዴ? የምን ቅናት ቅናት እማ አይደለም። ይሄ መከዳት፣ መበደል፣ መገፋት፣ የወለደው መጥፎ ስሜት እንጂ ተራ ቅናት ሊሆንማ አይችልም። ይህን አይቶ እና ሰምቶ ፍቅረኛው ጋር ያለውን እውነት ለማወቅ ተከትሎ የማይመጣ ወንድ አለ እንዴ? ኧረ የለም። ቀናተኛ ነህ፣ ትጠረጥረኛለህ፣ አታምነኝም ስለዚህ በድብቅ ትከታተለኛለህ ትነዛነዛለህ ፣ ትጨቃጨቃለህ ላለመባል ብዙ ታግሻለሁ ይህንን ግን ልታገስና አይቼ እንዳላየሁ ላልፈው አልችልም። ባልፈውም ሰላም አላገኝም ፣ ሰላም ፍለጋ ሰላሜን አጣሁ፣ ፍቅርን ፍለጋ ፍቅሬን እስከማጣ መታገስ ምን ፋይዳ አለው? ምንም። ፍለጋዬን ልጀምርና እውነቱን ልጋፈጥ ብዬ ፍላጋዬን ከመጀመሬ እሷ ሳታየኝ እኔ ቀድሜ ባያቸው እንዳያዩኝ የምደበቅ መስሎ ተሰማኝ።

" እንዴ ቆይ ለምንድን ነው የምደበቀው ?" አልኩት የራሴ ስሜት እኔኑ አስደንግጦኝ።

እሺ ምን ታደርጋለህ አለኝ ያ ለብዙ ወራት ድምፁን አጥፍቶ የነበረውና ቃልዬ ውስጤ ያስቀመጠችው ጠበቃዋ እስኪመስለኝ ድረስ እኔና ቃልዬ ፍቅር በጀመርን ሰሞን ሲሞግተኝ የነበረው የራሴ ሀሰብ።

በርግጥ አሁን ላይ ምን እንደምላና ምን እንደማደርግ አላውቅም ፣ በቃ ልክ ሳያት የሚሰማኝን፣ ውስጤ በል በል የሚለኝን እላለሁ። ልክ ሳያት ተደበቅ ተደበቅ የሚል ነገር ከተሰማኝም የምደበቀው መጨረሻቸውን ለማየት ነው። ተደብቄ ለመከታተልና እዚሁ አብረው አንድ ክፍል ውስጥ እንደሚያድሩ ለማረጋገጥ እንጂ ለመሸሽ አይደለም። እንዴ ለምን እሸሻለሁ? እኔ ምን አጠፋሁና እሸሻለሁ? ከዚህ በላይ እውነቱን ላለመጋፈጥ ብሸሽሽስ ሸሽቼ የት እደርሳለሁ? ፣ ብቻ ላግኛት እንጂ ልክ ስንተያይ እሷ እራሷ የምታሳየኝ ስሜትና የምትለኝ ነገር ምን ማድረግ ምን ማለት እንዳለብኝ ያመላክተኝ የለ እንዴ ። ባገኛት ምንድን ነው የምላት እያለኩ ምን ያስጨንቀኛል?" ብዬ ለራሴም ለቃልዬ ጠበቃ ለሆነው የውስጤ ስሜትም ምላሽ እንደሰጠሁ ፣ ••••ቆይ አንተ ሳታያት እሷ ብታይህስ የሚል የላኪ አድራሻ የለለው ጥያቄ አቃጨለብኝ።

ይህንን ነው መፍራት፣ ድንገት ቀድማ ከሩቅ ብታየኝ እንኳን እንዳትለየኝ ምን ላድርግ? የሆነ እራሴን የምደብቅበት ኮፍያ ነገር መግዛት አለብኝ ። ኮፍያ ብቻ ሳይሆን ማክስም ማድረግ አለብኝ።ዘወር ዘወር አልኩና ዙርያዬን ቃኘሁ። ከሚርመሰመሰው የከተማው ሰው መሀል ማክስ ያደረገ አንድም ሰው አልታየህ አለኝ። አይኑራ ታድያ እኔ ባደርግ ምን ችግር አለው። ያየኝም በውስጡ የሚለውን ከማለት ባለፈ ቀርቦ ለምን ማክስ አደረክ የሚለኝ የለ። ይልቅ ኮፍያና ማክሴን ልግዛና የት ሊሆኑ የት ሊሄዱ እንደሚችሉ ማሰብና ፍለጋዬን መጀመር ነው ያለብኝ። መነፀርም ልግዛ እንዴ? አይ አይ መነፀሩስ ቢቀር ይሻላል ፣ ኮፍያና ማክስ አድርጌ በዛ ላይ መነፀርም ጨምሬበት ከተማ ውስጥ ወደዚህ ወደዛ ስል ፖሊስ እራሱ ቢያየኝ ዝም ብሎ የሚያልፈኝ አይመስለኝም። እራሴን ለመደበቅ የምሞክር ወንጀለኛ ልመስላቸው ሁላ ችላለሁ።

አይ መነፀሩ ይቅርና ማክስና ኮፍያውን ብቻ ልግዛ ብዬ ወሰንኩና ገዝቼ በኮፍያና በማክሱ እራሴን በመጠኑም ቢሆን ለመደበቅ ሞክሬ ፍለጋዬን ለመጀመር ተሰናዳሁ። ከሱሪዬ በስተቀር ከላይ የለበስኩትም ከዚህ ቀደም ለብሼው አይታኝ ስለማታውቅ ቃልዬ ቀረብ ብላ ካላየችኝ በስተቀር ከሩቅ ብታየኝ እንኳን ቁመናው እና አካሄዱ ኤፍሬምን ይመስላል ብላ ትጠራጠር ይሆናል እንጂ እርግጠኛ መሆን እንደማትችል እርግጠኛ ነበርኩ።

ፍለጋ ጀመርኩ በአንድ ድፍን ከተማ ውስጥ ሁለት ሰው መፈለግ መጃጃል መስሎ ቢታየኝም ሊሄዱ ይችላሉ ብዬ የማስባባቸውን ቦታዎች ብቻ ኢላማ አድርጌ ስለምፈልጋቸው አላገኛቸውም የሚል ተስፋ መቁረጥ ውስጥ ሳልገባ እየፈለኩ በየመሀሉ ግን ሴትና ወንድ ሆነው ተቃቅፈው አልያም ጎን ለጎን ሆነው የሚሄዱ ጥንዶችን ባየሁ ቁጥር ምንም እንኳን ቃልዬና ዛኪ ከግቢ ሲወጡ የለበሱትን ልብስ ያየሁና ያን አለባበሳቸውን እንኳንስ በዛች ቀን ወደፊትም እድሜ ልኬን የማልረሳው ቢሆንም ምናልባት እዚህ ደርሰው ቀይረው ቢሆንስ እያልኩ ጥንዶች ባየሁ ቁጥር ልቤ እየደለቀ ጥንዶቹ ወዳየሁበት አቅጣጫ ስገሰግስ፣ አንዳንዶቹን ቀርቤ እነቃልዬ እንዳልሆኑ ሳረገግጥ አንዳንዶቹ እኔ አጠገባቸው ከመድረሱ በፊት ታክሲ

ይዘው ሲፈተለኩ ቀልቤ አብሯቸው ሲፈተለክ እነቃልዬን ሳላገኛቸው መፈለግ ደከመኝ።

ቀኑ ደንገዝገዝ አለ። እንዴ ስንት ሰአት ሆኖ ነው ብዬ ሰአት ስመለከት አስራ ሁለት ሰአት አልፏል። ሳይታወቀኝ ምን ያህል ሰአት እነሱን ፍለጋ ከተማው ውስጥ እንደባዘንኩ አሰብኩና ለራሴ አዘንኩ።

የከተማ ውስጥ ፍለጋዬን ገትቼ ካንዱ ሆቴል ወደ ሌላ ሆቴል ስገላበጥ እነቃልዬን የበላ ጅብ ሳይጮህ ከምሽቱ ሁለት ሰአት ሆነ።

ነገሩ የሀረር ጅብ ምን በወጣው እሱ መች ሰው ይበላና ቃልዬን የበላትማ ዛኪ የተባለ ...•ብዬ ያሰብኩትን ተናግሬ ሳልጨርሰው ተውኩትና ፣ ምናልባት የሀረርን ለማዳ ጅቦች ልታሳየው ይሄዱ ይሆን? እሷ ባለፈውም መጠጋት ፈርታ ነበር ምናልባት ለሱ ለማሳየት ስትል ይዛው ትሄድ ይሆናል እያልኩ ወደዛው አቀናሁ።
.
.

ከ 200 ላይክ በኃላ ክፍል 46 ይለቀቃል❤️

6.8k 0 16 8 191

❤️ ተማሪዋ ❤️

🌹…….. ክፍል 44 ………..🌹

.
.
.
.
.

.
እኔማ ግዜ እውነቱን ያውጣው ብዬ ትቼው ነበር እድሜ ለኪያ የቃልዬን እና የዛኪን ዱካ እየተከታተለ አልፈልግም ብለውም በግድ ወሬ እያቀበለኝ ወዳሉበት ሁሉ ይልከኛል። ካየሁዋቸው ደግሞ መረበሼ አይቀርም። ምንሽ ነው አልላት ነግራኛለች ። ለምን ከሱ ጋር እንዲህ ትሆኛለሽ እንዳልላት የምከታተላት፣ የማላምናት፣ የምጠረጥራት ይመስላታል ትጣላኛለች ብዬ እፈራለሀ። የጨነቀ ነገር ሆኖብኝ እንጂ የምቀየረው እሄስ ባህሪ የኔ አልነበረም።

አቦሉን እንደጠጣን..

"ኤፍዬ"

"ወዬ ቃል"

"እስቲ ስለኔም እናውራ" ስትለኝ ደነገጥኩ።

ስላንቺ ምን ቃሌ?"

"አንተስ የምትወድልኝን እና የምትጠላብኝን ባህሪ አትነግረኝም?"

"ቃልዬ የምወድልሽን ነገር መናገር ብጀምር እየደለም እሄ ምሽት ነገ ቀኑም ቢጨመር መሽቶ እስኪነጋ አውርቼ የምጨርስ የሚበቃኝ ይመስልሻል?"

"እሺ በቃ የምትጠላብኝን ባህሪ ንገረኝ"

"ቃሌ የምጠላው ሳይሆን ብትሆኝልኝ ወይ ብትለምጂልኝ ብዬ የምመኘውን አንድ ሁለት ነገር ልንገርሽ አንደኛው ቃልዬ ውሎ እንዴት ነበር ? የሚባል ነገር አለማወቋ ያበሽቀኛል" ስላት "ማለት?" አለችኝ።

"ማለትማ በፍቅር ሂወት መሀል አንዱ ወሳኝ ነገር ውሎ እንዴት ነበር ብሎ ማውራት ነዋ፣ አንቺ ደሞ አልፈጠረብሽም "

"አልገባኝም ኤፍዬ"

"እኔ ስንገናኝ ከመገናኘታችን በፊት ባሳለፍነው ቀን የነበርንበትን ሁኔታ ብናወራ ደስ ይለኛል ፣ አንቺ ግን እንኳንስ ሳልጠይቅሽ ልትነግሪኝ ስጠይቅሽም ደምሽ ይፈላል" ስላት ትን እስኪላት ሳቀች።

"ወይ ኤፍዬ እና አንተ እምትፈልገው ልክ ስንገናኝ ዛሬ ጥዋት ልክ አስራ ሁለት ሰአት ከአርባ አምስት ደቂቃ ላይ ከእንቅልፌ ነቃሁ፣ ሁለት ተኩል ላይ ቁርስ በላሁ፣ አራት ሰአት ክላስ ገባሁ፣ ስድስት ሰአት ከክላስ ወጣሁ፣ መንገድ ላይ አንድ ለከፈኝ፣ ግቢ ውስጥ አንዱ ወደድኩሽ አለኝ፣ ከግቢ ውጪ አንዱ ሰደበኝ እያልኩ ሪፖርት እንዳቀርብልህ ነው ኪኪኪ"

"አትሳቂ ቃልዬ ኮተታ ኮተቱን ሁሉ እንድታወሪልኝ ሳይሆን በጥቅሉ ያለውን ነገር እና ወጣ ያለ ፕሮግራም ምናምን ሲኖርሽ መናገሩ ጥሩ ነው ፣ ደስ ይላል እኮ፣ ደስ ስለሚል ብቻ ሳይሆን አብረን ባልሆንበትም ሰአት አብረን እንዳለን ያህል እንዲሰማን ያደርጋል፣ ግልፅነትን እና መተማመንን ያጠነክራል፣ብዙ ጥቅም አለው ቃሌ"

"ኦ. ማይ. ጋድ. ግን በጣም አሰልቺ አይሆንም ኤፍዬ እሺ ሌላስ?"

"ሌላውም ያው የዚሁ ግልባጭ ነው ። ስለነገ ማውራትም አትወድን ቃልዬ። ይሄም ግን አስፈላጊ ነው። ስለነገ ስልሽ ሰለነገ ሳይሆን ስለወደፊት እንዲሆን እምትፈልጊውን እንዲሁም ለማድረግ ያሰብሽውን ነገር ማውራት ደስ ይላል ለምሳሌ እኔ ሁሌም ሀሳብ የሚሆንብኝ ቃልዬ ከተመረቀች በሁዋላ የት ነው ተቀጥራ ስራ መስራት የምትፈልገው ድሬ ነው ወይስ አዲስ አበባ የሚለው ነገር በጣም ያሳስበኛል። እንኳን ስለወወፊቱ ስለዛሬም ስጠይቅሽ ጭቅጭቅ ስለሚመስልሽና ቶሎ ስለሚሰለችሽ ግን ጠይቄሽ አላውቅም ።"ስላት በስስት እያየችኝ ከተቀመጠችበት ተነስታ ወደኔ መጣችና አቀፈችኝ። ኤፍዬ ሙት አንጀቴን አላወስከው። እንደተመረቅኩ ያው ቤተሰቦቼ ለምርቃቴ መምጣታቸው ስለማይቀር አብሪያቸው ሄዳለሁ ትንሽ ቆይቼ ወደዚህ ተመልሼ ነው ስራ መፈለግ የምጀምው ከፈለክ አንተ ወደ አዲስ አበባ ትመጣና ወደዚህ አብረን እንመለሳለን ፣ይሄንን ቀደም ብዬ ሳስብት ነበር ኤፍዬ አፈቅርሀለሁ እሺ" ስትለኝ ያለንበት ቤት ብቻ አይደለም ምድር የጠበበችኝ እስኪመስለኝ በደስታ ተጥለቀለቅኩ። እንቅፋት የገጠመው የመሰለኝ ፍቅራችን በዚች በቃልዬ ንግግር እንቅልፋቱ ሁሉ ሲጠራረግ ታየኝ። ተስፋዬን አለመለመችው። በዚች ምሽት ቃልዬ ልትመረቅ ሁለት ወር ነበር የቀራት። መድረሱ ያስፈራኝ የቃልዬ ምርቃት ቀን ናፈቀኝ። እህቴ እገዛልሀለሁ ያለችኝ ሚኒባስ ደግሞ ሶስት ወር ነው የቀረው። እያንዳንዷ ቀን መሽታ በነጋች ቁጥር የምመኘውን ሂወት ወደምጀምርበት ቀን የምታወጣኝን መሰላል እየወጣሁ ያጋመስኩ ያገባደድኳት መስሎ ይሰማኝ ነበር።

ቃክዬ መመረቂያ ግዜዋ እየደረሰ ነው አንድ ወር አከባቢ ሲቀረው የመመረቂያ ፅሁፍ ገለመሌ እያለች በጣም ትዋከብ ነበር።ልክ ቃልዬ ልትመረቅ ሁለት ሳምንት ሲቀራት ስራ ላይ እያለሁ፣ በአንድ ቀን አመሻሹ ላይ ከምሽቱ ሁለት ሰአት አከበቢ ባጃጄ ውስጥ ቁጭ ብዬ ሞባይሌን እየነካካሁ ቴሌግራም አካውንቴ ላይ መልዕክት ገባ። ቴሌግራሜን ከፍቼ ስመለከተው መልዕክቱ የተላከው ደግሞ ከዛ ከማላውቀው ቁጥር ነው። ቃልዬ ጭፈራ ቤት ከዛኪ ጋር ያመሸች ቀን የጭፈራ ቤቱ ስም ተፅፎ የተላከበትን ቁጥር የማይታወቅ ብዬ ይዤው ነበር።
ቴሌግራም ላይ የተላከው መልክት በዛ ቁጥር ነው፣ የተላከው መልክት ፎቶ ነው።ጫን ብዬ ካልከፈትኩት ምንነቱ የማይታወቅ ፎቶ መልክቱን ከፍቼ ማየት ፈራሁ። ሳመነታ ቆየሁ፣ በመጨረሻም ከፈትኩት ። ፎቶው የሰው ፎቶ አይደለም፣ ሁለት ሰዎች የተላላኩትን መልክት 'እስክሪን ሹት' አድርገው ነው የላኩልኝ። የመልክት ልውውጡ እንዲህ ይላል•••

"ዛኪ ነገ የት ነህ አንገናኝም?"

"ነገ ግቢ የለሁም ባክህ?"

-"የት ልትሄድ ነው?"

" ከችኳ ጋር ሀረር ልንሄድ ነው"

"ኧረ ባክህ ደስ ይላል ፈታ ልትሉ ነዋ ፣ ስንት ሰአት ነው የምትሄዱት በጥዋት ነው ያቺን መፃፍ ፈልጌ ነበር?''

