ለጠየቅሽኝ እንቆቅልሽ ፣ ሲጠፋብኝ እኔ መልሱ
"ሀገር ስጠኝ" የምትዪኝ ፣ መልስ አታውቂም አንቺ ራሱ!
ሁሉ ሀገሩን ተከፋፍሎ፣ ክልልሎችን እያጠረ
ከየት አምጥቼ ሀገር ልስጥሽ ?፣ ሀገር ማለት ሰው ነበረ።
ሰውም በዘር ተደራጅቶ ፣ ሀገር መሆን አቅቶታል
ገድሎ ሚኖር ተበራክቶ ፣ ሞቶ ሚያኖር ከሀገር ጠፍቷል!
ይህን እውነት እያወቅሽው ፣
ሀገር ስጠኝ አትበዪኝ ፣ በእንቆቅልሽ ልትለውጭኝ
ክልልና ዘር ነው ያለኝ ፣ እባክሽን ዘርንና ክልልን ወስደሽ ሀገር ስጭኝ!
"ሀገር ስጠኝ" የምትዪኝ ፣ መልስ አታውቂም አንቺ ራሱ!
ሁሉ ሀገሩን ተከፋፍሎ፣ ክልልሎችን እያጠረ
ከየት አምጥቼ ሀገር ልስጥሽ ?፣ ሀገር ማለት ሰው ነበረ።
ሰውም በዘር ተደራጅቶ ፣ ሀገር መሆን አቅቶታል
ገድሎ ሚኖር ተበራክቶ ፣ ሞቶ ሚያኖር ከሀገር ጠፍቷል!
ይህን እውነት እያወቅሽው ፣
ሀገር ስጠኝ አትበዪኝ ፣ በእንቆቅልሽ ልትለውጭኝ
ክልልና ዘር ነው ያለኝ ፣ እባክሽን ዘርንና ክልልን ወስደሽ ሀገር ስጭኝ!