በመሬት መንቀጥቀጥ ሳቢያ የመማሪያ ክፍሎች በከፊል ከጥቅም ዉጭ ሆነዋል ተባለ!
በአፋር ክልል በአዋሽ ፈንታሌ ወረዳ በተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ በወረዳው በሚገኙ የመጀመሪያ እና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ላይ ተፈጥሯ ጉዳት እንደደረሰባቸው የአዋሽ ፈንታሌ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አደምበላህ ሀመዱ ለአሐዱ ተናግረዋል፡፡
በወረዳው በተደጋጋሚ እየተከሰተ በሚገኘው የመሬት መንቀጥቀጥ በስፍራው የሚገኙ ትምህርት ቤቶች በከፊል ጉዳት እንደደረሰባቸው የገለጹት ዋና አስተዳዳሪው፤ በዚህም ምክንያት ተማሪዎች ከትምህርት መማሪያ ክፍል ውጭ ትምርታቸውን እየተከታተሉ እንደሚገኙ ተናግረዋል፡፡"በአካባቢው እየተከሰተ የሚገኘው የመሬት መንቀጥቀጥ ከዚህ ቀደም በተሰነጠቀ ቦታ ላይ በተመሳሳይ አደጋው የሚከሰትበት ሁኔታ በመኖሩ ስጋት ፈጥሯል" ሲሉም አክለዋል፡፡
ከዚህ ቀደም በወረዳው ሳቡሬ ቀበሌ ኡንጋይቱ አንደኛ ደረጃና የሁለተኛ ደረጃ ት/ት ቤት በመሬት ማንቀጥቀጡ ምክንያት የት/ቤቱ ጣሪያ፣ ግድግዳ እና ወለል በመሰነጣጠቁ በመምህራን እና ተማሪዎች ላይ ጉዳት እንዳያስከትል መምህራን ተማሪዎቹ በሜዳው ላይ ለማስተማር መገደዱን አስታውቆ ነበር።
በክልሉ እየተከሰተ ያለው ተደጋጋሚ የመሬት መንቀጥቀጥ በአንዳንድ አካባቢዎች የመሬት መሰጠንቅ፣ መኖሪያ ቤቶች ላይ ቀለል ያለ መፍረስና መሰንጠቅ እንዲሁም በእንስሳቶች ከፍተኛ ድንጋጤ እና መጠነኛ ጉዳት ማስከተሉ የተነገረ ሲሆን፣ የመሬት መንቀጥቀጡ ያስከተላቸው ተደጋጋሚ ንዝረቶች አዲስ አበባ ድረስ መሰማታቸው መዘገቡ ይታወሳል፡፡ይህም የመሬት መጥቀጥቀጥ የሬክታል ስኬል መጠን ከ4 ነጥብ 5 እስከ 4 አጥብ 9 እየጨመረ የሚገኝበት ሁኔታ እንዳለ መነገሩ የሚታወስ ነው፡፡
Via Ahadu
@YeneTube @FikerAssefa