"አይ በጥዋት አይደለም ከምሳ ሰአት በኋላ የምንሄድ ይመስለኛል እስከስድስት ሰአት አለሁ ናና ውሰድ ወይ እኔ እራሴ አቀብልሀለሁ"

"በቃ ለማንኛውም ጥዋት እንደዋወል"

የሚል ነበር ። ዛኪ ከአንድ ግቢ ካለ ወንድ ጋደኛው ጋር የተለዋወጠው መልክት መሆኑ ግልፅ ነው።

ያንን ፎቶ አንስተው የላኩልኝ ዛኪ ሀረር የሚሄደው ከቃል ኪዳን ጋር እንደሆነ ሊነግሩኝ መሆኑን ሳስበው በተቀመጥኩበት ቢዥዥዥ አለብኝ። አዞረኝ። ባጃጄ ውስጥ የነበረውን ኮዳ አነሳሁና ውስጡ ያለውን ውሃ አናቴ ላይ አፈሰስኩት። በውሃ የሚቀዘቅዝ መች ሆነና። ምን እንደማስብ ምን እንደማደርግ ግራ ገባኝ። ከባጃጄ ላይ ወርጄ ጭለማ ቦታ መርጬ ድንጋይ ላይ ቁጭ አልኩ።

ለብዙ ደቂቃዎች ምናልባትም ለአንድ ሰአት ያህል ቁጭ አልኩ። ትንሽ ስረጋጋ ወደ ቃልዬ ስልክ ደወልኩ።,በቃ ነገ እፈልግሻለሁ እላታለሁ፣ አይመቸኝም ካለች የማይመቻት ከዛኪ ጋር ሀረር ለመሄድ እንደሆነ በግልፅ እነግራታለሁ። እኔ ብሸሸውም እየተከተለ ስቃዬን ያበላኝን እውነት አፍርጬው የምትለውን እሰማታለሁ ። ብዬ ከወሰንኩ በኋላ ነበር ወደ ቃልዬ ስልክ የደወልኩት።ስልኩን አንስታ.. "እንዴት ነህ ኤፍዬ?" ስትለኝ ደፍሬ ያንን ልበላት አልበላት ግን እርግጠኛ ልነበርኩም ። ብቻ ደውልኩ ። የቃልዬ ስልክ ጥሪ አይቀበልም።ከደረሰኝ መልክት በላይ የቃልዬ ስልክ ዝግ መሆኑ ቅስሜን ሰበረው። በሩጫ ግቢያቸው ድረስ ሂድና ስሟን እየጠራህ ጩህ ጨህ አለኝ ። ነገርግን ከተቀመጥኩባት ድንጋይ ላይ አልተነሳሁም። ሶስት ግዜ እየቆየሁ እየቆየሁ ብሞክርላትም ስልኳ ጥሪ አይቀበልም፡፡ ሀሳቤን ቀየርኩ ቃልዬ ስልክ ላይ መደወሌን ትቼ ፍፁም ወደሚባል እንደኔው ባጃጅ ያለው ጋደኛዬ ጋር ደወልኩ ለነገ ባጃጁን እንዲያውሰኝ እና ከፈለገ የኔን ባጃጅ መጠቀም እንደሚችል ስነግረው ።
እኔ ነገ ስራ አልወጣም ናና ውሰድ አለኝ። ምንም ሳልተኛ አደርኩ። ጥዋት ሶስት ሰአት ላይ የሱን ባጃጅ ይዤ እነቃልዬ ዩንቨርስቲ መግቢያ አከባቢ አደፈጥኩ።
.
.

https://vm.tiktok.com/ZMk1XrBAJ/

8.2k 0 17 16 190

❤️ ተማሪዋ ❤️
.
.

🌹🌹 ክፍል 43 🌹🌹


.

አለች እንጂ የኔዋ ያፈር ገንፎ የመሰለች ወድጄ መሰለህ እንዴ እንዲህ አፈር የመስልኩት። እቺ እኮ ጣፋጭ ጠረኗ ሁሉ እስካሁን እስካሁን ባጃጁ ውስጥ አለ ። አለች እንጂ የኔዋ የላብ ገንቦ ወድጄ መሰለህ እንዴ አፍንጫዬ ላይ ማድያት ያወጠሁት።
ያንተ እኮ ሀፒታይዘር በላት ሽንኩርት የሆነች ልጅ አለች እንጂ የኔ ዘጊ ምግብ ስነላ ፊቴ ተቀምጣ ካፈጠጠች ምግቡ ይዘጋኛል ወድጄ መሰለህ እንዴ እንዲህ ባጥንቴ የቀረሁት።"

ወድጄ መሰለህ እያለ ሁሉንም የሱን እንከን በሚስቱ ላይ ሲለድፍ ግራ ገብቶኝ ከሳቄ መልስ ..ቆይ ጠልፋህ ነው እንዴ ያገባሀት?" አልኩት
"እንዴት?
"ፈልገህ አደል እንዴ ያገባሀት?" አልኩት።
"መጀመሪያ እማ ያገባሁዋት ላባቷ አንድ ልጅ ነች ብቸኛ ወራሽ እሷ ነች ብዬ ነበር።
አባቷ ሲሞት ለካ በየቀበሌው ሁለት ሁለት ወልዷል ተጠራርተው ስምንት ሆነው መጡ ከኔዋ ጉድ ጋር ዘጠኝ አትልም አንዷን ውርስ ለዘጠኝ በጣጥሰው ሲካፈሏት ክው አልኩ። ለሚስቴ የደረሳት ብር አመትም አልቆየ አለቀ፣  ከዛ በሀላ በሰላም ውለንም አድረንም አናውቅም ጭራሽ ያባቷን ፈለግ ተከትላ ስምንት ልጅ በየቀበሌው ልትወልድ ነው መሰለኝ አርፋ አትቀመጥም ወድጄ መሰለህ እንዴ እንዲህ የምጠጣው ?"  ብሎኝ ወረደ።

የቃልዬ ዳንስ አይኔ ላይ እየተርገበገበ፣ የኪያ ንግግር ጆሮዬ ላይ እያቃጨለ አልጠፋ አለኝ። ለሶስት ቀን ያህል ከገባሁበት ድባቴ አልወጣሁም። ከቃልዬ ጋር በስልክ እንደነገሩ ከማውራት ውጩ ሶስቱንም ቀን አልተገናኘንም።ቃልዬ በደወልኩም በደወለችም ቁጥር ምን ያህል እንደምታፈቅረኝ ሳትነግረኝ ስልኩን አትዘጋም።
ናፍቆት ፀናብኝ። የቃልዬ ናፍቆት ዳንሱንም ከአይኔ ላይ የኪያን ንግግርም ከጆሮዬ ላይ ጠራርጎ ድራሹን አጠፋው። ሶስት ቀን ያላየኋት  ቃልዬ በብርቱ ናፈቀችኝ።
ንዴቴም ፣ ብሶቴም፣ ኩርፊያዬም በቃልዬ ናፍቆት ታጥቦ ገደል ገባ። እሷን ከማግኘት ረሀብ ውጪ የሚሰማኝም የሚታየኝም ነገር ጠፋ። በሶስተኛው ቀን ማታ ወደቃልዬ ስልክ ደወል።
"ሄሎ" አለኝ የወንድ ድምፅ ነው ። ክፉኛ ደንግጬ ስልኩን ከጆሮዬ ላይ አወናጭፌ አወረድኩትና አፈጠጥኩበት ። አልተሳሳትኩም ቃልዬ ላይ ነው የደወልኩት ..ሄሎ ....አልኩ ደግሜ ካሁን አሁን ዛኪ ነው መቸስ ስልኳን ያነሳሁ ማነህ አንተ ቢለኝ ማነኝ እንደምለው እያሰብኩ ሄሎ አልኩ። ቃልዬ ''ኤርሚያስ ምነካህ የሰው ስልክ አይነሳም እሺ ብልግና ነው " እያለች ስልኩን ስትቀበለው ተሰማኝ።
"ሄሎ ቃልዬ!" አልኩ በልቤ አወይ ጣጣዬ ኤርሚያስ ደሞ ማን ይሆን እያልኩ።
"ሄሎ ኤፍዬ ይቅርታ እሺ አንዱ የክላስ ልጅ ነው መመረቂያ ፅሁፉን በግሩፕ ስለምናዘጋጅ አንድ ግሩፕ ነን እና ዶክመንት ልላክ ብሎ ተቀብሎኝ ስልኬ እሱ ጋር ነበር ይቅርታ እሺ?"አለችኝ። "ችግር የለውም ቃልዬ ናፍቀሽኛል ቃሌ ነገ ላገኝሽ እፈልጋለሁ" አልኳት። እኔም ንፍፍፍቅ ነው ያልከኝ" አለችኝ። በቃ ምንም እንዳልተፈጠረ በንጋታው ምሳ ሰአት ላይ ቃልዬን እስካገኛት ጓጓሁ።

በንጋታው ምሳ ሰአት ደረሰ አልደረሰ እያልኩ አራት ሰአት ላይ ጌትነት ስልኬ ላይ ደወለ። የደወለው ማን እንደሆነ እንዳየሁ ነበር ገና ስልኩን አንስቼ ሳላናግረው የኔና የቃልዬ የምሳ ቀጠሮ ወደ አዳር እንደሚቀየር እርግጠኛ የሆንኩት። "ሄሎ ጌትሽ አማን ነው ?" ወዬ ኤፍዬ እንዴት ነህ ? አቦ ድንገት ለሆነ ጉዳይ ተደወለልኝ እና ከድሬ ልወጣ ነው ፣ እቤት እንድታድርልኝ ላስቸግርህ ነው ጋደኛዬ" ኧረ ጣጣ የለውም አባቴ ገና ስትደውል ነው ባየር ላይ የምሳ ቀጠሮዬን ወደ እራት የቀየርኩት" ካካካ ያው እራት ማለት ደሞ አዳር ነው በለኛ"
''እሱ ግልፅ ነው መጠየቁስ" ሀዬ ኤፍዬ በቃ ቁልፉን የተለመደው ቦታ ሱቋ ውስጥ አስቀምጬ ሄዳለሁ"

"እሺ ጌት ሰላም ግባ"

ወድያው ለቃልዬ ደውዬ የምሳ ቀጦሮኣችን ወደ አዳር መቀየሩን ከነ ምክንያቱ ስነግራት እሺ ኤፍዬ ልትወስደኝ ስትመጣ ደውልልኝ" አለችኝ። እስከ ምሽቱ አስራ ሁለት ሰአት ስሰራ አመሸሁና ቃልዬን ይዣት ወደዛው አመራን።
"ዛሬ እራት ምርጥ ጥብስ ነው የምሰራልህ ስጋ ገዝተን እንግባ ኤፍዬ" ጥሬ አይሻልም ቃል?" "ጥሬማ ምን ስራ ያስፈልገዋል? እኔ ግን ጥብስ ሰርቼ ባብላህ ነው ደስ የሚለኝ ቡናም እናፈላለን " አለችኝ። አልገባትም ቃልዬ። ጥሬ አይሻልም ስላት የሀረሩ ትዝ ብሏት ትስቃለች ብዬ ጠብቄ ነበር። ገብተን እየተጋገዝን እራት ሰርተን እየተጎራረስን በልተን እንዳበቃን ቡና እየጠጣን "ቃልዬ ቅድም ጥሬ ምናምን ስልሽ ምንም ትዝ አላለሽም እኔ ታስታውሽዋለሽ ብዬ ጠብቄ ንበር" ምኑን ኤፍዬ?"

"ትገርሚያለሽ የሀረሩን ቆይታችንን ረስተሽዋል ማለት ነው"

"ኦኬ. ካካካካ የእውነት ግን ጥሬ ስትለኝ አልመጣልኝም እንጂ የሀረሩን ቆይታችንን አንድም ቀን ሳላስታውሰው አድሬ አላውቅም ሁሌ ነው ስተኛ ስተኛ ትዝ የሚለኝ" "እህ ለምንድን ነው ስተኚ ስተኚ ትዝ የሚልሽ ቀንስ?"

"ያው ቀን በተለያየ ነገር ማለት በትምህርት፣ በጥናት፣ ባንተ ሀሳብ፣ በቃ በብዙ ነገር ቢዚ ሆኜ ስለምውል ነዋ ። ጋደም እንዳልኩም ስላንተ አስባለሁ ያኔ ለመጀመሪያ ግዜ አብረን ያደርንበት ሀረር ትዝ ትለኛለች ። ከዛ ያንተ ወሬ ፣ ጥሬ ስጋው ዳንሱን ሁሉ በየተራ አስታውሰዋለሁ"

''ለመጀመሪያ ግዜ አብረን ያደርነው ሀረር ነው እንዴ ቃል" ሂድ ወደዛ እና በተገናኘን በዛው ምሽት ያደርነውን አዳር እንደአዳር ላስታውሰው እንዴ?" ለምንድን ነው የምታስታውሽው ያኛው በደረቁ ስለሆነ ነው"

"ኪኪኪኪ አቦ ያድርቅህ ወደዛ ሞዛዛ" አለችኝ። ቃልዬ አፈረች።

"እኔማ ሀረርን የረሳሻት መስሎኝ ገርሞኝ ነበር"

"እንዴት ይረሳል ኤፍዬ ያኔ ስታወራ የነበረውን ወሬ ባስታወስኩት ቁጥር እስቃለሁ አይ ኤፍዬ ግልፅነትህ እኮ ደስ ይላል!! ስትለኝ ሀረር እያለን ከግልፅነቴ ውጪ የምትወጁልኝ ምንድን ነው ስላት ሌላ ግዜ ነግርሀለሁ ያለችኝ ትዝ አለኝ። ጠየኳት።

" ኤፍዬ ሙት ሁሉ ነገርህን እወድልሀለሁ ብቻ አንዳንዴ•••'' ብላ እያየችኝ ዝም ብላ ቆየችና

"በቃ አሁን ቡናውን እንጠጣ አታስለፍልፈኝ " አለች፡፡

"ቃልዬ ደሞ አንዴ ጀመርነው እኮ ቆይ ከኔ ባህሪ የማይመችሽ ወይ የማትወጂው አለ ? እሱን ንገሪኝ እስቲ"

"ኤፍዬ ሙት ብዙ የለም ብቻ አንዳንዴ ድንገት የሚቀይርህ ነገር አለ ዝም ብሎ የሚከፋህ ነገር ያኔ እጨነቃለሁ"

"ሌላስ?"..

"ሌላው ደሞ ቶሎ ግንፍል የምትለው ነገር ያስፈራል ኤፍዬ እኔ ላይ አይደለም ግን በቀደም ያንን ሰካራም ሰውዬ ልታንቀው ስትንደረደር ላየህ ሁኔታህ በጣም ያስፈራ ነበር እኔ እራሴ ፈራሁህ። እንዴ ኤፍዬ እንዲህ አይነትም ባህሪ አለው እንዴ ነው ያልኩት። ሀረር እያለንም እየደንነስን አንዱ ሳያውቅ ገፋ አድርጎኝ እንዴት እንዳሽቀነጠርከው ትዝ ይልሀል ? ደስ አይልም ቶሎ ወደ ፀብ የምትገባ ሰው እንድትሆን አልፈልግም"

"እሺ ቃልዬ አስተካክላለሁ" አልኳት።

ቃልዬ እንዳለችው ቶሎ ወደ ፀብ የመግባት ድክመቴን አምኜ እቀበላለሁ። በርግጥ ከድሮው አንፃር አሁን እሻላለሁ። ቃልዬ ድሮ ብታውቀኝ ደንብራ ካጠገቤ ትጠፋ ነበር አልኩ በውስጤ። ድንገት የሚቀይር ድንገት የሚከፋህ ያለችው ነገር ግን በሷና በዛኪ ድፍንፍን ባለ ግኑኝነት ምክንያት የመጣብኝ አዲስ ህመም ነው።

ምን ላድርግ ተናግሬም የማይወጣልኝ ትቼም የማልተወው ህመም ሆነብኝ።
.
.

https://vm.tiktok.com/ZMhTas2wC/

9k 0 18 20 210

❤️ተማሪዋ ❤️

.

🌹…………ክፍል 42 ……….. 🌹
.
በአይነ ህሊናዬ ታየኝ ፣ ከዚህ ጭለማ በላይ የኔ ሂወት ሲጨልም ታየኝ  እውን የሆነ ያህል ደንግጬ •••
"ኧረ ቃልዬ!" አልኩ ሳይታወቀኝ በደመነፍስ ።
"ምንድን ነው የምትለኝ ኤፍዬ ግባና ንዳ እንጂ ቀስ እያልክ ንዳ ማለት ይህን ያህል ያናድዳል?" ስትለኝ ከሄድኩበት የሀሳብ አለም ባንኜ።
"ምናልኩሽ?" አልኳት ደንግጬ።
ግባና ንዳ እራስሽ ንጂው አልነዳም እየተባባልን ስንጨቃጨቅ አንድ ስካር ጢንቢራውን ያጠናገረው ሰካራም ከየት እንደመጣ እንጃ ጎንበስ ቀና እያለ መጣና ድንገት ባጃጇ ውስጥ ጥልቅ አለ።
"ወይኔ ኤፍዬ ድረስ !!" ብላ ጮኸች ቃልዬ ደንግጣ። ዛኪዬ ድረስ አለማለቷም ተመስገን ነው።
"እሰይ  እኔን እብድ ስትይ የለየለት መጣልሽ " አልኩ በውስጤ ሰውየውን እያየሁት።
"የየየየየ የምን ኤፍዬ ነው ? የኔ ስም ገረመው ነው ቆንጅት ኤፍዬ ትያለሽ እንዴ ገረመውብለሽ ጥሪኝ ህቅ•••እስቲ ገረመው በይ?" አላት ። ከመስከሩ የተነሳ ቁጭብ ሎም መሸከም ያቃተው ጭንቅላቱ ብቻውን ይንገዳገዳል።
"አሁን ትወርዳለህ አትወርድም ገረመው እኔ ሰው አልጭንም " አልኩት።
"ምናልክ ሹፌሩ ሰው አልጭንም እና ኩንታል ልትጭን ነው እንዴ የቆምከው በባጃጅ ኩንታል ወግ ነው ሲዳሩ ማልቀስ አቅምን አውቆ መኖር ጥሩ ነው የሚለውን ዘፈን ጨርሰህ ዝፈነው እሺ ያኔ አቅምህን ታውቃለህ። እኔ እዚህ ጨለማ ውስጥ ባጃጅ ጥበቃ ስንት ሰአት እንደቆምኩ ታውቃለህ  ሰው አልጭንም ይላል እንዴ እና ይቺ ከጎኔ የተቀመጠችው ኩንታል ነች እንዴ ? እሄው በደንብ አየኃት አይደለችም " እያለ ወደ ፉቷ ጠጋ ብሎ ሲመለከታት ቃልዬ ሽምቅቅ ብላ  ባጇጇ ላይ ተጣበቀች።
"አይዞሽ የኔ ቆንጆ አስደነገጥኩሽ አደል ይቅርታ አንቺኮ  በጭለማ ውስጥ ያለሽ   የ-የ-የ-የ የብርሀን ጭላንጭል ነሽ ።
አይገርምሽም ታምሪያለሽ አይገልፅሽም።
  አለች እንጂ የኔ ሚስት በጨለማ አትታይ በፀሀይ አትታይ ምኗን አይቼ  እንዳገባሁዋት  ግራ ገብቶኛል።
ወድጄ መሰለሽ የምጠጣው ምናልባት ምኗን አይቼ እንደወደድኳት ስጠጣ ቢገለጥልኝ ብዬኮነው።
ሴት መሰለችሽ ሰላቢ በያት እሄው እሷን ስከታተል ስንት አመት ሆነኝ እሳን እጅ ከፍንጅ እይዛለሁ ብዬ  ስከተላት  ስንት ቦታ ፈንጅ ረገጥኩ መሰለሽ።
እኔና ሚስቴኮ አብረን እየኖርን የተፋቷን ብቸኛ ባለትዳሮች ነን ።
አብረን እየኖርን አብረን እያደርን ነው አሁንም ድረስ ግን ተፋተናል።
ብዙ ወሬ ሰማሁ ወሬ ሰምቼ ከምወስን በገዛ አይኔ አይቼ ቢለያኝ ይሻላል ብዬ ምንም እንዳልሰማ ባል ሆኜ በድብቅ እከታተላት ጀመር እኔ እሷን ተደብቄ ልከታተል እሷው ተደብቃ እኔን ትከታተለኝ እስከሚምታታብኝ ድረስ እንኳንስ በማታ በቀንም ላገኛት አልቻልኩም ቀን ከስራ እቤት መጥቼ የለሽም የት ነበርሽ ስላት አጠገብህ ትለኛለች ። በቃ ሁሌ ያለሁበት ቦታ ሁሉ ያለች ይመስለኛል ወድጄ መሰለሽ ድምፄን ቀንሼ የማወራው የምትሰማኝ እየመሰለኝ እኮ ነው ።
" ባጃጁን ያቆምኩት ላንተ አይደለምና ውረድ!" አልኩት በንዴት!።
"ስማ ሹፌሩ አንተም ወንድ ነህ ነገ ማግባትህ መውለድህ አይቀርም የጀመርኩትን ወሬ ልጨርስበት አታቋርጠኝ ምን ይመስላል በሚስቴ ሞት።
ለኔማ ነው ያቆምከው!  ለሌላ የቆምክ መስሎህ ነው እንዴ?
እኔን  እኮ ነኝ  እዛ ጋር ቆሜ ያየከኝ።  ሌላ ሰው ቢኖር ለምን እስካሁን አልመጣም?  ይልቅ አንተ ስራህን ስራ ከልጅቷ ጋር ላውራበት" ሲል ቃልዬ ሳቀች። አንገቱን ከኔ ላይ መንጭቆ  በፍጥነት ወደሷ ዞረና•••
"ምን ምን ምን ምን እስቲ በናትሽ ሳቅሽን ድገሚው  የተኮረኮረ ህፃን ልጅ እኮ ነው የምትመስይው !
ግን ግን በናትሽ ካላስቸገርኩሽ ያሁኑን ሳቅ አንዴ ድገሚልኝ !" አላት ። ተበሳጨሁ።
"ስማ ሰውዬ  የሷ ሳቅ ስትጋት ያመሸከው ጠጅ መሰለህ እንዴ የሚደገመው  አሁን የምትወርድ ከሆነ በፀባይ ውረድልኝ? አልኩት።

