የደቡብ አፍሪቃ፣ ፖሊስ በሕገወጥ አዘዋዋሪዎች ታግተዉ የነቡር 26 ኢትዮጵያዉያንን አስቀቀ!
የደቡብ አፍሪቃ ፖሊስ የጉዞ ሰነድ ያልነበራቸው እና በህገ ወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎች ታግተው የነበሩ 26 ኢትዮጵያዉያንን ማስለቀቁን አስታወቀ።ነጻ የወጡት ኢትዮጵያዉያኑ በጆሃንስበርግ ከተማ ዳርቻ በሚገኝ አንድ ቤት ውስጥ እርቃናቸውን ታግተዉ ነበር።የደቡብ አፍሪቃ ፖሊስ የቅድመ ወንጀል መከላከል ክፍል እንዳለው ፖሊስ ታጋቾች ወደነበሩበት ህንጻ በደረሰበት ወቅት ታግተው ከነበሩ ሰዎች በተጨማሪ 30 ያህል ሰዎች መስኮት ሰብረው ሳያመልጡ አልቀረም።
ፖሊስ ታጋቾችን ለማስለቀቅ የአካባቢው ነዋሪዎች ያልተለመደ እንቅስቃሴ መመልከታቸውን ተከትሎ ጥቆማ ከሰጡ በኋላ እርምጃ መውሰዱን የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት ዘገባ ያመለክታል። ታጋቾቹ ለምን ያህል ጊዜ ታግተው እንደነበሩ አልተገለጸም ። ነገር ግን ነጻ ከወጡት ታጋች ኢትዮጵያዉያን መካከል የጤና መታወክ የገጠማቸው አስራ አንዱ ለህክምና ወደ ሆስፒታል ተወስደዋል።ከዚህ ህገ ወጥ የሰዎች ዝውውር ጋር በተያያዘ የሀገሪቱ ፖሊስ ሦስት ኢትዮጵያዉያንን በቁጥጥር ስር ማዋሉን አስታውቋል።
ባለፈው የነሐሴ ወር 2016 በተመሳሳይ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 80 ሰነድ አልባ ኢትዮጵያዉያን ስደተኞች ማስለቀቁን የጠቀሰው የሀገሪቱ ፖሊስ በወቅቱ ታጋቾቹ ያለ በቂ ምግብ እና ዉሃ ኢሰብአዊ በሆነ መንገድ ታጉረው እንደነበር አስታውሷል።ኢትዮጵያዉያንን ጨምሮ ስራ እና የተሻለ ኑሮ ፍለጋ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ስደተኞች ከተለያዩ የአፍሪቃ ሀገራት በህገ ወጥ መንገድ ወደ ደቡብ አፍሪቃ እንደሚጓዙ ዘገባው አስታውሷል።
Via DW
@YeneTube @FikerAssefa