♥️ ፅናት ♥️...!!!
.
.
🥀..ክፍል 5..🥀
.
.
ከ አልጋዋ እንድትነሳ እረድቷት ወደ እህቷ ወሰዳት።ደረጃውን እየወጡ ሳሉ ዶክተሩ "እየውልሽ አንቺ በጣም ስለተጨነቅሽ ላሳይሽ ብዬ ነው እንጂ አይፈቀድም እህትሽን ከ ግማሽ ሰአት በኋላ ወደ ቀዶ ጥገና ክፍል እንወስዳታለን" አላት። ፅናት "ምን እህቴ አትሞትብኝም አደል? "አለችው። ዶክተሩ አዘነ ግን ፈገግ ብሎ "አታስቢ ምንም አትሆንም የህክምና ወጪዋንም የገፍታሪው ወላጆች ናቸው የሚችሉት" አላት። ፅናት እሺ ብቻ ብላው መሄድ ጀመረች ትንሽ ኮሊደሩን እንዳጋሙሱ ነይ እዚህ ነው አላት።
፨ክፍሉ ደረሱ በፀሎት ያለችበት ፤ በፀሎት የተኛችበት ፤በፀሎት የምታቃስትበት ክፍል ዶክተሩ" ደረሰናል ይህኛው" ነው። አላት ለፅናት እንድትገባ እየጠቆማት ፅናት ለመግባት ፈራች ክፍሉ ብትገባ የእሪሳ ሳጥን ውስጥ እህቷን የምታያት መሰላት። ውስጧ መግባትን ቢፈልግም እግሮቿ ግን ፍፅሞ አልቻሉም። ዶክተሩ ከትከሻዋ ገፋ ገደፍ አድጎ ሊያስገባት ሞከረ።
፨ ፅናት ግን "አይ አይሆንም፤ በጭራሽ አይሆንም" አለች። ዶክተሩ ግራ ተጋባ "ምኑ" አላት።ፅናትም የዶክተሩን ሁለት እጆች ይዛ " እህቴ በህይወት አለች አደል?"፤ ምንም አልሆነችም አደል? "አለችው። ዶክተሩ "አዎ አታስቢ! ነይ ገብተሽ እያት" አላት። ፅናት እንደምንም እግሮቾን ጎትታ ገባች።
፨ እህቷን ስታያት በጣም ደነገጠች። በደፈረሱ አይኖቿ ለእህቷ በድጋሜ፤ አለቀሰችላት ፤ አዘነችላትም። ዶክተሩ የፅናትን ፊት ሲያየው እሱም በጭራሽ ውስጡን አጀግኖ መቆየት አልቻለምና አለቀሰ እንባ አፈሰሰ። ፅናት ዶክተሩን አየችና "እንዴ ለምን ታለቅሳለክ ስለማትድን ነው?" አለችና ዶክተሩ ፊት ላይ አፈጠጠች።
ዶክተሩ ውብ አይኖቿ አፈዝዘውት በአትኩሮት ያያት ጀመር። ፅናት ግራ ገባት ዶክተሩ በመጨረሻ ወደ እራሱ ተመልሶ እራሱን ታዘበ በብላቴና እና በታናሽ ታናሹ አይን መማረኩን እሱንም አስገረሞታል። ደንገጥ ብሎ "አይ አይ እንደዛ አደለም አታስቢ ደና ትሆናለች" አለና ሁለት መዳፎቹን አይኖቹ ላይ አርጎ ሽቅብ አንገቱን አድረጎ "ኡፍፍፍፍፍ" አለ።
፨ፅናት ወደ እህቷ ተጠጋች መንካትም ፈራች እጇን ወደ በፀሎት ሰደደችው ግን መንካት አልቻለችም። እጆን መልሳ ፊቷን አዙራ በሩን ጓ አድርጋ ወጣች። ዶክተሩ ወደ በፀሎት ተጠጋ በፀሎት እግሯ ወደላይ በጅብሰን ታስሯል የወደቀችው የትምህርት ቤቱ መናፈሻ ሳር ላይ በመሆኑ እግሯን የፓርኩ አጥር ስለመታት እግሯ ተጎድቷል። ፊቷ ምንም አልሆነም ጭንቅላቷ ግን ተመቷል። ጭንቅላቷ ላይ የተጠመጠመው ፋሻ እንዳለ ሆኖ ፊቷ ግን ውብ ነው። ዶክተሩ "እነዚህ ልጆች ከምን ቢፈጠሩ ነው እንዲህ ውብ የሆኑት?" አለ ድምፅ አውጥቶ።
፨ከዛ ክፍሉን ለቆ ወጣ። ይህ ከሆነ ከግማሽ ሰአት በኋላ የሆስፒታሉ ዶክተር እና ነርሶች በፀሎትን ኣፕራሲዮን በማድረግ ላይ ናቸው። ፅናት ግን ተኝታለች ዶክተሩ። የእህቷ ኣፕራሲዮን ከ ግማሽ ሰአት በፊት እንደሆነ የነገራትን ዘንግታ ሳይሆን ሳታስበው ነው። የትግስት ኣፕራሲዮን ጊዜ 8 ሰአት የሚፈጅ በመሆኑ ግማሽ ሰአት ከፈጀ በኋላ ፅናት ከእንቅልፏ ባነነች ከ አልጋዋ ተነስታ ኮሊደሩን እየተደገፈች ፣ እየተጓዘች በድጋሜ እራሷን ስታ ወደቀች።