"ጠጅ አልጠጣሁም አረቄ ነው ጠጅ ስጠጣ አይተሀል? ነበርክ? እኔ ጠጅ አልጠጣሁም  አረቄ ነው ነው የጠጣሀት ዝም ብለህ በመላ ምት ጠጅ ትላለህ እንዴ?
ደሞ ሳቅ እንጂ ሌላ ነገር ድገሚኝ አላልኳት ምን አቃጠለክ ኪኪኪኪ " ብሎ ሳቀና ደሞ ወደሷ ዞሮ
"እኔኮ ተሳፋሪ መስለሽኛል  ! ፍቅረኛሽ ነው እንዴ ለካ! በቅናት አንገበገብኩልሻ  አንበሳ ነኝ አደል አንበሳ••••" እያለ ሳቁን ቀጠለው።
ትግስቴ አለቀ።  አንቄ ላወርደው ገና ያዝ ሳደርገው•••
"ኤፍዬ ኤፍዬ ለኔ ስትል ስሞትልህ ኤፍዬ ልቀቀው እራሱ ይወርዳል!" አለች ቃል ግብግብ ብላ።
" አፌ ቁርጥ ይበልልሽ  አንቺ ባትኖሪ ምን  ይውጠኝ ነበር  ሆሆሆሆ ሊበላኝ ነው እንዴ?
እራሱ ድብን ይበል አንቺ ለምን ብለሽ ነው የምትሞችው?  እውነቴን ነው  እድሜ ለሴቶች እንበል  እናንተ ባትኖሩ እኮ እኛ ወንዶች እሄን ግዜ እንደ ዳይኖሰር እርስ በርስ ተበላልተን ከምድረገፅ በጠፋን ነበር! ምኑ ዳይኖሰር ነገር ነው በሚስቴ ሞት ተከመረብኝ እኮ"
"እሺ አሁን ትወርዳለህ አትወርድም?"  አልኩት ወደሱ እየተጠጋሁ..

"እራስህ እኮ ነህ አቁመህ የጫንከኝ !"
"ላንተ አልቆምኩም አልኩህ እኮ!
"ታድያ ለማን ነው የቆምከው?"
"ለሷ!"
"ለሷ ካካካ እሷኮ አብራህ ነው የመጣችው አሃሃሃ  ልታወርዳት ነበር እንዴ የቆምከው ገባኝ !
ታድያ ምን አጣደፈህ ቀስ ብለህ አትቆምም  ብቻሽንማ አትወርጂም ነይ በይ እንውረድ!"
ሲላት•••
ሳላውቀው  በንዴት ውስጥ ሆኜ  ሳቄ መጣብኝ እንደምንም ላለመሳቅ እየታገልኩ ኮሌታውን ይዤ ጎትቼ ላወርደው ስል•••
"እባክህ  ተወው እንደዛ አታድርግ ! ቆይ የት ነው መሄድ እምትፈልገው አንተ ?!" አለችው።
"ብዙ አርቅም እኮ እሄኛው  መጠጥ ቤት ስለተዘጋብኝ  እቅዴ ደሞ አዳሬን መጠጣት ስለሆነ ቤት ልቀይር ነው እዛች ጋ ያለችው ግሮሰሪ ልጠጣ እየሄድኩ ነው ።
ያቺ ግሮሰሪ  አትዘጋም።  ሙች እውነቴን ነው  ያቺ ግሮሰሪ  ካልታሸገች በስተቀር  አትዘጋም
ወደዛ ነው እምሄደው. ዝግ ከሆነች ወደ ከተማ እመለሰላሁ"ሲላት
"በናትህ ኤፍዬ ጣል አርገነው እንለፍ ?" እለችኝ ባይኗ እያባበለችኝ።
ብስጭት እንዳልኩ ባጃጇን አስነስቼ ከነፍኩ።
"ምን አርጊ ነው እምትላት እነጨርሳለን እንጫረሳለን እያልክ ታስፈራራለህ እንዴ?" አለ

እስቲ ዝምበል ስለው ጭራሽ ባሰበት•••
"ዝም አልልም እንደውም እሱን ተይው አንቺ ብቻ  እሺ በይኝ ?"
"ምን ?"
"አንዴ ብቻ የቅድሟን ሳቅ ድገሚልኝ " አላት ቃልዬስ ሳቂልኝ የሚላት  አግኝታ ነው ለቀቀችው። ደስ አለው።
በናትሽ ይህን ሹፌር እናቃጥለው አሁንም ድገሚው ሲላት እኔ እራሴ ሳልፈልግ ሳቄ መጣ።
"ግን ምን ሆነሽ ነው ከዚህ ባለ አስፈሪ ፊት ሹፌር ጋር በጭለማ ብቻሽን የምትሄጂው ?" ሲላት አልቻልኩም። ሳቄን ለቀቅኩት።
"ግሮሰሪዋ ዝግ ነች ምን ይሻልሀል?"
" ዉ ይ ዝግ ነው እንደውም ባንተ ባጃጅ መሄድ አልፈልግን እዛው የጫንከኝ ቦታ መልሰኝ "
"ምን ?" አልኩት እያቆምኩ።
"ኪኪኪኪ ኤፍዬ በናትህ በቃ አድርሰኸኝ ስትመለስ ጣል አድርገው"
"አንቺ ደሞ አበዛሽው!"
ቃልዬን ግቢ በር ላይ አድርሻት እንደወረደች ።
"ኬት ጠብ አደረካት ይቺን የመሰለች ልጅ እባክህ አንባሳ ነህ አባቴ ይሙት ኮራሁብህ ጀግና " ሲለኝ አሁን ገላጋይ የለም ብሎ እያባበለኝ መሆኑ ገባኝና ፈገግ አልኩ።

https://vm.tiktok.com/ZMh7Q9na4/

9.5k 0 25 11 224

❤️….. ተማሪዋ ……❤️

🌹🌹ክፍል 41 🌹🌹

አልኳት አዎ አውቀዋለሁ " አለችኝ ፀጉሯን በጣቶቿ እየነካካች።
"ስንቴ መጥተሻል?"
"አንድ ሁለቴ"
"ከማን ጋር?"
"ከግቢ ልጆች ጋር ነዋ ብቻዬን አልመጣ ምነው ኤፍዬ?"
"አይ ምንም መች ነበር የመጣሽው?"
"እህህህ ኤፍዬ ምንድን ነው፣ መጥቻለሁ ከግቢ ልጆች ጋር አልኩህ ፣ የግድ ቀንና ሰአቱን ማስታወስ አለብኝ  የወንጀል ምርመራ ጥያቄ አስመሰልከው እኮ"
"በይው"
"በ. ይ. ው. ምኑን ነው እምለው ኤፍዬ. መነታረክ ትተን ነበር ደሞ ሊጀምርህ ነው?" ስትለኝ ሀሞቴ ፍስስ አለ። በቃ እኔ የምጠላው ነገር በቃልዬ መፈረጅ ነው። ቃልዬ ጨቅጫቃ፣ ነትራካ፣ ተጠራጣሪ፣ የሚቀና ወንድ አድርጋ ስታስበኝ ያመኛል ። ምንም ነገር መጠየቅም መስማትም ያስጠላኛል።  መነታረክ ትተህ ነበር ሊጀምርህ ነው ስትለኝ ገና እራስ ምታቱ ጀመረኝ።ዝምምም አልኩ።
" በቃ እንሂድ " አለችኝ።
"ለምን ቃል?" አልኳት በደከመ ድምፅ ። የራሴ ሁኔታ እኔኑ አሳዘነኝ።
"ብዙ አልቆይም ስለናፈቅከኝ አግኝቼህ ልመለስ ብዬህ አደል የመጣሁትአለች። መግባት አለብኝ " አለች።
ብዙ ግዜ ብዙ አልቆይም አየት አድርጌህ ልመለስ ብላኝ መጥታ አብረን አድረናል። አሁን ለምን ጥያቄ አበዛብኝ ብላ እንጂ ሌላ የምትሄድበት በቂ ምክንያት ቢኖራት ትነግረኝ ነበር። ። እንድትቆይ ላግባባት አልችልም ውስጤ በሚያስጠላ ስሜት እየተተራመሰ ነው ፣ መበሳጨቴን መደበቅ አልቻልኩም።
ቃልዬን ክፉ ነገር ከምናገራት ብሸኛት እንደሚሻል  አሰብኩና
"እኔም እራሴን እያመመኝ ነው ልክ አይደለሁም ነይ በቃ ላድርስሽ"  ብያት ወጣን ።
የራስ ምታቴ ምክንያት ምን እንደሆነ መች ይገባታል። ምን ሸቶህ ነው ፣ ጉንፋን ሊይዝህ ይሆን ለምን ከፋርማሲ መድሀኒት አንገዛም እያለች ስትወተውተኝ
"ተይኝ ቃልዬ እፈልገዋለሁ!"አልኳት።
" ምኑን?" አለች ግራ ገብቷት።
"በሽታውን እራስ ምታቱን "
"ኤፍዬ ምን ሆነሀል ዛሬ?"
"እራሴን አሞኛል አልኩሽ አይደል ቃሌ"
"እሱን እማ ፈልገዋለሁ ተመችቶኛል እያልክ አይደል እንዴ"
"አንዳንዴ ቢያሳምሙሽም  አብረውሽ እንዲሆኑ እምትፈልጊያቸው ነገሮች አሉኮ
"በናትህ ኤፍዬ አታላግጥ ይልቅ መድሀኒቱን እንግዛ"
"አልገዛም መታመሙን እፈልገዋለሁ አልኩሽ እኮ"
ተናዳ ዝም አለች። እኔም ዝም አልኩ። ከግማሽ መንገድ በላይ በፀጥታ ከሄድን በኋላ
"ኧረ ቀስ ብለህ ንዳ  ኤፍዬ ! እንዴ እንዴት እንዴት ነው የምትነዳው ? ያስፈራል " አለችኝ።
ባጇጇን ቀጥ አደረኩና " ሰአቱ ሄደ መሸብኝ እቤት ይቆጡኛል ገለመሌ ብለሽ ያጣደፍሽኝ አንቺው አይደለሽ እንዴ? ነይ ንጂዋ እንግዲህ እስቲ ንጂውና እንዴት እንዴት መሄድ እንዳለብኝ አሳይኝ!" ስላት እሷ ገና እቤት ይቆጡኛል የሚለው ንግግሬ ጋር መሳቅ ስለጀመረች ከዛ በኋላ የተናገርኩትን የሰማችኝ አልመሰለኝም።
እኔ በብስጭት የምይዝ የምጨብጠው ጠፍቶኛል እሷ ትስቃለች።
"እና አሁን ለምንድን ነው እዚህ ጭለማ ውስጥ የቆምከው"
"በቃኣ አነዳድህ አልተመቸኝም እያልሽ አይደል ነይና ንጂዋ"
"ሆሆሆ እብድ" አለችኝ። ካበድኩ ስለቆየሁ ስድብ ሳይሆን ስሜ መሰለኝ።ጭራሽ ከባጇጇ ወርጄ በቀኝ በኩል በመቆም " ውረጂና ንጂ እኔ ከጀርባ እቀመጣለሁ ያለበለዚያ እዝቹ ባጃጅ ውስጥ እናድራታለን እንጂ አልነዳም አልኳት።
"አሪፍ ነዋ እንደውን ወደፉት እያስታወስነው የምንስቅበት ጥሩ ትዝታ ይሆነናል " ስትለኝ ደሞ በረድ አልኩ።
በአንዲት ቃል ስታቀዘቅዘኝ እራሴን ታዘብኩት " ምን ይሻልሀል ኤፍሬም በቃ ቃልዬ ስትፈልግ የምታነድህ ስትፈልግ በአንዲት ንግግር ብቻ የምታበርድህ የኤሌትሪክ ምድጃ ሆነህ አረፍከው የኤሌትሪክ ምድጃ እንኳን በጣም ከጋለ በኃላ ሶኬቱ ቢነቀልም ለመቀዝቀዝ ግዜ ይወስድበታልኮ!" አልኩት እራሴን ።
ለወደፊቱ እያስታወስን የምንስቅበት ጥሩ ትዝታ ይሆነናላ ስትለኝ ቃልዬ ከኔ ጋር እስከመጨረሻው መዝለቋን ያረጋገጠችልኝ ያህል በንዴት ውስጥም ሆኜ ደስ ስሊኝ ገርሞኝ።
በርግጥ ለወደፊት በፍቅር በትዳር አብሮ ስለመዝለቅ ከቃልዬ አንደበት ሲወራ ሰምቼ አላውቅምና ይህ ንግግሯ ብርቅ ቢሆንብኝ በኔ አይፈረድም። ቢሆንም ባጃጁን አለመንዳትና ቃልዬን ማበሳጨት የኔን ንዴት ያበርደው ይመስል ባለመንዳት አቋሜ ፀናሁ።
ንዳ አልነዳም ስንነታረክ ለምን ትናንት እዛ ጭፈራ ቤት ኮንትራት የፈለገ ሰው ደውሎልኝ ስመጣ አየሁሽ ብያት አልገላገልም በውስጤ ይዤው ከምብሰከሰክ እንደዛ ብያት ብገላገልስ አልኩ።
ያው መልሷ የታወቀ ነው መቸስ ።
"ትናንት የዛሬው ጭፈራ ቤት አየሁሽ ልበላት እንዴ?"
ጭንቅላቴ ከመፈንዳቱ በፊት ተንፍሸው ልገላገል የምትለውን ትበል።
በቃ ለኔ ሁለቱም ያው ነው ፣ እኔ በጭንቀት ከመፈንዳቴ በፊት ጭንቀቴን ተንፍሸው ያበጠው ይፈንዳ።
ምን ብዬ ልጠይቃት•••
"ቃልዬ ከአንድ ቀን በፊት ዛሬ የሄድንበት ጭፈራ ቤት አየሁሽ ልበል?" ስላት
ቃልዬ  ብስጭት ንጭንጭ እያለች
" አዎን እኔና ጓደኞቼ  እና የአክስቴ ልጅ  ሆነን ወጣ ብለን ነበር "
"ኡፍፍፍ••• እና ያክስትሽ ልጅ ከሆነ  ከሱ ጋር እንደዛ እየተሻሹ መደነሱ ለምን አስፈለገ?"

