በኦሮሚያና አማራ ክልል ያሉ ጦርነቶች እንዲቆሙና በ ትግራይ ክልል አስተዳዳሪዎች አለመግባባት እንዲፈታ ፓትርያርኩ ጥሪ አቀረቡ!
በኦሮሚያና አማራ ክልል እንዲሁም በሀገሪቱ በልዩ ልዩ አካባቢዎች ያሉ ጦርነቶች ቆመው ነዋሪዎች ሰላምን እንዲያገኙ፤ በትግራይ ክልል ያለው የአስተዳዳሪዎች አለመግባባት ተፈቶ ዕረፍት ያጣው ሕዝብ መረጋጋት እንዲችል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተወህዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ጥሪ አቀረቡ።
ፓትርያርኩ ትናንት ባስተላለፉት የሰላም ጥሪ “እስካሁን ድረስ የብዙ ነገሮች ዋጋ ታውቋል፤ የሰላም ተመን ግን አልታወቀም” ያሉት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ፤ ሰላም ጠብን መግደል፣ ከእኔ ይልቅ ወንድሜ ይድላው ብሎ የልብ ስፋት ማግኘት ነው ብለዋል።
በትግራይ ክልል የምትገኙ የሃይማኖት አባቶች “መበደላችሁን እናውቃለን፣ በኀዘናችሁ ሰዓት አብረን መቆም ባለመቻላችን ማዘናችሁም እርግጥና ተገቢ ነው” ያሉት አቡነ ማትያስ፤ “ሁሉም ነገር የሚካሰው በእርቅ ሲሆን ልባችሁን ለሰላም፣ ለአንድነት እንድታዘጋጁ” ሲሉ ጠይቀዋል።
Via AS
@YeneTube @FikerAssefa