#ኢብራሂም ነብዩሏህ_ዒስማኢል እና #ነብዩሏህ_ዒስሃቅ
አሁን ዒስማኢል (ዐሰ) ጎርምሷል፣ለሁሉ ነገር ብቁ የሆነ ወጣትም ሆኗል።ውሀ
ፍለጋ መጥተው እዛው ኑሮዋቸውን ያደረጉት የጁርሀም ብሄረሰቦችም
ኢስማዒልን እጅጉን ይወዱታልም።
ቋንቋቸውንም አስለምደውት ባህላቸውንም አላብሰውታል።ለአቅመ አዳም
መድረሱን በተመለከቱም ግዜ ከራሳቸው ዘር የሆነችን እንስትም ዳሩለት።
ኢስማዒል (ዐ ሰ) ትዳር እንደያዘ እናትየው ሀጀር ብዙም ሳትቆይ ነበር
ለፈጣሪዋ ነፍሷን ያስረከበችው።ኢስማዒልም ያለ አባት ያሳደገችው እናቱ
ስትለየው እጅጉን ቢያዝንም ምላሹ ግን ዱዓ ብቻ ነበር።
ምንም እንኳን የኢስማዒል አባት ኢብራሂም (ዐ ሰ) በዛ ግዜ ትልቅ ሽማግሌ
ቢሆኑም የአብራካቸውን ክፋይ ለመጎብኘት ከፊለስጢን ምድር መካ ድረስ
በየግዜው ይመላለሱ ነበር።ነገር ግን አሁን ትንሽ ሰንበትበት ብለዋል መካ
ከመጡ...
ልክ መካ እንደደረሱ ልጃቸው ቤት ሲገቡ የልጃቸውን ሚስት
ያገኟታል።ኢስማዒል የት እንዳለም ሲጠይቋት ለአደን ከከተማ እንደራቀ
ነገረቻቸው።
እሳቸውም ቀጠል አድርገው ፦"ልጄ ኑሯቸሁ እንዴት ነው?" ብለው ሲጠይቋት
እሷም፦"ኑሮዋችን በጣም ዝቅተኛ ነው..."በማለት ብዙ ስሞታ አቀረበች።
እሳቸውም፦"በይ ልጄ እኔ መሄዴ ነው።ኢስማዒል ሲመጣ ሰላምታዬን
አድርሺልኝ።በመቀጠልም የበሩን መዝጊያ እንዲቀይርም ንገሪው" ብለዋት
ትተው ሄዱ።
ኢስማዒልም ከአደን ሲመለስ ሚስቱ፦"አንድ ሽማግሌ ሰውዬ መጥቶ
ነበር።ሰላም በይልኝ ብሎ የበርህንም መዝግያ እንድትቀይር አዞሀል" ስትለው
አባቱ መሆኑን አውቆ የበር መዝጊያ ደሞ ሚስቱን እንደሆነ በመረዳት ሚስቱን
ፈታት።
ኢስማዒልም ሌላ አዲስ ሚስት አገባ።ከእለታት አንድ ቀንም የልጃቸው ናፍቆት
አላስቀምጥ ያላቸው ኢብራሂም ከ ፊለስጢን ምድር ልጃቸውን ሊያዩ ሲከንፉ
መጡ።
ቤት ሲደርሱ ሌላ ሴት ተመለከቱ'ና፦"ልጄ ኢስማዒል የት ነው" ብለው
ሲጠይቋት
እሷም፦"ለአደን ራቅ ወዳለ ቦያ ሄዷል ኑ ግቡ"አለቻቸው።
እሳቸውም፦" ኑሮዋችሁስ እንዴት ነው?" ሲሏት
እሷም፦"በጣም ጥሩ ነው ሁሌ ድሎት ሁሌ ምቾት ነው" ብላ መለሰችላቸው።
እሳቸውም፦" በይ ልጄ እኔ መሄዴ ነው።ኢስማዒል ሲመጣ ሰላምታዬን
አድርሺልኝ።በመቀጠልም የበሩን መዝጊያ ጠበቅ አድርጎ እንዲይዝ ንገሪልኝ"
ብለዋት ሄዱ።
ኢስማዒልም ከአደን ሲመለስ ሚስቱ፦"አንድ ሽማግሌ ሰውዬ መጥቶ
ነበር።ሰላም በይልኝ ብሎ የበርህንም መዝግያ ጠበቅ አድርገህ እንድትይዝ
አዞሀል" አለችው።
ኢስማዒልም አባቱ ይህችኛዋን ሚስቱን እንደወደዱለት ተረድቶ ይልቅ
ያከብራትም ጀመር።
ለዚያ አካባቢ እና በዙሪያዋ ላሉ ነገዶች፣ለአማሊቃዎች፣ለጁርሀሞች እና
ለየመኖች በነቢይነት ሲያገለግል የነበረው ኢስማዒል (ዐ ሰ) ቀደምት አባቶቹ
የቀመሱትን የሞት ፅዋ መቅመሻው ግዜ ሲደርስ ነስማ የተባለችውን ሴት
ልጁን የወንድሙ የኢስሀቅ ልጅ የሆነው ዒስ እንዲያገባት ተናዝዞ በተወለደ
በ173 አመቱ የሙታንን መንደር ተቀላቀለ።...{ዐለይሂ ሰላቱ ወሰላም}
አሁን እግረ መንገዳችን የኢስሀቅን ህይወት ጎራ ብለን እንመልከት...