ምን ? ምናልክ እንኳንም በግዜ አወቅኩህ ለካ እንደዚህ አይነት ሰው ነህ?"
"እንዴት"
"ኦኦኦ ተደብቀህ እኔን መከታተል ጀመርክ ገና ፍቅረኛህ ሆኜ እንዲህ እየተደበቅክ የምትከታተለኝ ብታገባኝማ እቤት ውስጥ ቆልፈህብኝ ነው የምትወጣው እንኳንም በግዛ አወቅኩህ ። እንኳንም ወደፊት ምን አይነት የቅናት ዛር የሚያንዘረዝርህ ቅናታም ባል እንደምትሆን በግዜ እንድነቃ አደረከኝ።  ከዚህ ቀደም ዛኪ ማነው አልከኝ፣ ማንነቱን በግልፅ ነገርኩህ ፣ ከዚህ በላይ ምን ፈለክ ?  ተሻሸሽ ይላል እንዴ እንኳን ተሻሸሁ ደግ አደረኩ በራሴ ገላ ምን አገባህ።  ሆ•••• አንሶላ ስጋፈፍ የያዘኝ አይመስልም በጌታ፣ ምን ውስጥ ነው የገባሁ ትገርማለህ ግን ከማንም ጋር ያሻኝን የመሆን መብት አለኝ እሺ፣ ምንም ነገር የማደርገውም የማላደርገውን አንተን ፈርቼ ከመሰለህ
ለራስህ የሰጠኸው ቦታ የተሳሳተ መሆኑን እወቀው። ሰማንያ ቆርጠህ፣ ሽማግሌ ልከህ ፣ ደግሰህ ያገባኸኝ መሰለህ እንዴ?
ያኔማ  በየመንገዱ ምንድን ነው ለሰውየው ፈገግ አልሽለት እንዴ ? ለምንድን ነው ትኩር ብሎ ያየሽ ? ታውቂዋለሽ እንዴ? እና ካላወቅሽው በየመንገዱ ምን ያስገለፍጥሻል? እያልክ መሳቅ ስፈልግ በናትህ ሳቅ አፈነኝ ልሳቅ እንዴ ኤፍዬ እያልኩ እንዳስፈቅድህ ሳታስገድደኝ አትቀርም።
ተሻሸሽ ይለኛል እንዴ እንኳን ተሻሸሁ ፣ ታድያ አሁንስ ከኔ ጋር ምን ታደርጋለህ አንተም አንዷን ፈልገህ አትተሸሽም?።
ይሄው አንድ አመት ሊሞላን ነው ካንተ ያተረፍኩት ነገር ቢኖር ጭቅጭቅ ብቻ ነው። እኔ ነፃነቴን እፈልገዋለሁ። ቤት ገባት ቤት ወጣሽ ? ማንን አገኘሽ? ከማን ነሽ? እሚለኝ ፍቅረኛ አይደለም እንዲኖረኝ በጭራሽ አልፈልግም!። ካሁን በሁዋላ እንዳትደርስብኝ አልደርስብህም። ድርሽ እንዳትልብኝ። ዞርበልልኝ አትጠጋኝ ኤፍሬም ። እንዳትጠጋኝ እኔ ጮኻለሁ ኤፍሬም!"
እያለች ኤፍዬ ስትለኝ እንዳልነበር ስሜን ከነአሰስ ገሰሱ እየጠራች ፣ እንደአብድ እያደረጋት ፣ ንፋስ ላይ እንደተሰጠ ጨርቅ እየተወናጨፈች ሜዳ ላይ ገትራኝ ስትሄድ....
.
.
ከ 150 ላይክ በኃላ ክፍል 42 ይለቀቃል

https://vm.tiktok.com/ZMhYMxcmU/

9.5k 0 20 22 221

❤️ ተማሪዋ ❤️
.
.

🌹…… ክፍል 40……..🌹

ኢትዮጲያ ውስጥ የትም ቦታ የትኛዋም ሴት ከአክስቷ ልጅ ጋር እንደዚህ የምትደንስ አይመስለኝም ።ለቃልዬ ባክስት ልጅ እና በኔ መካከል ያለው ልዩነት ምንድን ነው ።  ጭፈራ ቤቱ ጥግ ላይ እንደግርግዳ ቋሚ ተለጥፌ እነቃልዬን እያየሁ ስንጨረጨር ስልኬ ጮኸች። ከጭፈራ ቤቱ እየወጣሁ ስልኬን ስመለከታት ያ መልክት የተላከበት የማይታወቅ ስልክ ነው። አነሳሁት።ሄሎ ስል የሚያስጠላ የሴት ልጅ ሳቅ። ፈጣሪዬ ሆይ እኔ አላብድ ያልኳቸው ሰዎች በዙርያዬ አሉ እንዴ ? ደሞ ይሄንን ሳቅ አውቀዋለሁ። መቼ እና የት እንደሆነ ባላውቅም ይህንን ሳቅ የሆነ ቦታ አውቀዋለሁ። ለማስታወስ ሞከርኩ። የመክሊት ሳቅ ነው ። አዎ እራሷ ነች ። በገንኩ ። እንደእብድ አደረገኝ ። አይ ኪያ የቶማስ ሳያንሰው ለመክሊትም አሳልፎ ሰጠኝ ። ደግማ ከሳቀች ለማረጋገጥ ደወልኩ አይነሳም ።
ይሄ ልጅማ ከኔ ጋር የከረረ ፀብ ፈልጓል ፣ጭራሽ ለመክሊት ፣ ወይኔ ኤፍሬም እኔና ኪያ የሚለይልን ዛሬ ነው።
ወደ ጭፈራ ቤቱ መመለስ ይኑርብኝ ወደኪያ መሄድ መወሰን አቅቶኝ ጭለማው ላይ እንዳፈጠጥኩ ደቂቃዎች አለፉ። ኪያን ምን እንደበደልኩት ለማስታወስ ሞከርኩ። ምንም ትዝ አይለኝም ። አንድ ሰፈር ተወልደን አንድ ላይ ተምረን እንደየፍላጎታችን በምንፈልገው የስራ ዘርፍ ተሰማርተን ሂወትን ለማሸነፍ መፍጨርጨር እስከጀመርንበት ድረስ የከረረ ፀብ እንኳን ተጣልተን አናውቅም እንደማንኛውም ያንድ ሰፈር ልጆች በተለያየ ግዜ በተለያየ ጉዳይ ከመከራገር ከመበሻሸቅ፣ከመኮራረፍ እና መልሶ አስታራቂ መሀላችን ሳይገባ በጫወታ ሞቅታ ከመታረቅ ያለፈ ክፉ ነገር በመሀላችን ተፈጥሮ አያውቅም።
ቢያውቅም የዛሬን ያህል በኪያ የተከፋሁበት ቀን የለም የማትነካውን እየነካብኝ ነው ኪያ በማይመጣው እየመጣብኝ ነቅ ኪያ ማንንም ልታገስ በማልችልበት ደካማ ጎኔ እየመጣብኝ ነው። ኪያ ሁሉ ነገሬ ከራሴም በላይ በማፈቅራት በቃልዬ ከመጣብኝ አብሮ ማደግ፣ አብሮ መማር፣  ጓደኝነት፣ወንድምነ ሁሉ ለኔ ቦታ አይኖራቸውም ምክንያቱም ቃልዬ እንኳንስ ከኪያ ከራሴም በላይ አፈቅራታለሁ። እሷ ካጣሁ እኔ እራሴ የታለሁና ቃልዬ እኮ ነች እጅ ላይ በሚጠለቅ ቀለበት ሳይሆን በፍቅሯ ልቤ ላይ ቃልኪዳን ያሰረች የኔ ፍቅር ቃልኪዳን ነች ድጋሚ ወደ ጭፈራ ቤቱ ብገባና ቃልዬን በዛ መልኩ ከልጁ ገር ስትጨፍር ባያት  ያስችለኝ ይሆን በጭራሽ ።
መሀላቸው ገብቼ ቃልዬን ከዛኪ ላይ መንጭቄ እየጎተትኳት ስወጣና ማንው ደሞ ይሄ ጥጋበኛ እያለ ስከተለኝ በደምፍላት ዞሬ አፍንጫውን ብዬ ደሙን ሳንዥቀዥቀው ታየኝ። ከዛ ቡሀላስ በኔና በቃልዬ ማሀል ምን ይፈጠራል?
ሁሉም ነገር  ድብልቅልቁ  ሲወጣ ታየኝ። ስልኳ ላይ ሞከርኩ አሁንም ጥሪ አይቀበልም። የማደርግ የምሆነው ነገር ግራ ገባኝ።
የቃልዬ አደናነስ ፉቴ ላይ ይውለበለባል ተቃጠልኩ።  በኪያ ተንኮልና ወሬ ቃልዬ ላይ መናደድ የሱን ሀሳብ ማሳካት መስሎ ቢታየኝም አለመናደድ አልቻልኩም። እኔኮ የቃልዬን ገላ አይደለም የቃልዬን ቀሚስ ንፋስ እንኳን ሲገልበው እቀናለሁ። ታድያ  እንደዛ ተጠብቃበት ስትጨፍር እያየኃት እንዴት ብዬ ነው አለመናደድ የምችለው።

ስለኔና ስለቃልዬ ለኪያ ያወራሁባትን ቀን ያቺን አርብ ምሽት ክፉኛ ጠላኋት ፣ከአያቴም ከእናቴም የሰማሁትን እርግማኖች ሁሉ ረገምኳት።
ግን ቀኗ ምን ታድርገኝ ። በግድ አፌን ፈልቅቃ አላስወራችኝ። እራሴው ነኝ የግል ሚስጥሬን  ሳልጠየቅ የለፈለፍኩት ሊያውም ለኪያ ። እሄ የተረገመ ልጅ አሁን የት ነው ያለው? በሱ ወሬ ከቃልዬ ጋር ሳይሆን ከሱ ጋር እንደምጣላ ከዚህ ቀደም ነግሬዋለሁ ። ዛሬ በተግባር አሳየዋለሁ እያልኩ ባጃጄን አስነስቼ ከነፍኩ።
እንዴት እና በምን ፍጥነት እቤት እንደደረስኩ አላውቅም። ኪያ እቤት ውስጥ የለም። ገራዡ ዝግ ነው። ገኒ ጋርም ፈለኩት እዛም የለም።
ጭለማ ውስጥ ባጃጄን ተደግፌ እንደቆምኩ እንድ ጥያቄ ውልብ አለብኝ። አዋ እንዴት ግን ቅድም ልክ ጭፈራ ቤቱ በር ላይ ስደርስ ጠብቀው "አትወጣም" ብለው መልክት ላኩልኝ? ያ ማለት እኮ ስገባ እያዩኝ ነበር ማለት ነው። በቃ ኪያ ከመክሊት ጋር እዛው ጭፈራ ቤት አልያም እዛው አከባቢ ነው ያለው። እሄን ሁሉ ነገር የሚያደርገው መክሉትን ለማስደሰት እንደሆነ ግልፅ ነው ። እሱ መክሊትን ለማስደሰት ቶማስን ከዛኪ ጋር እንዲተዋወቅና የት ምሳ እንደሚበሉ የት እንደሚያመሹ መረጃ እንዲያቀብለው አደረገ።  ከዚህ የከፋ ነገር አለመሸረቡንስ ማን ያውቃል እስቲ እንተያያለና እንግዲህ ። ድጋሚ ወደ ጭፈራ ቤቱ ገሰገስኩ።
እነቃልዬ ጭፈራ ቤቱ ውስጥ የሉም ሄደዋል። ኪያንም በዛው ጭፈራቤትና በአከባቢው ባሉ ሆቴሎች ፈልጌ አጣሁት። ቃልዬ ስልክ ላይ ሞከርኩ አሁንም ዝግ ነው። ወደቤት ስመለስ ኪያ አልገባም። ጭራሽ ሳይመጣ አደረ። እንቅልፍ ባይኔ ዝር ሳይል አስቀያሚና ረጅሙ ለሊት እንደምንም ነጋ። እንደተነሳሁ ቀጥታ ወደ ገራዥ አመራሁ። ከኪያ ጋር ክፉኛ ተጣላን። የገራዡ ሰራተኞች  መሀላችን ገብተው ባይገላግሉን ከሱ ጋር ከመነጋገር መደባደቡ ይሻለኝ ነበር።
በዛ ተምዘግዛጊ ምላሱ ከአስር ግዜ በላይ  •••" ኤፍሬም ይልቅ አይንህን ግለጥ !" ይለኛል። ጭፍኜ ስሄድ የት እንዳየኝ እሱ ነው እሚያውቀው ስለኔ እንደማይመለከተው ደጋግሜ ስነግረው እየደጋገመ
"ኤፍሬም ይልቅ አይንህን ግለጥ ከኔ ጋር በመጣላት የምታተርፈው ነገር የለም ትርፉ መቀያየም ነው ። አንተን እና ቃልኪዳንን የማውቃችሁ እኔ ብቻ ነኝ እንዴ? ድሬ ዳዋ ዩንቨርስቲ የሚማረው የድሬ ዳዋ ልጅስ ቶማስ ብቻ ነው እንዴ? ብዙ ተድሬ ልጆች እኮ እዛ ይማራሉ። እሷን ስታደርስ እና ስትመልስ የሚያይህ ብዙ ነው ። ከኔ ላይ አይንህን አንሳና ዙርያህን ተመልከት ፣ እውነቱን በመሸሽ ወይም ከኔ ጋር በመጣላት ፍቅርህን ማትረፍ የምትችል መሰለህ እንዴ? ና ምታኝ ምታኝ ችግር የለውም ፣ እኔን በመምታት ንዴትህ የሚወጣልህ፣ ቃል ኪዳንም ታማኝ የምትሆንልህ ከመሰለህ ምታኝና ደስ ይበልህ!" ሲለኝ እራሴን አቅቶኝ ዘልዬ አንገቱን አነቅኩት። ምታኝ ምታኝ ከማለት ውጪ ለመሰንዘር አልሞከረም ። የገራዥ ልጄች እንዳላቀቁን ምንም ማለት ምንም መናገር አልቻልኩም ወወቤት ገብቼ ተኛሁ።

አመሻሹ ላይ እህቴ ጋር ሄጄ እራት በልቼ ስመለስ ኪያ የራሱን ልብስና መኝታ ይዞ አብረን ከምኖርበት ቤት ለቋል።
እራስ ምታት እያጣደፈኝ ነው የዋለው ። ማታም አለቀቀኝም። ለቃልዬ አልወልኩም እሷም አልደወለችም ።
በሁለተኛው ቀን አመሻሹ ላይ ደወልኩላት። እንዳነሳችው ገና  ለምን ስልክሽን ዘጋሽ  ብዬ ሳልጠይቃት ቀድማ ከትናንት ወድያ ቻርጅ ዘግቶባት እንደነበርና ቻርጅ ስታደርገው ብዙ ግዜ መደወሌን መልክት እንደደረሳት መደወል ፈርታ እስክደውል እየጠበቀችኝ እንደነበር ፣ እንደናፈቅኳትና አሁን ለአጭር ሰአትም ቢሆን ልታገኘኝ እንደምትፈልግ፣  ከቻልኩ ወደ ግቢ ሄጄ እንድወስዳት ነገረችኝ ።
መጣሁ እየወጣሽ ጠብቂኝ ከማለት ውጪ ምንም አላልኳትም።
ግቢ ስደርስ ቆማ እየጠበቀችኝ ነበር።  ምንም ሳልናገር ቀጥታ ከአንድ ቀን በፊት ከዛኪ ጋር ወደጨፈረችበት ጭፈራ ቤት ይዣት ሄድኩ።

በሩ ላይ ስንደርስ "እንዴ ኤፍዬ ዛሬ እዚህ ነው የምናመሸው?" አለችኝ።
"አዎ" ብያት ገብተን ትንሽ እንደቆየን
"ምነው ቃል ቤቱ አልተመቸሽም እንዴ ? ይሄን ቤት ከዚህ በፊት ታውቂዋለሽ?"
.

ከ150 ላይክ በኃላ ክፍል 41 ይለቀቃል 🌹

https://t.me/saloda_trading

7.9k 0 21 19 258

❤️ተማሪዋ❤️


ክፍል 39

.


.


.
ማነው ምናልባት ኮንትራት የፈለገ ደንበኛዬ ይሆን በማላውቀው ስልክየላከው። እንደዛማ አይሆንም ቢያንስ ናልኝ እዚህ ቦታ መሄድ ፈልጌ ነው ይል ነበር። እና ማነው እያልኩ መልክቱ በተላከበት ቁጥር ላይ ደወልኩ ። አይነሳም። ደግሜ ሞከርኩ ተነሳ።
"ሄሎ ሄሎ ሄሎ" ከአንድ የታፈነ ከሚመስል የሴት ልጅ ሳቅ በስተቀር መልስ የለም። እንዴ ቃልዬ ትሆን እንዴ የምታላግጠው እያልኩ ቃልዬ ስልክ ላይ ስደውል ጥሪ አይቀበልም።

"ኦኦኦ ነገር አለ" አልኩና ወደ ጭፈራ ቤቱ መሄድ ጀመርኩ። እኔ ከነበርኩበት ትንሽ ራቅ  ቢልም መንገዱ ነፃ ስለነበር አስር ደቂቃም ሳይፈጅብኝ ነበር በሩ ላይ የደረስኩት።እንደነገሩ ስሰራ አምሽቼ ወደቤት ስገባ ኪያ እንቅልፍ የወሰደው ለመምሰል ማንኮራፋት ጀመረ የለበሰውን ገፍፌ ቀሰቀስኩት።
"ምንድን ነው ኤፍሬም ? ምን ሆነሀል ሰላም አይደለህም እንዴ?" አለኝ የተደናገጠ በመምሰል።
"ምን ሰላም አለ አንተ እያለህ"
"እንዴት ምን እያልክ ነው?"
"ማነው ቃልዬ እዛ ሆቴል ምሳ እየበላች እንደሆነ የነገረህ ቶማስ ነው አይደል? እሺ ከፈለገችው ሰው ጋር ምሳ በላች እና ምን ይሁን ? መብቷ መሰለኝ ከፈለገችው ሰው ጋር ምሳ መብላት ፣ ስማኝ ኪያ ለአንዴና ለመጨረሻ ግዜ አንድ ነገር  ልንገርህ ጓደኛዬ ነህ ከዛም በላይ አብሮ አደግ ወንድሜም ነህ ፣ነገር ግን ልለምንህ ለኔ መተው ያለብህን አንዳንድ የግሌን ጉዳዬች ለኔ ብቻ ተውልኝ።
በቃ ለኔ አስበህ ለኔ ብለህም ቢሆን በኔና በቃል መሀል አንድትገባ አልፈልግም።
እኔና ቃልዬ ጥሩ ሁኔታ ላይ ነን  አንተ ቆፍረህ የምታወጣልኝ ምንም ጥሩ ነገር የለም። ስለቋልዬ ስተትም ይሁን ጥፋት ለማወቅ  ደግሞ እንኳንስ ሌላ ሰው እኔም በድብቅ ልከታተላት አልፈልግም። የሷን መጥፎ ፍለጓ ለምን እባዝናለሁ?
እንደዛ የሚያደርገው እኮ  ያፈቀረ ሳይሆን ለመጣላት ሰበብ የቸገረው ሰው ብቻ ነው።
እኔን የቸገረኝ የቃልዬን ፍቅር መቋቃምና እራሴን መቆጣጠር እንጂ ከሷ ጋር የምጣላበት ሰበብ አይደለም።

ያ ማለት ግን ቃልዬ ልቤን የሚሰብር ስህተት እየሰራች ተሰብሬም አብሪያት እቀጥላለሁ ማለት አይደለም።
ነገር ግን  ቃልዬ ከኔ ጀርባ ድብቅ ማንነት ካላትና ከኔ ጀርባ እኔን የሚያስከፋ ነገር እያደረገች ከሆነ እኔ ባልከታተላትም ፈጣሪ በፈቀደ ግዜ እውነቱ መውጣቱ አይቀርም።

እኔ ግን አሁን ላይ አይደለም  የሷን ስተት ለመፈለግ  የሷን ፍቅር ለማጣጣም እንኳን ቀንና ሳምንቱ አልበቃ ብሎኛል።
ማንም ሰው ቃልዬ እንዲህ ነች እንዲህ እያደረገች ነው ብሎ ቢነግረኝ ቀድሜ የምጠላው የነገረኝን ነው።