፨ያያት ሰው አልነበረም ከትንሽ ቆይታ በኋላ የአንድ ሴት ወደ ኮሊደሩ ስትመጣ አየቻት። ሴቲቷ አልጮከችም በቀስታ ወደ ፅናት ከሄደች በኋላ ፅናትን ተሸክማ አቅራቢዋ ወዳለው የአግዳሚ መቀመጫ ወንበረ ላይ አስተኝታ የፅናትን መንቃት መጠባበቅ ጀመረች። ፅናት ግማሽ ሰአት አስቆጥራ ነቃች ስትነቃ የአንድ ሰው ታፋ ላይ ጋደም ብላለች። ቀስ ብላ ቀና ለማለት ስትሞክር አቅም አጥሮ አቃታት ። ሴቲቷ "ተኒ አዎ ተኒ መተኛት ፈረተሽ ነው አትፍሪ የአሁኑን መተኛት ከፈራሽ ለዘላለም መተኛትን እንዴት ልትቀበይው ሚጢጢዋ" አለቻት ፀጉሯን እያሻሸች።
፨ ፅናት ደነገጠች ቀስ ብላ በድጋሜ ለመነሳት ስትሞክር ተሳካላትና ቀና አለች። ይህቺን ሴት ፅናት ታውቀዋለች ይንን ፊት የት እንዳየችውም በጭራሽ ልትዘነጋው አትችልም ይህቺን ሴት የምታውቃት የእናት እና የአባትዋን መቃብር ለማየት ከ እህቷ ጋረ ስትመጣ ሁሌም ባይሆን በብዛት ታያታለች። ሁሌም በእጆቿ አበባ ይዛ መቃብሮቹ ጋር ትበትናለች። ሽቶም ትነፋባቸዋለች ፅናት ይህቺን ሴት በጣም ትፈራታለች። ፊቷ ልክ እንደ ቆንጆ እንጀራ ምልክት አለው። ፀየም ያለች እና ፀጉሯን የተከረከመች ናት ሁሌም የምትለብሰው ልብስ ጥቁር ግን ፅዱ ነው ጠረኗ መቃብሮቹን የምትቀባው ሽቶ ነው። አቋሞ ቀጠን ያለች እና እጅና እግሮቿ እረጃጅም ናቸው።
፨ፅናት እና በፀሎት የሚፈሩት ሴት እሷን ሲያዩ ሞት ትዝ የሚላቸው ሁሌም ነው። ፅናት ፈራች የእህቷ በፀሎትን የሞት መረዶ ልትነግራት የመጣች መሰላት። ከሴቲቱ ላይ ተፈጨረጭራ ተነስታ ወንበሩ ላይ ቁጭ ብላ አንገቷን ደፍች እጆቾን ቆላልፋ በታፋዎቾ መሀል አረገቻቸው ። ሴቲቱ እጆቿን ወደ ፅናት እጆች ሰዳ ከታፍዋ ፈልቅቃ ያዘቻቸው ፅናት ፈራች። ሴቲቱ የቀኝ እጃን ወደ ፅናት አገጭ ሰዳ ቀና ካረገቻት በኋላ "ምነው ፈረተሽ ነው? አይዞሽ አትፍሪ! ያሰብሽውን እና ለእሱ የምትጨነቂለትን ሰው እንደማታጪ ተስፋ አደረጋለው" አለቻት።
፨ የሴቲቱ አይን ከ ፅናት አይኖች ጋር ተገጣጥመው ተፍጠጡ ፅናት አይኗን ስታየው ድንገት ደነገጠች ደርቃ ቀረች የልብ ምቷ ጨመረ ልቧ መታ እንደጉድ ድው ድው ድው ድውው። ሴቲቱ የፅናትን ድንጋጤ አስተውላለች "ምነው ለምን ደነገጥሽ?" አለችና እጆን ከፅናት እጅ እና አገጭ አነሳች። ከዛም የቀኝ እጆን ወደ ፅናት ዘረግታ "እንተዋወቅ ሚጢጢዋ ሊባኖስ እባላለው" አለቻት።
ፅናት የሊባኖስን እጅ በአይኗ አተኩራ አየቻቸው። "ያንቺ ስም ማነው?" አለቻት። ፅናት እረብትብት አለች። እጆቿን በቀስታ ወደ ሊባኖስ እጃች ወስዳ አጣመረቻቸው ከዛም የፅናት ትንፋሽ ተቆራረጠ "እኔ የእኔ የእኔ ስም ደሞ ፅፅፅፅፅፅፅናትትትትት ይባላል"። አለቻት ሊባኖስ "እሺ የተጨነቅሽ ትመስያለሽ ሚጢጢዋ ፅናት መጣው ውሀ ይዜልሽ" አለችና ሄደች።
፨ ሊባኖስ ከመቀመጫዋ ስትነሳ አንድ ደብተር ነበር። ሊባኖስ ከሄደች በኋላ ፅናት ጠጋ ብላ እጇእየተንቀጠቀጠ ደብተሩን አነሳችው። የደብተሩ የመጀመሪያ ገልፅ ላይ "በትልቁ ሞት ህይወት ነው! ህይወት ሞት ነው!?" ይላል
ይቀጥላል like. Share ቤተሰብ✨