✞ ጥምቀተ ክርስቶስ ✞
በሊቀ ሊቃውንት ዕዝራ ሐዲስ
ጥር ፲ ቀን፳፻፱
ክፍል ሁለት (፪)
ያውስ ቢኾን ጥምቀቱን በዮርዳኖስ ያደረገው ስለምን ነው? ቢሉ ትንቢቱን፣ ምሳሌውን ለመፈጸም ነው፤
ትንቢቱ፦"ባሕርኒ ርእየት ወጐየት ወዮርዳኖስኒ ገብአ ድኅሬሁ፤ ባሕር አይታ ሸሸች፤ዮርዳኖስም ወደ ኋላው ተመለሰ፡፡ … ርእዩከ ማያት እግዚኦ ርእዩከ ማያት ወፈርኁ፤ አቤቱ ውኆች አንተን አይተው ሸሹ፤"ተብሎ ተነግሯል።
መዝ. ፸፮፥፲፮፤ ፻፲፫፥፫/፡፡
ምሳሌው፦ ዮርዳኖስ ከላይ ነቁ (ምንጩ) አንድ ነው፤ ዝቅ ብሎ በደሴት ይከፈላል፤ ከታች ወርዶ ይገናኛል፡፡ ዮርዳኖስ ከላይ (ነቁ) ምንጩ አንድ መኾኑ የሰውም መገኛው (ምንጩ) አንድ አዳም ለመኾኑ፤ ዮርዳኖስ ዝቅ ብሎ በደሴት መከፈሉ እስራኤል በግዝረት፣ አሕዛብ በቍልፈት ለመለያየታቸው፤ ዮርዳኖስ ከታች በወደብ መገናኘቱ በክርስቶስ ጥምቀት ሕዝብና አሕዛብ አንድ ወግን ለመኾናቸው ምሳሌ ነው፡፡
ዳግመኛም አብርሃም ለአምስቱ ነገሥተ ሰዶም ረድቶ አራቱን ነገሥተ ኮሎዶጎሞር ድል ነሥቶ በተመለሰ ጊዜ ደስ ቢለው "በመዋዕልየኑ ትፌኑ ቃለከ ወሚመ ታርዕየኒሁ ኪያሃ ዕለተ፤ በዘመኔ ቃልህን (እግዚአብሔር ወልድን) ትልከዋለህን? ወይስ ያቺን የማዳንህን ቀን በዓይኔ ታሳየኝ ይኾን፤" ብሎ በጠየቀው ጊዜ "ምሳሌውን ታያለህና ዮርዳኖስን ተሻግረህ ሒድ፤" ብሎታል፡፡ አብርሃምም ዮርዳኖስን ተሻግሮ ቢሔድ መልከ ጼዴቅ ኅብስተ አኮቴት፣ ጽዋዓ በረከት ይዞ ተቀብሎታል፡፡
ይኸውም አብርሃም የምእመን፤ ዮርዳኖስ የጥምቀት፤ መልከ ጼዴቅ የካህናት፤ ኅብስተ አኰቴት፣ ጽዋዓ በረከት የሥጋው የደሙ ምሳሌ ነው።
ዘፍ. ፲፬፥፲፫-፳፬/፡፡
ኢዮብና ንዕማን በዮርዳኖስ ወንዝ ተጠምቀው ከደዌያቸው ድነዋል። ፪ኛነገ.፭፥፰-፲፱/፡፡
ኢዮብና ንዕማን የአዳምና የልጆቹ፤ ደዌ የመርገመ ሥጋ፣ የመርገመ ነፍስ፤ ዮርዳኖስ የጥምቀት ምሳሌ ነው፡፡ ኢዮብ፣ ንዕማን፣ ጌታ የተጠመቁበት ዮርዳኖስ ወደቡ አንድ ነው፡፡
እንደዚሁም እስራኤል ከግብጽ ከወጡ በኋላ በኢያሱ ጊዜ ወደ ምድረ ርስት ሲሔዱ ከዮርዳኖስ ወንዝ ደረሱ፡፡ ታቦቱን የተሸከሙና ልብሰ ተክህኖ የለበሱት ሌዋውያን ካህናት በፊት በፊት ሲጓዙ ታቦቱን የሚያጅቡ ሕዝበ እስራኤል ከታቦቱና ከሌዋውያን ካህናት ሁለት ሺሕ ክንድ ርቀው ዮርዳኖስ ከላይና ከታች ተከፍሎላቸው በየብስ ተሻግረው ኢየሩሳሌም ገብተዋል፡፡ ምእመናንም በማየ ገቦ ተጠምቀው ገነት መንግሥተ ሰማያት ለመግባታቸው ምሳሌ ነው፡፡