እስቲ ንገረኝ ኪያ የሷን ሚስጥርም ይሁን ከኔ የደበቀችውን እውነት ለማጣራት ይህን ያህል ጠልቀህ መቆፈሩ እኔን የማያስደስተኝ ከሆነ ለማን ብለህ ነው የምትደክመው።
ለኔ ያልተገለፀልኝ ድብቅ ማንነት ካላትም በግዜው ይገለፃል። እውነትም ይሁን ሀሰት ስለቃልዬ መጥፎ ነገር መስማት እንደሚያሳምመኝ አወቅ። ህመም ልትሰጠኝ አትጠደፉ።

መታመም ካለብኝ መታመም ባለብኝ ሰአት ልታመም እንጂ በሽታዬን  ፍለጋ አልሯሯጥም ካንተም ለመቀበል አልፈልግም።
እና ኪያ በቃል ዙርያ የምታደርገውም ልታደርግ ያሰብከውም ካለ ተወው ፣ ያሰማራኸው ወሬ አቀባይም ይሁን ወሬ አነፍናፊ ካለም ከዛሬ ጀምሮ አስቁመው ። አደራ !" አልኩት።
ዝም ብሎ በግርምት ሲያዳምጠኝ ቆየና
"ሲጀመር እኔ አየኋት አልኩህ እንጂ ማንም አልነገረኝም "
"እሱን ተወው ኪያ በአካል አይተዃት የማታውቀውን ልጅ ፌስ ቡክ ላይ ፎቶዋን በማየት ብቻ በባጃጅ ስታልፍ ከሩቅ አይተህ ለየኻት አይደል ? የማይመስል ነገር አትናገር እኔ አሁን ከዚህ በፊት ስላለው ነገር ማን ነገረህ ? አየሀት አላየሀት እያልኩ ልነታረክ አልፈልግም ግን በቃ ከዚህ በኋላ ፍላጎቴን ተረድተህ እሷን መከታተልህን አቁም እያልኩህ ነው"
"እሺ " አለኝ ።
"በቃ ጨርሻለሁ እሄው ነው ብዬው ተኛሁ" እሱም ተኝቶ ትንሽ ቆየና
"እህህህም አንዳንድ ተረቶች ግን ይገርማሉ" አለ።
"የምን ተረት?" ቀና ብዬ
"አይ አንቺው ታመጪው አንቺው ታሮጪው የሚለው የድድድድሮ ተረት ገርሞኝ ነው"

"አይ ኪያ ነገር ማርዘም ግዜ ከመግደል ያለፈ ፋይዳ የለውም በግልፅ አትናገርም
ስለቃል እኔ እንደነገርኩህ፣ ስለልጁ ለማጣራት የፈለከውም በራስህ ሳይሆን እኔ በነገርኩህ ነገር ላይ
ተነስተህ እንደሆነ አላጣሁትም ግን በቃ አላስፈላጊ መሆኑን አስቤ ተወው እንዳልኩህም እንዳትረሳው"
"ኧረ አረሳውም በቃ ተውኩት እኮ ኤፊ"
"አዎ ተወው ካሁን በሁዋላ በዚህ ጉዳይ ላይ ማውራት አልፈልግም " ብዬው ተኛሁ።
"ለማንኛውም የፈለገ ብታፈቅርም ማሩን ብቻ ሳይሆን እሬቱንም አምነህ ለመቀበልና ሁሉንም እንደየአመጣጡ ለማስተናገድ እራስህን ዝግጁ ብታደርግ ይሻልሀል ጓደኛዬ የከረረ ነገር ጥረ እይደለም ፍቅርም ቢሆን "
"የሚሻለኝን የማውቀው እኔ ነኝ ኪያ በፈጠረህ በቃ ከዚህ በላይ ምንም አትበለኝ"
"እሺ ደና እደር"
"ደና እደር" ተኛን።

ቃልዬን ስለምሳው  ምንም አልጠየኻትም በነበርንበት ሁኔታ ፍቅራችንን ቀጠልን።
ኪያ ከኔና ከቃል መሀል እንዲወጣ በነገርኩት ልክ በአምስተኛው ቀን ጥዋት ላይ ኪያ ወደ ሽንት ቤት በሄደበት ቅፅበት ስልኩ ጠራ አየት ሳደርገው ቶማስ ይላል አንስቼ  ወሬ አተመላልስ አርፈህ ተቀመጥ ልለው ዳዳኝና የሰውን ስልክ አንስቶ ያን መናገር መቅለል መስሎ ስለተሰማኝ መልሼ ተውኩት።
ኪያ ከሽንት ቤት ሲመለስም •••
"ቃልዬ ቁርስ የት እየበላች እንደሆነ ሊነግርህ ነው መሰለኝ በጥዋት የደወለው ጠርቶ ነው የዘጋው ደውልለት" ልለው አልኩና  ካፌ መለስኩት በቃ ስለቃልዬ ከኪያ ጋር ማውራት በጣም ነበርና ያስጠላኝ ምንም ማለት አስጠላኝ ስልኩን አንስቶ ተመለከተው ቀና ብዬ እንኳን ላየው አልፈለኩም ። ወደስራ ወጣ እኔም ትንሽ ቆይቼ ወደ ስራዬ ሄድኩ።

ይህ በሆነ ከስስት ከአራት ሳምንት በኋላ ቅዳሜ ቀን ከምሽቱ አራት ሰአት ላይ ስራ ላይ እያለሁ ከአንድ ከማላውቀው ስልክ መልክት ደረሰኝ።
መልእክቱ ቡም ጭፈራ ቤት ብቻ ነው የሚለው ። ቡም ጭፈራ ቤት ምን ? ግራ ገባኝ በቃ ቡም ጭፈራ ቤት ብቻ ከፊትም ከውሃላም ማብራሪያ የለውም  በቅርቡ አዲስ የተከፈተውን የጭፈራ ቤት ቅፅል ስም ብቻ ነው ተፅፎ የተላከልኝ።

ከባጃጄ ውስጥ በቅርብ የገዛሁትን ባለ ኮፍያ ጥቁር ጃኬት ለበስኩና ኮፍያውን አጥልቄ ወደ ጭፈራ ቤቱ መግቢያ ጠጋ እንዳልኩ በድጋሚ በዛው ስልክ መልክት ደረሰኝ። ሌላ መልክት በዛው ስልክ። መልክቱ •••
"አትመለስም!" ይላል።ማነው በዚህ ሰአት የህፃን ልጅ ቀልድ የሚቀልደው እያልኩ ወደጭፈራ ቤቱ ዘው ስል ቃልዬን ፊት ለፊት ስትውረገረግ አየኋት። ክፉኛ ደንግጬ በገባሁበት በር የውሀሊት ወጣሁ። ተመልሼ ገባሁ ፣ አዎ እራሷ ቃልዬ ነች ከፊቷ ከሷ ጋር እየተሳሳቁ የሚደንሱ ሁለት ሴት ጓደኞቿ አሉ። ቃልዬ የምትደንሰው ግን ከሴት ጋር ሳይሆን ከወንድ ጋር ነው። ያክስቴ ልጅ ከምትለው ከዛ መከረኛ ልጅ ከዛኪ ጋር እየተሻሸች ስትደንስ አየኋት።
ደሜ ቀጥ አለ።ከመደነሷ አደናነሷ በጣም ያበሳጫል። ምን ነካት ግን? ከአክስት ልጅ ጋር እንዚህ ሲደነስ የት ነው ያየችው።
.
.
ከ 150 Like በኃላ ………….

https://vm.tiktok.com/ZMhpWGFL5/
TikTok · salodatrading
55 likes, 2 comments. “ከሳሎዳ ትሬዲንግ ➡️ የአልጋ አሞዛተር 🔷የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ🔷 ☎️+251914855557 ☎️ . . .”

8k 0 19 10 201

❤️ተማሪዋ❤️


❤️….ክፍል 38 ….❤️
.
በመሀላችሁ ያለው ፍቅር ነዋ አሁንም እንደሞቀ ነው?"
"ጭራሽ ብሶበት እየተንቀለቀለ ነው"ስለው አስቀያሚ ፈገግታ ከንፈሩን ወደ ጎን ለጥጦ ፈገግ ይልና
" ለማንኛውም በረድ ቀዝቀዝ ማለቱ ጥሩ ነው የተንቀለቀለን ነገር በቀላሉ ማጥፋት ከባድ ነው"ይላል።  ዝም ብለውም ሲደጋገም

"ሁሌም እንዲህ ትላለህ ኪያ ቆይ ምን ልትለኝ እየሞከርክ ነው?••••

በክፋት አትየው ኤፊ ጋደኛዬ ሁሉም የመጀመሪያ ፍቅር አይሳካም በቃ እንከን አያጣውም አብዛኛው ሰው መጀመሪያ የፈቀራትን ወይ የፈቀረችውን አያገባም መጀመሪያ ከፈቀሩት ጋር የተጋቡ በጣም ጥቂቶች እንደሆኑ ደሞ እኔ ሳልሆን ያለው ሀቅ ነው የሚያረጋግጠው ። ቢሳካልህ እና ከቃልኪዳን ጋር ብትዘልቁ እኔም ደስ ይለኛል። ምናልባት ባይሳካ ግን በጣም እንድትጎዳ አልፈልግም ። እና በረድ አርገው የምልህ ለዛ ነው በሌላ አትየው"
ይለኛል።
"እባክህ ኪያ እኔ በቃ ምንም ልልህ አልፈልግም። ለምን እንዲህ አልክ ምን አየህ ምን ሰማህም አልልህም።  ነገር ግን ፍቅር ስትፈልግ እምታነደው ስትፈልግ ውሃ አርከፍክፈህ የምታጠፋው የምድጃ ፍም አይደለምና ይህንን ብቻ ተረድተህ እኔን ተወኝ። በቃ እኔና አንተ ማውራት ካለብን ከኔና ከቃልዬ ውጪ በሆነ ነገር ላይ ብቻ እናውራ ካልሆነ ዝም ማለቱ ይሻላል" አለዋለሁ ኪያ ግን በሆነ ሰበብ ስቦ እንደዚህ አይነት ነገር እንድናወራ ከመወትወት ታቅቦ አያውቅም።
አንዳንዴ ንድድ ብዬ መልስ አልሰጥ ስለው ዝም ይላል፣ በሌላ ወሬ መሀል ሲያነሰብኝ እንዳልሰማሁ ሆኜ አልፈዋለሁ አልያም በቀጥታ ወደሌላ ርእስ በመሄድ አጨናግፍበታለሁ።
በዚህ ሁኔታ እኔና ቃልዬ ፍቅራችንን እያጣጣምን ቀጠልን። ከሀረር በመጣን ሁለት ወር እንደሞላን አከባቢ ስራ ላይ እያለሁ ድሬ ዳዋ ያለወትሮዋ ሰማዩዋ ጭፍግግ ብላል፣   አየሯም ይበርዳ፣  ባልተለመደ ሰአት ቀን አስራ አንድ ሰአት አከባቢ ጃኬት ልወስድ ወደቤት እየሄድኩ ከዋናው አስፋልት ወደኛ ሰፈር መግቢያው ጫፍ ላይ ኪያ ከቶማስ ጋር ቆሞ እያወራ ከሩቁ አየሁት።

ሳልጠጋ ባጃጇን አዙሬ በሌላ መንገድ ወደ ቤት ገባሁና ጃኬት ደርቤ ወደስራዬ ወጣሁ።
ከምሽቱ አምስት ሰአት አከባቢ ወደ ቤት ስገባ  ኪያ  ገነት ሱቅ በር ላይ ቁጭ ብሎ እየጠጣ ነው።
"ገኒ ሰላም ነው ? ኪያ እንዴት ነህ?  ቀዝቀዝ ያለ ገኒዬ "  አልኳትና ሄጄ አጠገቡ ተቀመጥኩ።
በሌላ ርእስ ላይ ስንጨዋወት ቆየንና በመሀል
"ዛሬ ከቶማስ ጋር ቆመህ አየሁህ ልበል እላይ መግቢያው አከባቢ?" አልኩት።
"ምነው?" አለኝ።
"አይ ምንም ከሩቁ ስለሆነ ያየኋችሁ ለማረጋገጥ ነው"
"አዎ ቆመን ነበር ድንገት ተገናኘንና ቆመን ሰላም ተባብልን ምነው እኔና ቶማስ ካንተ ጉዳይ ውጪ ሌላ ነገር ማውራት አንችልም እንዴ?"
"ቆማችሁ ነበር ወይ አልኩህ አዎ አልክ አደል አበቃ ትርፍ ነገር ማውራት አያስፈልግም ስለኔ ምን ታወራላችሁ አንተ ነህ እንጂ እዛው ላይ የተቸነከርከው እኔ ከረሳሁት ቆየሁ እኮ ምን ያለበት ምን አይችልም አሉ " ብዬው በመነሳት ወደቤት ስሄድ።

"አይ እንደዛ መስሎህ ከሆነ ብዬ ነዋ ግን እርግጠኛ ነህ ኤፊ ረስተኸዋል? አለኝ።
መልስ ሳልሰጠው ወደቤት ገባሁ። ከቶማስ ጋር ባየሁት በሳምንቱ ስራ ላይ ሆኜ ምስ ሰአት ላይ ስልኬ ጠራ። አውጥቼ ተመለከትኩት ኪያ ነው። የጫንኳቸው ሰዎች መውረጃቸው ተቃርበው ስለነበር ዝም አልኩት ። ወድያው ደግሞ ደወለ፣ አላነሳሁትም። ሰዎቹን አድርሼ ሂሳቤን ከተቀበልኩ በኋላ እዛው እንደቆምኩ ደወልኩለት።
" ሄሎ ኤፊ"
"እ  ኪያ አማን ነው"
"አማን ነኝ የት ነህ?"
"የት ነህ ማለት? ስራ ላይ ነኛ"
"እርግጠኛ ነህ ? ተው ባክህ ስራ ላይማ አይደለህም"
"ምን ማለት ነው ስራ ላይ አይደለህም ማለት?"
"አሁን ኮኔል መለዋወጫ ገዝቼ ስመለስ ያየሁት እናንተን አይደለም እንዴ?"
"እናንተን ማለት?"
"በርግጥ እሷን ነው እንጂ በደንብ ያየኋት አብሯት ያለው ወንድ አንተ ሁን አትሁን መለየት አልቻልኩም"
"ምን እያወራህ እንደሆነ ሊገባኝ አልቻለም ኪያ ለምን በግልፅ አትናገርም?"
"አሁን ከአንድ ከአስር ደቂቃ በፊት ከቃልኪዳን ጋር ምሳ ልትበሉ ወደ ሆቴል ስትገቡ አልነበር?"
"እንደዚህ አይነት ቀልድ ያስጠላኛል ስራዬን ልስራበት እሺ"
"በእውነት እየቀለድኩ አይደለም ቃል ኪዳንን በደንብ አይቻታለሁ የተሳፈርኩበት ባጃጅ ፍጥነር ስለነበረው እልፍ ስንል አብሯት የነበረውን ወንድ በጨረፍታ ስላየሁት ነው እርግጠኛ ያልሆንኩት "
እሄ ልጅ ከኔና ከቃልዬ አናት ላይ አለመውረዱን ሳስብ  ውስጤ ሲነድ ተሰማኝ።
"የት ሆቴል ነው ስንገባ ያየኸው?" አልኩት የሆቴሉን ስም ነገረኝ። ቻው በቃ አልኩትና ወደሆቴሉ በረርኩ። እሄ ልጅ የምሩን አይቷት ይሆን እንዴ ? በፍፁም ሊያያት አይችልም ። በዛው በቶማስ በኩል የማጣራት ስራውን እንደቀጠለበት እርግጠኛ ሆንኩ።
ሆቴሉ አብዛኛውን ደንበኛቹን የሚያስተናግደው እቤት ውስጥ ሳይሆን ሰፋ ባለው ነፋሻማ ግቢው ውስጥ ነው። ከውጪ ወደ ግቢው በደንብ ስለሚታይ ወደ ውስጥ መግባት አያስፈልገኝም።
ባጃጄን ጠጋ አድርጌ አቆምኩና ሳልወርድ እዛው ባጃጄ ውስጥ ሆኜ ወደ ውስጥ አማተርኩ። ከሆቴሉ በር በስተቀኝ በኩል ካሉት ተስተናጋጆች መሀል ቃልዬ የለችም።
ትንሽ ዝቅ ብዬ አየት ሳደርግ ከሆቴሉ መግቢያ በር በስተግራ ባለች አንዲት ዛፍ ስር ባለ ወንበር ላይ ቃልዬን አየሁዋት።እየበሉ ነው። አጠገቧ ያለው ዛኪ ነው። ጠቅልሎ ሲያጎርሳት አብሪያት አፌን ከፈትኩ።

ምን ሆኖ ነው ለሴት ልጅ ይህንን የሚያህል ጉርሻ ፣  የሚሰፋ ይስፋው እና አፏን ሊያሰፋው ነው እንዴ?••••
እያልኩ ወጥተው ወዴት እንደሚያመሩ ብቻ ለመመልከት ራቅ ብዬ አደፈጥኩ።

ቃልዬ ከዛኪ ጋር ምሳ መብላቷ ሳይሆን  የኪያ ቃልዬን መከታተል አንጀቴን አሳረረው። ደሞ ሳልፍ አየኋችሁ ሲል አያፍርም እንዴ ገገማ!" እያልኩ እነቃልዬ ከሆቴሉ ወጥተው ወደግቢ ስሄዱ ከጀርባ ሆኜ ሸኘኋቸውና ለአንዴና ለመጨረሻ ግዜ ከኔና ከቃልዬ መሀል እንዲወጣ ላስጠነቅቀው ኪያ ወደሚሰራበት ገራዥ በደም ፍላት እየተንተከተኩ ባጃጄንም እያንተከተኩ  ሄድኩ።
ገራዥ አብረውት የሚሰሩ ጓደኛቹ ኪያ የለም እቃ ሊገዛ ወጥቷል ቢሉኝም አልተዋጠልኝም። ደወልኩለት አያነሳም ። እዛው ገራዥ ውስጥ ሆኖ የለም እንዳስባለ እርግጠኛ ነበርኩ።
ወደስራዬ ብመለስም ቀልቤን ሰብስቤ መስራት አልቻልኩም። እርብሽብሽ አልኩ። ለቃልዬ ደወልኩላት፣ እንደሁልግዜው በፍቅር አወራችኝ። ከዛኪ ጋር ምሳ ስትበይ አየሁሽ አላየሁሽ ልላት ባልፈልግም እኔ ባልጠይቃትም ብትነግረኝ ግን ደስ ይለኝ ነበር። ባለመናገሯ ቅር አለኝ።
ኤፉዬ ዛሬኮ ከአክስቴ ልጅ ጋር ምሳ ልበላ ወጣ ብዬ ነበር ብላ ብትነግረኝ ሲሆን ሲሆን ዛሬ ከዛኪ ጋር ወጣ ብለን ምሳ ልንበላ ነው ብላ ብትነግረኝ ምናለበት? ቆይ ምናለበት? ምንም በቃ ምንም የለበትም። ምሳ ከሱ ጋር መብላቷ እኔን አያስከፋኝ።
እሷ ያን ያህል ግልፅ ብትሆን ግን ኪያን ከመሳሰሉ ፀረ ፍቅር ሰላዬች አትጋለጥም ነበር። እኔንም ከመረበሽ ታድነኛለች። ግን እሷ ምን ታድርግ እራሴው አይደለሁ እንዴ ለኩያ የቀባጠርኩት?። ኡፍፍፍፍ ።
.
.
.

https://vm.tiktok.com/ZMhgxmFMK/
TikTok · salodatrading
76 likes, 2 comments. “#cornerclamp #habesha #ethiopian_tik_tok🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹 #ethiopiafurniture #salodatrading #የፈርኒቸር #የፈርኒቸር_ጨረታ #የፈርኒቸርገበያማእከል #liqfurniture #ertirantiktoka🇪🇷 #eastafricantiktoks #viralvideo #ethiopian_tik_tok🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹ሀገሬ #legsofa #passyourwavytalk ”

8.5k 0 21 2 160

♥️ ተማሪዋ ♥️ ...
.
.
🌹...ክፍል 37...🌹
.
.