ለኢስሀቅ አባቱ ኢብራሂም (ዐሰ) በህይወት ሳለ በ40 አመቱ ነበር ረፍቃ ቢንት
በትዋዪል ከተባለች እንስት ትዳር ያስያዘው።
ምንም እንኳን ረፍቃ መውለድ የማትችል መሃን ብትሆንም በባለቤቷ ያላሰለሰ
ዱዓ ሁለት መንታ ልጆችን ለመታደል በቅታለች።
አንደኛው፦ዒስ ሲሆን
ሁለተኛው፦ያዕቁብ (ዐሰ) ይባላል።
ዒስ የሮም ህዝቦች ቅድመ አያት ሲሆን፤ ያዕቁብ ደሞ የእስራኢላውያን ቅድመ
አያት ነው። የሁለቱም አባት ሁለቱንም ልጆቹን በጣም ቢወዳቸውም ከያዕቁብ
ይልቅ ለዒሱ ግን ለየት ያለ ቦታ ነበረው።
እናታቸው ረፍቃ ግን ያዕቁብ ታናሽ ስለሆነ ይበልጥ እሱን ነበር የምትወደው።
ኢስሀቅ ከእርጅና የተነሳ አይናቸው ማየት ካቆመ ትንሽ ሰንበትበት ብሏል።
ከእለታት አንድ ቀን ኢስሀቅ (ዐሰ) ስጋ ያምራቸውና የሚወዱትን ልጃቸውን
ዒስን አደን አድኖ ስጋ እንዲያመጣለቸው እናም ከባድ ዱዓም
እንደሚያደርጉለት ነግረውት እሱም ለአደን ሄደ።
ይህን በድብቅ ስትሰማ የነበረችውም የልጆቹ እናት ረፍቃ ለያዕቁብ ነግራው
ከፍየሎቹ ወፍራሙን ሙኩት እንዲያርድ ካደረገች በኋላ የወንድሙን ዒስን
ልብስ አልብሳው እራሱን(ዒስን) አስመስላ የሰራውን ስጋ ለአባቱ እንዲያቀርብ
አደረገች።
ያዕቁብም ያዘጋጀውን ምግብ ይዞ አባቱ ዘንድ ሲያቀርብ
አባቱ፦"ማን ነህ አንተ?" አሉት።
ያዕቁብም፦"ልጅዎት ነኝ"አለ።
አባቱም(ኢስሀቅ)፦"ድምፅህ የያዕቁብ ነው፤ልብስህ ግን የዒስ ነው" በማለት
የቀረበላቸውን ምግብ በሉት።
ምግቡን በልተው እንደጠገቡም ምግቡን ላቀረበው አላህ ክብሩን ከፍ
እንዲያደግለት፣ የበላይ ዘርም እንዲያደርገው፣ልጆቹንም ሪዝቁንም አላህ
እንዲያበረክትለት ዱዓ አደረጉ።
ልክ ዱዓውን እንዳጠናቀቁ ያዕቁብ አሚን ብሎ የአባቱን ክፍል ለቆ
ወጣ።ያዕቁብም ሲወጣ ዒስ በታዘዘው መልኩ ያደነውን ስጋ ጠባብሶ ለአባቶ
አመጣ'ና አቀረበ። አባቱ ግን ቅድሙኑ ጠግበዋል።
ዒስ ምግቡን ሲያቀርብላቸው፦"ልጄ ይህ ምንድነው?" አሉት።
ዒስ'ም፦"አምጣልኝ ያሉት ስጋ ነዋ" አላቸው።
አባትየውም፦"አሁን አምጥተህልኝ በልቼ ዱዓ አላደረግኩልም እንዴ!!!"ሲሉት
ወንድሙ ያዕቁብ እንደቀደመው እና ዱዓውንም ሸውዶ እንደተቀበለ በመረዳት
ሀይለኛ እልህ ያዘው።
