በትግራይ ክልል ባለው ወቅታዊ የፖለቲካ፣ የአስተዳደርና የፀጥታ ሁኔታ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት ውይይት ተካሄደ!
በዛሬው ዕለት በትግራይ ክልል ባለው አጠቃላይ የፖለቲካ፣ የአስተዳደር እና የፀጥታ ሁኔታ እንዲሁም ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ላይ የፌደራል መንግሥት ከፍተኛ አመራሮች በክልሉ ካሉ የፖለቲካ እና የፀጥታ አመራሮች ጋር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት ሰፊ ውይይት አድርገዋል።
በውይይቱም ላይ በክልሉ የሚታዩ ችግሮችን እንዴት በጋራ መፍታት እንደሚገባ ምክክር ተደርጓል።በተደረገው ምክክርና ውይይት በተለዩ አንኳር ጉዳዮች ላይ በተቀመጡ የጋራ አቅጣጫዎች መሠረት በጋራ ለመስራት እና የክልሉን ህዝብ የፀጥታ፣ የመልካም አስተዳደር እና የልማት ፍላጎት ለማሟላት አስቻይ ሁኔታ ለመፍጠር መግባባት ላይ ተደርሷል።
በተለይም ከመኖሪያቸው የተፈናቀሉ ዜጎችን ወደቀዬአቸው እና የቀድሞ ታጣቂዎችን ደግሞ ወደ መደበኛ ሕይወት የመመለሱ ሂደት በትኩረት በሚሰራበት እና በሚሳለጥበት ሁኔታ ላይ መግባባት ላይ ተደርሷል።
በተጨማሪም በክልሉ ያሉ የተፈጥሮ ሀብቶች አጠቃቀም የህዝብን እና የሀገርን ጥቅም በሚያስጠብቅ ሕጋዊ አግባብ እንዲሆን፣ ለህዝብ የሚቀርቡ የመንግሥት አገልግሎቶች የህዝብን ፍላጎት በሚመጥን አግባብ በሚሻሻሉበት ሁኔታ ላይ ቀጣይነት ያለው ጠንካራ ስራ እንዲሰራ በውይይቱ አቅጣጫ ተቀምጧል።
በመጨረሻም የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ክልላዊ ምርጫ እስኪያካሂድ ድረስ ያለበትን ኃላፊነት ለመወጣት በሚያስችለው አግባብ ላይም አቅጣጫ በማስቀመጥ ውይይቱ ተጠናቅቋል።
Via EBC
@YeneTube @FikerAssefa