አይ ኤፍዬ የሆነ ሌላ አገር የምሄድና የምንራራቅ አስመሰልከው እኮ ሁለታችንም የተለያየ ቦታ እንሁን እንጂ ከድሬ አልወጣን ዛሬ ብንለያይ መገናኘት በፈለግን ሰአት በደቂቃዎች ውስጥ መገናኘት እንችል የለ እንዴ የሆነ አየር መንገድ አድርሰኸኝ የምትመለስና ወደ ሌላ ቦታ የምበር መሰለህ እንዴ?"
"ልክ ነሽ መገናኘቱንማ ማን ይከለክለናል" አልኳትና አሁንም ዝም አልኩ። ንግግሯ በድጋሚ አቃጨለብኝ።
  ለካ እሱም አለ። ያንን ስሜትማ መቋቋምም አልችል። አያምጣው ነው እንጂ አያድርስ አለች ዘፋኟ።
እስከግቢ ሸኝቻት ስመለስ ወደዛ ቤት መግባት ቢያስጠላኝም ግድ ነው እና ገባሁ። ፍራሼ ላይ ጋደም እንዳልኩ ምን ግዜ እንቅልፍ እንደጣለኝ አላውቅም ብንን ስል መሽቷል ።
ተነስቼ ከቃልዬ ጋር በስልክ አወራሁና ወጣ ብዬ ገኒ ሱቅ ሄጄ በሩ ላይ ቁጭ እንዳልኩ  ገኒ ሳላዛት ቀዝቀዝ ያለ ቢራ ይዛ መጥታ ከፍታ ሰጠችኝና እዛው አጠገቤ ቁጭ አለች።

እንዴት ነበር የሄድክበት ፕሮግራም ኤፍዬ መች መጣህ ?"
"አሪፍ ነበር ገንዬ በጥዋት ነው የመጣሁት ገብቼ ተኛሁ"
"ኪያ ክከትናንት ወዲያ መጥተህ መሄድህን ሲያውቅ ቆሌው ነው የተገፈፈው ••••" ብላ ልትቀጥል ስትል
"እንኳን ቆሌው ቆዳውም ይገፈፍ አይመለከተኝም በናትሽ ገንዬ በዚህ ርእስ ላይ የማውራት ፍላጎቱ የለኝም ሌላ ነገር እናውራ ከይቅርታ ጋር" አልኳት።
"ውይ እንደዚህማ አታምርር ኤፍዬ ደሞ ቀሽት ያዱገነት ችክ መያዝህን ነግሮኛል"  እያለችኝ  ሌላ ሰው ለማስተናገድ ተነስታ ሄደች ። መልስ አልሰጠኋትም።
ትንሽ ቆይቶ ኪያ እራሱ መጣ ሱቁ በር አከባቢ እስኪደርስ መኖሬን ስላላስተዋለ እንዳየኝ እንደመደንገጥ አለና
"አማን ነው ኤፏ የት ሄደህ ነው እህትህ ትናንት ካንድም ሁለቴ መጥታ አጣችህ ስልክህን ዘግተህ የት ጠፍተህ ነው?"
"የትም" አልኩት። ዝም አለ ።
ለህቴ ሳልነግራት መሄዴ ልክ እንዳልነበር እያሰብኩ አሁን ብሄድ ባለቤቷ እቤት ስለሚሆን እሱ ደሞ ለኔ ካለው ጥሩ አመለካካት የተነሳ እንድትናገረኝ ስለማይፈልግ እሱ ፊት ብዙ አትበሳጫጭብኝም አሁኑኑ ሄጄ ብገላገል ይሻላል አልኩና ተነስቼ ወደ እህቴ ቤት ሄድኩ።
ስገባ ባሌቤቷ እቤት የለም።
"ቁጭ በል"  አለችኝ ። ቁጭ አልኩ። የታላቅነቷን ትንሽ ቆጣ ቆጣ አለችና ወድያው ቀዝቀዝ ብላ እራት እንድበላ እያቀረበችልኝ
"ኤፍዬ እቁቡን ችላ አትበለው እንጂ፣ ቆይ ባጃጅ ሹፌር ሆነህ   መቅረት የምትፈልገው? እስካሁን ስምንት ወር ጥለኻል የቀረህ አራት ወር ብቻ ነው። እኔ እቁብ ጥለህ ባጃጁ የተገዛበትን  ሂሳብ ለኔ ትመልሳለህ ያልኩህ ሆን ብዬ ነው። ላንተው መሻሻል ነው ጭንቀቴ እንደምንም ብለህ ጨርስ። ከዛ ሀረር ያለውን የአያቶቻችንን ቤት •••"
ስትል አቋረጥኳት።
"እታለም እንሸጠዋለን ልትይኝ ባላሆነ ? ተይ መሸጥ በሚባል ነገር እኔ አልስማማም እንዲሁ እየተከራየ ቢቆይ ይሻላል ። መሻሻል ካለብኝም በራሴ ደክሜ በማመጣው እንጂ በመሸጥ መሆን የለበትም"
"እስቲ መጀመሪያ እኔን አስጨርሰኝ እኔም ሙሉ በሙሉ ቤቱን እንሽጠው አላልኩም ። ግቢው  ሰፊ ነው አምስት መቶ ካሬ ሜትር ስለሆነ ሁለት መቶ ሀምሳውን ከፍለን ባዶ መሬቱን ብቻ በመሸጥ ከእቁቡ ጋር ቀላቅለን የሚበቃ ከሆነ ሚኒባስ ገዝተህ ሀረር ድሬ መስመር እንድትሰራ ነው ያሰብኩት። ካልበቃ እኔ እጨምርልሀለሁ የሚተርፍህ ከሆነ ደግሞ ጎሮ አነስ ያለች ቦታ ገዝተህ ቀስ በቀስ ጎጆህን ትቀልሳለህ" አለችኝ። በእህቴ ሀሳብ በጣም ደስ አለኝ። ከሀረር መልስ የተጫነኝ ድብርት በኖ ጠፋ።
"አመስግናለሁ እህቴ በጣም ምርጥ ሀሳብ ነው" አልኳት።
"በል በርታ በልና የቀረችውን እቁብ ጥለህ ጨርስ ። መንጃ ፍቃድም ማውጣት አለብህ ነገ ዛሬ ሳትል ጀምር!"
"የምን መንጃ ፍቃድ መንጃ ፍቃድማ ገና አስራ አንደኛ ክፍል እያለሁ እኮ ነው የወሰድኩት እቴቴ"
"ነው እንዴ ? እና እሱ የባጃጅ አይደል እንዴ?"
"ኧረ የምን የባጃጅ የባጃጁንማ አስረኛ ክፍል ሆኜ ነው የወሰድኩት ከዛ ሶስተኛ ወሰድኩ ረሳሽው እንዴ እታለም?"
"ለካ ገና ሳትፈተን ነው የወደቅከው ?"
"ማለት?"
"ሹፌር የመሆን ህልምህን ስታሳድድ ነዋ ትምርቱን ችላ ያልከው ቤት በኩል ታልፋለህ ፣ የማይፈልጉት ፈተና አይታለፍ"

"እህእ በይው " ብያት  ከእህቴ ቤት በጣም ደስ ብሎኝ ነው የወጣሁት። ከአራት ወር በኋላ የሚኒባስ ባለቤት እንደምሆን ሳስበው ፊቴ ድቅን ያለችው ቃልዬ ነች።
አብሮ የመኖር ህልሜ በአጭር ግዜ ውስጥ እንደሚሳካ ሳስበው መንገድ ለመንገድ እንደህፃን ልጅ እየቦረቅኩ ነበር ወደ ገኒ ሱቅ የሄድኩት።
የጀመርኩትን ቢራ እንደቅድሙ በድባቴ ሳይሆን በአዲስ ተስፋ እና ደስታ እያጣጣምኩ  ስጎነጨው ቆየሁና ገብቼ ተኛሁ።
በንጋታው በአዲስ የመነቃቃት ስሜት ስራዬን ጀመርኩ። ቀንም ማታም በርትቼ መስራቴን ቀጠልኩ።
ሀረር ሄደን ከመጣን ግዜ ጀምሮ በኔና በቃልዬ መሀል ያለው ፍቅር ይበልጥ ተጋግሎ ሳንተያይ ማደር ሁለት ሶስቴ ሳንደዋወል መዋል የማይሞከር የማይታሰብ ሆኗል።
ሀረር ከመሄዳችን በፊት በነበሩት ስድስት ወራት ፍቅር እኔን እያንገላታ ቃልዬን የሚያሞላቅቅበትን ምክንያት እንዲነግረኝ እንዳልጨቀጨኩት ለምን ፍትሀዊ አትሆንም  እያልኩ እንደወቀስኩ እንደረገምኩት ሁሉ ቃልዬንም ተቆጣጥሮ ፍቅራችንን በማመጣጠን እኩል የምንነፋፈቅ፣ እኩል የምንንሰፈሰፍ፣ እኩል አንዳችን ለአንዳችን የምንጨነቅ አድርጎ ሲሰራንም ከማመስገን አልቦዘንኩም።
ቃልዬ አብራኝ ሆና የሚደወልም ከኔ አጠገብ ሄዳ የምታናግረውም ፣ ብዙ ግዜ ሀሙስ እና ቅዳሜ አይመቸኝም የምትለው ነገርም ከሀረር መልስ ቀርቷል።
እኔ እንደማፍቅራት ታፈቅረኝ ይሆን እኔ እንደምታመንላት ትታመንልኝ ይሆን በሚባል የስጋት ማእበል የማይናጥ ፣ ከዛኪ ጋር ሌላ ግኑኝነት ይኖራቸው ይሆን? ቢሚል የጥርጣሬ ውሽንፍር  የማይናወጥ ፍቅራችንን  ተዝቆም ተቀድቶም በማያልቀው የፍቅር ውቅያኖስ ላይ በፍቅር እየቀዘፍን መንሳፈፉን የየእለት ውሎ አዳራችን ሆነ ።
በሳምንት ውስጥ በትንሹ ሁለት ቀን አብረን እናድራለን።   ጌትነት የሚባል እናቱ በሂወት የለሉ አባቱ በስራ ምክንያት ብዙ ግዜ ድሬ ዳዋ የማይኖሩ ለቤተሰቦቹ ብቸኛ የሆነ ጓደኛዬ ከድሮም ጀምሮ እሱ ካባቱ ጋር ከድሬ ውጪ ከሆነ እቤታቸው እያደረን የምንጠብቅላቸው እኔና ጓደኞቼ ነን።
ደውሎ ኤፊ ፋዘር ጋር ልሄድ ነው ከጓደኛህ ጋር እቤት እደሩልኛ ይለኛል  (ጓደኛ የሚለው ኪያን መሆኑ ነው )
ከሀረር መልስ እንደዛ ብሎ ሲደውልልኝ የምን ጓደኛ ፍቅረኛህን አትልም እንዴ እያልኩ በሆዴ ቃልዬን ይዣት እሄዳለሁ።እዛ  ዙርያውን በግንብ በታጠረ ሰፊ ግቢ ውስጥ ባለ ቪላ ቤት እኔና ቃልዬ ብቻችንን ስናድር ስሜቱ ልዩ ነው። በተለይ ቃልዬ እንደድሬ ሴቶች ሺቲዋን ለብሳ እራት ለመስራት ቡና ለማፍላት ጉድ ጉድ ስትል ሳያት አባ ወራ የሆንኩ ይመስለኛል።
እንዲህ በራሳችን ቤት የምንኖርበት ግዜ መች ይሆን እያልኩ በምኞትም እቀልጣለሁ መሆኑ እንደማይቀር እስብና በነገ ተስፋ ዛሬዬን በደስታ እሞላታለሁ። በቃልዬ ደስተኛ ነኝ።
ሁሌም የሚረብሸኝ ኪያ አለፍ አለፍ እያለ በሚሰነዝረው ቀፋፊ ሀሳብ እና በሚጠይቀኝ ግራ የገባው ጥያቄ ብቻ ነው።
ገብቼ ገና አረፍ ስል ይጠብቅና "ኤፊ ቃልዬ እንዴት ነች?"
"ደና ነች "
"እንዴት ነው ታድያ?"
"ምኑ"

8.1k 0 22 5 178

♥️ ተማሪዋ ♥️ ...

🌹...ክፍል 36...🌹
.
.

.
.
ጆሮዬን ማመን ተሳነኝ። ከባልቦላው ያጠፋችኝ ያህል ውስጤ ድርግምግም አለ። ከነበርኩበት ጣፋጭ  የፍቅር ትኩሳት ወርጄ በረዶ ሆንኩ።
ተወርውሬ ደብዘዝ ያለውን መብራት ቦግ ሳደርገው ከስሬ የተንጋለለችው ቃል  አይኗን ከሀይለኛው ብርሀን ለመከላከል በክንዷ እንደመጋረድ እያለች "ምነው ኤፍዬ?" ስትለኝ በዝምታ አፈጠጥኩባት።
"ምነው ኤፊ ለምን አበራኸው?" አለችኝ ደግማ ክንዷን ገለጥ አድርጋ እየተመለከተችኝ።

"አአአአ አሁን ምንድን ነው ያልሽው ቃል?" አልኳት
"ለምን አበራኸው ነዋ ያልኩህ አይሰማህም እንዴ ኤፍዬ"
"አይ ከዛ በፊት"
"ከዛ በፊት ማለት?"
"ከማብራቴ በፊት ምንድን ነው ያልሽው

ኪኪኪ እንዴ እሱንም እማ አልደግመውም "
"ለምን ? ለምንድን ነው እማትደግሚው?"
"እህ በፍቅር እና በስሜት ውስጥ ሆነህ ያወራኸውን ነገር እኮ ሲደገም ይለዛል ለዛው ይጠፋል ደስ አይልም"
"ግድ የለም እኔ መስማት ስለምፈልግ ድገሚው"
"መስማት ስለፈለክ ነው ወይስ ደግመህ መስማት ስለፈለክ"
"ደግሜ መስማት ስለፈለኩ ?" አልኳት እሷ በፈገግታ ውስጥ ሆና እያወራችኝ ስለነበር ደግማልኝ እስክሰማው መደንገጤም መለወጤም እንዳይታወቅብኝ እየሞከርኩ።
"በናትህ መብራቱን እንደቅድሙ አድርገው ኤፍዬ?"
"ንገሪኛ መጀመሪያ"
"እንዴ ካልደገምኩልህ አታጠፋውም እኔ አጠፋዋለሁዋ ምነው ማሽከርከር የሚያቅተኝ መሰለህ እንዴ ብላ ቀና አለችና ማብሪያ ማጥፉያውን ወደ ግራ ዘውራ አደበዘዘችው።
" እና አትነግሪኝም "
"አልነግርህም "
"ቃልዬ እባክሽ "
"እንዴ••የምርህን ነው አንጣ  ወረቀትና እስክርቢቶ ያልኩትን ልፃፍልህና ሌላ ግዜ አልተሸነፍኩም ብዬ ብክድ እንኳን   ማስረጃ ይሆንሃል ከፈለክም  ደጋግመህ  ታነበዋለህ ኪኪኪኪ"
ቃልዬ ምን እያለች እንደሆነ ሊገባኝ አልቻለም።በዚህ ሰአት ወረቀትና እስክርቢቶ ኬት ያመጣል ብላ ነው አደል የምትጫወትብኝ አልኩና ስልኬን አንስቼ  ከስልኬ ላይ የማስታወሻ መፃፊያውን መተግበሪያ ከፍቼ
"ይሄው መጨረሻ ላይ ያልሽኝን እዚህ ላይ ፃፉልኝ ወረቀት ምናምን  ኬት ይመጣል በዚህ ሰአት "
"አይ ኤፍዬ!" እያለች ሞባይሉ ላይ ፃፈችና ሰጠችኝ።