ዒስ አባታቸው ኢስሀቅ ከሞተ ያዕቁብን እንደሚገድለውም ይዝትበት
ጀመር።ያን ግዜ አባት ለልጃቸው ዒስ ማስተዛዘኛ ይሆም ዘንድ፦"አላህ
ዝርያዎችህን ጠንካሮች ያድርጋቸው፣ፍራፍሬዎችን እና ሪዝቆቹንም አላህ ሰፋ
አድርጎ ይስጥህ" በማለት ዱዓ አደረጉለት።
ነገር ግን እናት ልጇ ያዕቁብ ላይ ሚዛተው ዛቻ እረፍት ነስቷት ስለነበር የዒስ
ቁጣ እስኪበርድለት ድረስ ያዕቁብን ሀራን በሚባል አካባቢ ወደሚገኘው
ወንድሟ (ላባን) ላከችው።
ያዕቁብም ስንቁን ይዞ ወደ አጎቱ ላባን እየተጓዘ ሳለ መንገድ ላይ መሸበት እና
አንድ ድንጋይ ተንተርሶ ፏ ያለ እንቅልፍ ተኛ።
እዛው በተኛበትም በህልሙ ወደ ሰማይ መወጣጫ ይመለከታል።በዚያ
መወጣጫ መላዕክት ይወጣሉ...ይወርዳሉ።በዚያ መሀከል አላህም፦"እኔ
አንተን እባርክሀለሁ።ዝሪያዎችህንም አበዛልሀለሁ...ምድርንም ላንተ እና
ለዝርያዎችህ አደርጋታለሁ" አለው። በህልሙ ማለት ነው....
ልክ ይሄን እንዳየ ከእንቅልፉ ነቃ። ባየው ነገርም በጣሙን ተደሰተ'ና፦"ጌታዬ
አሁን ከምሄድበት በሰላም ከመለስከኝ እዚህ ቦታ ላይ ላንተ አምልኮ እሚሆን
ቤት እገነባለሁ።ከሚኖረኝም ሀብት አንድ አስረኛውን ባንተ መንገድ አውላለሁ"
በማለት እዛ ቦታ ላይ የሆነ ምልክት አድርጎ ስለት ገብቶ ጎዞውን ቀጠለ።
ብዙ ተጉዞ የሀራንን ምድር ደረሰ'ና ከአጎቱም ተገናኘ።ለአጎቱ ሁለት ሴት ልጆች
ነበሩት አንዷ (ለያ) ስትባል ታናሿ ደሞ (ራሂል) ትባላለች።
ምነው ለያ ራሂል...ስል የዩሱፍ ፊልም ትዝ አላችሁ ሀ....!!! ቆይ ዩሱፍንም
ደርሰነዋል ትንሽ ነው የቀረን።
ትንሸኛዋ ራሂል ቆንጅዬ ነገር ስትሆም ትልቋ ግን እስከዚህም ነገር
ነበረ።ከዚያም ያዕቁብ ትንሸኛዋ ራሂል በልቡ መግባቷን ሲያውቅ አጎቱን ላባንን
እንዲድረው ጠየቀው።
አጎቱም፦"7 አመት በጎችን ካገድክልኝ እድርሀለሁ" በማለት ቃል ገባለት'ና
ያዕቁብም ቆንጂዬዋን ራሂልን ለማግኘት ለ7 ተከታታይ አመታት እረኛ ሆኖ
አሳለፈ።
የማይደርስ የለም'ና ሰባቱ አመት ተጠናቅቆ የቀጠሮው ቀን ብቅ አለ።ላባንም
ድል ያለ ድግስ ደግሶ ዘመድ አዝማድ ከጠራ በኋላ ኒክህ እስሮ ሙሽሪትንም
ለያዕቁብ አስረከበው።
በማግስቱ ጠዋት ላይ ጨለማው በብርሀን መገፈፍ ሲጀ..
@yenebiyattaric