ኤልያስም ዮርዳኖስን ተሻግሮ ብሔረ ሕያዋን ገብቷል፡፡
የኤልያስ ደቀ መዝሙር ኤልሳዕ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር በዮርዳኖስ ዳር እንጨትና ሲቈርጡ መጥረቢያው ከውኀው ውስጥ ወደቀ፡፡ ኤልሳዕ የእንጨት ቅርፊት በትእምርተ መስቀል አዘጋጅቶ ምሳሩ ከወደቀበት ላይ ቢጥልበት የማይዘግጠው ቅርፊት ዘግጦ የዘገጠውን ብረት አንሳፎ አውጥቶታል፡፡ እንደዚሁም ዅሉ በባሕርዩ ሕማም ሞት የሌለበት አምላክ ከሰማየ ሰማያት ወርዶ፣ ከቅድስት ድንግል ማርያም ተወልዶ፣ በአጭር ቁመት በጠባብ ደረት ተወስኖ፣ በዮርዳኖስ ተጠምቆ፣ በቀራንዮ በዕፀ መስቀል ተሰቀሎ፣ ከጎኑ ጥሩ ውኀና ትኩስ ደም አፍስሶ በሲኦል የወደቀው አዳምን ለማዳኑ ምሳሌ ነው።
፪ኛነገ. ፮፥፩–፯፡፡
ይህንን ዅሉ ምሳሌ ለመፈጸም ጌታችን በዮርዳኖስ ተጠምቋል፡፡
ከዚህ በተጨማሪ ጌታችን በዮርዳኖስ የተጠመቀበት ምሥጢር ምንድን ነው? ቢሉ ዲያብሎስ በአዳምና በሔዋን የጨለማ መጋረጃ ጋርዶ አገዛዝ ስቃይ አጸናባቸው፡፡ ከዚያም "አዳም ገብሩ ለዲያብሎስ ሔዋን ዓመቱ ለዲያብሎስ፤ አዳም የዲያብሎስ ተገዥ፤ ሔዋንም የዲያብሎስ ተገዥ አገልጋዮች ነን" ብላችሁ ስመ ግብርናታችሁን (የተገዥነታችሁን ስም) ጽፋችሁ ብትሰጡኝ መከራውን አቀልላችሁ ነበር" አላቸው፡፡
እነሱም መከራው የሚቀልላቸው መስሏቸው "አዳም ገብሩ ለዲያብሎስ ሔዋን ዓመቱ ለዲያብሎስ" ብሎ በማይጠፋ በሁለት ዕብነ ሩካም (ዕብነ በረድ) ጽፎ አንዱን በዮርዳኖስ፤ አንዱን በሲኦል ጥሎት ይኖር ነበር፡፡
በዮርዳኖስ የጣለውን ጌታችን ሲጠመቅ እንደ አምላክነቱ አቅልጦ እንደ ሰውነቱ ተረግጦ አጥፍቶልናል፡፡ በሲኦል የጣለውንም በዕለተ ዓርብ በአካለ ነፍስ ወርዶ ነፍሳትን ከዲያብሎስ ባርነት ነጻ ሲያወጣ አጥፍቶልናል፡፡ ጌታችን በዮርዳኖስ የተጠመቀበት አንደኛው ምሥጢርም ይህ ነው፡፡
ጌታችን ጥምቀቱን በውኀ ያደረገው በሌላ ያላደረገው ስለምንድን ነው ቢሉ...
ክፍል ሦስት ይቀጥላል...
🙏 ይቆየን 🙏
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
@yemezmur_gexem