ፅሁፉን ሳነበው ሽምቅቅ ብዬ አንድ ፍሬ አከልኩ ። ቃልዬ ሞባይሌ ላይ ፅፋ የሰጠችኝ •••" ዛልኩልህ የኔ ፍቅር ይላል።

ጆሮዬ እና አይኔ መስማማት አቃታቸው። ማንን እንደምረግም ግራ ገባኝ ።  ጆሮዬን ልርገም ሀሳቤን? ። ውስጤ ያ ሀሳብ ያ ጥርጣሬ ባይኖር ጆርዮ ኬት አምጥቶ "ዛልኩልህ የኔ ፍቅር " የሚለውን ንግግር ዛኪዬ የኔ ፍቅር ብሎ ይሰማል።
ጥርጣሬ የፍቅር ሰንኮፍ የደስታ ጭንጋፍ ነው ። እኔ የምፈልገው ከቃልዬ ጋር በደስታ እና በፍቅር መቀጠል ነው። ስለዛ ልጅ ማሰብ ካላቆምኩ ደግሞ ያንን ማጣጣም አልችልም።  ለአንደና ለመጨረሻ ግዜ ከአይምሮዬ ላወጣው ምንም ሳይፈጠር ምንም የተጨበጠ ነገር ሳይኖር ዝም ብዬ ስለሱ ላላስብ ላልጨነቅ ቃልዬንም ላላስጨንቅ ለራሴ ቃል ገባሁ።
"አንተ ጨቅጫቃ ሴቭ አድርገውና ሁሌ አንበበው እሺ መሸነፏን ትክዳለች ብለህ ነው አደል ካልደገምሽው ብለህ እርርይ ያልከው ኪኪኪ ሆሆ በቃ አሸንፈኻል ተሳክቶልሀል እሺ ኤፍዬ እሁንስ ደስ አለህ? " አለችኝ። አቅፋኝ እየተኛች። በኔና በቃልዬ መካከል ያለውን የሀሳብ ልዩነት ሳስበው ዘገነነኝ። እኔ ሌላ ነገር ልቀሰቅስ ደስታችንን ላደፈርስ ያልተናገረችውን ተናገረች ብዬ ላስደግማት ስጋጋጥ እሷ ግን እዚህ ሀረር ከመጣን ጀምሮ ስናወራ ስንቃለድ ከነበርንበት ርዕስ ሳትወጣ እዛው የፍቅር ወግ ላይ ነበረች። እንኳንም ለነገር ቸኩዬ እንዲህ ስትይ ሰማሁ አላልኳት እያልኩ  ከጎኗ ጋደም አልኩ።
ምን ብዬ እንደማመልጥ ግራ ገብቶኝ በዝምታ ቆየሁና መንተዕፍረቴን " አይ አመመኝ በቃህ ያልሽኝ መስሎኝ ነበር ለዛ ነው እሺ ቃልዬ" ስላት።
"እስካሁን እዛው ላይ ነህ እንዴ በቃ እርሳው  እንተኛ  እቀፈኝ"አለችኝ አቅፊያት ተኛሁ። አይነጋ የለ ነጋ ። አይደርስ የለ ወደ ድሬ የምንሄድበት ሰአት ደርሶ ተነሳን።
ተሳፍረን ትንሽ እንደሄድን
"ኡፍፍፍ ምናለበት ባትሄጂ በቃ አሁን ሄደንም አብረን አንድ ቤት ውስጥ የምንገባ ቢሆን ቃልዬ" አልኩና የልቤን መሻት ተነፈስኩላት። ጣቶቼን በጣቶቿ መሀል እያፍተለተለች
"እኔም እንደዛ መሆን ቢችል ደስ ይለኝ ነበር ፣ አሁን ባይሆንም ሁሉም ነገር በግዜው ይሆናል፣ ሂወት እኛ በፈለግነው ልክ ቀላል አትሆንም ያንን አውቀን  መቅደም ያለበትን ማስቀደም ግድ ነው አደል ኤፍዬ?"
"አዎ ልክ ነሽ " አልኳት ። ቃልዬን ማስጨነቅም መጨቅጨቅም አልፈልግም። የሀረርን ደስ የሚል ቆይታ ልበርዘው አልፈልግምና እሷን ልክ ነሽ ብዬ ፋይሉን ዘጋሁና በውስጤ ከፍቼው ከራሴ ጋር መጨቃጨቄን ቀጠልኩ
መቅደም ያለበትን ማስቀደም ስትል ምን ልትለኝ ፈልጋ ይሆን? ለቃልዬ ከፍቅር በፊት መቅደም ያለበት ምን ይሆን?
ቃልዬ ከፍቅር እና በፍቅር ተሳስሮ አብሮ ከመኖር በፊት እንዲሟላ  የምትፈልገው  የህይወት ጣጣ ምን ይሆን?
እሱማ ስንት ጣጣ አለ። ይህቺ አለም ጣጣዋ መች ያልቅና ?። እኔ ከቃልዬ ጋር ብኖር የሚርበኝ ሁላ አይመስለኝም።
ቢሆንም መምስል እና መሆን እንደሚለያይ ማመን ግድ ነው። የማይርበኝ ቢመስለኝም ሊርበኝ ይችላል። ነገሩ ከሆድ ውጪ ስንት ጣጣ አለ ። ለሆድማ የባጃጇ ገቢ መች ያንሰናል። ግን ብዙ ነገር አለ በትንሹ ቃልዬም ትምህርቷን መጨረስ እኔም አሁን ካለሁበት የተሻለ ደረጃ ላይ መድረስ ግድ ይላል።
አይ በኔ በኩል እንኳን ችግር የለም ከቃልዬ ጋር ሆኜ ለመስራት ለመለወጥ ለማደግ ምን ይከለክለኛል ? ምንም ። ቢሆንም የቃልዬን እቅድ እና ፍላጎትም ማክበር አለብኝ።

ማን ያውቃል ልክ ስድስት ወር ሙሉ ተገናኝተን እና ተጨዋውተን ስንለያይ በዚህ ሁኔታ እስከመቼ ነው የምንቀጥለው ለምንድን ነው ? የግኑኝነታችን  ሁኔቴ ወደ ሌላ ደረጃ ማደግ የለበትም እንዴ?  ብዬ ሳልጫናት፣ ሳልጨቀጭቃት፣ እሷ በፈለገችና በፈቀደች ሰአት ይህንን ጣፋጭ የሀረር ቃይታችንን  እንዳመቻቸችው ሁሉ  የኔን የአሁን ፍላጎት ተቀብላ አብረን መኖር እንድንጀምር መወሷንን ታበስረኝ ይሆናል።
እያልኩ በሀሰብ ማእበል ስወዘወዝ "ኤፊዬ" የሚለው የቃልዬ ጥሪ አባነነኝ።
"ወዬ ቃል"
"ምን እያሰብክ ነው ረጅም መንገድ ዝም ያለከው? ዘጋኸኝ እኮ"
"ምንም ቃልዬ ብቻ እንደትናንት ማታው አይነት ስሜት እየተሰማኝ ነው"ትናንት ማታ ብዙ ስሜቶች አስተናግደናል የተኛው ነው አሁን የተሰማህ?"
"ሚኒባስ ውስጥ ከገባን ቡሀላ  ድሬ እንደደረስን አንቺም ወደግቢ እኔም ወደቤት እንደምንሄድና እንደምንለያይ ሳስበው የተሰማኝ ውረድ ይዛሀት ውረድ የሚል ስሜት"
"ካካካካ በቃ አሁንም እንውረድ "
'የት እዚህ ሀሮማያ ደርሰናል እኮ"
"እህህህህ አንተ የምሬን መሰለህ እንዴ ?"
"የምርሽን ቢሆን ደስ ይለኛል በቃ ሀረር እንመለስና አያቴ ቤት የተከራዩትን ሰዎች አስወጥተን እንኑር""ሂድ ወደዛ"
"የትም አልሄድም ቃልዬ ካንቺ የሚለየኝ "
"እንዳጨርሰው ኤፊ እንደዚህ አይነት ንግግር ይረብሸኛል"
"እሺ አልጨርሰውም" ብያት ዝም አልኩ ከንቺ የሚለየኝ ሞት ብቻ ነው ልላት ነበር  እውነትም የሚረብሽ ነገር አለው አልኩ ለራሴ ።
.
.
ከ 150 ላይክ ቡኋላ ክፍል 37 ይለቀቃል🌹
https://vm.tiktok.com/ZMhV8Ma3n/           

9.8k 0 24 16 224

♥️ ተማሪዋ ♥️ ...
           .
          .
🌹...ክፍል 35...🌹
.
.

.
.
ኤፍዬ"
"ወዬ ቃል"
"ልቀቀኝ እኔ መጨፈር እፈልጋለሁ አልኩህ እኮ አሰማም ? ቆይ እኛ ዶሮ ነን እንዴ በዚህ ሰአት ገብተን የምንተኛው?
እንብየው እንብየው እኔ መግባት አልፈልግም ልቀቀኝ "
እያለች እቅፍ አድርጌ የመሸከም ያህል ይዣት ስወጣ•••
"ቆይ እንቅልፍ ምን ያደርጋል? እንቅልፋም ነገር ነህ እሺ ኤፍዬ እንቅልፍም፣  ኪኪኪኪ ቆይ ቆይ ፣ አቅም ግንባታ ፣ያልጋ ላይ ጫወታ፣  እግዞዬታ ኡኡታ እያልክ ስትፎክር የዋልከው ገብቶ ለመተኛት ነው እንዴ ? እስቲ ወንድ ዛሬ ገብተህ ትተኛና እንተያያለና ኪኪኪ ቆይ ቆይ ቆይ ኤፊዬ. "ድብድቡ ሳይጀመር አንድ ቢራ"  ያለው ማን ነበር. ኤፊዬ ? እኛም ድብድቡ ሳይጀመር የምንጠጣው አንዳንድ ቢራ ይዘን መግባት አለብንኮ ባዶ እጃችንን ልንገባ ነው?  ቆይ እሺ ልቀቀኝና ሁለት ቢራ ይዘን እንምጣ"
"ቃልዬ በጣም መሽቷል እኮ ስድስት ሰአት አልፏል"
"ይለፋ ገና አሁን አይደል እንዴ የወጣነው ፣  ስማ ስማ ኤፍዬ ቆይ የሰከርኩ መስሎህ ነው አደል ? እሄው እይ ባንድ እግሬ ስቆም እሺ ብሰክር ባንድ እግሬ እቆማለሁ ልቀቀኝ ቆሜ ላሳይህ "
ትልና አንድ እግሯን ብድግ አድርጋ ሳጨርስ ተንገዳግዳ እኔው ደረት ላይ ዘፍ ትላለች።
"ካካካካካ " በቃ ሳቋ ማቆሚያ የለውም።
"እሺ እሺ በናትህ ኤፍዬ ስሞትልህ በዚች ዘፈን ብቻ እንደንስና እንገባለን ሰማው ዘፈኑን እዚህ ድረስ ይሰማል እኮ ይሰማሀል ኤፍዬ የፀሀዬ ዮሀንስ ዘፈን••
ጥንድ ጥንድ ሆነው ሲሄዱ ባይ 
ሳጣሽ የኔን ሲሳይ ፣  ቀናሁ በሰዎች ላይ
ዛሬም ሳላይሽ ላድር ነው ወይ እባክሽ ነይ
ዝርያዬን ባስስ ባስስ አንቺ እንደሁ የለሽም
ባንጋጥጥ ወደሰማይ ዘፈኑን   ፍቅረኛው አጠገቡ የለለች ሰው ይመሰጥበት እኛ እንግባ  እኛ እኮ ጥንድ ነን ቃልዬ "
"ምን አልክ ኤፊ? ጥንድ ነን ነው ያልከው? መስሎህ ነው ባክህ እኛማ ጥንድ ብቻ አይደለንም። ከጥንድም በላይ ነን። ቆይ ከጥንድ በላይ የሆኑ ፍቅረኛሞች ግን ምንድን ነው የሚባሉት ?
ታውቃለህ እንዴ? ባክህ አታውቅም እኔ ነኝ እንጂ ማወቅ የነበረብኝ አንተ ምን በወጣህ ፣ ግን እስከዛሬ ፍቅረኛሞች ከጥንድ በላይ ይሆናሉ ብለህ አስበህ  ታውቃለህ ኤፊዬ?
" አላውቅም"
"እኔም አስቤ አላውቅም ነበር ግን ሆነ አይገርምን ኤፊ"
"አይገርምም" አልኳት ምን እያለች እንደሆነ ስላልገባኝ ።
"ኪኪኪኪኪ አይገርምም ይላል እንዴ ፣ ባክህ አንተ ስለማታውቅ ነው ያልገረመህ "
ስትለኝ ምን እያወራችልኝ ነው? ምን ማለቷ ነው? ከጥንድ በላይ የሆኑ ፍቅረኛሞች ማለት ስንት ነው? ስስት ነው አራት? ወይስ ከዛ በላይ። አራት ከሆኑ ያው ሴትና ወንድ ሴትና ወንድ ሁለት ጥንዶች ማለት ነው ። ሶስት ከሆኑስ እንዴት ነው የሚሆነው?
ሁለት ሴት እና አንድ ወንድ ነው ? አይ እንደዛማ አይሆንም እሺ ሁለት ወንድ እና አንድ ሴት ቢሆንስ ብዬ ሳስብ ወረረኝ።
ቃልዬ ስለምን እያወራች ነዉ በሷ በኩል ሌላ ወንድ ይኖር ይሆን ብዬ ከማሰብ በላይ ምን የሚወር ነገር አለ?
እና ቃልዬ ምን እያለችኝ ይሆን  ይሄ ነገር "ሆድ ያባውን ብቅል ያወጣዋል " ይሉት አይነት ንግግር ነው  እንዴ?
"ስማ ኤፊዬ "
"እ ምንድን ነው?"
"ኤፊዬ  አንተኮ ታማኝ፣ ንፁህ፣ደግ፣ ግልፅ ፣ ተጫዋች በቃ የሆንክ ፍቅር የሆንክ ልጅ ነህ ፣ የኔ የዋህ፣ አፈቅርሀለሁ እሺ ?"
አለችኝ። ቃልዬ ያን ያህል ብዙም አልጠጣችምና ከሞቅታ ውጪ የለየለት ስካር ውስጥ አልገባችም።
በምትናገረው ነገር ግን የተዘበራረቀ ስሜት ውስጥ እየከተተች እኔኑ  አሰከረኝ።

እንደምንም መንገድ ለመንገድ እየተጓተትን ክፍላችን ገባን።
አልጋው ላይ አረፍ እንዳለች እኔ ወደ መታጠቢያ ቤት ገባሁና ልብሴን ውልቅልቅ አድርጌ ይሄን የሀረር ቀዝቅልዛ ውሃ አናቴ ላይ ለቀቅኩት።
ኳኳኳ " ክፈት ኤፊ"  ከፈትከላት።
"ለምንድን ነው ብቻህን የምትታጠበው እኔም መታጠብ እፈልጋለሁ "
ብላ ከነልብሷ ልትነከር ስትል ያዝ አደረኩና ከላይ የለበሰችውን አውልቄ ፀጉሯ እንዳይበላሽ ቦርሳዋ ውስጥ የያዘችውን የተለየ ስም ይኑረው አይኑረው ባላውቅም ብቻ  ሴቶች ድንገት መንገድ ላይ ሆነው ዝናብ ሲመጣ እና ሲታጠቡ የሚያጠልቁትን ከፍያ መሳይ ላስቲክ ነገር ጭንቅላቷ ላይ አጠለኩላት  ።
"አመሰግናለሁ እሺ የኔ አሳቢ !" ብላ ብላ ሳመችኝና አብረን መታጠብ ጀመርን።
እየተሳሳቅን ተጣጥበን እንደወጣን ለቀቃት ቀዝቀዝ አለች። ጋደም ብለን ስንጨዋወት ቆየን።  ውስጤ ጥያቄ ቢፈጥርብኝም ቅድም በጥንዶች ዙርያ እንዲህ ብለሽ ነበር ምን ለማለት ፈልገሽ ነው? ብዬ በመጠየቅ ሌላ ውዝግብ ውስጥ እንድንገባና  ያንን ደስ የሚል የሀረር ቆይታችንን ላደበዝዘው ስላልፈለኩ ተውኩት።
መብራቱን ሳየው አይኔን እያጭበረበረኝ ነው የሚቀነስ ከሆነ ሀይሉን ቀንሰው ያለበለዚያ አጥፋው አለችኝ።
በጣም እንዳይጨልም በጣምም ቦግ እንዳይል አድርጌ አደበዘዝኩት። እድሜ ለቴክኖሎጂ። ትንሽ ቆይቶ በኔ እና በቃልዬ መሀል  መነካካት ተጀመረ። ቀስ ነቀስ መሳሳም ቀጥሎም ወደ ወናው ወደ ጥሎ ማለፍ ጫወታው ሰተት ብለን ገባን።
የመጀመሪያው ግብግብ በኔና  በቃልዬ መሀል ብዙ የጎላ ልዩነት ሳይኖር ተመጣጣኝ በሆነ የሀይል ሚዛን ተጠናቀቀቅ።
"ሽንቴን ልሽና መጣሁ ኤፍዬ መተኛት አይፈቀድም ብላኝ ወደ ሽንት ቤት  ስትሄድ  ሳቅ እየተናነቃት እንደሆነ አነገገሯ ያስታውቅ ነበር።
ከአንደበቷ ባይወጣም "እንደፎከርከው አልሆነልህም ምን ትሆን እንግዲ ድንቄም ጥሬ ስጋ ?" እያለች ያላገጠችብኝ ያህል ነው ተሰማኝ።
በእረፍት ሰአት የታክቲክ እና የቴክኒክ ለውጥ ማድረግ እንዳለብኝ ሳስብ ቆየሁ። ሁለተኛው ዙር ላይ አዲሱን ስልት መተግበር ጀመርኩ።
ቅልጥ ያለ የፍቅር  ጦርነት ውስጥ ከመግባታችን እና ቃልዬ እንደእንዝርት ከመሾሯ  በፊት ስልታዊ ማፈግፈግ በማድረግ እና  መላ አካሏን  በመውረር ቁልፍ ቁልፍ ቦታዎችን በመሳም፣  በዳበሳ እና በዳሰሳ  ማጥቃት ጀመርኩ ።
ወደ ወሳኙ ጦርነት ሳንገባ  ቃልዬ አተነፋፈሷ እየተቀየረ የልብ  ትርታዋ እየጨመረ መጣ።
ለደቂቃዎች በተደረገባት የጣት እና የከንፈር ወረራ  መላ አካላቷ ላይ በሚርመሰመሱት ጣቶቼና እና ካንገት በላይ  የስራ ድርሻውን በሚወጣው ከንፈሬ ገና ሳይጀመር የጋለችው  ቃልዬ በፍቅር ጫወታው ትግበራ ላይ   የጫወታውን አይነት ፣የጫወታውን ቦታ፣  የጫወታውን  ፍጥነትና ሁኔታ የመወሰኑን ስልጣን ለኔ ለማስረከብ ተገደደች።
ሁሉም ነገር በኔ  ስልጣን በኔ ቁጥጥር ስር ዋለ። እስካሁንም የጫወታው ቁልፍ  ቅድመ ጫወታ ላይ ያለው የማሟቂያ ግዜ መሆኑን አለማስተዋሌ ነው የጎዳኝ አልኩ ለራሴ ። ቃልዬ እኔ በምልክትም በቃላትም ሁኚ የምላትን መሆን ብቻ ሆነ እጣ ፋንታዋ።በዚህ መልኩ የደስታን ጥግ እያጣጣም ደቂቃዎች አለፉ።
  ወደ ማሳረጊው አከባቢ  ቃልዬ ስሜት ውስጥ ሆና የተናገረችው ነገር በሚሳኤል የተመታሁ ያህል ጆሮ ግንዴን አደባየው።
ቃልዬ ድክም በለ ድምፀት በስሱ "ዛኪዬ የኔ ፍቅር አልቻልኩም"  የሚሉ ቃላቶች ብትናገርም ወደ ጆሮዬ ሲደርሱ ግን ጩኸታቸው የመብረቅ ያህል አስደንጋጭ ነበር።
.
.
ከ 200 ላይክ ቡኋላ ክፍል 36 ይለቀቃል🌹
https://vm.tiktok.com/ZMh9xdBnV/           
TikTok · salodatrading
110 likes, 4 comments. “📌 ባለ 2 መገልበጫ ፍሬም 📌 በነጭ ቀለም ☎️ ይደውሉ ☎️ +251914855557 ☎️ . .”

