ነብዩሏህ ሷሊህ_(ዐ.ሰ)
ክፍል 1⃣
ሳሊህ ዐ ሰ በነቢይነት ከመመረጣቸው በፊት ህዝቡ ዘንድ በምልካም ስነ
ምግባራቸው የሚታወቁ፣ከከበርቴ ቤተሰብ የተወለዱ፣ከዚያም አልፎ ሰዎች
ለፍርድ ሚያስቸግር ክርክር ሲገጥማቸው እሳቸው ጋር የሚሄዱ ምርጥ የአላህ
ባርያ ናቸው።
ወደፊት ሀገሪቷን በንግስና ያስተዳድሯታል ተብሎም ይገመት ነበር።
በንዲህ አይነት ሁኔታ ላይ ሳለ ሳሊህ ዐ ሰ የጌታቸውን ተልዕኮ እንደተቀበሉ
በትኩስነቱ፦" ወገኖቼ ሆይ! አላህን ተገዙ፡፡ ከእርሱ ሌላ ለእናንተ ምንም
አምላክ የላችሁም፡፡ ከዓድም በኋላ ምትኮች ባደረጋችሁና በምድሪቱም ላይ
ባስቀመጣችሁ ጊዜ አስታውሱ፡፡ ከሜዳዎቿ (ሸክላ) ሕንጻዎችን ትገነባላችሁ፡፡
ከተራራዎችም ቤቶችን ትጠርባላችሁ፡፡ ስለዚህ የአላህን ጸጋዎች አስታውሱ፡፡
በምድርም ውስጥ አጥፊዎች ኾናችሁ አታበላሹ" በማለት ጥሪውን አስተጋባ።
ይህን በሰሙ ግዜ ትዕቢታቸው አናታቸው ላይ ወጣ...ኩራታቸው
ገነፈለ...የከተማይቱ መሳፍንትም፦"አንተ ሳሊህ! ቆይ አንተ ከኛ በምን ተሽለህ
ነው አላህ መልዕክተኛ አድርጎ ሊመርጥህ የቻለው? ይልቁኑ አማልክቶቻችን
በመጥፎ አይን ሳያዩህ አልቀሩም'ና አብደሀል" አሉት።
ከዚያም እንደተለመደው ሳሊህ(ዐ ሰ) የድሆች እና ምስኪኖች ተከታይ
ይበራከቱለት ጀመር።ይሁን እንጂ በለፀጋዎች እና ጉልበተኞቹ ዝም ማለትን
አልመረጡም'ና ምእመናኑ ዘንድ በመሄድ፦"እናንተ ባመናችሁት ነገር እኛ
ክደናል" በማለት ይሳለቁባቸው ነበር።
ከዛላችሁ እነዚህ አመፀኛ ህዝቦች አንደ ቀን የሳሊህን ዐ ሰ ጥሪ ለማስቆም
እና ተከታዮቹን ከሱ ለማራቅ ምን ማድረግ እንዳለባቸው ሊመካከሩ አንድ ቦታ
ተሰበሰቡ።
ብዙ ከመከሩ በኋላ በመጨረሻም ሳሊህን (ዐ ሰ) ያለ ተከታይ ብቻውን
ለማስቀረት አንድ መፍትሄ አገኙ።
እሱም፦"ሳሊህን የሚከተል ከአማልክቱ በኩል የማይድንን በሽታ
ይይዘዋል።ከሳሊህም የሚርቅ ከነዚህ ነገሮች የተጠበቀ ይሆናል" በማለት
ከተማይቷን ቀወጧት።
ነገር ግን ትክክለኛይቱ የዳዕዋ ጥሪ መንገዷን ይዛ ቀጥላለች።በዚህ ሁኔታ ላይ
ሳሉ አንድ ቀን ሳሊህ ዐ ሰ ጥሪያቸውን በህዝብ ፊት ሲያደርሱ ህዝቡም፦"አንተ
ሳሊህ እውን አንተ ነቢይ ከሆንክ ማረጋገጫ ይሆነን ዘንድ እስቲ ተዐምር
አምጣልን" አሉት።
የከተማይቱ ሹማምንት እና የተከበሩ ሰዎች በቦታው ነበሩ።የማይችለውን ነገር
በመጠየቅ እንዳደናገሩት በማሰብ የማላገጥን ሳቅ ይስቁበትም ጀመር።(ወላሂ
ነቢያቶች አላህ ምንዳቸውን ከፍ ያድርግላቸው።በገዛ ሀገራቸው ይሳቀቃሉ)
ከመሳፍንቱ መሀክል አንዱ ቆመ'ና፦"አንተ ሳሊህ ተዐምር ማሳየት እችላለሁ
የምትል ከሆነ የተዐምሩን አይነት እኛ ነን ምንመርጠው ያንተ ስራ እኛ
የመረጥነውን ተዐምር መተግበር ብቻ ነው" አሉት