9.8k 0 26 19 233

♥️ ተማሪዋ ♥️ ...
           .
           .
🌹...ክፍል 34...🌹

.
.
"አመረርክ እንዴ ትናንት እኮ እኔን ለማሳቅ ብለህ እኔን አሸናፊ አንተን ተሸናፊ አድርገህ  እንደቀለድክ እንጂ ከልብህ እንዳልሆነ ነበር ያሰብኩት፣ ኤፊዬ ሙት እኔ  ትናንት በነበረው ነገር በጣም ደስተኛ ነኝ፣  ምንም ያጎደልክብኝ  ነገር የለም ተመችቶኛል"
"ገሎ ማንሳት፣ ጠብሶ ማሸት የሚባል ነገር ታውቂያለሽ"
"ገሎ ማንሳት አላውቅም ጠብሶ ማሸት ግን ለበቆሎም ሊሆን ይችላል ለሰውም ይሆናል ያው ጠብሰክ እያሸኸኝ  አይደል እንዴ ኤፊዬ?"

"ካካካ አንቺ ነሻ ገለሽ የምታነሽው ጥሬ ስጋ ወንድ ያደርጋል እንዴ ብለሽ ከገደለሽኝ በሁዋላ አይደለም በሽንገላ በክሪክ አልነሳም።
ያለው  አማራጭ ወንድነቴን ማሳየትና ማስመከር ብቻ ነው"
"ክሪክ ምንድን ነው ኤፊ ?"
"የተሽከርካሪ ጎማ ለመቀየር ለሌላም ጉዳይ ብቻ መኪናው  ከፍ የምናደርግበት ነዋ " አልኳት በቃ ወሬህ ዞሮ ዞሮ ከትራፊክ ህግና ከተሽከርካሪ አይወጣም አይደል እንዳትለኝ  ውስጥ ውስጡን እየተሳቀቅኩ።
"እኔ እንግዲህ ወንድነትህን አይቼዋለሁ ሌላ የምታሳየኝ አዲስ ነገር አለ?"
'አዎ አለ"
"እና አሳየኛ "
"አሁን አይደለም ስንመለስ " ብዬ እጇን ይዤ በመጎተት ከአልጋው ላይ አነሳኋትና ይዣት ወጣሁ።
እየሄድን መንገድ ላይም "አይ ኤፊ" እያለችና ዝም ብላ እያየችኝ ትስቃለች።
"ለምንድን ነው  የምትስቂው ቃልዬ?"
" ኤፊዬ ግልፅነትህ በጣም ደስስስስስ እንደሚለኝ ታውቃለህ ግን?"
"አላውቅም ነበር ይሄው አሁን ነገርሽኝ። እና ግልፅነቴ ብቻ ነው ደስ የሚልሽ?"
"ሌላውን ሌላ ግዜ እነግርሀለሁ"
"በጣም የሚገርመኝ ባህሪሽ የሆነ ነገር ለማውራት ቀጠሮ የምትይዥው ነገር ነው"
"ሁሉም ነገር እኮ ባንድ ግዜ አይወራም ኤፍዬ"አለችኝ ወገቤን አቀፍ አድርጋ ወደሷ በመጎተት በዳሌዋ ገጨት እያደረገችኝ።
ተንገዳግጄ ልወድቅ ነበር ። የሴት ቀጭን የለውም አለች አያቴ። ቃልዬ በርግጥ የሰማዩ ንጉስ ክብሩ ይስፋና  ከወገቧ ቀጠን ከዳሌዋ ሰፋ አድርጎ ስላስዋባት በዛ ዳሌ ተገጭቼ ብንገዳገድ በኔ አይፈረድም።  ቃልዬ
" ና በደንብ ልግጭህና ውደቃ በቃ ነጋ ሳረግህ ተንገዳገድክኮ መውደቅ አምሮህ ነው" እያለች ድጋሚ ልገጨኝ ስትሞክር አንገቷን አቅፌ ተረፍኩ።
ለጥሬ ስጋ እስከዚህም ብትሆንም አንተ የበላኸውን ነው የምበላው ሌላ ምግብ አላዝም ብላ አብራኝ በላች።
በልተን እንደጨረስን እዛው በስሱ ማወራረጃውን እየተጎነጨን ቆየን። እንደትናንትናው ከዚህ በላይ እንዳትጠጣ  በቃህ አላለችኝም። እኔም በነፃነት በላይ በላይ እልፈው ጀመር።
ነገር ግን ቃልዬም እንደስከዛሬው ከሁለት በላይ አልጠጣም የምትለውን ረስታው ይሁን ትታው ደገም ደገም ስታደርግ ኦኦ ሁለታችንም ከሰከርን ማን ማንን ሊጠብቅ ነው ? አልኩና የኔን መጠጣት ገታ ማድረግ እንዳለብኝ ወሰንኩ።
ጭራሽ " ጠጣ እንጂ ኤፊዬ"  ስትለኝ እየጠጣሁ ነው ጠጪ እያልኩ ከንፈሬን እያረጠብኩ መመለስ ጀመርኩ።
እንዲሁም በትንሽ በትልቁ ሳቅ ሳቅ የሚላት ቃልዬ ምንም ሳናወራ ሁላ  ዝም ብላ እያየችኝ መሳቅ ጀመረች።
ይውጣላት አልኩና ከምግቤቱ ይዣት በመውጣት  ቅልጥ ወዳለ ጭፈራቤት ይዣት ሄድኩ።
እንደገባን ጭፈራውን ታቀልጠው ጀመር ። ጭፈራው ላይም የዋዛ አልነበረችም። እኔ ደከመኝ ብዬ ጥግ ጥግ ላይ ወዳሉ
"ባለጌ ወንበሮች" ሄጄ ለመቀመጥ ስሞክር እየጎተተች ታስነሳኛለች።
ያልጨፈረችበት የዘፈን አይነት የለም። ወደጆሮዋ ጠጋ ብዬ•••
"ቃልዬ ያ የውዝዋዜ ዳኛው ትናንት ያደነቀሽ የእውነት መሰለሽ እንዴ? አቀለጥሽው እኮ" ስላት
ሙዚቃውን  ያስናቀም ያሳቀቀም ሳቅ ሳቀች ። መቀመጥ የሚባል ነገር የማይሞከር ሆነ ።
"ተነቅቶብሻል ባክሽ ወይ በዳንስ አድክመሽ ልታስተኝኝ አስበሻል ወይ ትናንት የጀመርሽውን ወገብ ሰበራ በዳንስ ልትጨርሽው ፈልገሻል " አልኳት።
ቃልዬ እኔ ባወራሁ ቁጥር ስትስቅ በተለይ ቀዝቀዝ ያለ ዘፈን ሲሆን የሷ ሳቅ ጎልቶ እየወጣ በቤቱ ያሉ የተወሰኑ ሰዎችን ትኩረት መሳባችንን እንዳስተዋልኩ ማውራቴን ተውኩት።
ቃልዬ ግን እኔ ማውራት ባቆምም ከዚህ ቀደም ከወር እና ከሁለት ወር በፊት ያወራነውን ሁሉ እያነሳች በትዝታ መሳቅ ጀመረች።
ከምሽቱ አምስት ሰአት አለፍ እንዳለ ሌላ ቦታ የተሟሟቁና የሰከሩ ወጣቶች ወደ ጭፈራ ቤቱ በብዛት መግባት ጀመሩ። ሰው እየበዛ ቤቱም እየሞላ መጣ። ይዣት ለመውጣት ብወስንም ቃልዬን ከዛ ቤት ይዞ መውጣት ቀላል ስራ አልነበረም።
በብዙ ውትወታ  እና ልመናም እሺ ብላ አልወጣ አለችኝ። በግድ  ተሸክሜም ቢሆን ይዣት መውጣት ነበረብኝ።
"እንግባ ይበቃናል ቃልዬ ነገ ጥዋት አራት ሰአት ክላስ አለሽ እኮ በጥዋት ስለምንሄድ ገብተን መተኛት አለብን" 
.
.
ከ 200 ላይክ ቡኋላ ክፍል 35 ይለቀቃል🌹
Like አርጉ እኛም ቶሎ እንልቀቀው 🙏           
https://vm.tiktok.com/ZMh9xdBnV/
TikTok · salodatrading
110 likes, 4 comments. “📌 ባለ 2 መገልበጫ ፍሬም 📌 በነጭ ቀለም ☎️ ይደውሉ ☎️ +251914855557 ☎️ . .”

10.2k 0 23 35 264

♥️ ተማሪዋ ♥️ ...
           .
           .
🌹...ክፍል 33...🌹
.
.

አጥብቄ አቀፍኳት።ሀረር መሀል ከተማ  አላፊ አግዳሚው ሳያስጨንቀን እኔም በሷ ጉያ እሳም በኔ ጉያ  ውስጥ ተጣብቀን ቀረን።
" እና እሺ አሁን ወዴት እንሂድ ?" አለችኝ ከቅፌ ሳትወጣ።
እና አሁን የት እንሂድ
"እኔ እንጃ ቃልዬ"
"እንዴ እኔ እ ን ጃ እና እንዲሁ መንገድ ለመንገድ እየዞርን እንደር?"
"እሺ የት እንሂድ  እዛው የነበርንበት እንመለስ ቤቱን ወደሽዋል ነው እንቀይር ?"
"ኧረ እዛው ይሻላል ፀጥታው ደስ ይላል'
" ነይ በቃ አልጋ እንያዝና ቦርሳሽን አስቀምጠሽ እንወጣለን"
ተያይዘን ሄድን ።
ልክ ቃልዬ አዋክቤ ከመኪናው ላይ ሳወርዳት እቃ የረሳሁ እንደመሰላት ሁሉ የቤቱ ጥበቃ የሆኑት ጠና የሉ ሰውም እንዳዩን እቃ ረስተን የተመለስን መስሏቸው"
"ምነው ልጆቼ ምን ዘንጋታችሁ ወጣችሁ?" አሉን።
"አይ ምንም አረሳን አባቴ የመሄድ ሀሳባችንን ለነገ አሻገርነው ና ተመለስን" አለቻቸው ቃልዬ።
"ይሁን ከመሸ መሄዱም ደግ አደለም ነገ ብትሄዱ ይሻላል ግቡ ግቡ ልጆቼ " አሉን።
"አየሽ እኔም ታውቆኝ ነበር እኮ ለ አዛውንት እና ለህፃን ልጅ እኮ ይታየዋል "አልኳት የክፍላችንን ቁልፍ ተረክበን  ትናንት ከነበርንባት በተቃራኒው በኩል ጥግ ላይ ያለችን ክፍል ውስጥ ከፍተን እንደገባን።
"ምኑ ነው የሚታየው ኤፍዬ?"
"በማታ ሲጓዝ መንገድ ላይ  ምን እንደሚያጋጥመው ነዋ"
"ኪኪኪ እና እሺ አዛውንቱ እሳቸው ናቸው እንበል ህፃኑ ታድያ ማነው ኤፍዬ?"
"እኔ ነኛ "
"ማመንህም ደስ ይላል"
"ምኑን?"

"ህፃንነትህን ነዋ"
"ማነው ህፃን?"
"ኪኪኪ እንዴ ትቆጣለህ እንዴ ? አንተው እኮ ነህ ያልከው"
"እሺ እኔ ለማለት ያህል ልበል አንቺ ግን አጋጣሚውን ተጠቅመሽ የልብሽን መተንፈስሽ ይገርማል"
"ይሄኔ ነው መሸሽ አለ መሸሻ" አለች እየሳቀች።
"ማነው ደሞ መሸሻ"
"የድሬ ዩንቨርስቲ ጥበቃ"
"እሱ ደሞ ጥበቃ ሆኖ ማባረር ሲገባው ጭራሽ ይሸሻል እንዴ?  ፈሪ በይው ፣ ለማንኛውም የልብሽን ተናግረሽ በመሸሻ ማምለጥ እይቻልም ማብራሪያ እፈልጋለሁ ቃልዬ ሙች አለቅሽም "
አልኳት አንገቷን አንቄ አልጋው ላይ በጀርባዋ እያንጋለልኳት።
"ታድያ ማብራሪያውን የምትፈልገው በተግባር  ነው በአንደበት" አለችኝ በታነቀ ድምፅ።
"እንዴት?"
"አንገቴን አንቀኸኝ እንዴት ላብራራልህ?
" በተግባር ብልሽስ እንዴት ልታብራሪው ነው?" አልኳት አንገቷን ለቀቅ አድርጌ ፀጉሯን እየነካካሁ።
"እንደትናንት ማታው  ነዋ" ስትለኝ ህፃን ተባልኩ ብዬ  ኮስተር ለማለት የሞከርኩት ሙከራ መክኖ ሳቅ አፈነኝ።
"ምን ያስቅሀል?"  አለችኝ እራሷ እየሳቀች።።
"እሺ በአንደበት ይብራራልኝ"
"ምነው የተግባር ማብራሪያውን ፈራኸው እንዴ?"
"አልፈራሁትም ፣ ለምንድን ነው የምፈራው ዛሬ ከድሬ ያስቀረሁሽ ለምን ሆነና እልህ ስለያዘኝ አይደል እንዴ"
"የምን አልህ ኤፍዬ?"
"ትናንት በመበለጤ ነዋ!"
"ኪኪኪ እና ምን ልትሆን?"
"ምን ልትሆን አልሽ ቃል ? ዛሬ አቅም ግንባታ ላይ ትኩረት አድርጌ በመስራት ልክሽን ላሳይሽ ነዋ"
"ኪኪኪ ምንድን ነው  ደሞ አቅም ግንባታ ?"
"አሁን ከዚህ ስንወጣ የሀረርን ሰንጋ ጥሬ ስጋ ነው የምበላው ከዛ ወንዱና ሴቱ ይለያል እንግዲህ"
ስላት ጥበቃው " አቤት  ጠራችሁኝ እንዴ ልጆች?"  ብሎ ክፍላችን ድረስ እስኪመጣ ነበር ሳቋን ጥበቃው ቤት ድረስ እስኪሰማ  የለቀቀችው።
ጥበቃውን  ነገሩ ወዲህ  ብዬ በሩን ዘግቼ   ስመለስም እየሳቀች ነው።
"ኪኪኪ አይ ኤፍዬ •••ኤፍዬ ሙት ጫወታህ እኮ አይጠገብም ።
" የምን ጫወታ ?  አዎ ላንቺ ጫወታ ነው ዛሬ ልክሽን ካላሳየሁሽ ወንድ ያባቱ ልጅ አይደለሁማ"
"በ. ም. ን   በ ጥሬ. ስጋ ?" እያለች በሳቅ ስትንከተከት እኔም አብሩያት ስንተከተክ ቆየሁና•••

ቃልዬ ሙች ትናንትም እኮ መብላት የፈለኩት ጥሬ ስጋ ነበር ግን ያንቺ ምርጫ ስላልነበር ነው የተውኩት"
"እና ዛሬም የኔ ምርጫ ጥሬ ስጋ መብላት  ባይሆንስ?"
"ብቻሽን ትበያታለሻ ቀልድ የለም ፣ ከጥሬ ስጋ ውጪ ወይፍንክች ብያለሁ ወይ ፍንክች"
"ቆይ ቆይ ጥሬ ስጋ ወንድ ያደርጋል እንዴ?"
"ይሄኔ ነው መሸሽ ማለት ያለበት አሁን ነው መሻሻ!  እንዴ ቃልዬ እንደቀልድ እያዋዛሽ ሞራሌ ላይ ታንክ መንዳት ጀመርሽ አደል?"
"እንዴ እንዴት  ስለምን ታንክ ነው የምታወራው?"

"ከዚህ በላይ የሰውን ሞራል በታንክ መደፍጠጥ አለ እንዴ የምን ታንክ ትያለሽ እንዴ ደሞ?  ጥሬ ስጋ ወንድ ያደርጋል እንዴ ? ማለትሽ ትናንትና ወንድ አልነበርክም ዛሬ ጥሬ ስጋ በልተህ ወንድ ልትሆን ነው ወይ? ማለትሽ አይደል እንዴ?"
"ጫ. ን.   ያ.  ለ.  ው መጣ" አለች ቃልዬ ጋደም ካለችበት ቀና እያለች።
"ማን ነው ጫንያለው?  የጥበቃው ስም ጫን ያለው ነው እንዴ?" አልኳት ወደ በሩን አየት አድርጌ።
"ኤፍዬ ሙት አንዳንዴ እየቀለድክ ይሁን እያመረርክ ይምታታብኛልኮ ለማንኛውም ኤፍዬ እኔ እንደዛ ለማለት ፈልጌ አይደለም ወንድማ ወንድ  ነህ ሊያውም መለሎ ቁመት፣ ጠይም ፊት ፣ ያልወፈረ ም ቀጭን የማይባልም ተክለሰውነት ያለው ፣ ፊቱ ላይ ያለው የደስደስ ወደሌላው የሚጋባ ደስ የሚል  የሀበሻ ወንድ!" አለችኝ።
የሰውነቴ ሙቀት በአንድ ግዜ እጥፍ ሲሆን ተሰማኝ። የድሬ ከተማ ህዝብ በሙሉ ተሰብስቦ ቃልዬ አሁን ያለችኝን ቢለኝ እንካን ይህን ያህል ሙቀቴ የሚጨምር አይመስለኝምበሚያፈቅሩት ሰው መሞካሸት  የሚፈጥረው የደስታ ስሜት ልዩ ነው።
"አመሰግናለሁ ቃልዬ!" አልኳት። ከሰከንዶች ዝምታ በኃላ•••
"ኤፍዬ "
"ወዬ ቃል"
.
.
ከ 200 ላይክ ቡኋላ ክፍል 34 ይለቀቃል🌹
https://vm.tiktok.com/ZMhu2unUT/           

10.9k 0 27 21 239
Показано 20 последних публикаций.