እኛ እያየን ከዚህ ተራራ ውስጥ በግዝፈቷ አቻ የሌላት የአስር ወር እርጉዝ
የሆነች፣መልኳም ቀይ የሆነ፣ከግዝፈቷ የተነሳ የከተማይቱ ይዝብ እና እንስሳት
የሚጠጡትን ውሀ በአንዴው መጠጣት የምትችል ትልቅ ግመል
አውጣልን"አሉት።
ነቢዩላህ ሳሊህም (ዐ ሰ) ህዝቡ ሁሉ ተዐምሩን አይተው በማመን ከጀሀነም
ይድኑ ዘንድ የከተማይቱ ሰው ሁሉ እንዲሰበሰብ አዘዙ'ና ሁሉም ተሰበሰቡ።
ከዚያም ሳሊህ (ዐ ሰ) ለጌታቸው ሱጁድ በመውረድ ጌታቸውን ይማፀኑ
ጀመር።አላህም የሱን መልዕክተኞች በህዝባቸው ፊት አያሳፍራቸውም'ና
ተራራው በጣም መንቀጥቀጥ ጀመረ።
ህዝቡ ሁሉ አይኑን ተራራው ላይ ተክሏል።ካሁን አሁን ምን ሊከሰት ነው
በማለት እርስ በርስ ይተያያሉ።
በዚህ ሁኔታ ላይ ሳሉ ተራራው ከፍተኛ ጩኸት ካስተጋባ በኋላ በጣም
በመሰንጠቅ ከመሀከሉ ህዝቡ በጠየቀው መልኩ ትልቅ እና እርጉዝ ቀይ
ግመል ወጣች።
ይህን ባዩ ግዜ አይኖቻቸው ፈጠጠ፣ አንደበታቸው ደረቀ፣ምላሶቻቸው ተሳሰሩ።
ሳሊህም ዐ ሰ፦"ህዝቦቼ ሆይ! ይህች ግመል የአላህ ተዐምር
ናት።ታይዋታላችሁ፤ ትዳስሷታላችሁም እናንተ ዘንድም ትኖራለች።
ባስቀመጣችሁት መስፈርት መሰረት ትልቅ እና እርጉዝ ሴት ግመል እንደመሆኗ
መጠን ካሁን በኋላ ውሀችሁንም ለጋራ ነው ምትጠጡት።
አንድ ቀን ግመሊቱ ስትጠጣ ቀጣይ ቀን እናንተ ትጠጣላችሁ። ምክንያቱም
መጀመርያ ያስቀመጣችሁት መስፈርት ይህ ነው'ና።
ነገር ግን ይህችን ግመል አንዳችሁ በመጥፎ ከተተናኮላችኋት የአላህ ፈጣኑ
ቅጣት ይወርድባችኋል" በማለት አስረዳቸው።
ከዚያም ህዝቡ ለሳሊህ ዐ ሰ ያለው አመለካከት 100% ተቀየረ።ሁሉም
ከማንም በላይ ሳሊህን ያከብር ጀመረ።ብዙ ሺህ ሰውም የሳሊህ ተከታይ ሆነ።
ይህ ያሳሰባቸው የከተማይቱ ሹማምንት አንድ ቀን ተሰብስበው ምን ማድረግ
እንዳለባቸው ሲወያዩ ውለው በመጨረሻም ግመሊቱን በመግደል ተስማሙ።
ይህ የተወሰነውም በአንድ መጠጥ ቤት ውስጥ ሆነው ነበር።አጋጣሚ እዛው
መጠጥ ቤት ሳሉ የመጠጥ ጥማቸው ሳይቋረጥም ከመጠጡ ቤት ጓዳ
"መጠጥ አልቋል" የሚል መርዶ ደረሳቸው።
ሹመንቱም፦"ለምንድነው በርከት አድርጋችሁ ማትሰሩት" ብለው ሲጮሁባቸው
የመጠጥ ቤቱ ባለቤት፦"ዛሬ ውሀ የግመሊቱ ተራ ስለሆነ ውሀ የለም'ና ብዙ
መስራት አልቻንም" ብላ መለሰችላቸው።
ከመሀከላቸውም አንድ ቀዳር ኢብን ሳሊፍ ኢብን ጁንደዕ የተባለ አመፀኛ
ከመሰል ጓደኛው ጋር ተነሳ'ና ግመሏን ሊገድል ጉዞ ጀመረ።በጉዞ ላይ ሳሉም
ሌላ ሰባት ሰዎችን መንገድ ላይ በመቀላቀል ዘጠኝ ሁነው ግመሏ ውሀ
የምትጠጣበት ስፍራ ደረሱ።
ክፍል2⃣ ኢንሽአላህ
ይ.........ቀ..........ጥ........ላ........፡፡
👉@yenebiyattaric
@yenebiyattaric